Thursday, May 31, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር! በቀሲስ መልአኩ

ቀሲስ መልአኩ ባወቀ  «ስውሩ አደጋ» ከሚለው መጽሐፍ  ስለ «ማኅበረ ቅዱሳን እና ሃይማኖተ አበው » ከጻፉት የተወሰደ።
 ተሐድሶ ምንድነው ?
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን በሰፊው እያነጋገረ ያለው ነገር ቢኖር "ተሐድሶ " የሚለው ቃል ነው ቃሉ እንዲህ  እንደ አሁኑ ፕሮቴስታንታዊ ለሆነ አስተሳሰብ ከመዋሉና አከራካሪ ከመሆኑ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚጠቅሱት ታላላቅ የነገረ መለኮት ቃላት አንዱ ነውንስሐንና ውስጣዊ የሆነ የሕይወት ለውጥን፤ ወደ እግዚአብሔር መመለስን የሚያመለክት ነውበሌላ በኩል ደግሞ ሲኖዶሳዊ የሆነ ለውጥን (መሻሻልን ) ሊያመልክት ይችላል። ለምሳሌ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታስቦበትና ተመክሮበት ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ይረዳሉ የሚባሉ መሻሻሎችን፤ ለውጦችንና አዳዲስ ተቋሞችን ሁሉ ይመለከታል።  ከዚህም ታላቁና ቤተክርቲያንን በአስቸጋሪ መከራ ውስጥ መከታ ሆኖ እንድታልፍ ያደረጋት የሰበካ ጉባኤ መቋቋምና የቃለ ዓዋዲ ድንጋጌ ነው :: ይህ ድንጋጌ ብዙዎች እንደሚያስቡት የሰዎች የአስተሳሰብ ፈሊጥ ሳይሆን የሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔ ነው።  አሁን ግን "ተሐድሶ " የሚለውን ቃል ፕሮቴስታንቱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የፖሊቲካው ዓለምም እየተጠቀመበት አስቸጋሪ ቃል ሆናል።
«ተሐድሶ በኦርቶዶክሱ ዓለም»
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትን የምትጠብቅ እንጂ እምነትን በዘፈቀደ ወይም ባሰኛት መንገድ የምትቀያየር ስላይደለች ዛሬ ኣንዳንዶች ከዚህ ቤተክርስቲያን የወጡ ሰዎች እንደሚናገሩት «ተሐድሶ» የሚለውን ቃል እምነትን በተመለከተ አታውለውምሃይማኖት ምን ዓይነት መልክ እንዳላት ሐዋርያው ይሁዳ በመልእክቱ ጽፎልናል "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለቅዱሳን የተሰጠች በማለት " ስለሆነም አትበረዝም፤ አትከለስም ወይም ብልየት እርጅና አያገኛትም። በሌላ በኩል ግን የክርስቲያን ሕይወት ዕለትለት ይታደሳልውስጣዊ የሆነውን የሕይወት ተሐድሶ የሚያገኘውን በንስሀ በጾም፤ በጸሎት ነው :: ይህን በተመለከተም በብዙ ቦታዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራ።
በሌላ በኩል ደግሞ አስተዳደራዊ የአሠራር ለውጦችና አልፎ አልፎ ቀኖናዊ ለውጦች ይኖራሉ :: እነዚህም ቢሆኑ የሚከናወኑት በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ስለሆነ ለውጡ ሲኖዶሳዊ ነው እንጂ የአመጽ ወይም የጥቂት ግለሰቦች አይደለም።
ይህም በኦርቶዶክሱ ዓለም የተለመደ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያንችን የከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ለብዙ ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ የተሰማሩትና አያሌ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ሉሌ መላኩ "የቤተ ክድርስቲያን ታሪክ " በሚለው መጽሐፋቸው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ሲኖዶሳዊ ተሐድሶ ሲገልጡ ,,,«በኮፕቶች (በግብጾች ) ዘንድ የተሐድሶ አባት በመባል የሚታወቀው ቄርሎስ አራተኛ (1854-1861) የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ነው :: ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ትምህርትን ማስፋፋት (የማሰራጨት ) ሰለነበር በግብጽ ካህናት ዘንድ ሰፍኖ የነበረውን የትምህርት ጉድለት፤ ዝቅተኛነትን ለማሻሻል ካህናት ተግተው እንዲማሩ አደረገከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ከፍቶ ዓለማዊና መንፈሳዊ ዕውቀት የነበራቸውን በማሰማራት መጻሕፍትን በገፍ በማቅረብ ካህናትና ምእምናን የቅብጥ (ኮፕት ) የዐረብኛ፤ የእንግሊዝኛ፤ የፈረንሳይኛ፤ የኢጣልያንኛ፤ የቱርክ .. ወዘተ ቋንቋዎችና የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንዲማሩ አደረገ »ይሉናል።
የገሞራው ጋዜጣ ጽሑፍ እና የሃይማኖተ አበው መዘጋት "
እንግዲህ በዚህ ወቅት ነው ማን እንደጻፈው የማይታወቅ ጽሑፍ "ገሞራው " በሚባልና አሁን ከሕትመት ውጭ በሆነ የግል ጋዜጣ ላይ የወጣው።  ጽሑፉ ሰፊ የሆነና የተሐድሶ ማኅበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስና ዓላማውም ምን እንደሆነ የሚገልጥ ነበር።  ከሁሉ የሚገርመው ግን ጽሑፉ ሰለተሐድሶ ሆኖ ሳለ ከጽሑፉ ጋር አብሮ የወጣው ግን በጎፋ ገብርኤል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉና  የኢትዮጵያዊው ስማእት የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ልጅ የሆኑ መነኩሴና እርሳቸው የሚያስተምሩዋቸው የሃይማኖተ አበው ተማሪዎችን የያዘ ፎቶ ነበር እኚህ አባት ጋዜጣው በወጣ ማግሥት ያለ ምንም ጥያቄ ከሚያገለግሉበት ደብር እንዲወገዱ ተደረገእምነት፤ ክህደታቸውን የጠየቀ፤ አጥፍተውም  ከሆነ በንስሐ እንዲመለሱ የመከረ ማንም አልነበረምማኅበረ ቅዱሳንም አባ እገሌ መናፍቅ ናቸው እያለ ይጽፍ ጀመረይህ ሁኔታ ቢያሳዝናቸውና  አቤት የሚሉበት ቦታ ቢያጡ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው፤ ከብዙ እንግልት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ተፈርዶላቸዋልዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በታላቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ ናቸውየጋዜጣው ጽሑፍ መደምደሚያ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር የተሐድሶ ድርጅት አካል እንደሆነ የሚናገር ነበ።


ወዲያው በግል ጋዜጣ የተጀመረውን ሰፋ አድርጎ ማኅበረ ቅዱሳን «ስምዓ ጽድቅ » በሚባለው ጋዜጣው ላይ አወጣውሃይማኖተ አበውም እንዲዘጋ ጥያቄ አቀረበ።  ለዐርባ ዓመት በቤተ ክርሲቲያን ውስጥ ታላቅ ሥፍራ የነበረውን ብዙ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያኖችን አባቶች ያፈራ፤ በሃይማኖት ያጸና ማኅበር በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ በተጻፈ ጽሑፍና በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት እንዲዘጋ ተወሰነበት። በየሳምንቱ ቅዳሜ ያሰባስብ የነበረውንም በሺህ የሚቆጠረውንም ወጣት መናፍቅ ስለሆናችሁ በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ ሥፍራ የላችሁም ተብለው አውሬ እንዲበላቸው በውጭ ተጣሉይህ ሁሉ ሲሆን ጉዳዩን እናጣራ ያለ የእነዚህ ሁሉ ወጣቶች ዕጣ ፋንታ ምንድን ነው? ያለ አንድም ሰው አልነበረም።  አምላካችን የአንድ ሰው መጥፋት የሚያሳዝነው አምላክ ነው :: እንዲያውም ወደዚህ ዓለም እኛን ለማዳን የመጣበትን  ሁኔታ የገለጠልን  «የጠፋችውን አንዲት በግ፤ የጠፋውን አንድ ልጅ፤ የጠፋውን አንድ መሀልቅ፤ የጠፋውን አንድ ድሪም ሊፈልግ በምሳሌ በማቅረብ ነው።  ለአንዱ የሚገደው ነውናለዚህ ነው ለአንዱ አርዮስ እኒያን የመሰሉ ቅዱሳን አበው ተሰብስበው የለመኑት፤ የመከሩትበዚያ ወቅት ግን ለነዚያ ለተበተኑት ልጆች ዕድል የሰጠ እስቲ አንድ ደቂቃ እናናግራቸው ያለ የለም ነበርከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ በየሳምንቱ ቅዳሜ በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥ ይሰበሰብ  የነበረው ሕዝብ «ሃይማኖተ አበው» መዘጋቱን ያወቀው ቅዳሜ ሲመጣ አጥሩ ላይ ከተለጠፈ ወረቀት ነው።
ይህም ሁኔታ ለማኅበረ ቅዱሳን አመቺ ስለሆነለት በተቻለው መጠን የሃይማኖተ አበውን ስም ማጥፋት  ገፋበትትናንት፤ ከትናንት ዲያ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ፕሮፌሰሮችና ታላላቅ ምሁራን ጋር ሆነው በአባልነት የደከሙበት ሊቃነ ጳጳሳት ምን እንዳሉ ባላውቅም ማኅበረ ቅዱሳን ግን የሃይማኖተ አበውን ወንጀል ይዘረዝር ገባከወንጀሎቹ አንዱ « የዓለም ተማሪዎች ህብረት ፌደሬሽን አባል»  መሆኑ ነበር :: አይ አለማወቅ ለንግሥና ሲያበቃ :: የዚህ መጽሐፍ ዓላማ አይደለም እንጂ ብዙ ለማለት ይቻል ነበር :: አባልነትን ካነሳን ከአባልነት በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን  በስራ አስኪያጅ  አባልነት ውስጥ የነበረችና መሪዎቹ እየመጡ የሚጎበኙን «የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት» ምንድን ነው ? በእምነት አንድ ስለሆንን አባል የሆነው ? አይደለም :: አንድ በሚያደርጉን ሌሎች ነገሮች አብሮ ለመሥራት ነው እንጂ በእምነት ከሆነ የመጨረሻው የስህተት አጋፋሪዎች የሚገኙት በዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ነው ::
ሃይማኖተ አበው ምንም እንኳን ከመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥ በግፍ ቢባረርም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት አባላቱ በሃይማኖታቸው ጸንተው ሁኔታውን በትግስት እንዲያሳልፉ አሳሰበበሐረር በጅጅጋ በደብረ ብርሀን በባህር ዳርና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙት አባላቱም ወደ አባቶች አቤት ማለቱን ተያያዙት።
ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈልገው ደግሞ የሃይማኖተ አበውን ስም አጠራር ከምድረ ገጽ አጥፍቶ የርሱን ድርጅት ከዳር እስከ ዳር ማጠናከር ነበር።  ይህ አልሆን ሲለው ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ ሌላ ነገር ማድረግ ወሰነ። ያም በጉልበት መጠቀም ነበር።
በድሬዳዋ ያለው የሃይማኖተ አበው ቅርንጫፍ የተደራጀና በቁጥር በዛ ያሉ አባላት ያሉት ሲሆን ለቤተ ክርስቲያናቸው ቀናዒ የሆኑ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ናቸውበግል ጋዜጣ ላይ የወጣውን ጽሁፍ ተከትሎ ዋናው ጽሕፈት ቤት በመዘጋቱና የማኅበሩ ተቃዋሚዎች በየአቅጣጫው በሚያናፍሱት ወሬ አባላቱ በመደናገጣቸው አባላቱን ለማረጋጋት ቅርንጫፍ ማኅበሩ ነሐሴ 21 ቀን 1986 . የእመቤታችን ዕለት ታላቅ ጉባኤ ለማድረግ አባላቶችን ጠራ።
ሁኔታው የማኅበሩን መበተን ለማየት የሚጠባበቁትን ስላናደዳቸው ጉባኤው እንዳይካሔድ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አቀረቡ :: በተለይም አቀራረባቸው የዛቻና የዱላ ስለነበረ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ ከማድረጉም በላይ ጥያቄውን ባቀረቡት ግለሰቦች አማካይነት አንዳች ጉዳት ቢደርስ በኃላፊነት የሚጠየቁ እንደሆነ አስጠነቀቃቸው :: ሆኖም ማስጠንቀቂያውን ወደ ጎን በመተውና ጥቂት የዋህ ምእመናን «ሃይማኖትህ ተወረረብህ»  በማለት እንዲሁም ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን በገንዘብ በመስጠት የኃይማኖተ አበው ተማሪዎች ማኅበር አባላት ወደ ተሰበሰቡበት አዳራሽ መጥተው አዳራሹን ከበቡት ::
ዕለቱ የእመቤታችን ቀን ስለሆነ የጉባኤው መክፈቻ  «ወትቀውም ንግሥት በየማንከ፤  «ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች » የሚለው ተሰብኮና ጸሎተ ወንጌል ደርሶ የዕለቱ መምህር የዕለቱን ወንጌል ማስተማር ሲጀምሩ ማኅበረ ቅዱሳን የቀጠራቸው ነፍሰ ገዳዮች አዳራሹን ወረሩትዱላ ጩቤና ሌላም የጦር መሳሪያ ይዘው ስለ ነበረና በቁጥርም የሚበዙ ስለ ነበሩ ከፍተኛ ጉዳት አደረሱበድብደባውም ነፍሰ ጡሮች የተጎዱ ሲሆን በተለይም ለመውለድ ሦስት ቀናት የቀራት ልጅ «ስለ እመ ብርሃን ልወልድ ሳምንቴ ገብቷል» ብላ ስትለምናቸው ክፉኛ ደብድበዋት ሆስፒታል ሄዳ በከፍተኛ ችግር ልጁ ወጣ :: ሦስት ልጆች አካለ ጎዶሎ የሆኑ ሲሆን አንድ ወንድማችንን ገደሉት።  በቦታው የነበረውንም ግምቱ መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የመንግስት ንብረት ጠፋ።
ከሁሉ የሚገርመው በጊዜው ለጵጵስና እየተዘጋጁ የነበሩትና በስተኋላም የሐረርን ሰንበት ትምህርት ቤት ያዘጉት መምህር ብርሃነ ሥላሴ በኋላም እዚህ አሜሪካ ባሉት ታላቁ አባት በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ምትክ ዜና ማርቆስ የተባሉት በእነዚህ ልጆች ተንኮል ውስጥ መግባታቸው ነው ::
በጊዚው የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ መርስኤ ኃዘን አበበ ለአቡነ ጳውሎስ ባቀረበው ሪፖርት  «የጸቡ ምክንያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር በማለት ራሳቸውን በመጥራታቸው በቤተክርስቲያን ስም መናፍቃን ሊነግዱ አይችሉም» በሚል ነው  ካለ በኋላ ሰለ ሃይማኖተ አበውም ሲናገር «ራሱን ሃይማኖተ አበው፤ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር በማለት የሚጠራው አካል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት ውስጥ ባሉት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በቡድን ተደራጅተው ከቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት ውጭ እየንተንቀሳቀሱ በመገኘታቸው በተለያዩ ስንበት ትምህርት ቤቶች እንዲታገዱ ተገልጧል»ይላል :: ከሁሉ የሚያስቀው ደግሞ ማኅበሩ ስብሰባውን የጠራው  «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር»  በሚል ስም ነው ማለቱ ነው ::
ጋዜጠኛው መርስዔ ሃዘን አበበም ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያን ሀፍረት መሆኑን ዘንግቶት በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ለገዳዮቹ  ሽልማት እንዲሰጥ አደረገ።
ይህ መቼም በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አዲስ ክስተት ነበር :: መግደል ንስሐ ያስገባል፤ ያሳዝናል፤ ከሹመት ያሽራል እንጂ አያሸልምም። በወንበዴዎቹ  የወደመውን ንብረት እንዲከፍል ቤተ ክህነት ስለተጠየቀ  ኃላፊነት ወስዶ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ አድርጎ ከፈለ።  በድሬዳዋ የነበሩትን ወጣቶች ቅስም ሰበረበገዛ ወገናቸው የተደበደቡም በደም እንደጨቀዩ በዚያው አምርረው እንደወጡ ቀሩ።
በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ላይ የተጀመረው ዘመቻ
ማኅበረ ቅዱሳን ሃይማኖተ አበውን ካስዘጋና ድሬዳዋን ካስደበደበ በኋላ  መንገዴ ላይ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ ያላቸውና በአባልነት ወደ እርሱ ጎራ ለመግባት እምቢ ያሉትን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን  «ተሐድሶዎች » ናቸው በማለት ስማቸውን በዝርዝር በጋዜጣ ላይ ማውጣት የጀመረው ውሎ ሳያድር ነው :: አገልጋዮች የሆኑ ካህናትንም ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ የየሀገሩ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆችና ሊቃነ ጳጳሳትን መወትወት ጀመረ :: በጥቂት ጊዜ ውስጥ ማንም የማያውቀውና እዚህ ግባ የማይባለውን በፕሮቴስታንቶች የተጀመረው ተሐድሶ ተብዬ እንቅስቃሴ ማኅበረ ቅዱሳን ለመላው እትዮጵያ ከማስተዋወቁም በላይ የየእለቱ መነጋገሪያ አደረገው።  በተለይም የማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች ጳጳሳቱም አሉበት በማለት መናገር ስለ ጀመረ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሙሉ፤ ጳጳሳት ሁሉ ያሉበት ይህ «ተሐድሶ» የሚሉት ምንድን ነው? ማለት ጀመረ።
ሁኔታው በኦርቶዶክሳዊት ቤ ተክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ በማይታይ ሁኔታ «በጫካ ሕግ» የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የተረገጡበት፤ በአላዊቂዎች የተዋረዱበት ነበር :: ማኅበረ ቅዱሳን በነዚያ ወቅቶች ያከናወናቸው ድርጊቶች ሁለት ወቅቶችን ያስታውሰኛል :: አንደኛው ቁስጥንጥንያ ውስጥ የተደረገን  ነገር ሲሆን ሌላው ካምቦዲያ ውስጥ የተደረገ ነው ::
ጊዜው እግዚአብሔር ያስነሳው ታላቁ ፓትርያርክና የሰባክያን  መስፍን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መላዋን ቁስጥንጥንያን በትምህርቱ ይገስጽ፤ ይመክር የነበረበት ወቅት ነው :: ትምህርቱ የቁስጥንጥንያ ቤተ መንግሥት ስዎች ቢጎረብጣቸውም  የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የትምህርት ጸዳል ያገለላቸውን ጥቂት ወሮበሎች አስነሡበት :: ከእስክንድርያ ደግሞ የሥልጣን ጥም ያናውዛቸውን ስዎች አመጡበት :: ሌላው ቀርቶ መናፍቃንን በትምህርቱ ይመክት የነበረውን ኤጲፋንዮስን እስኪያሳስቱ ድረስ  «ዮሐንስ አፈወርቅ መናፍቅ ሆኗል ድረስልን» ብለው አመጡት።
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ግን ነገሩን  አይቶ  ቀስ ብሎ ወደ ሀገሩ ቆጵሮስ ሲመለስ መንገድ ላይ አረፈሌሎቹ ግን ያን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ዓይን መናፍቅ ነው ብለው ፈረዱበትከገዛ መንበሩ አጋዙት፤ አንገላቱት በስደት ሳለም ከሕመምና ከእንግልት የተነሳ አረፈየሚገርመው ግን መናፍቅ ነው ብለው የፈረዱበትና ያወገዙት ቤተክርስቲያኒቱን የማያውቁ ጊዜ ያነሳቸው ወሮበሎች መሆናቸው ነውአለማወቅ አዋቂነት የሆነበት፤ አዋቂነት ወንጀል የሆነበት ዘመን ነበርና።
ይቀጥላል………………………………..