ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
- አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ላለማስረከብ አስቂኝ መከራከሪያ አቀረቡ
- ማኅበሯ ሌላው መንገድ ሁሉ አላስኬድ ሲላት አይመጥንም በሚል የሰንበት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነትን ከመምህር እንቍባህርይ ላይ ለመንጠቅ የምታድረገው ሙከራ አልተሳካላትም።
- ማኅበረ ቅዱሳንን የመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ውድቅ እንዲሆን እንቅልፍ አጥቶበት የነበረ ሲሆን ድጋሚ እንዲጠና ታዟል።
አባ
አብርሃም ርስት ጉልቴ ነው ያሉትን የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ የታዘዙትን ትዕዛዝ ለመቃመም ከተነሳው ጥያቄ ጋር የማይሄድ እኔ ከእርስዎ እሻላለሁ የሚል መከራከሪያ አቀረቡ። እኔ ምን አለኝ እና ነው መልስ የምባለው? ሲሉ የነበሩት ሰው አሁን በራሴ ወጪ አጣሪ ተልኮ ከእኔ እና ከእርሰዎ ማን ጥሩ ስራ እንደሰራ ይጣራ? ሲሉ ጠይቀዋል። ይህም ጥያቄ አሜሪካ ለመመለስ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት ያሳያል ተብሏል። ስውየውን የሚያስጨንቃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተገኝተው አባትነትን ማሳየት ሳይሆን ጥቅምና ምቾት ባለበት ቦታ ላይ መንቀባረር መሆኑንም አሜሪካ ለመመለስ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ያሳያል።
አሁን
በቅርቡ እንኳ ወደ ሐረር ሀገረ ስብከት እንደ ደረሱ ለኔ የተመደበችው መኪና የትኛዋ ነች? ብለው ሲጠይቁ ከእሳቸው በፊት ነበሩት አቡነ ዮሴፍ ይሄዱበት የነበረቸውን መኪና ሲያሳዩዋቸው ከት በለው ስቀው! እኔ በዚህ
መኪና ልሄድ? ብለው ጠይቀው ይህ መኪና ስለማይመጥነኝ በአስቸኳይ «ከሞኤንኮ» አዲስ መኪና ይገዛ ብለው አዲስ መኪና አስገዝተው በእስዋ መንፈላሰፍ ጀምረዋል። ድንቄም አባትነት።
ለነገሩ
ለማቅ የሚያስጨንቀው የማኅበሩ ጉዳይ ነው እንጂ የቤተክርስቲያን ህልውና ስላልሆነ ለማኅበሩ ዓይናቸውን ጨፍነው ለሚታዘዙት አባት አይኑን ጨፍኖ መከራከሩ አይገርምም።
የሰንበት
ማደራጃውን ጉዳይ አሁንም በተለያየ ዘዴ ለማሳካት እየሞከረ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ደግሞ መምህር እንቍባሕርይ ለቦታው አይመጥኑም የሚል መከራከሪያ አቅርቧል። የተመሰከረላቸው የአቋቋም መምህር የሆኑትንና በማደራጃ መምሪያው በምክትል ኃላፊነት ከ10 አመት በላይ የሰሩት መምህር እንቍ ባህርይ ለቦታው አይመጥኑም ብሎ ማሰብም መከራከሪያ ማቅረብም አሳፋሪ ነገር ነው። ለዛውም ደግሞ ከአንድ ደብር ዐቃቢነት የዘለለ ስልጣን ባልነበራቸውና በማደራጀው ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳንን ፍላጎት በማስፈጸም ለ6 ወራት ቆይተው የነበሩት አባ ኅሩይ ከመምህሩ የተሻሉ ናቸው ብሎ ማውራቱ የሁለቱንም ሰዎች ሥራና ኃላፊነት ለሚያውቁ ሰዎች የሚያሳዝን ነው። ማቅ መምህሩ አይመጥኑም የሚል መከራከሪያ ያነሳው መምህሩ ስለማይመጥኑ ሳይሆን ለኔ አይታዘዙም ከሚል መነሻ ነው።
ማኅበረ
ቅዱሳንን የመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ ጥናቱ በቀረበ ጊዜ
ቅዱሳን አባቶች በጥናቱ ሙሉ በሙሉ ተስማምተው የነበሩ ቢሆንም ማቅ ልፈርስ እችላለሁ በማለት ደጋፊ ጳጳሳትዋን ቀስቅሳ እንደገና ይጠና በሚል ተወስኗል። የማኅበሯ ፍላጎት ውድቅ እንዲሆን ቢሆንም እንደገና ይጠና መባሉ ታውቋል።
እርቀ ሰላሙን በተመለከተ የማቅ ብሎጎች አቡነ ጳውሎስን ለማጥላላት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እሳቸው ግን እርቀ ሰላሙን እንደሚፈልጉትና መካሔዱም ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። እሳቸውን ለማጥላላት የሚሞክሩበት ዋነኛው ምክንያትም የአሜሪካው ሲኖዶስ የእነሱን ዘገባ አምኖ በእርቁ ላይ ልቡን እንዲደፍን ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የእርቀ ሰላሙ መሳካት ለህልውናዬ አደጋ ነው ብሎ ያምናል። እርቀ ሰላሙ በሐምሌ ወር ይቀጥላል።
ከዚህ ቀደም ደጀብርሃን ብሎግ እርቅን አስመልክቶ
ያቀረበውን አጭር ዘገባ ለማየት