Tuesday, May 8, 2012

«የሁለቱ ማቆች የታክሲ ውስጥ ወግ »

                                 ምንጭ፦ደጀ ሰላዓም ብሎግ
ሁለቱ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት በትላንትናው ዕለት ሰኞ ከምሽቱ 3፡20 ሰዓት ላይ ከአራት ኪሎ ወደ ቤላ በሚሄደው ታክሲ ጋቢና ውስጥ ጎን ለጎን ተቀምጠው ወጋቸውን ይጠርቃሉ፡፡ በእነርሱ ቤት በታክሲዋ ከተሳፈሩት ሰዎች ውስጥ ከእነርሱ በስተቀር ስለቤተክርስቲያን ሚስጥርና ወቅታዊ ሁኔታ የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ያላዩት አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነና እነርሱን በደንብ የሚያውቅ ዘጋቢያችን ከጀርባቸው ልጥፍ ብሎ የሚነጋገሩትን በጥንቃቄ ያዳምጥ ነበር፡፡
ሰዎቹ ማንያዘዋልና ዘማሪ ኤፍሬም ነበሩ፡፡ ማንያዘዋል ትውልዱ ከወደ ደብረብርሃን ሲሆን፣ የዘርዓ ያዕቆብ ዘር ነኝ በሚል እየተመፃደቀ ዘወትር ነጭ በነጭ ለብሶ በመንሸራሸር ባህርይው ሰው ሁሉ ሊለየው ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የልማትና ተራድዖ ክፍል ውስጥ ሲሠራ በፈጸመው የሙስና ተግባር ከሥራው መባረሩ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ደግሞ "ማኅበረ ቅዱሳን" በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አካባቢ የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር ተጠሪ እንዲሆን አስመድባው እዚያ ላይ ሆኖ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤፍሬም የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባል ከመሆኑ በስተቀር ይህን ያህል የሚታወቅበት የጎላ ገጽታ የለውም፡፡
ታዲያ እነዚህ ሰዎች ቅድስት ማርያም ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት አካባቢ ወዲያ ወዲህ ውር ውር ሲሉ ውለው የዕለት ውሏቸውን ታክሲ ውስጥ ሆነው ከገመገሙ በኋላ ወደ አንድ ጠቃሚ አጀንዳ አመሩ፡፡ ሃሳባቸውን በጥያቄና መልስ መልክ ይለዋወጡ ጀመር፡፡
ኤፍሬም ጠየቀ:- «ስማ ማንያዘዋል ተነገ ወዲያ (ግንቦት 1 ቀን   2004) የሚከፈተው የሲኖዶስ ጉባዔ ትንሽ ከበድ የሚል አይመስልህም»?
ማንያዘዋል:- «ምን ይከብዳል? ሁሉም ከልኩ አያልፍም»፡፡
ኤፍሬም:-  «ማለቴ፣ ጠንከር ጠንከር ያሉ ውሳኔዎች  ሳይወሰኑ  አይቀርም ብዬ እገምታለሁ»፡፡
ማንያዘዋል:- «ምን ውሳኔ ይኖራል? ሁሉም ነገር ተመቻችቷል፤ ምንም አዲስ ነገርአይኖርም»፡፡
ኤፍሬም:- «እንዴት እንደዚያ ትላለህ? ሁሉም ነገር እየሰማነው ነው እኮ»!!
ማንያዘዋል:- «ይሄ እኮ ሊያስጨንቅህ አይገባም፡፡ እምቢ ካሉ የ2001ዱን እንቅስቃሴ መድገም ነው»፡፡
ኤፍሬም:- «እንዴት»?
ማንያዘዋል:- «በ2001ዱ የሲኖዶስ ጉባዔ ሊቃነጳጳሳቶቻችን አምፀው ፓትርያርኩን ብቻቸውን ከጥቂት ሊቃነጳጳሳት ጋር አስቀርተው አልነበረም እንዴ? ትረሳዋለህ»?
ኤፍሬም:- «ታዲያ ያንን ዛሬ ማድረግ ይቻላል እንዴ? ሁኔታዎች እኮ ተለውጠዋል»፡፡
ማንያዘዋል:- «ግዴለም አታስብ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷል፡፡ ማንኛውንም ውሳኔ ማሳለፍ እንችላለን፡፡ ሠርተን ጨርሰነዋል»፡፡
ይህንን ቃለ ምልልስ ያዳመጠው ዘጋቢያችን መውረጃው ስለደረሰ ከታክሲው ወረደ፡፡ እነርሱ እንዲህ እንዲያ እያሉ የማቅን ሚስጥር እየዘሩ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ማቅ ልቧ በትዕቢት አብጦ ቤተክርስቲያን የማመስ አራራዋ ገና አልወጣላትም፡፡ ከኃያሉ ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ትግልና ትንቅንቅ መጨረሻው የት እንደሚያደርሳት ለልጅ ልጆቻችን ለመተረክ ያብቃን፡፡ 

ይህንን የምትጠራጠሩ ማንያዘዋልን አግኝታችሁ ጠይቁት!!

እግዚአብሔር አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን!!!
አሜን!!!