«ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሠረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውንን የኃይማኖት ህጸጽ የለባቸውም ተሃድሶ መናፍቃንም አይደሉም አለ»
Adiós ማቅ !!!!! bienvenidos አባ ሠረቀ ወበጋሻው!!
የጽሁፉ ምንጭ፦ ዐውደምህረት
በትናንትነው
ዕለት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጀመረው ከጥቅምቱ ስብሰባ ወደ ግንቦት የተዘዋወሩ ጉዳዮችንን በመመልከት ሲሆን የመጀመሪያ አጀንዳውም ሊቃውንት ጉባኤው “የሐይማኖት ህጸጽ” አለባቸው ተብለው ስለ ቀረቡ ወገኖች አጣርቶ የደረሰበትን እንዲያቀርብ ማድረግና ውሳኔ መስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ማቅ ይወገዙ ይከሰሱልኝ ሲል ካቀረባቸው ሰዎች መካከል የአባ ሠረቀ ብርሃን እና የዲ/ን በጋሻው ጉዳይ ታይቶ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ይህ ውሳኔ ለማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ውድቀት እንደሆነ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።
ማኅበረ
ቅዱሳን ዲ/ን በጋሻውንን ከሚቃወምበትና መናፍቅ እያለ ስሙን ማጥፋት የጀመረበት ምክንያቶች ሦስት ሲሆኑ እነርሱም ከአቡነ ጳውሎስ ጋር መታረቁ፣ ማኅበሩን በስህተቶቹ አደባባይ ላይ መውቀሱ እና በካሴት ሽያጭ ደግሞ የአንበሳውን ድርሻ ወውሰዱ ናቸው።
ከአቡነ
ጳውሎስ ጋር በታረቀ ጊዜ “ገዝግዘን ገዝግዘን ልንጥላቸው በነበረ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ታርቆ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎቹን ለእሳቸው ያለው አስተያየት ወደ መልካም እንዲለወጥ አድርጓል። ይህም ለፓትርያርኩ ተጨማሪ ጥንካሬን ሰጥቷል። በማለት ገና የማጥላላት ዘመቻውን ከመጀመራቸው በፊት በንዴት ሲናገሩ የተሰሙት አንዳንድ የአመራር አባሎች ይህ ንግግራቸው በወቅቱ በቅርብ በሚያውቁዋቸው ሰዎች ዘንድ ለከፍተኛ ትዝብት ዳርጓቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ማቅ ችግር በሚፈጥርባቸው ነገሮች ላይ መናገር መጀመሩ በማህበሩ በተሃድሶነት ለመወገዝ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዳለው ደግሞ በጋሻው ማኅበሩን መንቀፉ “ተሀድሶ” ተብሎ የተነከሰበት ጥርስ እንዲጠብቅ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። ዲ/ን ዳንኤል ባለፈው አመት በለቀቀው ጽሁፉ ስለ ዲ/ን በጋሻው እንዲህ ብሎ ነበር “ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው? ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ? በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም። በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው። ከዚህ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሳ ቤተክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ።” ይህ የዳንኤል ውስጥ አወቅ ጽሁፍ ማኅበሩ እንዴት ባለ ውድቀት ውስጥ እንዳለ እና እኔን የተቃመወና ስህተቴን የነገረኝ ሁሉ የቤተክርስቲያን ጠላት ተሃድሶ መናፍቅ ነው በሚል አባዜ እንደሚመራ ያሳየ እና የበጋሻው ችግር ሃይማኖታዊ አለመሆኑን ያሳወቀ ነበር። (በነገራችን ላይ ዲ/ን ዳንኤል ከማኅበሩ ጋር የገባው ውዝግብ በይቅርታ ሳይፈታ አንድ ሳምንት እንኳ ቢዘገይ ኖሮ በዘሪሁን ሙላቱ አማካኝነት ዕንቁ መጽሔት ላይ እንዲወጣ የተዘጋጀ ጽሁፍ ነበር። እርቁ የዘሪሁን ተሳዳቢ ብዕር ያጠቆረውን ወረቀት ማረፊያ አሳጥቶታል።)
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የዲ/ን በጋሻው የስብከት ሲዲዎች በከፍተኛ ቁጥር መሸጣቸው የማኅበሩን ሲዲዎች ከገበያ ውጭ በማድረጉ ማቅ በሚመራበት የቢዝነስ ሕግ ደግሞ “ተቀናቃኝህን እና ገበያ ላይ ፍርሀት የሆነብህን ሰው ማንኛውንም መንገድ ተጠቅመህ አስወግድ” የሚል በመሆኑ በጋሻውን ከገበያ ለማስወጣት “ተሃድሶ መናፍቅ”
የሚል ዘመቻውንን በተጠናከረ መንገድ ለመጀመር አስችሎታል።
ማቅ
በተለያየ መንገድ ሊያጠፋ ሚፈልገውን ሰው ሁሉ ህዝቡን በቀላሉ ለማሳመን በሚረዳው “ታድሰዋል መንፍቀዋል” በሚል
መንገድ ከሶ ስለሚያጠቃ ምንም እንኳ አባ ሠረቀ እና ዲ/ን በጋሻው ከእነርሱ ጋር ያልተግባቡበት መንገድ የተለያየ ቢሆንም የከሰሱዋቸው ግን በአንድ ስም “ተሀድሶ መናፍቅ” ብለው ነው።
የቅዱስ
ሲኖዶሱ ውሳኔ ማኅበረ ቅዱሳን አካሄዱን እንዲፈትሽና እኔን ያልተቀበለ ሁሉ መናፍቅ ነው ከሚያሰኝ አባዜው በቶሎ ሳይመሽበት ነጻ እንዲወጣ አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑም ተመልክቷል።