Saturday, May 12, 2012

የማይዘልቅ ማኅበር በጠጅ ይጀመራል የማያድግም ልጅ ዓይነምድሩ ይበዛል!


                  
                 የጽሁፉ ምንጭ፤ አባ ሰላማ Wednesday, May 18, 2011 ፖስት
አንድ ማኅበር ለመጀመሪያ ጊዜ በጠጅ ከተጀመረ የሰካራሞች መሰብሰቢያ ይሆንና በመጨረሻ በብጥብጥ ይበተናል፤ ምክንያቱም ማህበሩን የጀመረው ግለሰብ በጠጅ ከጀመረው የሚቀጥለው ተረኛም ከማን አንሼ በሚል ስሜት ለአባላቱ ጠጅ ስለሚያቀርብ፤ ቀጥሎ ማህበር የሚደግሰውም እንዲሁ እንደጓደኞቹ ስለሚወዳደር ማህበሩ በጠጅ ተጀምሮ በጠጅ ይበተናል ማለት ነው ሰካራሞች የሚናገሩትን እና የሚሠሩትን ስለማያውቁ ሁልጊዜ መስከራቸው ሕይወታቸውንም ሆነ ኢኮኖሚያቸውን ያቃውሳልና።
የማያድግ ልጅም ከሚበላው ፍሬ ነገር ይልቅ ወደ ውጭ የሚያወጣው ዓይነ ምድር ከበዛ ሰውነቱ ንጥረ ምግቦችን መቀበል ስለማይችል ሆዱ ተነፍቶ መሞቱ ወይም ቀጭጮ አቅመ ቢስ ሆኖ መቅረቱ አይቀርም፤ የማያድግ ልጅ እንትኑ ይበዛል የተባለው ለዚህ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳንም ገና ሲጀመር ዓይነምድሩ የበዛ በነገር የተጀመረና በጠንቋዮች ምክር ስለሚመራ ባጭሩ መቀጨቱ የማይቀር ነው። ማህበረ ቅዱሳን በነ አቡነ ማቴዎስ፤በነ ቀሲስ ዳኛቸው፤ በነ ኃይለ ጊዮርጊስ በነ አቶ ታየ [የሽዋ ንጉሥ ሊሆን የነበረ] ወዘተ በደገሱት የተንኮል ድግስ ወጣቱን በነገር እያሰከረ ሲያወላግድ ከዚህ ደርሷል። ዛሬም መካኒሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በሚደረግ ምሥጢራዊ ስብሰባ ነገር እየተቀበለ ወደ ቤተ ክህነት ብቅ ይልና በግማት የተሞላውን ዓይነምድሩን ጥሎ ይሄዳል። 
 እነ ዶክተር እስራኤል የሚሳተፉበት የላፍቶው ስብሰባ ደግሞ በስለላ ሥራ ተሰማርቶ አይነምድሩን በየከተማው ያሰራጫል፤ የወያኔ አባል በመሆን በውጭ ጉዳይ ሚስቴር እና በደህነነት ቢሮዎች የተሰገሰገው የማህበረ ቅዱሳን የፖለቲካ ክንፍ በረቀቀ ዘዴ የሚፈራቸውን በመንግሥት ያስመታል።
በኤፍሬም እሸቴና በብርሃኑ ጎበና የሚመራው የውጭ ግንኙነት ክፍል ደግሞ አቡነ  አብርሃም [ 1 ] ሃይማኖታዊ ሽፋን እየሰጡት ከውጭ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር ይሞክራል። ማህበረ ቅዱሳን ዓይነምድሩ የበዛ ነው።
ከዋናው ማዕከል ውስጥ ሆኖ የፕሮፓጋንዳ ሥራ የሚሠራው የነ ዳንኤል ክብረት ቡድን ደግሞ የሕዝቡን የልብ ትርታ እያዳመጠ ከሚዲያ ክፍሉ ጋር በመቀናጀት አይነ ምድሩን በተለያዩ ሚድያዎች ይጎይጻል።
አሁን ከሞት ያድነኛል፤ ፓትርያርኩን ያጠቃልኛል፤ ሕዝቡን ከኔ ጋር ያሰልፍልኛል ያለው ፕሮፓጋንዳ ደግሞ ተሃድሶዎች ሊያጠፉን ነው የሚል ነው። ተሃድሶ ምን እንደሚል ግን የሚያስተውል በጣም ጥቂት ነው፤ የሐዋርያትን እምነትና የአጼ ዘርዓ ያዕቆብን ድርሰት ለይቶ የማያውቀውን ሕዝብ የፕሮፓጋንዳ ሰላባ በማድረግ ወደ ደም ማፍሰስ ደረጃ ለማድረስ ጫፍ ላይ ደርሷል።
በመሠረቱ ማህበረ ቅዱሳን በጠንቋዩ ደብተራ ቀለመወርቅ አመራር ሰጭነት ሲመሠረት ጀምሮ ደም በማፍሰስ መሆኑን ስንቶች ታውቃላችሁ? ቄስ እሸቱ እና አንዲት ውሽማው ጠንቋዩ ዘንድ በመመላለስ የሰባት ሴቶችን ድንግልና እንዲገስ፤ እንዲሁም የማህብሩን የልብስ ጃኖ ቀይ ጥለት እንዲያደርግ፤ ከተነገረው በኋላ የደናግሉን ድንግልና ማርያም ትመልስላችኋለች በማለት ስላበላሸ እሥር ቤት ገብቶ እንደነበር እና በፖሊስ ፕሮግራም ሲቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።
በዚህ ሰይጣናዊ ሥራ የተጀመረ ማህበር ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ደም ለማፋሰስ የሚያደርገውን ቅሥቀሣ ዝም ብለን አናልፈውም። እስካሁን በሥውርም ሆነ በአደባባይ ያፈሰሰው ደም እየጮኸበት ባለበት ባሁኑ ወቅት ሌላ ተጨማሪ ደም ለማፍሰስ ሕዝብን መቀስቀሱ ሰይጣን በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ደም ለማፍሰስ ያለው አላማ ገና ያላለቀ መሆኑን ያስገነዝበናል።
የተክለ ሃይማኖት መንበር የኔ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ የሚለው የነ ሊቀ ካህናት ክንፈ መፈክር ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት መክፈሉ የማይቀር ነው። የተክለ ሃይማኖት መንበር ለኛ ምናችን ነው? እንዲህ ሰላም አጥተን ከምንኖር የራሳችንን መንበር እንድናበጅ የሚገፋፋን ነው። ጉዳዩን የሃይማኖት ሽፋን በመስጠት የተክለ ሃይማኖትን መንበር የማስመለስ እንቅሥቃሴ ሰላማችንን ነሥቶናል፤ በርካታ ውድ ኢትዮጵዮጵያውያን ሊቃውንትን አጥተንበታል። ለምሳሌ አቡነ ቴዎፍሎስን ያስገደላቸው የመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥያቄ ነው፤ አቡነ መርቆርዮስን አገር ጥለው እንዲሄዱ ያደረጋቸው ይሄው የመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥያቄ ነው።
ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ናቸው፤ ለምን ሲያበጣብጡን እንደሚኖሩ ግን አይገባንም? አንድ ነገር ግን ማሳወቅ እንፈልጋለን፦ ይኸውም ማህበረ ቅዱሳን የሚሾመውን ፓትርያርክ ፈጽሞ የማንቀበል መሆናችንን ነው። እኛ ሕዝባችን መንፈሳዊና ማህበራዊ ሕይወቱ ታድሶ ሰውነቱ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ እረፍት እንዲያገኝ ተግተን የምንሠራ እንጂ በመንበር ሽሚያ ውስጥ ገብተን መፈትፈት አንፈልግም።
ማህበረ ቅዱሳንም በነገር ሥራ፤ በመናፍስታዊ ቅንብር፤ በሥጋዊ ሥልጣን ፍለጋ የሰከረ ሰካራም በመሆኑ ከብዙ ዛፍ ጋር እየተጋጨ መሞቱ አይቀርም።
ይቆየን
ተስፋ ነኝ
 _________________
[1] የአባ አብርሃምን ስራ የሚያመልክት ሊንክ