Tuesday, May 22, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ከዳላስ ሚካኤል የዛሬ 2 ዓመት የቦጨቀው 120 ሺህ ዶላር የት ደረሰ?

ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!!!!
የሚካኤልን ታቦት የከሰሱ ሰዎችን በማስቀደም ቤተክርስቲያኑን ለማፍረስ የሚታገሉት የወያኔ ተስፈኞች የጠሩት ስብሰባ መክሸፉን እንደሰማችሁ እናውቃለን። ህዝቡ እንደማይፈልጋቸው
፩ኛ፦ በምርጫ
፪ኛ፦ በጠሩት ስብሰባ ላይ ባለመገኘት እንደተፋቸው በድጋሚ አረጋግጦላቸዋል።

የሚካኤል ቤተክርስቲያን ከተቋቋመ ጀምሮ አንድ ጊዜ እንኳን በቦርድ አባልነት ተመርጠው  አገልግሎት ሰጥተው በማያውቁት በአቶ ጌታቸው ትርፌና ቤተክርስቲያኑ ከተመሰረተ ከቦርድ ወጥተው በማያውቁት በአቶ እዩኤል ነጋ አማካኝነት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተሰገሰገውና የተሰባሰበው የፖለቲካ ድርጅት በቦርድ አባላት ምርጫ ላይ ተሳትፎ መሸነፉን ሁላችሁም የምታውቁት ነገር ነው።

ይህ ቡድን የሰላምና የአንድነት አስተባባሪ ኮሚቴ በመባል ይታወቃል። በውስጡም፦
፩ኛ፡- የሽማግሌዎች ኮሚቴ
፪ኛ፦ የአባላት ኮሚቴ እና
፫ኛ፦ የቀሳውስት ኮሚቴዎች አሉበት።
ለክፉ ቀን ያዋቀሩት ሽምቅ ድርጅት ነው። ይህ ሁሉ ደባ የሚፈጸመው ቤተክርስቲያናችንን ተገን በማድረግ ነው። ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ግለሰቦች ባለፈው ምርጫ ላይ ያቀረቧቸው ተወዳዳሪዎች ከዚህ ቡድን ድጋፍ በማግኘት ስልጣን ላይ አንዲቆዩና ደግመው እንዲመረጡ የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ይታወሳል። በምርጫው ሲሸነፉ በመደናበር ሮጠው ከወያኔ እግር ስር ተደፉ። ወያኔም በገንዘብ ኃይል ድምጽ ገዝቶ ቢለግስም የምርጫዉን ዉጤት ግን መለወጥ አልቻለም።

የህዝብን ድምጽ አክብሮ መቀበል የተሳናቸው አቶ ጌታቸውና አቶ እዩኤልም ቀደም ሲል ምርጫውን እንዲያሸንፉ ሊረዳቸው ሞክሮ አቅም ወዳነሰው ቡድን ተመልሰው በውስጡ የተዋቀሩትን ኮሚቴዎች እንዲያንቀሳቅስ ትእዛዝ አስተላለፉ። ሁለቱ ግለሰቦች ደግሞ ቀደም ሲል ፕሮግራም በተያዘለት አመታዊ የምእመናን ስብሰባ ላይ ዶክተር ግርማንና አቶ አበራን ለማስወጣት የተንኮል ስራ ለመስራት ወስኑ። በምርጫ ያጡትን ወንበር ሁለቱን ተመራጮች በማባረር ዙረው ለመያዝ የተጠነሰሰ ሤራ ነበር። በዚህ መሰረት የወያኔ ተወካዮችም ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ለመስራት ተስማሙ። በተደረሰው ስምምነት መሰረት ተስፈኛ ባለ ሃብቶች ሰብሰባውን እንዲጠሩ ተወሰነ። በጉባኤው ላይ የወያኔ ካህን መጋበዛቸው ይፋ ሲወጣ አቶ ጌታቸውና አቶ እዩኤል ከነተከታዮቻቸው ራሳቸውን ከስብሰባው አገለሉ። ወያኔወችም ብቻቸውን ቀሩ። ስብሰባውም ከሸፈ።

ግንባር ቀደም የስብሰባው መሪዎች የነበሩትም ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
፩ኛ፦ አቶ ኃይሉ እጅጉ-

    (ሀ) ብዙ ሰዎችን ሽርክና አስገብተው ገንዘባቸውን የዘረፉ
    (ለ) ከቄስ ሞገስ እጅጉ ጋር በመተባበር ቂርቆስ ቤተክርስቲያንን የመሰረቱ
    (ሐ) የፓትሪያርክ ጳውሎስ ወዳጅ
    (መ) የታቦቱ ከሳሾች በጉልበትና ገንዘብ ደጋፊ።

፪ኛ፦ አቶ ሙልጌታ ወራሽ (ሙላው)-

    (ሀ) ብዙ ሰዎችን ሽርክና አስገብተው ገንዘባቸውን የዘረፉ
    (ለ) ቤተክርስቲያናችንን ለወያኔ ለመስጠት ሌት ተቀን የሚጥሩ።

፫ኛ፦ መነኩሴ ታደሰ አርአያ (ቄስ ታደሰ አርአያ) በሚል መጠሪያ የሚታወቁ- ከባለቤታቸው ጋር ለአመታት ተጣልተው ተለያይተው ስለነበረ በህገ ቤተክርስቲያን መሰረት ቅስናቸውን ያፈረሱ ሲሆኑ፤ባለቤታቸውም የጴንጤ ሃይማኖት ተከታይ ናቸው።

    (ሀ) ዘረኛ በመሆናቸው ቤተክርስቲያንን ጥለው የወጡ
    (ለ) በወያኔ ድጋፍ ተክለሃይማኖት/አቡነ አረጋዊ የሚባል ቤተክርስቲያን ያቋቋሙና የሚመሩ።

፬ኛ፦ ዲያቆን አርአያ ኃይለመስቀል- መጻህፍት ለመግዛት የወሰደውን አምስት ሽህ ዶላር ይዞ ከቤተክርስቲያን የተሰወረ ግለሰብ።
፭ኛ፦ አቶ መስፍን ወልደየስ - ለማህበረ ቅዱሳን ድርጅት የሰጠውን አንድ መቶ ሃያ ሽህ ዶላር አስከዛሬ ድረስ ሂሳብ ማወራረድ ያቃታውና፤ ኦዲት አልደረግም አሻፈረኝ ያለ ሽፍታ
፮ኛ፦ አቶ ጸሀይጽድቅ ቤተማርያም

    (ሀ) ኢትዮጵያ ውስጥ የደርግ ዘበኛ በነበረበት ወቅት ንጹሃን ዜጎችን በጥይት የረሸነ (ያረገፈ)
    (ለ) አስመራ ከተማ ላይ ላቅመ ሄዋን ባልደረሱ ልጃገረዶች ላይ በግዳጅ የወሲብ በደል (RAPE) የፈጸመ፤ ሲሆኑ፦

በሌላ በኩል ደግሞ የሽማግሌዎች ኮሚቴ ብለው የሰየሙት ቡድን በዚሁ ቀን ወደ አስተዳደር ቦርድ ልከውት ከቦርዱ ጋር ውይይት ማድረግ ችሏል።  እንዲሁም  የቀሳውስቱ ኮሚቴ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ፕሮግራም የተያዘለት ለእሁድ ነበር። ቅስቀሳ እንዲያደርጉ የታዘዙት ቄስም ተሳክቶላቸው ነበር። "በዚህ አጋጣሚ በማስተምረው ትምህርት አንዳንድ ሰዎች ሊቀየሙኝ ይችላሉ! እኔ ግን እዉነትን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም" በማለት ለኮሚቴው ታማኝነታቸውን አረጋግጠዋል። ስለሆነም የካድሬነት ሥራቸውን ተወጥተዋል ማለት ይቻላል። በዲስኩራቸውም መሃል አንዳንድ ወገኖች የሚናገሩትን ቃላት እያጣመሙባቸው መቸገራቸውን ምርር ብለው ሲናገሩ ተሰምተዋል።

ውድ አንባብያን!!
ቀጥሎ ያለው ጽሁፍ ምኑ ላይ ነው የተጣመመው? እስቲ አብረን እናንብበው!
እርስዎና ሌላው ካህን ጓደኛዎ ካሁን ቀደም በእንግድነት ተጋብዘው በመጡት መምህር ላይ ወረቀት ለምን በተናችሁ? በቅዳሴና በትምህርት ሰዓት ከእንግዳው ጋር አብራችሁ ላለመቀደስ ለምን አድማ መታችሁ? ለአምስት ሰዓት ያህል ሽንት ቤት ውስጥ ለምን ዘግታችሁ ተሸሸጋችሁ? በሌላ ጊዜ ደግሞ መቅደስ ውስጥ በመቋምያ አንጋፋውን ካህን ለመማታት ለምን ሞከሩ? ይህ ድርጊት ልክ ነው ወይ? ተብሎ ነው የተጻፈው።

"ነገርን ነገር ያነሳዋል" እንዲሉ፤ በቅርቡ አንድ አዛውንት ወዳጅዎ ማግባታቸውን ሰምተናል። እርስዎም በሰርጉ የመዝናኛ ምሽት ላይ ያሰሙትን ቀልድ አድምጠናል። እርሰዎን ከሚያክል አዋቂ ነኝ ባይ የማይጠበቅና ያለቦታው የቀረበ ቅሌት ነበር የተናገሩት፤ ለምን?  የአዛውንቱን ወዳጅዎን ባለቤት እንደቆሎው ተማሪ ከጅለው የተናገሩት ይሆን? ወይስ በአቶ እዮኤል ቤት አድራሻ በተቋቋመው የገለልተኞች ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት ውስጥ ለመቀጠር መለማመጥዎ ነበር?

ውድ አንባብያን!
በሽምቅ ተዋጊዎቻቸው በኩል የፈጸሙትን ሴራ አነበባችሁ። በአመታዊው ጉባኤ ላይ የሰሩትንም ስራ አወቃችሁ፤ ተገነዘባችሁም። እንግዲህ ከዚህ በኋላ የምንጠብቀው የዚህ የሽምቅ ተዋጊ ቡድን አካል የሆነውን የሂሳብ አገናዛቢ ቡድን ሪፖርትና ድራማ ማየት ነው። የዚህ ቡድን ቀነ ቀጠሮ ማርች (March) 6, 2010 ዓ/ም መሆኑን ዘንገተውታል። የስብሰባ ጥሪ አላደረጉም። ድርማውን መሸምደድና ዝግጅት ማድረጉ ጊዜ ፈጅቶባቸው ይሆን? እኛም ለዛሬው በዚህ ይብቃን እንላለን።
ቸር ይግጠመን።
አሜን!
ምንጭ፦ ሰንበቴ ብሎግ /http://senbete.blogspot.com