- · መምህርን ዕንቍባሕርይ ከሰንበት ማደራጃ አይነሳም
- · የሚወገዝ ሰውም የለም
- · የዶ/ር መስፍን ክህነት መሻር ይነሳልን ብለው ነበር ፤ አልተሳከላቸውም
- · አባ አብርሃም የአሜሪካውን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ታዘዋል
- · የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጾች ውሸት እየፈበረኩ መዘገባቸውን ቀጥለዋልና የዘገቡትን ገልብጦ መረዳት ያስፈልጋል
ምንጭ፦ዐውደ ምሕረት ብሎግ
ከሲኖዶስ
ስብሰባ በስተጀርባ ሆኖ እንዳሻው ከሚጋልብባቸው ጳጳሳቱ ጋር የመከረውን ሁሉ ከስብሰባው መካሄድ ቀደም ብሎ የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን በተሳሳተ መረጃ ማደናገርና የተናገረው ሳይሆን ሲቀር ሊያፍር ሲገባው፣ ነገር ግን «ማፈር ደህና ሰንብት» ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በድረገጾቹ ውሸት እየፈበረከና ምኞቱን የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ ማቅረቡን ቀጥሏል። ከሰሞኑ እንኳ እነእገሌ ዛሬ ይወገዛሉ አለ። ነገር ግን እንኳን ውግዘት እዚያ በሚያደርስ ሁኔታ የተደረገ ማጣራት አልተካሄደም። ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁና ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ «ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።» ሲሉ የማቅ ድረገጾች እንደተለመደው
የልባቸውን ተምኔት ጽፈዋል። ይህ እንደማይሆን፣ ቅዱስነታቸው 10 ጳጳሳትን ይዘው ለቅዱስ ያሬድ በዓል ወደአክሱም ተጉዘዋልና፣ ዛሬ፣ እንኳን ይህ ፈጽሞ ያልተጣራና በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተወሰነበት ደረጃ የሚገኘው ጉዳይ ውሳኔ ሊያገኝ ቀርቶ የሲኖዶስ ስብሰባም እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።
ሌላው
የማኅበሩ ምኞትና የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ የተዘገበው መምህር ዕንቍባሕርይ ከማደራጃ መምሪያ ሀላፊነታቸው እንዲነሱ ተወሰነ፤ አባ ኅሩይም ወደሃላፊነታቸው እንዲመለሱ ሲኖዶሱ አዘዘ የሚለው ዘገባ ነው። ይህ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል የማህበሪቱ ምኞት ነው።
በማኅበራት
ጉዳይ ላይ አጀንዳው እንደቀረበ ጳጳሳቱ ሁሉ መስማማታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ «ጉዳዩ እኔን ለማፍረስ የተደረገ ነውና እንዴት እንዲህ ያለ ስምምነት አድርጋችሁ ትወጣላችሁ?» በማለት ጳጳሳቶቿን ከመጋረጃ በስተጀርባ ሰብስባ ጉዳዩን እንደገና እንዲያንገራግሩበት ለማድረግ ባደረገችው ጥረት ጳጳሳቶቿ በጉዳዩ ላይ አቧራ ለማስነሳት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በሁሉ ጥርስ ውስጥ የገባችውን ማኅበሯን ከመፍረስ ይታደጓታል ተብሎ አይታሰብም።
ማኅበሩ
ከሲኖዶስ ስበሰባ በፊት በየድረገጾቹ አቡነ ጳውሎስን በግንቦቱ ሲኖዶስ ማውረድ አለብን የሚል ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ሲታወስ፣ ይህን ለማሳከትም በጥንተአብሶ ሰበብ ጳጳሳቶቿ ሙከራ እንዲያደርጉ ተልእኮ ሰጥታቸዋለች። ሌሎቹ ይህን ለማለት ባይደፍሩም፣ መቼም ያልተማረ ደፋር ነውና፣ ጨዋው (በትምህርት) አባ አብርሃም ቅባትነታቸውን፣ ኪራይ ሰብሳቢነታቸውን ሸፍነው ቅዱስነታቸውን «መናፍቅ» ለማለት መዳዳታቸው ብዙዎችን አስገርሟል። እርሳቸው ምን ያድርጉ አእምሮውአቸውን የተቆጣጠረችው ማኅበሯ በግንቦቱ ስብሰባ ላይ ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ የእርሷቸውን ተልእኮ እንደምትፈልገው አድርገው ለመፈጸም በመፋጠናቸው በትምህርት ሳይሆን፣ ፓትርያርክን በማንጓጠትና የማኅበሯን ተልእኮ ለመወጣት ከሌሎቹ ጳጳሳቶቿ ይልቅ አንደኛ ስለወጡ «ነደ ተሐድሶ» የሚል እንግዳ ማዕረግ ሰጥታዋለችና ለዚህ ይሆናል፤ ሽቅብ የተንጠራራው።
ሌላው
ቄስ ነኝ ብሎ ሲዘላብድ የነበረው መስፍን የተባለ
ግለሰብ ክህነት ይመለስልኝ አቡነ ፋኑኤል ይገሰጹልኝ ብላ ማኅበርዋ ብትንደፋደፍም የአቡነ ፋኑኤል ስልጣንንና ክብር የሚጋፋ ምንም ነገር አልተፈጸመም። የመስፍን የክብር ቅስናም ሳይመለስለት ቀርቷል።
የአሜሪካ
ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትን በተመለመተ ሲኖዶሱ የተነጋገረ መሆኑ ሲታወቅ አባ አብርሃም ከአንዲት ሴት ወ/ሮ ጋር የገዛሁት ቤት ነው፤ ምኑን ነው
የምመልሰው? ብለው ለመከራከርና በዚህም አቡነ ፋኑኤልን ለመስደብ ቢሞክሩም አቡነ ፋኑኤል ግን ለስድቡ መልስ ሳይሰጡ በሰከነ መንገድ ነገሩን ለማብራራት በመቻላቸው ሲኖዶሱ አባ አብርሃም ቤቱን እንዲመልሱ አዟል።