Saturday, May 12, 2012

የሲኖዶስን ውሳኔ የሚያወራ ግን እሱ ሊፈጽመው የማይፈልግ፣ በሌሎች ላይ ለመጫን የሚሮጥ አፄ በጉልበቱ ማኅበር ብቻ ነው!



ቅዱስ ሲኖዶስ ባሳለፈው የ2002 ውሳኔ እንደተመለከተው መጻሕፍት፤ መጽሔት፤ የመዝሙር ካሴት፤ ሲዲ፤ ቪሲዲ፤ በአጠቃላይ የድምጽና የህትመት ውጤቶችን ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም አሳትሞ ለማውጣት በቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጉባዔ በኩል አስመርምሮና የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት ጠብቆ ለመሆኑ ሲፈቀድለት ብቻ እንዲሆን አስረግጦ ይወስናል። ይህንኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የማኅበሩ አፈ ጉባዔ የሆነው ደጀ ሰላም ብሎግ «እሰይ ቅዱስ ተግባር» በማለት ድጋፉን በድረ ገጹ ላይ በግንቦት 10/2010 ዓ/ም ጽሁፉ ያወጣል። ይህንኑ በማኅበሩ አፈ ጉባዔ «ደጀ ሰላም» አድናቆት የተቸረውን  ውሳኔ ተከትሎም አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል  የማደራጃ መምሪያ ኃላፊው የማቅ  የ20 ዓመት ልሳኖቹና ሌሎች ህትመቶቹን ሁሉ  በሊቃውንት ጉባዔው በኩል እየተመረመረ እንዲወጣ ትእዛዝ ይሰጣሉ።  አፄ በጉልበቱ ማኅበርም ጆሮ ዳባ ልበስ ይልና በነበረው መልኩ ኅትመቶቹን በጓሮው  እያሳተመ ይቸበችባል።  አባ ሠረቀም የሲኖዶስ ውሳኔ ተከብሮ ለሕትመት ማለፍ በሚገባው መንገድ ለመሄድ ባለመቻሉ የአፄ በጉልበቱ ማኅበር ደንበኛ  ለሆነው «ሜጋ ማተሚያ ድርጅት» ምክንያቱን ጠቅሰው የአፄው መጽሔቶች መታተም እንደሌለባቸው ማገጃ ይጽፋሉ።
አፄ በጉልበቱ፤ «አሁን በዓይኔ መጣህ!» ይልና ሀገር ይያዝልኝ በማለት ቀውጢ በማድረግ አቧራ ያስነሳል። የአፄ በጉልበቱ ጉዳይ ፈጻሚ የማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በግላቸው ቲተር፤ ማመልከቻቸውን ለሥራ አስኪያጁ በማስገባት እግዱ እንዲነሳና ህትመቱ እንዲቀጥል አቤቱታቸውን ያቀርባሉ። እንግዲህ ይታያችሁ!! ሲኖዶሱ በሊቃውንት ጉባዔ በኩል ማንኛውም ህትመት ተመርምሮ እንዲያልፍ መወሰኑን ልብ በሉ!! በውሳኔው ላይ የነበሩት ሊቀጳጳስ ግን ለአፄው ሲሆን እንዲሻር በደብዳቤ ጭምር የሚጠይቁበት ቤተክህነት መሆኑንም አስተውሉ!!  እነ በጋሻው፤ ትዝታውና ምርትነሽ ላይ ሲሆን የሲኖዶሱን ውሳኔ ጥሰዋል እያለ የሚጮኸው አፄ በጉልበቱ ህግ ማስከበሩ በእሱ ላይ ሲመጣ ግን ተላላኪ ጳጳሶቹን ሳይቀር ተጠቅሞ ህግ መሻር እንደሚችል ስንመለከት ከመግረም አልፎ ያሳዝናል።
አፄው በማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በኩል ያቀረበው ማመልከቻ፤ የአባ ሠረቀ ብርሃን  የማገጃ ደብዳቤ እንዲነሳ ከመደረጉ በፊት ህትመቱ  በጓሮ ማተሚያ ቤት ታትሞ ገበያ ላይ ይውላል። እንግዲህ የሲኖዶስ ውሳኔ ውሃ በላው ማለት ነው። ሊቃውንት ጉባዔም  የአፄውን ኅትመቶች ለመመርመር እንደተመኘ አፉን ከፍቶ ቀረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ቤተክህነቱ ለእውነት የቆመ መስሏቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ሕግ ይከበር በሚል አቋማቸው ሲዳክሩ አፄ በጉልበቱ ይህንን ሰውዬ ከዚህ ቦታ ካላሽቀነጠርኩት ይልና «የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶና የሙስና ምሕዋር» የሚል ታርጋ ይለጥፍና ዘመቻውን አጧጥፎ አባ ሠረቀን ያስነሳል። አፄውም በትግሉ ውጤት «እፎይ» ብሎ በመተንፈስ «ድሮስ ከእኔ ጋር መወዳደር ለመላላጥ!» በማለት በአባ ሠረቀ ድካም ላይ እንደተሳለቀ  እኛም ግምታችንን አኑረናል። አባ ሠረቀ ብርሃን ለጻፉት ደብዳቤና በአፄው ላይ ህግን ለማሳየት በመጣራቸው የተሰጣቸው ስም ይህንን ይመስላል።
አፄው በሀሰት ስብከቱ ያሰከረው ምድረ ደጋፊ ሁሉ በአባ ሠረቀ መነሳት «እልል!» በማለት ድጋፉንና ደስታውን ለመግለጽ ጊዜ አልፈጀበትም።  አባ ሠረቀ ግን የአፄው ዱላና እንግልት ያረፈባቸው ሲኖዶስ የወሰነውንና ራሱ «ደጀሰላም» ብሎግ የዘገበውን መመሪያ ለመተግበር እንጂ በግል ከልባቸው አንቅተው አፄውን ለማጥቃት ያመነጩት አካሄድ አልነበረም። ይሁን እንጂ አፄው የቀኝ እጁ ጳጳሳት የራሳቸውን ውሳኔ እንኳን እስከመሻር የት ድረስ እንደሚሄዱለት በማሳየት አንድ እውነት ያረጋገጠ ነበር።
 እነ ትዝታውና ምርትነሽ እንኳን የስብከትና የዝማሬ  መድረክ ሊሰጣቸው ይቅርና አንድ የልብ ሕሙም በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ውስጥ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እነሱ ባሉበት ማድረግ እንዳይችሉ «ሮቶ» በተባለው ቄስ በኩል ጉባዔውን  በመከልከል ኃይሉን በማሳየት ለህመምተኛ እንኳን ርኅራሄ የሌለው ልቡን አሳይቶበታል። ይህንን ስንመለከት የአፄው ረጅም እጅ ከላይ እስከታች ምን ያህል የተዘረጋ መሆኑን  ነው።  ሲኖዶስ ፈቃድ ያልሰጠው እያለ ሲያላዝን እሱ ግን መልዕልተ ሕግ የሆነ ያህል ራሱን ከሕጉ አውጥቶ በነ ምርትነሽ ላይ መጮሁን ብዙዎቹ ደጋፊዎቹ «አንተ ባትኖር እኰ ቤተክርስቲያን ትፈርስ ነበር» እንዲሉ ተጽእኖ የመፍጠር አቅሙ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ  አረጋግጧል። ከዚህ በታች ያለው ጽሁፍ የሲኖዶስን ውሳኔ አፄው ስለመቀበሉ የገለጸበት አፈጻጸሙ ግን ከነበጋሻው በቀር እሱን እንደማይመለከት በተግባር ያሳየበት ሆኖ ያለፈ «የደጀ ሰላም» ጽሁፍ ነውና አንብበው እግዚአብሔርን ዳኛ አድርገው ኅሊናዊ  ፍርድዎን ይስጡ!
 /ሲኖዶስ ሰባክያንንና ዘማርያንን የተመለከተ ያወጣውን ሕግ ለሚመለከታቸው አካላት አስተላለፈ
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 10/2010) /ሲኖዶስ ባለፈው ዓመት ያወጣውን ስለ ሰባክያንና ዘማርያን የተመለከተውን መመሪያ በማጠናከር ፈቃድ ሳይኖራቸው ስለሚሰብኩ እንዲሁም በሊቃውንት ጉባዔ እና በሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ሳይታዩ ስለታተሙ ሕትመቶች ጉዳይ ለመንግሥት አቤቱታ አቀረበ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ በአዲስ ሊቀ ጳጳስ በተተኩት በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፊርማ ወጪ የተደረገውና ለበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ የተላከው ደብዳቤከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰባክያነ ወንጌል እና ዘማርያን ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ በግል ፈቃዳቸው እየተነሡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ደንብ ተጠብቆየታተመ በሚል መጻሕፍት፣ የስብከት እና የመዝሙር ካሴት፣ ሲዲ፣ በቪሲዲ በማሳተም ለሕዝበ ክርስቲያኑ እያሰራጩ ከመሆኑም በላይ በየአብያተ ክርስቲያናቱ አካባቢና በልዩ ልዩ ጎዳናዎች ላይ ትልልቅ ድምፅ ማጉያዎችን በመኪና በመትከል ድምፅ በመበከል በቤተ ክርስቲያናችን ስም እየነገዱ ሕዝቡን ግራ በማጋባት ላይእንደሚገኙ ገልጿል።
ከዚህ በኋላ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እነዚህን ሕትመቶች ሊያሰራጭ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ ከሊቃውንት ጉባዔ ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባው የሚያትተው የብፁዕነታቸው ደብዳቤ ይህንን መመሪያ ሳይከተሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ተጠቅመው የሕትመት ውጤቶችን ለሚያሰራጩ በሙሉ ግን ኤጀንሲው ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጥ ይጠይቃል።
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጥያቄ ሥራ ላይ የሚውል ከሆነ፦
1.      ማንኛውም ሰው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት እና ከየአህጉረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት የስብከተ ወንጌል ፈቃድ ከሌለው መስበክ አይችልም፣
2.     በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም መጻሕፍትም ሆነ የኦዲዮ/ቪዲዮ ሥራዎችን ማሰራጨት በሕግ ያስጠይቃል ማለት ነው።
/ሲኖዶስ ይህንን መመሪያ ባለፈው ዓመት የካቲት 2001 . ባደረገው ጉባዔ ያስተላለፈው መሆኑን ማስረጃዎች ቢያመለክቱም እስካሁን ድረስ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል። ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ዓመታት ሰባክያንን የተመለከቱ መመሪያዎችን የማውጣትና የማስተላለፍ ልምድ ቢኖረውም ራሱ /ሲኖዶሱ የሚያወጣውን ሕግ በተዋረድ ያሉ አህጉረ ስብከትና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሮች ስለሚጥሱት መመሪያዎቹ የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን አልፈው አያውቁም ነበር። ይህ አዲሱ መመሪያ ከወረቀት ነብርነት አልፎ ትርጉም ያለው ሥራ ይሠራ እንደሆነ በጊዜ የሚታይ ይሆናል።
Posted by DSelam DSelam
ሥራ አስኪያጁም የሲኖዶስን ውሳኔና የደጀ ሰላምን መግለጫ በመሻርና አባ ሠረቀን ለመቃወም ቀኝ ክንድነታቸውን በዚህ ደብዳቤ አሳይተዋል። ነ (ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)
 ዳሩ ግን በአፄ ጉልበቱና በአባቱ ከመፍረሱም በላይ የመምሪያውንም ኃላፊ አሸቀንጥሮ የሚጥል እርምጃንም አስከተለ።

  ሥራ አስኪያጁ የጻፉት ይህንን ደብዳቤ መልሰው ለምን ሻሩት? ለህግ የምትቆሙ ከሆነ ለተግባራዊነቱ ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር ለምን አልሰራችሁም? አባ ሠረቀ ብርሃን የተሻሩት አፄውን መፈናፈኛ ስላሳጡት ብቻ ነው እንጂ ጥፋተኛ ስለነበሩ አይደለም።
ህግ የሚሰራው ለማነው? የጉልበት ህግ ቀኑ ሲጎድል ይከዳል።
 መልስ ባይኖርም አፄ በጉልበቱን  ጎድልያድን የጣለ አምላክ እንደሚጥለውን ግን ቅንጣት ጥርጥር የለንም። የሚወድቀው ስለጠላነው ሳይሆን አንድም ቀን ለእውነት ቆሞ የማውቅና አስመሳይ ስለሆነ ሥራው ራሱ ለጥፋቱ ይከተለዋልና ነው።
የአፄው  ቀንደኛው አባል ዳንኤል የተባለው ወንበር  አስደንግጥ መምህር በሊቃውንት ጉባዔ  ስለመምህርነቱ የተፈቀደ ማረጋገጫ ሳይኖረው አዋሳ ሄዶ በስደት በተዋከበ ህዝብ መካከል ሲጮህ እንደሰነበተ (dejeselaam) ብሎግ ዘግቦ ነበር። (Click Here) 
በምን የፈቃድ ወረቀት?
እንግዲህ ሕግ፤ ሕግ እያለ የሚጮኸው አፄ በጉልበቱ ማኅበር ሕጉን የሚጠቀምበት ሌሎቹን ለመምታት፤ ለማስደንገጥና ለማንበርከክ፤ እንደሆነና ይህንንም በደጋፊ ጳጳሳቱ በኩል እስከፈለገው ድረስ መርዘም የሚችል እጁን ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር ስለእግዚአብሔር መንግሥትና ስለቤተክርስቲያን ግድ የሚለው ሆኖ አይደለም። ይህን ዳንኤል ራሱ ከማኅበሩ ጋር በገባበት የጥቅም ግጭት ወቅት እንዲህ ሲል አረጋግጦልናል።
«ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው) ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ) በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም፡፡ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሣ ቤተ ክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ»
ሲል ነግሮናል። ለነበጋሻው የሚሰራው ሕግ ለአፄው መምህራን ግን አያገለግልም ማለት ነው። በአጠቃላይ ለንግድና ለረጅም ጊዜ ዓላማው ስኬት ቀበሮነቱን በበግ ለምድ ከልሎ በየዋህ ምእመናን ልብ ውስጥ በመስቀልያ ነጭ ነጠላው ከመዘፍዘፉ በስተቀር ለህግ የቆመ እንዳይደለ ንግግሩና ተግባሩ ከምንም በላይ ያረጋግጥልናል።