Thursday, May 3, 2012

አዎ ኢትዮጵያ ውስጥ በትክክል አሸባሪነት አለ!

ሙስሊሞች ሁሉ አክራሪዎች ወይም ክርስቲያን የተባሉ ሁሉ ክርስቲያኖች ናቸው ብለን አናምን። ከሁለቱም ወገን ሃይማኖቱን ተጠግቶ የራሱን ገበያ የሚያደራና ስውር አጀንዳውን በሰው ላይ ለመጫን የሚፈልግ እንዳለ የአደባባይ እውነታ ነው።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት የፓርላማ መግለጫ ላይ በሁለት ወገን ስላሉት ሃይማኖታዊ ታዛውን የተጠለሉትን ኢትዮጵያውያን ችግር ፈጣሪዎችን ቀድሞውኑ ያወቅናቸው ቢሆንም የየግላችንን ጩኸት ከረፈደ በኋላም ቢሆን በግልጽ አውጀው ነግረውናል።
የሚገርመው ነገር ከእስላሞቹ አሸባሪዎች ወገን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድምጽ ከንቱ ስሞታ ለማለት ጊዜ ያልፈጀባቸው ሲሆን እውነታው ግን በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪነት ስለመኖሩ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሞክራት ይሆኑ አምባ ገነን ከእሳቸው ሥርዓት ጋር ሊያያዝ የማይገባውን ነገር ለማያያዝ በመሞከር ግራና ቀኝ የተቃውሞ ጅራፍ ማስጮህ በምድሪቱ ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጠው አይደለም። 


አዎ ኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪነትና ሃይማኖታዊ አክራሪነት አለ። ከእስልምናው ሰለፊያ/ወሀቢ በኩል እራሱን ቅዱስና ሃይማኖታዊ ግዴታውን እየተወጣ እንዳለ አድርጎ ለማሳየት ብዙ ድምጽ እያሰማ እንደሚገኘው ሁሉ በክርስትናው ረድፍ የተሰየመው ትንሹ አክራሪ ቡድንም መጠኑና የተሰለፈበትን መንገድ እየመዘነ ይህንን ያህል እኔን ከሰለፊያ ጋር የሚያስመዝነኝ አይደለም፤ እኔ እያደረኩ ያለሁት ቤተክርስቲያኒቱን  እየተከላከልኩ (defend) እያደረኩ ነው ቢልም እየሄደ ያለበት መንገድ የራሱን ፍላጎት በሌላው ላይ የመጫን ተግባር መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ነው። ቤተክርስቲያኒቱን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይጠብቃታል የሚባል አካል ሲኖዶስ እያለ ራሱን በራሱ ከሲኖዶሱ በላይ ተከላካይ አድርጎ የመደበ በመሆኑና  ምንም እንኳን ሰው በመግደል ጽድቅ ይገኛል ባይልም፣ ራስን ለመከላከል ሲባል በመደብደብ፤ በማሳደድ፤ በጽሁፍና በምስል አስደግፎ በሰዎች ማንነት ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ይጸደቃል የሚል አቋም ስላለው እንደሰለፊያው ከአክራሪው ተርታ ተመድቧል።  ማንም የተሳሳተ ሃሳብ ቢኖረውም  እንኳን ያንን ስህተት ወይም የእምነት አባባል በኃይል ለመጨፍለቅ ወይም ጸጥ ለማሰኘትና ለማሰደድ መሞከር በራሱ አሸባሪነት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገረ አፋቸውን በተግባር እጃቸው እንዲለውጡት ማሳሰብ የተገባ ይመስለናል። ጉዳዩ አንተን ማን ላከህ ነው? ያንተ የተከላካይነት መንፈስ በብላቴን በኩል ነው ወይስ በሲኖዶስ? በኩል  የወረደልህ ሊባል ይገባል።
ሰለፊያ/ወሀቢ ወይም ሌላም መደበኛ እስላም ከሚባልም ወገን አክራሪነት በሀገሪቱ ውስጥ ስለመኖሩ ከዚህ በታች የሚታየው ቪዲዮ ያረጋግጣል። ፓልቶክ ላይ ባለው «ኢንተር ፌይዝ» ከተባለው የአክራሪዎች መድረክ ላይ የተቀዳና በተለያየ ጊዜ አሸባሪዎች በኢትዮጵያ ላይ ያደረሱትን፤ ለማድረግ ያቀዱትን እና ስለ አሸባሪነት ትንተና የሰጡ ሰዎችን ንግግር የያዘ ነው። በሀገራችን ውስጥ ስላለው የእስልምና አሸባሪ ኃይል ከመንግሥት ጋር ጉዳዩን ከማያያዝ ይልቅ ጉዳዩ በትክክልም በህዝብ ላይ የመጣ አደጋ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። በፓልቶክ ስሙ «አቡ ሃይደር» የሚባለውና በመጠሪያ ስሙ «ሳዲቅ መሃመድ» የተባለው ዳዒ  ኢትዮጵያ ውስጥ ከእስልምና በቀር ሌሎቹ ከየት እንደመጡም አይታወቁም ይለናል። ምን ማለቱ ይሆን? ቤተክርስቲያን አቃጥሉ፣ ለኩሱ የሚሉ ዳዒዎች አሸባሪዎችም እዚያው ይገኛሉ። 
ቪዲዮው ለእይታ የማይመች ምስሎች እንዳሉት ለማስገንዘብ እንወዳለን።