በእውነቱ የት እንዳላችሁ፤ እነማን እንደሆናችሁ፤
ስንት እንደሆናችሁና ምን እንደምትፈልጉ ባናውቅም ያልጻፋችሁትና ያልደረሰን ደብዳቤአችሁ እንዲያው በደፈናው ደርሶናል።
እነዚህ ሩቅ ምሥራቆች የት ነው የሚኖሩት? ስንት
ናቸው? የጉባዔው ዋና ቢሮ መቀመጫው የት ነው? እነማን ናቸው?
ካልታወቁና በደፈናው ሩቅ ምሥራቆች ጽፈው የላኩት ደብዳቤ ደርሶናል እንዴት ትላላችሁ? ብላችሁ ብትጠይቁን መልሳችን፤ በዘንድሮው
ሲኖዶስ ያቀድነውና የጎነጎንነው ሁሉ ስላልተሳካ በዓለም የሚገኘው ምእመን ሁሉ በአዲስ አበባ «ታህሪር» አደባባይን እንዲፈጥር የሀገር
ውስጡን ሕዝብ ሞራል ለመገንባት የምንጠቀምበት ስልት እንጂ በእርግጥ ከላይ የጠየቃችሁትን ዓይነት ግምት ስናስብ ከምዕራብም ይሁን
ከምሥራቅ፤ ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላከ ምንም ዓይነት የአድማ ደብዳቤ እስካሁን እጃችን አልገባም። ደብዳቤዎቹን እኛው በቢሮአችን
እያረቀቅን፤ አቅጣጫ እያወጣንለት በግለሰብም ይሁን በጉባዔዎች ስም የምንጽፈው ራሳችን እንደሆንን እንድታውቁልን እንፈልጋለን።
ከላይ የተጻፈውን
ያልነው «ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ መጣልኝ በማለት ያወጣውን ንባብ ካየነው በኋላ የገባበትን ጭንቀት በመጋራት የሩቅ ምስራቁን
ደብዳቤ ግልጽ ለማድረግ ፈልገን እንጂ ለእኛ ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰን የፈጠራ ደብዳቤ ኖሮ አይደለም።
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከጥላሁን ገሠሠ ዓለማዊ ዘፈን
ጋር ወዳጅነት የያዘ መስሏል። ወደ ሩቅ ምሥራቅ ሄዶ «ጃፓኗን ወድጄ» እያለ ከሩቅ ምሥራቅ ተላከልኝ የሚለውን የፍቅር ደብዳቤ በገጹ
ጽፎ አስነብቦናል። ሩቅ ምሥራቅ ማለት ጃፓንና አካባቢዋ ያሉ ሀገሮች ናቸው።
የማቅ አፈቀላጤ «ደጀ ሰላም» ስንት ቆንጆዎችን ከወደ ሩቅ ምሥራቅ እንዳፈራ
ለጊዜው ባናውቅም እሱ ግን የተላከለትን «ውዴ አንተ ነህ፤ ዶ/ር መስፍን ውዴ ነው፤እኔም የአንተ ውድ ነኝ» የሚል ደብዳቤ ደርሶኛል
ሲል ያቀረበውን ደብዳቤ ተመልክተን በመግቢያችን ላይ ያልተላከ ደብዳቤ
ተላከ ለማለት ተገደድን።
«አዎ የማናውቃችሁ ሩቅ ምሥራቆች ያልተላከው ደብዳቤአችሁ
ደርሶናል» በማለት!!
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሌሎቹ የዓለም ማእዘን ተጻፈልን
ሲል እንደቆየው ሁሉ አሁን ደግሞ ከቀረው ሩቅ ምሥራቅ ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ እድሉን ለመጠቀም ደብዳቤውን ራሱ ጽፎ ወይም በዶ/ር መስፍን
አስጽፎ ሲያበቃ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰኝ ነው ሲል ብሎጉ ላይ በመለጠፍ ሰውን ሁሉ እንደጅል ሊያጃጅል ይሞክራል።
ስም የለሾች፤ አድራሻ ቢሶች፤ የማይቆጠሩና የማይጠሩ
መንፈሶች ሆነው ሾላ በድፍኑ እንዲሉ ዝም ብሎ «ከሩቅ ምሥራቅ» የተጻፈ ደብዳቤ በማለት ለማስነበብ መሞከር «ደጀ ሰላም» እንዳባቱ
ነገር ዓለሙ እንደዞረበትና ዳንኤል እንዳለው «ስታክ» በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል። ማቅ ከሌለ «ደጀ ሰላም» የለም። ስለማቅ
እንጂ ስለ ወንጌል አንድም ቀን አስተምሮ የማያውቅ ብሎግ የጫወታውን ስልት ቀይሬ ማስተማር ልጀምር ነው ቢል የተበላውን እቁብ ጨርሶ
አዲስ የማጭበርበሪያ እቁብ መጀመር ስለመሆኑ የማያውቅበት ማንም አይኖርምና የሚያዋጣው አይሆንም። እስከዚያው ግን በፈጠራ ሥራ ላይ
ተግቶ መሥራት የግድ ሆኖበታል።
ይልቅስ ከዚያ በፊት በንፋስ ላይ ያሉ ሩቅ ምሥራቆች
ደብዳቤ ጻፉልኝ እያለ አፍቃሪዎቹን በማጃጃል የማቅን ጉዳይ ከመስፍን ተገኝ ጉዳይ ጋር እያስተሳሰረ በዓለም ማዕዘናት ሁሉ ያለው
ምእመን በትኩረት እየተከታተለው ስለሆነ እንዳትቀዛቀዙ ሲል የማነቃቃት
ስልት መጠቀምን መርጧል።
ከሁሉም የሚገርመው የደጀሰላም ቅጥፈት እነዚህ
የሩቅ ምሥራቅ የደጀ ሰላም አመልካቾች የሚገኙት ተበታትነው በሩቅ ምሥራቅ ሀገሮች ሁሉ ሆኖ የራሳቸው ቤተክርስቲያን የሌላቸው ሆነው
ሳለ(ለዚያውም ሰዎቹ ራሳቸው ካሉ) ልክ የተደራጁና ቢሮ ያላቸው አስመስሎ ማቅረቡ ነው። ርእሱ እንደዚህ ይላል።
«በሩቅ ምሥራቅ የሚገኙ “የኢ/ኦ/ተ
ምእመናን ጉባኤ” ለቅዱስ ሲኖዶስ መልእክት ጻፈ»
ደግሞም የተጻፈው ደብዳቤ ቤተክርስቲያን ለመባረክ
ጳጳስ ይላክልን ወይም መምህር ስለሌለን የሚያጽናናን አንድ የወንጌል መምህር ይላክልን ሳይሆን ዶ/ር መስፍን ተገኝ እንዳይነካብን
እናስታውቃለን የሚል መሆኑ ነው።
እነደጀሰላምና መስፍን ተገኝ ምዕናባዊ ሩቅ ምሥራቅ ፈጥረው፤ ደብዳቤውን አዘጋጅተው፤ ልብ ወለድ ጉባዔ
መስርተው ከዓለም ማእዘናት ሁሉ ደብዳቤ በማዥጎድጎድ ሰውዬው ምን ያህል ታዋቂና ዓለሙን ሁሉ አነቃናቂ ነበር በማስባል በድስት ማእበል
የሚናጥ ሲኖዶስ እንዳለ ቆጥረው የላኩት ደብዳቤ መሆኑን ስናጤን ሌላው እንዳለ አላምጦ ይውጥልናል ብለው ማሰባቸውን አልዜይመር(alzheimer) ይዟቸዋል እንዴ እንድንል ያደርገናል።።
ፈጠራ ጥሩ ቢሆንም የእነዚህ ፈጠራ ያልተሳካና
የተበላሸ ስለሆነ ለመስፍን ተገኝ የሚሟገት የሩቅ ምሥራቅ ስደተኛ
ጉባዔ አለመኖሩን አስረግጠን እንነግራቸዋለን።
የሩቅ ምሥራቅን ሱናሚ የመሰለ የፈጠራ ደብዳቤ በማዘጋጀት በስም የለሾና፤ አድራሻ ቢሶች ጉባዔ ሽፋን ዶ/ር መስፍንን ለመርዳት መሞከር የአእምሮ ድኩም ዘዴ ከመሆን
ያለፈ ስላይደለ የሚያመጣው ምንም ለውጥ የለም። በእስካሁኑ ፈጠራ ስላልተሳካላችሁ ወደእውነት የሚቀራረብ ፈጠራ ለመስራት ሞክሩ!
«አንትሙሰ እምአቡክሙ ሰይጣን አንትሙ፤ ወፍትወቶ
ለአቡክሙ ትፈቅዱ ትግበሩ፤ ወውእቱሰ ቀታሌ ነፍሰ ሰብእ ውእቱ እምትካት፤ ወኢይቀውም በጽድቅ፤ እስመ አልቦ ጽድቅ በኀቤሁ» ዮሐ
፰፣፵፬