እንደሚታወቀው
የቆንጆዎችና የዓለመኞች ኢንተርቴይንመንት ማስታወቂያ በሆነችው «ዕንቁ» መጽሔት ላይ ጭቃ ጅራፉን ሲያጮህ እንደቆየው ሁሉ ዛሬ ደግሞ የሲኖዶስ ጉባዔ ሲቃረብ ጽሁፎቹን ሀገር ውስጥ ላሉ ለጋዜጦች እየላከ «አቶ ሽብሩ/ ማቅ » ዘመቻውን
እያጧጧፈ ይገኛል። እንግዲህ ይሄ በአንድ ወገን በኢንተርኔቱ አፈ ቀላጤው «ደጀ ሰላም» በኩል የሚያሰራጨው ዲስኩር ላልደረሰው ተከታይ፤
በህትመት ውጤት በኩል እንዲደርሰው ያቀደው ሌላኛው መላ መሆኑ ነው። ምንም እንኳን ማንም ሰው በመሰለው የሚዲያ መንገድ ሃሳብን
በነጻ መግለጽ መብቱ መሆኑ ባይካድም ተመሳሳይ ጽሁፍ በተለያየ ሚዲያ ላይ ሲወጣ ጽሁፉ የራሱ መሆኑን በስሙ ወይም ከሌላ ቦታ ያገኘው
ከሆነም ያገኘበትን ምንጭ መጥቀስ የተገባው መሆኑ ከጥያቄ የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ይሁን
እንጂ በእጅ አዙር አሰራር የተካኑ አባትና ልጁ «ደጀ ሰላም» በብሎግ ያወጣውን ጽሁፍ «ፍትህ» በተሰኘው የግል ጋዜጣ ላይ ምንም ሳይጨመርበትና ሳይቀነስበት
እንዳለ ተጽፎ አግኝተናል። ደጀ ሰላምም የራሱ እንደሆነ በስሙ ሲያወጣ «ፍትህ» ጋዜጣም ያንኑ ጽሁፍ ከደጀ ሰላም ብሎግ ያገኘው
መሆኑን ሳይናገር ለህትመት አብቅቷል። አንድ ዓይነት ጽሁፍ ባንድ ጊዜ እንዴት የተለያዩ ወገኖች ባለቤት ሊሆን ይችላል? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ የግድ ነው። እስከሚገባን ድረስ «ደጀ ሰላም» እና
«ፍትህ» ጋዜጣ አንድ ተቋም በባለቤትነት የሚመራቸው እንዳልሆነ ነው። ምናልባት ከኋላ ሆኖ መረጃውን እያጠናቀረ ሁለቱንም ሚዲያ የሚመግብና የሚልክላቸው ስውር
እጅ አለ ብለን ብንገምት ግምታችን ከእውነት የራቀ አይሆንም። ምክንያቶቹን እስኪ እንመልከት።
«ደጀ
ሰላም» ብሎግ በምድረ አሜሪካ በሀገረ ስብከት ስም አቡነ አብርሃም
የገዙትን የግል መኖሪያ በቢሮነት እየተጠቀመ እንደሚገኝ ከወደ አካባቢው የተገኙ ምንጮች ባለፈው ጊዜ ጠቁመውናል። የልማትና ክርስቲያናዊ
ተራድኦ ኰሚሽን ጽ/ቤት ደግሞ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት ተገትሮ የሚገኝ እንደሆነም እናውቃለን። የዚህን መስሪያ ቤት
ትኩስ ወሬና አባ ጳውሎስ ፈጥረውበታል የሚባለውን የቼክ መፈረም እግድ ዘገባ አጠናቅሮ ላፍቶ አካባቢ ለሚገኘው የፍትህ ጋዜጣ ቢሮ እንዲሁም
አሜሪካ ለሚገኘው ደጀ ሰላም ብሎግ የሚመግብ የጽሕፈት ሼፍ አለ ማለት ነው። ያ ቡድን ደግሞ ስሙን አይጠቅም። ስሙ ስለማይጠቀስ «ፍትህ»
ጋዜጣም ስሙን አልተናገረም ወይም ሊናገር አልፈለገም። «ደጀ ሰላም» ብሎግም ማንነቱን ቢያውቅም የጽሁፉን ባለቤት ሳይጠቅስ ራሱ እንዳዘጋጀው አድርጎ አወጣው።
በዚህም
የተነሳ ፍትህ ጋዜጣ ያወጣውን ጽሁፍ፤ እንዳለ ሳይጨምርበትና ሳይቀንስበት «ደጀ ሰላም» ብሎግ መረጃ መረብ ላይ የራሱ አስመስሎ
ሰቀለው። በሁለት የሚዲያ መንገዶች አንድ ዓይነት ጽሁፍ፤ ስሙ ካልተጠቀሰ ስውር እጅ ከልማት ኰሚሽን ቢሮ ተነስቶ ለሁሉም ደረሰ
ማለት ነው።
ለመሆኑ
ይህ ስውርና ስም የለሽ እጅ የማነው?
እንግዲህ
ሰሞኑን የሲኖዶሱ አየር በትኩስ ወሬ የሚሟሟቅበት ወቅት ነው። በዚህ መሃል ነገሮችን ከወዲያ ወዲህ እያላጉ የዓላማ ትርፋቸውን ለመሰብሰብ
በዚያ አካባቢ የሚያንዣብቡ አሞሮች መኖራቸውን ከጥርጥር ባለፈ እናውቃቸዋለን።
አባ
ፋኑኤል ከአሜሪካ እንዲነሱ፣ አባ ገብርኤል ባሉበት እንዲተከሉ፤ አባ
አብርሃም ደግሞ የወጣባቸውን የንብረት አስረክብ ደብዳቤ እንዲቀለበስ የሚጥሩ፤ አባ ሠረቀ ብርሃንና በጋሻው ተሃድሶ መሆናቸው እንዲወሰን፤
አሸባሪው ቡድንም የአሸባሪነት ስሙ እንዲለወጥ፣አባ ጳውሎስ እንዲሽመደመዱ የሚፈልጉና ሌላም
ሌላም ዓላማዎች ሁሉ ያነገቡ እነማንያዘዋል ቀደም ብለው በለፈለፉት[ 1 ] እቅድ መሠረት እንዲራመድ የሚፈልግ ስውር እጅ አለ። ያ እጅ ደግሞ የሚጠቀመው፤
1/
የኢንተርኔቱ አየር እንዲበከል በደጀ ሰላምና በተባባሪዎቹ ብሎጎች
2/
የሀገር ውስጥ ካህናትና ምእመናን በውጥረት ሲኖዶሱን እንዲከታተሉ ደግሞ የግል ጋዜጦችን በመጠቀም፤
3/
በአባላቱና በግብረ በላ አባላቶቹ በኩል ደግሞ የሽብር ወሬ በመርጨት
ጳጳሳቱ ጠንክረው በመቆም ኃይላቸውን እንዲያሳዩ በተቃራኒው ደግሞ አባ ጳውሎስ አሞታቸው ፈስሶ እጅ እንዲሰጡ ለማድረግ
ሚዲያዎችን እንደመጮኺያ መንገድ የሚጠቀመው ስውር እጅ «ማቅ» የተባለው የሀገር ቤቱ ጢም የሌለው አልቃኢዳ ቡድን ነው።
ከአላማው እና ከእቅዱ ስፋት አንጻር ያ
ስውር እጅ መጠቀሙን የሚጠቁሙን አንድ ዓይነት ጽሁፍ በአንድ ጊዜ፤ ስሙ ሳይናገር ማውጣቱ ነው። አሸባሪ ደግሞ ስሙን አይጠቅስም። ስሙ ከጠቀሰ እንዴት ማሸበር ይችላል?
በደጀ ሰላምና ፍትህ ጋዜጣ ላይ የወጣው የስውሩ እጅ ተመሳሳይ ጽሁፍ እነሆ ቀርቧል።ያንብቡት!
በደጀ ሰላምና ፍትህ ጋዜጣ ላይ የወጣው የስውሩ እጅ ተመሳሳይ ጽሁፍ እነሆ ቀርቧል።ያንብቡት!
ደጀ ሰላም
የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔና የኮሚሽኑን አሠራር በመጣስ የኮሚሽኑን ሊቀ ጳጳስ ከቼክ ፈራሚነት ሰርዘዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 3/2004 ዓ.ም፤ May 11/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)
ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከቼክ ፈራሚነት ለማንሣት በስውር በጠሩት የቦርድ አባላት ስብሰባ ተላለፈ የተባለን ውሳኔ ሕጋዊ ልባስ በማድረግ ከኮሚሽኑ ደንብና መመሪያ ውጭ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስና ኮሚሽነሩ በጣምራ ቼክ እንዲፈርሙ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ልከዋል፡፡ ቼክ ከመፈረሙ በፊት ግን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ደብዳቤውን አግኝተው በማገድ ቅዱስ ሲኖዶስ በ2000 ዓ.ም ያወጣውን ሕገ ደንብ እንደሚፃረር በመጥቀስ ለኮሚሽነሩና ለማኔጅመንት አባላት ጽፈዋል፡፡ ይኹን እንጂ አሁንም በድጋሚ ፓትርያርኩ በቀጥታ የኮሚሽኑ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሒሳብ ለሚገኙባቸው ባንኮች በመጻፍ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ፊርማ ተሰርዞ አሠራሩ እንዲለወጥ ማዘዛቸው ነው የተመለከተው፡፡
ፓትርያርኩ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ምትክ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ከኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋራ በጣምራ ፊርማ ቼኮቹን እንዲያንቀሳቅሱ ለኮሚሽኑ ያቀረቡት ጥያቄም በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተቃውሞ ሳቢያ ተቀባይነት እንዳላገኘ የኮሚሽኑ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የፓትርያርኩ ጥያቄ ጥቅምት 12 ቀን 2000 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወስኖ በሥራ ላይ በዋለው መመሪያ አንቀጽ 17 ቁጥር 2፡- “በኮሚሽኑ ስም የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ሁሉ በኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ፣ በኮሚሽነሩና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሦስቱ በሚገኙት በሁሉ ጣምራ ፊርማ ይንቀሳቀሳሉ” የሚለውን እንደሚፃረር በመጥቀስ በኮሚሽኑ በተከፈቱ ተንቀሳቃሽም ኾነ የቁጠባ ሒሳቦች ላይ እንደማይፈርሙ ሚያዝያ 22 ቀን 2004 ዓ.ም ለኮሚሽኑ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡
የብፁዕ ዋና
ሥራ አስኪያጁ የአቡነ ፊልጶስ ተቃውሞ አላገዳቸውም የተባሉት አቡነ ጳውሎስ በቁጥር ል/ጽ/439/301/04 በቀን 29/8/2004 ዓ.ም በቀጥታ ለአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አደራት ኪሎ ቅርንጫፍ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ቅርንጫፎች፣ ለወጋገን ባንክ አክስዮን ማኅበር አራዳ ቅርንጫፍ እና ለአቢሲኒያ ባንክ ፍልውኃ ቅርንጫፍ በጻፏቸው ደብዳቤዎች “ብፁዕ አባ ፊልጶስ ሌላ ጉዳይ ስላጋጠማቸው አልተመቻቸውም” በሚል የኮሚሽኑ የፋይናንስ መምሪያ ሓላፊ አቶ ከበደ በየነ ተተክተው ከኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋራ ሒሳቦቹን በጣምራ ፊርማ እንዲያንቀሳቅሱ ባንኮቹ ትእዛዝ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተመልክቷል [በዚህ የአቡነ ጳውሎስ ጥያቄ ምክንያት ለልማት ኮሚሽኑ በመቆርቆሩ እና የፓትርያርኩን ጥያቄ ተፈጻሚ በማድረግ መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት የኮሚሽኑ ፋይናንስ መምሪያ ሓላፊ በልብ ሕመም ሳቢያ በአንድ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ መኾኑ ተሰምቷል]፡፡
ፓትርያርኩ ጥያቄያቸው ተፈጻሚ እንዲኾን ትእዛዝ የሚያስተላልፉት በኮሚሽነሩ ኮሚሽነር በዶ/ር አግደው ረዴ በኩል ሲኾን የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል በበኩላቸው የኮሚሽኑ ሥራ ሕግንና ደንብን ተከትሎ እንዲከናወን በማሳሰብ ኮሚሽነሩ ዶ/ር አግደው ረዴ “ለግለሰባዊ ፍላጎትና ሐሳብ ቅድሚያ ከመስጠትና ተባባሪ ከመኾን እንዲቆጠቡ፤ የኮሚሽኑን የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ሥራ ማስፈታት እንደሌለባቸው” መጋቢት 24 ቀን 2004 ዓ.ም እና ሚያዝያ 22 ቀን 2004 ዓ.ም በቃል እና በጽሑፍ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
«ፍትህ» ጋዜጣ ግንቦት 3/2004 እትም ላይ የሰፈረ
ተመሳሳዩን የደጀ ሰላም ጽሁፍ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ለማንበብ ( ይህንን ይጫኑ )