Thursday, May 10, 2012

የሰናዖር ማበር



በትልቅ ቸርነት ሌሊቱን አንግቶ
በጽልመቱ ቦታ ፀሐይን አብርቶ
ጨለማን በብርሃን ለለወጠ ጌታ
ምስጋና ሊያቀርቡ፤ ሊያደርሱ ሰላምታ
ወፎች እንኳን አውቀው ሲያሰሙ እልልታ
ክፉ ማኅበር ክፉ  ያነሰ ከእንስሳ
ጠዋት ከመኝታው ከእንቅልፉ ሲነሳ
በስመ አብ ብሎ ማመስገን ሲገባው
መርዝ ሃሳብ ያወጣል ጠማማ ልቡናው
ከደካሞች ጋራ እንዳይኖር ተስማምቶ
ተንኰል የሚዘራ ከመካከል ገብቶ

 ጉባዔ ሲመጣ በስጋት የሚኖር
 ሰላም የማይመኝ ከአድማ በስተቀር
ሰለፊ የሚባል አንድ ማኅበር ነበር
ለእገሌ ነገርኩት እገሌንም ጫንኩት
የሃሳብ ፈረሴን ጋትኩት አሸከምኩት
ብሎ የሚደሰኩር ፤ ቆጥሮ ከጀግንነት
ለዓላማው ፍጻሜ ምቾቱን ለማግኘት
በክፋቱ ቢያብር  ቢመካ በከንቱ
እንደሰናዖር ግንብ ይፈርሳል ብልሃቱ
ትእቢት ትመጣለች ውርደት አስከትላ
የተመካ ሁሉ ይጠፋል በኋላ
ማኅበር ከሆነ ማደምና ማበር
ሰናክሬም ባልጠፋ በተንኰሉ  ነገር
አስተውለህ እየው አንተም ደግሞ ቆመህ
እንዴት ይቻልሃል ብጥብጥን ወደህ
አመልካለሁ እያልክ፤ ከአምልኰ ተጣልተህ?
የቆመ ሚመስለው ድንገት ይሰበራል
ኃይልን ከመታመን  በልኩ ይሻላል
በጉልበት ቀረርቶ ጎልያድም ወድቋል።
ይልቅ ማኅበሩ ከልብህ ተመለስ
ንስሐ ግባና ትቢያን ከላይ ነስንስ
የማሽላ መቅደም  ለመበላት በወፍ
አንድም ለመመታት በጠባቂ ወንጭፍ
ውሎ ያድራል እንጂ ከመሆን አያልፍም
የወጠሩት ነገር መበጠሱ አይቀርም።
                      መነሻ ሃሳቡ፤ ከከበደ ሚካኤል ታሪክና ምሳሌ መጽሐፍ የተወሰደ