Friday, May 4, 2012

አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ

በዋናነት ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” የሚባለው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ ይፋ አድርጓል።   በዲ/ን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል
 

በይበልጥም የኬብል ቁጥር 
ADDIS ABAB 00000451  002 OF 003  የሚለውን ይመልከቱ!!

 
በርካታ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ  እና በአካፋ ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል።

 ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ሚና እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ብዙዎቻችን አናውቅም። መንግስት ፓለቲካው ላይ ያለውን ፍለጎት በሌላ መንገድ እንዳይጠረጥረው ከመንግስት  ጋር የመንግስት ሰው መስሎ ለመስራት ይሞክራል። ከተቃዋሚዎች ጋር ደግሞ እነርሱን መስሎ ይመላለሳል። ይህን እውነት ምርጫ 97 ላይ የማኅበሩ አመራሮች ከቅንጅት ጋር የነበራቸው ግንኙነት በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ደግሞ እነርሱ esat esat ደግሞ ደጀ ሰላምን እየጠቀሱ የዋልድባን ነገር ለማጮህ የሚሄዱበትን መንገድ ማስተዋል በቂ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ማህበሩ ከውጭ አገር መንግስታትና ከሲ አይ ጋር ያለው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ እንደሆነ አናውቅም ነበር። እድሜ ለዊኪ ሊክስ እውነታውን አውቀናል። ይህን ነገር እኛ ብንዘግበው ውሸታም ትሉን ይሆናል። ዊኪ ሊክስ ግን ነገሩን ያገኘው ከአሜሪካ መንግስት ምስጢራዊ ፋይሎች ውስጥ ነው። የአሜሪካ መንግስት ወሬ አቀባይ አድርጎ ባያብል ሙላቱ የሚባል ሰውን እንደሚጠቀም ነግሮናል።
 ወሬ በማመላስና በመቅለስለስ ልዩ ችሎታ አለው የሚባለው ባያብል ባለፈው የጥቅምት ሲኖዶስ ላይ እንቅልፍ አጥቶ የማቅን አጀንዳ ለማስፈጸም አንዳንድ አባቶችን ከመግባባት አልፎ መመሪያም በመስጠት የስብሰባውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲደክም እንደነበር ይታወቃል። አንዳንዶች ከኋላ ሆኖ የሲኖዶስን ስብሰባ ለመምራት የሚሞክርደፋርሰው ነው ይሉታል። ባያብል የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን በሚመለከት የአሜሪካን መንግስትን በራሱ አቅጣጫ (ማኅበሩ በሚፈልገው መንገድ) ይመራው እንደነበር የዊኪ ሊክሱ ዘገባ ያስረዳል። ይህ የዲ/ ሙሉጌታ ጽሑፍም ይህን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችን ያስነብበናልና በትኩረት እናንብበው።

የጽሑፉ ዓላማ: "ማህበረ ቅዱሳን" በመባል ስለሚታወቀው ሀገር ለባዕዳን አሳልፎ የመስጠትና የማውደም ልዩ ተልዕኮ ያለው ድርጅት አባላት እነማን ናቸው? በምን ዓይነት የስራ ድርሻስ ተሰማርተው ይገኛሉ? የሚሉትንና ሌሎች በርካታ አንኳር ጥያቄዎችን ከወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ጋር አገናኝቶ ያብራራል:: ርእሱን ማዕከል ያደረገ ከፊል የጸሐፊው እውነተኛ የህይወት ምስክርነትም በጽሑፉ መግቢያ ላይ ተካቷል:: መልዕክቱን በእርጋታ ያንብቡት፡፡ ሀገርን ከእውነተኛ መሳይ አጥፊ ቡድን ለመታደግም የድርሻዎትን ይወጡ::
ወቅቱ በሀገራችን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ታህሳስ 2000 / ነበር፡፡ ጊዜው አመሻሹ ላይ 12:30 ይሆናል፡፡ ራዚል ካፊቴርያ (መኻል ፒያሳ) "ለአንድ ጉዳይ እፈልጋለሁ እባክህ" ተብዬ ነበር ከአንድ የቀድሞ ወዳጄ የጠበቀ ተማጽኖ ቀርቦልኝ ወደ ስፍራው ያቀናሁት:: በስፍራው ላይ ተገኝቼ ወንድማዊ ሰላምታ እንደተለዋወጥንም "እንዲህ እንኳን ተፈላልገን አናውቅም፡፡ ወደ 6 ወይም 7 ጊዜ ነው የደወልክልኝ በደህና ነው? የፈለግከኝ ለምንድር ነበር?" የሚለው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር:: ለጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ አስተናጋጅዋ ትደርስናምን ልታዘዛችሁ?” በማለት ከፊታችን ትቆማለች:: አስታውሳለሁ ወቅቱ የጾም ወቅት ነበር ታዲያ ይህ ወዳጄ "አይ! እኔ .." በማለት የጀምርኩትን ንግግሬን ያቋርጥና "ለእሱ ወተትና ለስላሳ ኬክ ለእኔ ደግሞ ቀጭን ሻይ አምጪልኝ" ይላል:: ደግሜ "አይ እኔ ምንም ነገር አልወስድም ይልቁንስ በጊዜ የፈለግከኝን ጉዳይ ንገረኝና ወደ ስራዬ ልሂድ እለዋለሁ" አስተናጋጅዋ እንደቆመች፣ እሱም አበክሮ እኔ የማዝልህን ካልጠጣህና ካልበላህ ብሎ የሙጥኝ ብሏል:: አማራጭ አልነበረኝም ፊቴን ወደ አስተናጋጅዋ በማዞር "የእኔ እህት እኔ ምንም ነገር አልወስድም ለሱ ግን ትእዛዙን አምጪለት" በሚለው ተስማምተን ስናበቃ አሁንምእንዲህማ አይሆንም ጋባዡ እኔ ነኝበማለት ነገሩን ሲያስረዝም "ስትስማሙ ጥሩኝ በማለት" አስተናጋጅዋ ሄደች::
"የጠራኸኝ ለምን ጉዳይ ነበር?"::አልኩት። አሱም  "አዎ! ነገሩ እንኳን የተወሳሰበ ነው" በማለት ይጀምርና እያለቃቀሰ ከአስር አመታት በፊት የነበረችውን የሴት ጓደኛውን ታሪክ አንስቶ ብዙ የግል ጉዳዮቹን ካወራ በኋላ በአሁን ሰአት የሚከፍለው የቤት ኪራይ ገንዘብ፣ የሚበላው ምግብ ጭምር እንደቸገረው ይገልጽልኛል:: አክሎምአንተን ለማግኘት ከኮልፌ ፒያሳ ድረስ የመጣሁት እንኳን በእግሬ እያቆራረጥኩ ነው::” ይለኛል፡፡ እኔ ደግሞ በበኩሌ ከእኔ የሚፈልገውን በአጭሩ ይገልጽልኝ ዘንድ "ታዲያ አሁን ከእኔ የምትፈልገው ምንድነው? ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?" ስል ጠየኩት::
ቋንቋው ስለገባኝ ነገሩን ራሴ ላሳጥረው በማለት "ምን ያህል ነው የሚያስፈልግህ?" አልኩት:: “ወዳጄሆዬ በጉዳዩ ሳይሆን በመልእክተኝነት ነበር የጠራኝ፡፡ በድጋሜ ስልኩ ይጮኸል (ቀደም ብሎም ሁለት ጊዜ ጠርቶ የካፊቴሪያው ጫጫታ አላሰማ ብሎኛል በማለት ወደ ውጭ ወጥቶ ሴኮንዶችን አነጋግሮ ተመልሶአል እኔምየጠራኸኝ አንተ ነህበማለት ስልኩን እንዲዘጋ ብጠይቀው የመለሰልኝ መልስይረዱኝ ዘንድ የደወለኩላቸውን ሰዎች እየጠበኩአቸው ስለሆነ ነው ይቅርታሲል ምላሽ ሰጠኝ:: እዚህ ላይ አንድ ነጥብ ማብራራት እፈልጋለሁ ይኸውም ወተትና ኬክ እንድበላና እንድጠጣ ግድ ያለኝ በጾም ወቅት ገደፈ ብሎ በመረጃ በማስደገፍ እኔን በአደባባይ ለማሳጣት ነበር::
በዚህ ሰዓት ልቤም እአምሮዬም ብቻ ሁለመናዬ ወትሮ ከማውቀው በላቀ ነቃ ብሏል:: ስሙን ጠርቼም "ትሰማኛለህ ለእኔም ቤቱ ስላልተመቸኝ ቦታ እንቀይር ብዬ ብደግ አልኩ" "እሺ እዚህ አጠገቡ ወዳለው ካፌ እንሂድ" በማለት ሻንጣዬን ከእጄ ነጥቆ ቀድሞኝ ወጣ:: ወደ ቤቱ እንደገባንም ገና ሳንቀመጥ "ይህማ የባሰበት ነው" በማለት ቀድሞኝ በመውጣት ወደ ራዚል መለሰኝ:: ወደ ወጋችን ተመልሰን ሳንገባም ለአራተኛ ጊዜ ስልኩ ጠራ:: እርሱም ገና አንድ ጊዜ እንደጠራ ቃል ካፉ ሳይወጣ ጥርቅም አድርጎ ዘጋው፤ (ኮድ መሆኑ ነው) አንድ ደቂቃ በማይሞላ ልዩነት ውስጥ አራት የሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች (የመንግስት የደህንነት አባላት መሆናቸው ነው) ወደተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ድረስ በመምጣት በቁጥጥር ስር እንደዋልኩና ምንም ነገር ለማድረግ ሙከራም ማድረግ እንደሌለብኝ፣ ተነስ ስባል ብቻ ተነስቼ ከካፍቴራው በር አጠገብ መጥታ በምትቆመው መኪና መግባት እንዳለብኝ በትእዛዝ መልክ ነገሩኝ:: ትዕዛዙ ከዚህ ትእዛዝ ያለፍኩ እንደሆነ በራሴ ላይ እንደፈረድኩ የሚያሳስብ ቃል ሁሉ ታክሎበታል::
በዚህ ተስማምቼ መኪናዋ እስክትመጣ ድረስ ለጥቂት ደቂቃዎች በአግራሞት ዓይኖቼን እንደ ዓይን ብሌን በጠራው መስተዋት አሻግሬ ወደ ውጭ ሳማትር ዓይኔም ቢሆን አልቀናውም:: በር አጠገብ ኩልኩል ብለው የቆሙት አራቱ ባያብል ሙላቱ የሚገኝበት በወቅቱ የማህበሩ ሰብሳቢና ዋና ጸሐፊ የነበሩትን ሳምሶንና ግርማ መታፈሪያን አራተኛውን ስሙን ለጊዜው ማስታወስ አልቻልኩም የማህበሩ (የማህበረ ቅዱሳን) ከፍተኛ የስራ አመራር አባል ዓይን ዓይኔን ያዩኛል:: እናማ መኪናዋም መጣችወዳጄምለበላተኛ አውሬ አስረክቦኝ ቀድሞኝ በመውጣት ከማህበሩ አባላት ጋር ቆሞ ያየኝ ጀመር:: በግራም በቀኝም ከፊትም ከኋላም ተከብቤ ከካፍቴሪያው እንደወጣሁም፣ ደህንነቶቹ የያዙት ሰው በትክክል የሚፈለገው / ሙሉጌታ ወልደገብርኤል የሚባለው ሰው ለመሆኑ ሲጠይቁ ከሁሉም ቀድሞ ፊት የቆመው ባያብል ሙላቱ ራሱን ነቅነቅ አድርጎ አረጋገጠላቸው "ግባ ምን ትጠብቃለህ" ተብዬ ወደ መኪናዋ አስገብተው ፒያሳ ወደሚገኘው 3 ፖሊስ ጣቢያ የነፍስ ግድያ ምርመራ ክፍል አስረክበውኝ ተለያየን፡፡
ከዚህ ቀደም "ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?" የሚለውን ክፍል አንድ መጽሐፌን እንዳሳተምኩ 24 ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውዬ (በማህበረ ቅዱሳን ከሳሽነት) በተለምዶ ገዳም ሰፈር በመባል በሚታወቀው ፖሊስ ጣቢያ ለሦስት ቀናት ከርሜያለሁ:: ቆይቼም አደገኛ ቦዘኔ ተብዬ ከሰሜን ሆቴል ማዶ ወደሚገኘው አንድ ማጎሪያ ጣቢያ ወርጃለሁ:: በዚህ ሁሉ ጎብኝዎቼ በባያብል ሙላቱ የሚመራ የማህበሩ የጀርባ አጥንት የሆኑ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት ነበሩ:: ልብ ይበሉ! ጉብኝቱ ራርተውልኝ ስንቅ ለማቀበል ሳይሆን ከእኔ አልፈው የጣቢያዎቹን አዛዦች ለማስፈራራት ጭምር ነበር::
ይህ ሰው (ባያብል ሙላቱ) እንዲህ ያለ የሽፍታ ስራ በመስራት እጅግ የታወቀ ነው:: በጠቅላይ ቤተ-ክህነት አከባቢም ቅጽል ስሙ "የቀን መጋኛ" በመባል ይታወቃል:: “የሌሊቱስ ማን ነው?” ያሉ እንደሆነ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት የሌሊት ዘቦች ነገሩን ቢተርኩት በእነርሱ ያምራል:: ውድ አንባቢ! የፈቀዱልኝ እንደሆነ የሰማሁትንና ሁሉ የሚያውቀውን ታሪክ በአጭር እንደሚከተለው ልተርክልዎት::
"ስሙ አይጠራም!" ይላሉ ጨዋታውን ሲያደምቁት:: አንዳንድ ጊዜ ጥቁር ካባ ለብሶ ዘውድ ደፍቶ ከታች ወደ ላይ ከላይ ወደ ታችም ይመላለሳል:: ደግሞም ወቅት አለው ይላሉ ጦር ይዞ፣ ህጻን ልጅ ታቅፎ የሚንቀሳቀስበት:: አንድ ጊዜ ይህን ያጫውተኝ ለነበረ ወዳጄ "ስፍራው ቤተ-ክህነት አይደል መልአክ ቢሆንስ" ስለው "ሲጋራ ያጨሳል አሉ" ብሎ እርፍ አለ:: በተለይ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ልዩ ዝግጅት ሲኖርና በታላላቅ ክብረ በዓላትማ ብርሌ አንቆ (“ጠጅእየጠጣ መሆኑ ነው) እሳት ሲሞቅ ነው የምናየው
በማለት የሰሚን የልብ ትርታ ይጨምራሉ:: ልብ ይበሉ: ካርታም ይጫወታል!
አንዳንድ ጊዜም በቁጥርም በርከት ብለው ከታች አከባቢ (አዲሱ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ህንጻ በቆመበት ማለት ነው) እሱን የሚመስሉ በቁመታቸው አጠር ያሉና መጠነኛ የሰውነት ቅርጽ ልዩነት የሚስተዋልባቸውን በግራ በቀኙ አቅፎ የሰው አይሉት የጅብ ዓይነት ሳቅ እየሳቁ ወደ ሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ቤት ሲያመራ እናየዋለንም ይላሉ:: ወደ በር አከባቢ የሚመጣበት ወቅትም እንዳለ ይናገራሉ::
በነገራችን ላይ እሳቱ የሚነድበት ስፍራ ላይ ዓመድ ያገኙ እንደሆነ በተደጋጋሚ በቀን ለማረጋገጥ ቢሞክሩም ምንም አዲስ ነገር እንደማያገኙ ይናገራሉ:: ታዲያ በዚህ የማይያዝ የማይጨበጥ ፍጥረት ግራ የተጋቡ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዘቦች እናቱ እንደጠፋችበት ቡችላ ከቤት ወደ ቢሮ ከቢሮ ወደ ቢሮ የሚተላለፈውን ሊቀ ጳጳስና መነኩሴ ሲሸኝና ሲያመላልስ ወዲያ ወዲህ ሲል ጸሐይ የምትጠልቅበት ሰው ነው ይሉታል፡፡ባህሪውን በሚገባ የሚያውቁት እነዚህ ሰዎች ፈልገው ከጠቅላይ ቤተ-ክህነት ቅጽር ግቢ የማያጡት ባያብል ሙላቱን "የቀን መጋኛ" በማለት ሰይመውታል::
ከጥቂት ጊዜያት በፊት አቢይ አፈወርቅ በተባሉ አንድ ጸሐፊ "የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዊክሊክስ ፋይሎች" ሲሉ ከአንዳንድ የኢንግሊዝኛ ሰነዶች ያገኙትን መረጃ ወደ አማርኛ በመመለስ ለንባብ ባበቁት ጽሑፋቸው ውስጥ ባያብል ሙላቱ ተብሎ ስለሚታወቀው ማህበሩን ለበርካታ ዓመታት በመምራት ስለሚታወቀው "የማህበረ ቅዱሳን" ከፍተኛ የስራ አመራር አባል ምስጢራዊ የስራ ድርሻ እግረ መንገዳቸውን እንደሚከተለው አጋልጠዋል::
"እንዲያውም ከሁለቱ ፓትርያርኮችና ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያለው ባይብል ሙላቱ የተባለው ታዋቂ ባንከኛ ከኤምባሲው የፖለቲካ ኦፊሰር ጋር ፌብሩዋሪ 7 ቀን 2007  ተገናኝቶ በሁለቱም ቤተክርስቲያናት መሀል ኦፊሽያል ያልሆነ ግኑኝነት ሲያደርግ መቆየቱን መስክሯል፡፡አክሎም "ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱ በሁለቱም ወገኖች መኸል ኦፊሽያል ያልሆነና በገለልተኛ ሰዎች መልእክት አስተላላፊነት የሚካሄድ ቋሚ ግኑኝነት እንደነበረው ነግሮናል::" (ገጽ 2)
1. ይህ ሰው ለኤምባሲው ከሁለቱ ፓትሪያሪኮች ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለኝ ሲል መናገሩ ከቅጥፈትም በላይ ወንጀል ነው:: ከአስርት ዓመታት በላይ እንደ ኪሩቤል ሰይፍ እየተገለባበጠ ከስልጣን ካብ ሳይወጣ በበላይነት የሚመራው ማህበር በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት እንደሌለው እየታወቀ እንዲያውም በአንጻሩ "መናፍቃን" ናቸው እያለ በሬ ወለደ ወሬውን በሚነዛባቸው ጋዜጦቹና መጽሔቶቹ እየዘመተባቸው የጠበቀ ግኑኝነት አለኝ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲን ማደናገሩ የማይነጋ መስሏት እንደሚባለው ነው፡፡
ይህን በተመከተ በውጭው የሚገኙት የሃይማኖት መሪዎች መልስ ቢሰጡበት የበለጠ ግልጽ ይሆናል:: በተረፈ ግን ባያብል ሙላቱ ማለት ከወንጀለኛም በላይ ሀገር ሻጭ ባንዳ መሆኑን ሁሉ ያውቀው ዘንድ ይገባል:: በሀገር ድህንነት ጉዳይ የሚመለከታቻቸው አካላትም ይህ በቀላሉ የሚታለፍ አጀንዳ ባለመሆኑ ነገሩን ትኩረት ሰጥተው እርምጃ ይወስዱበት ዘንድ በዚህ አጋጣሚ እጠይቃለሁ::
2. ይህ ሰው ማንን ወክሎ ማንስ ቢልከው ነው የቤተክርስቲያንን የውስጥ ጉዳይና መረጃዎቿን 3 አካል የሚያስተላልፈው? የሚለው ጥያቄ በቀላሉ የሚታለፍ አይሆንም:: ማህበሩን ወክሎ እንዳይባል ከሰ/// ስር የሆነው ማህበር አሁንም መምሪያው ሳያውቀው 3 አካል የመገናኘት ስልጣን የለውም፡፡ እንዲህ ዓይነት የዱላ ቅብብሎሽ እንዳለም ቤተ-ክርስቲያን የምታውቀው ነገር አለመኖሩ ጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንደሚሻ የሚያመላክት ነው፡፡ ተቀጥሮ መስራት አይችልም ወይ ለሚለው ምስጢሩ በአደባባይ ተገለጠ እንጂ ሌባም እስኪያዝ ድረስ ንጹህ ነው፡፡
3. “ታዋቂ ባንከኛየምትለዋን Martin Lawrence "Blue Streak" የተሰኘውን የአሜሪካ ሙቪን አስታውሶኛል:: ፊልሙን ከዚህ ቀደም ላያችሁት ምን እያልኩ እንደሆነ ግልጽ ነው:: እዚህ ፊልም ላይ ማርቲን ፍቅረኛውን የተዋወቃት የባንክ ባለ ሞያ ሆኖ ሳለ ነበር፡፡ ውሎ አድሮ የማይገለጥ የለምና በአንደበቱም እንዳረጋገጠላት ለካ ታዋቂ ካዝና ቦርቧሪ/ዘራፊ ሆኖ ኖሯል፡፡
አቢይ አፈወርቅ አሁንም በመቀጠል እንዲህ ይተረጉማሉ፡፡
 "አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችንና የቤተ-ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ያካተተ 20 ሰዎች ያሉበት ቡድን ለማደራደር ያደረገው ሙከራ መክሸፉን ያስታወሰው ሪፖርቱ፣ ግዝቱን በተመለከተም ውስጥ አዋቂ የሆነውና ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱ ያቀረበውን ትችት አጣቅሷል::"[1] ይልና ትችቱን በዚህ መልክ ያስቀምጠዋል "የሀይማኖትን ማእረግ መግፈፍ ማለት ልክ አንድ ሰው ከፖለቲካ ስልጣኑ እንደማውረድ ቀላል አይደለም:: ይህ ከአሁን በፊት ተወስዶ የማያውቅ ግዙፍ ርምጃ ነው:: ምክንያቱም ሹመቱ የእድሜ ልክ ነውና ብሏል::
ክህነትን ከፖለቲካ ጋር በማነጻጻር ሰው በፖሊቲካ አለም ቢያጠፋ ተመልሶ ወደ ስልጣን መምጣት/ወውጣት እንደሚችልና እንደሚቻል ሲናገር፣ የሃይማኖት ነገር ግን የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም እንደማለት ነው በማለት ይገልጸዋል:: ይህ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ነው ሲል በሪፖርቱ ነጮችን ሲያደናግር እናገኘዋለን:: እውነት ነው ክህነት ለዘለአለም ነው:: ግንብ አይደለም የሚፈርሰው! እንደ መጽሐፍ ቅዱስና እንደ ////ያን ስርዓተ ትምህርት አንድ ካህን ከክህነት አገልግሎት ሊያጎድለው የሚችለውን ስራ ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ በመሪዎች/አባቶች በሚሰጠው ቀኖና ለተወሰነ ጊዜ ከአገልግሎት ታግዶ ይቆያል:: የተሰጠውን የጾምና ጸሎት ጊዜ ገደብ ሲያገባድድም ወደ ቀድሞ ማዕረጉ ተመልሶ/በመመለስ አገልግሎቱን መስጠት ይቀጥላል:: ማቴ. 18:18 ላይ ቢመለከቱ ማሰር ብቻ ሳይሆን የታሰረም መፍታት እንዳለ ነው የሚያስተምረው፡፡ የዚህ ሰው ትንታኔ ግንየቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሐፍ አጠበችነው የሚያሰኘው::
ባያብል የእርቅ ሙከራውን በተመለከተ ደግሞ እንዲህ ይላል
 "የኢ/// 2 ሺህ ዓመታት ታሪኳ አይታው የማታውቀው አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባችው፡፡ ይህንን በሁለቱ ወገኖች መሀል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ምንም እንኳን በርካታ ታዋቂ ሰዎች ቢጥሩም ሁኔታው ከመስከኑ በፊት እየባሰበት መሄዱ አይቀርም አለ::" ይላል በገጽ 3 ላይ፡፡
ኤምባሲው አንዴ ተታሏልናታድያ አንተ ምን ትላለህ?” በማለት ውስጠ አዋቂ ነኝ ባይ ኪስ አውላቂውን ባያብል ሙላቱን መጠያየቃቸው አሁንም ባያስወቅሳቸውም የሰጠው መልስ ግን መመርመሩ ግድ ነው:: እንዲህ ላለ ጽንስን የሚያስወርድ/የሚያስጨነግፍ የማያምን ምላስ መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ እስኪታይ ድረስ ምላስህ ከትናጋህ ጋር ይጣበቅ ነው የሚለው:: ለበለጠ መረጃ የሉቃስ ወንጌል 1:20 ይመልከቱ::
ማሳሰቢያ፦
ኤምባሲው በየጊዜው ለበላዮቹ በሚልካቸው ሰነዶች ተሳስቶ ስለሚያስት አሳች ባያብል ሙላቱ ከተባለ "የማህበረ ቅዱሳን" ከፍተኛ የስራ አመራር የሆነው ግለሰብ የነበረውን ድብቅ/ምስጢራዊ ግንኙነት በተመለከተ ጻፍኩ እንጂ ስለ ተጠቀሰው የመረጃ መርበብ/ሚዲያ በቤተ-ክርስቲያን ላይ የተጻፈውን ዘገባ ተቀባይነት አለው - የለውም እያልኩ እንዳልሆነ አንባቢ ይገነዘብልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America
[1] ሰነዱ በተደጋጋሚከኤምባሲያችን ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱሲል ምን ማለት እንደሆነና ምን ዓይነት የስራ ድርሻ እንደሚያመላክት ልብ ይበሉ:: ያልሰማ ይስማ የሰማ ያሰማ!__
http://awdemihret.blogspot.com