Tuesday, May 8, 2012

አባትነት በገንዘብና በፖለቲካ ሲፈተን



                              የጽሁፉ  ምንጭ፦አውደ ምህረት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ተለምኖ በተገኘ ገንዘብ የተገዛውን የዲ.. እና አካባቢው መንበረ ጵጵስና /ቤት እንዲያስረክቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወሰነ። ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ራሱን በሚጠራው ድርጅት አቀንቃኝነታቸው የሚታወቁት ወጣቱ ጳጳስ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ በተለያየ ስቴቶች በተካሄዱ ጉባዔያት አማካይነት ከምእመናን በተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር 265 000.00 የተገዛው መንበረ ጵጵስና በራሳቸው እና በወሮ. ሀረገወይን ስም ለምን ለማዛወር እንደፈለጉ ባይታወቅም መንበረ ጵጵስናው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንብረት መሆኑ እየታወቀ አላስረክብም ማለታቸው በዘመናዊ አነጋገርየመርካቶ ቁጩዐይነት ቢሆንም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት እንዲያውቁት ተደርጎ በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ከዚህ በታች አባሪ በሆነው ደብዳቤ መታዘዛቸውን ቤተ ክርስቲያን ገለጸች።
 ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ(ጽሁፉን አሳድገው ያንብቡ)

መቼም መስከረም ሳይጠባእንደሚባለው የዋሽንግተንና አካባቢዋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናውን በሥርዐት እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ቢጽፍላቸውም አሻፈረኝ ብለው መንበረ ጵጵስናውን ለማኅበረ ቅዱሳን /ቤት (ደጀ ሰላምና አሃቲ ተዋህዶ ብሎግ ማዘጋጃ) አከራይተው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ታውቁዋል። እኒህ ጳጳስ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ከመርካቶው ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን ባካበቱት (በዘረፉት ቢባልም ሥራቸው ነውና ራሳቸው ይፈሩ!) ገንዘብ .ኤም.. አጠገብ ፎቅ ቤታቸውን ሠርተው ሳያፍሩ ያስመረቁ ሲሆን፣ በቅርቡም በባንክ ሂሣብ የተጠራቀመውን ከዲ. ከወሰዱት የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ እና አቶ አሥራት የሚባል (የጎጃሙ ባለአውሊያ) የቸራቸውን ብር 400 000.00 በመጨመር ሁለት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ልዩ ላንድ ክሩዘር ገዝተው -መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን እያከናወኑበት ይገኛሉ።
 ምንም እንኳ የህዝቡን ልብ ባያገኙትም መንበረ ጵጵስናውንን ርስት ጉልት አድርገን እንይዘዋለን ብለው የነበረው የማቅ አመራሮች ለእውነትና ለወንጌል የቆሙት አቡነ ፋኑኤል በቦታው መሾማቸው ከፍተኛ ነውጥ ይነሳብናል በማለት ከፍተኛ የሆነ የሽብር ቅስቀሳ ቢያደርጉም ሀሳባቸውንን ተቀብሎየአጥፍቶ መጥፋትእርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ የሆነ ሰለፊ በአሜሪካ  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምዕመናን  ባለማግኘታቸው በቂ ሥራ አልሰራንም ብለው ዶክትሬቱ አሜሪካን አገር ሲደርስ አፈር ልሶ በቀረበትና  የክብርቅስናውደግሞ አለአግባብ ሲዘባርቅ በተገፈፈበት፤ ከጎጋ ምዕመንነት ተነስቶ በአንድ ጊዜ በአቡነ አብርሃም ፈቃድየቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆነውጨዋው አቶ መስፍን መሪነት ቤንዚን እንዳለቀበት መኪና ቢንተፋተፍምም  ውጤት ሳያስገኝለት ቀርቷል።

ይህ የማቅና የአቡነ አብርሃም ሴራ በእግዚአብሔር ፈቃድና በምዕመኑ አስተዋይነት ከከሸፈ በኋላ የቅዱስ ሲኖዶስን ስልጣን ቸል በማለት የሀገረ ስብከቱን ጽህፈት ቤት አንመልስም፤ ማህተምም አናስረክብምም በማለት ከአሜሪካ ርስተ ጉልታቸው ላለመነቀል በጥፍራቸውምም በጥርሳቸውምም እየቧጠጡ ይገኛሉ።
አቡነ አብርሃምም ህመማቸውንን አርፈው እንዳያስታምሙ ሰላማቸውንን የሚያቃውስ ስጋዊ ትግል እያደረጉ መሆናቸው በታዛቢዎች ዘንድ የተጠሩበትን መንፈሳዊ አደራ የዘነጉ አባት አስብሏቸዋል።

ያዳቆነ ሠይጣን ሳያቀስ አይለቅምእንደሚባለው አቡነ አብርሃም አዋሳን ትኩረታቸው በማድረግ ለመዛወር የድጋፍ ድምጽ እያሰባሰቡ ነው ይባላል። የአዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን እምነቱን ለመዝባሪ አሳልፎ እንደማይሰጥ በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ነውና ሙከራቸው ፋይዳ እንደማይኖረው ተስፋ እናደርጋለን፣ በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በአዋሳ የፈጠረውን ችግር እየታወቀ አባ አብርሃም በጥቅም ለቆሙለት ማኅበረ ቅዱሳን አዋሳ ላይ ርስቱን ሊያስመልሱለት ቃል የገቡ ይመስላል፣ ግንሞኞ ሆይገደሉን ሳታይእንደሚባለው በዚህ አካሄዳቸው ከማን ጋር እንደሚላተሙ አዙረው ማሰብ አልቻሉም ማለት ነው - ገንዘብ ያውራል ይባል የለ!

ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያንን ተጠልሎ ምእመናንን እየከፋፈለ የፖለቲካ መሣሪያ እስከማድረግ የሚያደርገው ተልእኮ እንዲቀጥል ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አቅርቤ አቡነ ፋኑኤልን አስነሳለሁ በማለት ገንዘብና ተወካይ ላኩልኝ ባሉት መሠረት ገንዘቡም መልእክተኞችም (ከአሜሪካ አባ ዘሊባኖስና አባ ገብረ ወልድ) መጥተው አባ አብርሃም ቤት በሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጳጳሳትን ለመከፋፈል በዱለታ ላይ ይገኛሉ፣ ለተቀደሰ አገልግሎት ሊውል የሚገባውን ገንዘብና ጊዜ ጳጳሳትን ለመደለል እያባከኑት የሚገኙት አባ አብርሃም ጥፋተኞችን በመወከል የአድማ ምንጭ ሆነዋል። ምንም ቢሆን በቤተ ክርስቲያናችን የእምነት ትምህርትና ክህነት በገንዘብ አይሸጥም፣ ለአድማ ተግባርም አይውልም ብትልም አባ አብርሃም ግን የማኅበረ ቅዱሳንን የአድማ ተልዕኮ ለማጠናከርና የገንዘብ ምንጫቸው እንዳይደርቅባቸው፡ - አሜሪካ ከገቡ በኋላ እንደ ካንጋሮ እጅ አጥራበተማሩበትትምህርት የማትሰራ ዲግሪያቸውን ጥለው ቤተክርስቲያን  ውስጥ ተወሽቀው በስመክህነታቸውቤተክርስቲያንን የእንጀራ ገመዳቸው ያደረጉትንን 

  1/  ዶር. መስፍን የሚባለውን ምእመን ለቴነሲ ኪዳነምህረት አለቃ፣
   2/ ብርሃኑ ጎበና ለሜሪላንድና ፔንሲልቫንያ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
   3/ ቀሲስ ያሬድ /መድኅን ለኦሃዮ ገብርኤል አለቃ፣
    4/አቶ በላቸው ወርቁ (ፓርላማ የነበረና ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖር) ለኒውዮርክ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
    አቶ ገብረ ወልድ (ድሮ አባ የነበሩ ግን ከተለያዩ ሴቶች ልጆች  የወለዱ) ዳላስ አጠገብ ለሚገኘው ለቨርጂኒያ ራጉኤል አለቃ አድርገው በመሾም ከአባቶችዋ አንዱ ነኝ የሚሏትን ቤተ ክርስቲያናቸውን አዋርደዋል፤ ሀገረ ስብከቱንም የፖለቲካ መናቆሪያ አድርገዋል፤ መንበረ ጵጵስናውን በራሳቸው ስም አስመዝግበው ቀርተዋል። ይኽ እንግዲህ መንግሥት ለረጅም ጊዜ በትእግስት ይዞት የነበረውን የሰለፊያንን ጉዳይ በሳቸው ሀገረ ስብከት እንዲጠናከር ሲያደርጉ የት ላይ ለመቆም ፈልገው እንደሆነ ከወዲሁ ሃይ ሊባሉ ይገባል።
እንግዲህ አባ አብርሃም ዋሽንግተን በቆዩበት ጊዜ የግል ሥራቸውን ሲያሳድዱ መደበኛ ሥራቸው የተጎዳ መሆኑ፣ አብያተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ሙያው የሌላቸውን ግብረ በላ የማኅበረ ቅዱሳን አባላንት ሥልጣነ ክህነት እየሰጡ በመሾም ትርምሱን ለማጠናከር እንደሞከሩ ከአሠሪያቸው /ቤት በተጻፈላቸው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል። ይች ቤተ ክርስቲያን እንደ አባ አብርሃም ያሉ አባቶች የሚመሩዋት ከሆነ ከሀገርም አደጋ ነውና ቅዱስ ሲኖዶስም ምእመናንም ሊታገሉዋቸው ይገባል።

ቀደም ሲል ዳንኤል ክብረትአቡነ አብርሃምንን እንደማውቃቸውብሎ በብሎጉ እስከ ዛሬ ድረስ ተስሎ የማያውቅ የስዕል ደብተር በበጎ ባህርይ ኖረው ለማያውቁትአቡነ አብርሃምለሚባሉ ገጸ ባህሪ በመሳል  ለማቅ የሰሩትን ውለታበውዳሴለመመለስ መሞከሩ ይታወቃል።
ዳንኤልና አቡነ  አብርሃም በተመሳሳይ ነውር የሚታወቁ ከመሆናቸው አንጻር እና አቡነ አብርሃም በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሾሙዋቸው ሰዎች የማቅ ክፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ለተገነዘበ ሰው ዳንኤል ለአባ አብርሃም ያቀረበላቸውየውዳሴገጸ በረከትሲያንሳቸውነው ያሰኛል።

 ጳጳሱ በምንኩስና ሕይወታቸው የሚታወቁበት በርካታ ነውር ሕይወት ስላላቸው ይህ እንዳይገለጥባቸው በማኅበረ ቅዱሳን እቅፍ ውስጥ መደበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ አድርገው የወሰዱትና ለዚህም በታማኝነት መንቀሳቀስ ግዴታዬ ነው ብለው ቢያምኑም በአደባባይ የተሰራን ነውር ግን ከዚህ ብሎግ አዘጋጆች ጀምሮ በርካታ ሰዎች የሚያውቁት መሆኑን መገንዘብ አለመቻላቸው አሳዛኝና እርሳቸውንም አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ሰሞኑን እንቅልፍ አጥተውና ከፍተኛ ገንዘብ እየረጩ እየደከሙበት ያለውን የማኅበረ ቅዱሳንን አጀንዳ ረቡዕ በሚጀመረው የሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ የማስፈጸም ትግል እሳቸውን እራሳቸውን የት ያደርሳቸው ይሆን? የሚለው ጥያቄ በጉጉት ምላሽ የሚጠብቅ ሆኗል። ተንኮላቸውንን የአመጽ አካሄዳቸውንን ካላቆሙ በማኅብረ ቅዱሳን ጉያ ሊደብቁት የሚደክሙበትን ነውር በቅርቡ ይፋ መሆኑ እንደማይቀር ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

እግዚአብሔር ለአባ አብርሃም ልብ እንዲሰጣቸው፣ ጤናቸውንም እንዲመልስላቸው እንጸልይላቸዋለን።

                               ከታዛቢ