Wednesday, May 23, 2012

ሲኖዶሱ የሚመራው በማን ነው? በፓትርያርኩ ወይስ?


                                          ምንጭ፥ ዓውደ ምሕረት
የሰሞኑ የሲኖዶስ ስብሰባን ሂደት ላየ ሊለው የሚችለው ብዙ ነገር ይኖረዋል። በተለይ በስብሰባ ላይ በተነሳ ሀሳብ ሁሉ ላይ ከውጭ ካለው አየር ምክር የሚሹ አንዳንድ ጳጳሳት አካላቸውን ሲኖዶሱ ላይ አድርገው ልባቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ ውስጥ አስቀምጠው በማቅ ሳንባ ነው የሚተነፍሱት።  የሚተነፍሱበት አየር ደግሞ በልዩ ሁኔታ ማንያዘዋል በሚባል ኬሚስት የተሰራ ነው። ይህ ታዋቂ ኬሚስት የሚቀምመው ኬሚካል  በመጀመሪያ የሚሞክረውም አባ ሳሙኤል የሚባሉ ባለመንታ ችግር ጳጳስ ላይ ነው። እሳቸው ላይ በትክክል እንደሰራ ሲያውቅ እሳቸውን አስጨብጦ በእለቱ  የሚተነፍሱት አየር ለሚያጥራቸው ሌሎች ጳጳሳት ይልከዋል።
ከዚያማ ገበርዲኑን ለብሶ ቤተ ክህነት ግቢ ላይ መዞር ነው። ጋሻ ጃግሬዎቹ ሲከቡት የዛሬ አጀንዳ ይህ ይህ ነው፤ የሚወሰነውም ይሔ ነው እያለ ራሱን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ አስቀምጦ ያወራል። ማታ ላይም የኮሌጁ ምሩቃን ቢሮ ላይ መብራት አጥፍቶና መጋረጃ ጋርዶ ሰው የሌለ አስመስሎ ይቀመጣል እንዲህ እንደሚያድርግ የሚያውቁ የኮሌጁ ተማሪዎች ታድያ ማንያዘዋል የሚባል የሌሊት ሰይጣን አለ ብለውበመፍራትወደ ምሩቃኑ ቢሮ አካባቢ አይሄዱም።

ይህ ሰው  መሸት ሲል ሶስት ወይም አራት ሰዓት ላይ በአባ ሳሙኤል ስልክ ጥሪ መሰረት ወደ አባ ሳሙኤል ሄዶ ስብሰባው እንዴት ነበር? ብሎ ይጠይቃል። ታድያ አባ ሳሙኤልም በተለመደው ጀብደኛ ባህሪያቸው እንዲህ ተብሎ፤ እንዲህ ተደርጎ እንዲህ ተወሰነ ብለው ይነግሩታል። አጅሬም 6ሰዓት ወይም 7 ሰዓት ላይ ወጥቶ ይሄዳል። አንዳንዴም እዛው ያድራል። ያደረም ቀን፤ ወጥቶ የሄደም ቀን ተማሪ ያየዋል። ተማሪ ለጥናት ማታን ይመርጣልና ሹክክ ብሎ ከአባ ሳሙኤል ቤት ሲወጣ ያዩታል። ቀን ለደጀ ሰላም ብሎ አስቀድሞ ያዘጋጀውን ሪፓርት ያወጣና እሳቸው ካሉት ጋር ያስተያየዋል። የሚሻሻል ካለ አሻሽሎ፣ ቅመም መጨመር ካለበትም ጨምሮ «ደጀ ሰላም» ላይ ፖስት እንዲደረግ ለአሉላ ይልካል። አንዳንዴም ለአሉላ በስልክ ይነግረውና እሱ የራሱን ቅመም ጨምሮ ያወጣዋል። ታድያ ይህ ሁሉ ቅንጅት እያለ ደጀ ሰላም እውነት የማታወራው ብሎ ለሚጠይቅ ጠያቂ እንዲህ የሚል መልስ እንሰጠዋለን። ብዙ ጊዜ ደጀ ሰላም የተሳሳተ ዘገባ የምታወጣው በሶስት ዋና ዋና  ምክንያቶች ነው።

  • የመጀመሪያው በአባ ሳሙኤል ሪፖርት አሰጣጥ ስህተት ነው።
  •  ሁለተኛው ደግሞ በማንያዘዋል ስህተት ነው።
  •  ሶስተኛው ደግሞ በአላማ ነው።
ማንያዘዋል ስብሰባውን እሱ እንደሚመራው፣ እሱ እንደሚወያይበት፣ እሱ እንደወሰነው አድርጎ ሲያስብ ኩራት ይሰማውና ለራሱ በመስታወት ፊት ቆሞ እህሳ «ፓትርያርክ ማንያዘዋል እንዴት ነህይለዋል። እራሱን እንደፓትርያርክ ስለሚያስብም በኔ ላይ ተደረቡብኝ ብሎ የሚያስባቸውን ቅዱስ ፓትርያርኩን አምርሮ ይጠላል። በእሱ ፊት ወዳጄ ብሎ የሚጠራቸውን ሰዎች ሁሉ የወዳጅነት መስፈርት የግድ ማሟላት አለባቸው። እርሱም ፓትርያርኩን መጥላት ነው። አንዳንድ ወገኖች ማንያዘዋል ለምንድን ነው ነጭ ልብስ መልበስ የሚወደው? ብለው ይጠይቃሉ። መላሾች ሲመልሱ አንዳንዶቹ  ቅኖች ፈሪሳዊ ስለሆነ ነው ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ላደገበት አካባቢ ያለውን ፍቅር በአለባበስ ለመግለጽ ነው ይላሉ። ውስጠ ምስጢሩን የሚያውቁ ደግሞ በጓዳ በሚሰራው ስራ ፓትርያርኩ እኔ ነኝ ብሎ ስለሚያምን የፓትርያርክነት ህልሙን ያሳካ ስለሚመስለው ነው ይላሉ። ይህን የፓትርያርክነት ህልሙን  «ህልመያርክ» እንበለው ይሆን?
---------------------------
ከደጀ ብርሃን፤
«ደጀ ሰላም» የማኅበረ ቅዱሳን ነች! የሚለውን መረጃ [Internet Catche ] ያገኘነው  መረጃ ይህንን ያረጋግጣል። ያገኘንበት ድረ ገጽ ምስጢር ለጊዜው ይቆየንና የደጀ ሰላም ማኅበረ ቅዱሳንነትን ግን ማውንቴን ቪው/ካሊፎርኒያ ከሚገኘው የጉግል ብሎግስፖት ሰርቨር አድራሻ እንዲመለከቱ ጋብዘናል። ተጭነው ያሳድጉትና ያንብቡት።