Sunday, May 20, 2012

ለጠያቂያችን የተሰጠ መልስ

ALEMIN HULU YEFETERE AND AMLAK WOLDEABE WOLDEMARIAMNEW"KIDUS EGZIABHER BICHA NEW.GIN,MUZLIMOCH ALLAH (AMLK)MILUT MANIN NEW???
ከላይ በፈረንጅኛው ፊደል የቀረበው የአማርኛው ንባብ ጥያቄ፤ በጡመራ ገጻችን ላይ ባለው «ይጠይቁ» ዐምድ ላይ የተላከልን ነው።
ንባቡን ወደፊደላችን ስንመልሰው፤ ይህንን ይሰጠናል።
«ዓለምን ሁሉ የፈጠረው አንድ አምላክ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው። ቅዱስ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ግን ሙስሊሞች አላህ(አምላክ) ሚሉት ማንን ነው?»
ጥሩ ጥያቄ ነው። ሙስሊሞች የሚያመልኩትን «የአላህ» ማንነት ከመመልከታችን በፊት እነሱ ብቻ ትክክለኛ እንደሆኑ ቆጥረው  እኛ የምናመልከውን እግዚአብሔርን በተመለከተ የሚሉንን ጥቂት ለማሳየት እንሞክራለን።
በእኛ ዘንድ የሚነገረውን አንድነት በሦስትነት ሳይከፋፈል፤ ሦስትነት በአንድነት ሳይጠቃለል፤ አንድም ሦስትም ብለን ማምለካችንን ሦስት አምላኰችን እንደምናመልክ አድርገው ይቆጥራሉ። ይህንንም «ሽርክ»شرك ይሉታል። ይህም ማለት «አጋሪ» ፤ ከአንድ በላይ  አምላኪ ማለት ነው። ከዚያም በተረፈ ጣዖት አምላኪ ማለት ነው። አላህ አንድ ገጽ፤ አንድ አካል፤አንድ ግብር ያለው እንጂ አንድም ሦስትም ሊሆን ስለማይችል ክርስቲያኖች የሚያመልኩት አላህን ሳይሆን «ፍጡርን ነው» ይላሉ። አንድና አንድ ብቻ (Oneness) ወይም توحيد ተውሂድ(ተዋህዶ) ያልተቀበለ ሁሉ አላህን አልገዛም ያለ ነው ይላሉ። (ተዋሕዶ ማለት አንድ ገጽ ማለት  እንደሆነ ልብ ይሏል?) توحيد ወይም Oneness ማለት ነውና። لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ «እሱን የሚመስል ማንም የለም፤ ሁሉን የሚሰማ፤ ሁሉን የሚያይ እሱ ብቻ አንድ ነው» ቁርዓን ሱረቱል Ashura 42፤11
( Fundamentals of Tawheed/Islamic monotheism/  Dr Abu Ameenah Bilal Philips)
ስለዚህ ተውሂድን( ተዋሕዶን) (Unification) ያልቀበሉ ሁሉ ከሀዲዎች ናችሁ ይሉናል።
በዚህም ተውሂድን ባለመቀበል የተነሳ ዛሬ በዓለም ላይ ያለው ኃጢአት ሁሉ የመጣው የሽርክና ውጤት ነው ይላሉ። ስለዚህ በእነሱ ዘንድ ክርስቲያኖች  ሽርክ አማኞች  ስለሆኑ የኃጢአቶች ሁሉ  ምንጮች ናቸው ማለት ነው። ይህ እንግዲህ እነሱ ክርስቲያኖችን የሚተነትኑበት መንገድ ነው። http://www.allaahuakbar.net/shirk/crime.htm/ይመልከቱ።
ክርስቲያኑን እንዴት እንደሚመለከቱት የብዙ ገጽ ትንታኔ ማቅረብ ቢቻልም ለማሳያነት ይህ በቂ ሆኖ ክርስቲያኖች እስልምናውን እንዴት እንደሚያየው ጥቂት ለመግለጽ እንሞክራለን።
አሊ ሲና የተባለ የቀድሞ የእምነቱ ተከታይ (Why I left Islam?)በተባለው ጽሁፉ እንዲህ ሲል ጽፏል። የእስልምና እምነት ተከታይ በዚህ ዘመን ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ መድረሱን ይገልጽና ታዲያ ይህ ሁሉ ህዝብ የሚሳሳት ይመስልሃል? ብሎ ይጠይቃል።

 
እስላሞችም የቁጥራቸውን መብዛት ስለእምነታቸው እውነተኛነት እንደ አስረጂ ማቅረባቸውን ካተተ በኋላ አንድ ወይም ሁለት ወይም አስርና ሠላሳ ሰው ቢሳሳት እንኳን 1,2 ቢሊየን ሕዝብ ግን ይሳሳታል ማለት ይከብዳል የሚለውን( Logical Fallacy) አመክንዮአዊ ህጸጹን ያሳየናል። "argumentum ad numerum" በሚለው ቁጥርን እንደጭብጥ የማስያዝ ህጸጻዊ የብዙኅነት ክርክርን ውድቅ አድርጎ ብዙ ቁጥርና ደጋፊ ስላለ ብቻ ውሸት እውነት አይሆንም ሲል የሙስሊሞች መብዛት እውነተኝነታቸውን አያረጋግጥም ይለናል። አሊ ሲና ጽሁፉን በማያያዝ ይህች ዓለማችን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓለሙ ላይ ባለው ህዝብ ሁሉ ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ መሆኗ ይታመን ነበር፤ ያ ማለት ግን ዓለም ዝርግ ነበረች ማለት አይደለም ይልና የሙስሊሞች ቁጥር እውነተኛ እንደሆኑ በፍጹም አያሳይም በማለት ቁጥርን በተመለከተ በአራት ነጥብ ይዘጋዋል።መጽሐፍቶቹን አግኝቶ ያላነበበ  ከ45 ሚሊየን በላይ የጎበኘውን የአሊ ሲናን ድረ ገጽ መጎብኘት ብዙ መረጃ ስለእስላም ማግኘት ያስችላልና እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ።http://www.faithfreedom.org/Articles/sina/why_i_left_islam.htm/
ወደ ጠያቂያችን ስንመለስ የአላህን አምላክነት ለመመልከት እንሞክር።
አላህ/Allah/ ማለት ከሁለት ቃላት ጋር የተመሰረተ ቃል ነው። Al = ማለት በአረቢኛ ንባብ ወይም የእንግሊዝኛውን «The» የሚወክል ገላጭ /definite/ ነው። ILLAH = ኢላህ ማለት ደግሞ በአረቢኛ አምላክ ወይም ፈጣሪ ማለት ይሆናል። ያም ማለት አምላኩ ወይም ፈጣሪው ማለት ይሆናል ማለት ነው። ይህም የሚሳየን አንድን /ተውሂድ/ ሳይሆን ሌሎች ተቀጽላዎችን ያሳያል። ከቅድመ እስልምና በፊት በዐረቢያ ምድር የሚመለኩ ጣዖታት ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ትልቆቹ ሁባልና ካዓባ የሚባሉ ጣዖታት ናቸው። ካዓባ የሚባለው ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ እዚያው ሲሰገድለት የነበ አሁንም ተገትሮ የሚገኘው ጣዖት ነው። ሌሎችም ጣዖታት አል ላት፤ አል ማናትና አል ዑዛ የሚባሉ በሴት ስም የሚጠሩ ጣዖታትም እንደነበሩ ታሪክ ጽፎ አቆይቷል። ተመራማሪዎችም በጥናት አረጋግጠዋል።     First Encyclopaedia Of Islam, E. J. Brill, 1913-1936; Reprinted, 1987
ቁራይሾች ከእስልምና መምጣት በፊት ከሚያመልኳቸው 360 ጣዖታት በላይ የሆነና ሁሉን የሚገዛውን አል ኢላህ ይሉት ነበር። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው አምላኩ ወይም ፈጣሪው የሁሉ ገዢ ነው በማለት በገላጭ ቃል እንደስቀመጡት ማለት ነው። እስልምና በመሐመድ ከተፈጠረ በኋላ ድረስ ብዙዎቹ ጣዖታት ነበሩ። መሐመድ ሁሉንም ደምስሶ ብዙ ገቢ ስታስገኝ የነበረችውና በሴት ብልት ቅርጽ የተሰራችውን ካዓባ ብቻ በማስቀረት የቁራይሾችን አል-ኢላህ ወደ አላህ አንድ ቃል ቀይሮ የሁሉ ፈጣሪ እሱ ነው፤ እሱን ብቻ ተገዙ፤ አታጋሩ፤ ሽርክናን አስወግዱ ብሎ በማወጅ የጣዖቶችን አለቃ አላህን አምላኩ አድርጎ ሾመው።
Who Is Allah In Islam?, Abd-Al Masih, Villach, Austria, Light of Life, 1985, p. 36
Islam: Muhammad and His Religion, Arthur Jeffery, 1958
ውድ ጠያቂያችን ሲጠቃለል አላህ የጣዖቶች አባት ተደርጎ ከእስልምና መምጣት በፊት የተሾመ የቁራይሾች አምላክ ሲሆን ከዓባ ደግሞ ጥሩ የገቢ ምንጭ የምታመጣ ከ360 ድንጋዮች መካከል ተመርጣ የቀረች የሴት ብልት ቅርጽ ያላትና ከንፈሯን የሚስሙላት ድንጋይ መሆኗን ያገኘነው መረጃ ያስረዳናል። ተጨማሪ የካዓባን ምስሎች ለማየት ጉግል ኢሜጅ ላይ «kaaba black stone» ጽፋችሁ ተመልከቱ።