Friday, May 18, 2012

በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ህልውናውን የካደ ኮሌጅ

                                  የጽሁፉ ምንጭ፤ ዐውደ ምሕረት ብሎግ
                     To read in PDF ( Click Here )
 አንድ የቤተክርስቲያንን ልጅ ለማባረር ሲል እራሱን ሕጋዊ ሰውነት የሌለው አድርጎ የሚያሳይ የክስ ወረቀት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቀረበ
    ኮሌጁበሰበር ሰሚ ችሎት ከረታ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ አለው
                                                             
የኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር ጥቂት ዓመታት የቀሩትና ከተመሰረተ 69 ዓመት የሆነው የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመምህር አሰግድ ሣህሉ ጋር ባለው የሕግ ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ሽሮ በድል እንድወጣ ያስችለኛል ያለውን የይግባኝ አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ሲያቀርብ ሕጋዊ ሰውነት የሌለኝና ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነስኩ ነኝ ሲል ህልውናውን ካደ።
የኮሌጁ ጠበቃ እያለች የሕግ ክርክሩን በራሴ በኩል ልምራው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን አመራር በሆነው ደስታ በርሔ በተባለ ጠበቃ በኩል የሕግ ክርክሩን ቢቀጥልም በስር ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ይሽርልኛል ብሎ ላለፉት አምስት ወራት ሲያስብ ቆይቶ ባቀረበው አቤቱታ በተራ ቁጥር 2 ላይ ያለው የአቤቱታው ዝርዝር በሚለው አንቀጽ በግልጽ ህጋዊ ሰውነት የሌለው ኮሌጅ ነው ሲል የኮሌጁን ህልውና ክዷል።
እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው የጠላሁትም መናፍቅ ነው የሚል መመሪያ ያለው ማቅ ፍላጎቱ እንዲሳካ የማያደርገው ነገር እንደሌለው የሚያስረዳው አቤቱታ 69 አመቱን አንጋፋ ኮሌጅ እዚህ ግባ የሚባል ካሪኩለም የሌለው እናደረጃውም የትምህርት ሚኒስቴርን ተቀባይነት የማይመጥን በማለት የኮሌጁ ተማሪ የሆነው መምህር አሰግድ ይባረርልኝ የሚለው አቤቱታ ይህን ይመስላል።
የአቤቱታው ዝርዝር
በመሠረቱ አመልካች ኮሌጅ በራሱ ሕጋዊ ሰውነት የለውም፡፡ እንደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አውጥቶ የሚያስተምር ተቋም አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መንግስት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ በቀጥታ በመንግስት ፈቃድ ቤተክርስቲያኗ ከፍታ የሐይማኖቷን ተከታዮች ለማነጽ መምህራንን የምታፈራበት ነው፡፡ የሚሰጠው የትምህርት ዓይነትም ሆነ ብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት አይደለም፡፡ በመሆኑም በስሙ ሊከሰሰም ሆነ ሊፈረድበት አይችልም፡፡ በሕግ ‹‹ሰው›› የሚለውን መስፈረትም አያሟላምና፡፡ ስለዚህ የስር /ቤቶች ጉዳዩን ተቀብለው ማስተናገድም ሆነ አስገዳጅ ውሳኔ መስጠታቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡
ይህ አቤቱታ ቀላል የማይባሉ ስህተቶች ያሉትና እራሱ ኮሌጁ ባለፉት አመታት ባስተማርኩዋቸው ተማሪዎቼ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት የሚንድና ተማሪዎቹ ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት ሄደው ለመማር ያላቸውን ፍላጎት ከንቱ የሚያደርግ ነው። አንድ የቤተክርስቲያን ልጅን ካላባረርኩ በሚል ህልውና እስከመካድ ድረስ የደረሰ አቤቱታ ማቅረብ እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ተግባር ነው።

አቤቱታው ኮሌጁ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ    “…/ቤቱ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ከፍ እንዲል የታቀደበት ዋናው ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱን ከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ሊቃውንት ዘመናዊውንም ትምህርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀስሙ የማድረጉን ጥረት ሊሟሉ የሚችሉ የሃይማኖትና የግብረ ገብነት መምህራንና የወንጌል ልዑካንን መልሰው እንዲያፈሩ፣ ለማድረግ ከኮሌጁ በዘመናዊውና በጥንታዊው ትምህርት በከፍተና ደረጃ ሰልጥነው የሚወጡት መምህራንም ለተከታዩ ትውልድ የኢትዮጵን መንፈሳዊ ቅርስ ለማስተላለፍ እንዲችሉ ታቅዶ ነበር፡፡…”የሚለውን የኮሌጁን ራዕይና እንዲሁም ይህ ኮሌጅ በመከፈቱ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት ማለትም“…ተቋሙ 48 ዓመታት ዕድሜው በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ እና በሰርቲፊኬት ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በመንፈሳዊ አገልግሎት እስከ ፓትርያርክነት፣ በዩኒቨርስቲ መምህርነት እስከ ፕሮፌሰርነት፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤት አገልግሎት እስከ ሚኒስትርነት፣ ደረጃ የደረሱ ይገኙበታል፡፡የሚለውን ዋጋ የሚያሳጣ ነው።
የክስ ሂደቱ ዝርዝር ምንድን ነው?
ኮሌጁ የቀድሞ የዲፕሎማ ተማሪዎቹ የዲግሪ ፕሮግራም ለመቀጠል እንደሚችሉ በፈቀደው መሰረት መምህር አሰግድ ሣህሉ ከዚህ ቀደም የኮሌጁ ዲፕሎማ ያለው በመሆኑ እድሉን ለመጠቀም ለመማር ይመዘገባል። ወዲያውኑ ያለበቂ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለምን ታገለግላለህ? በማለት በማኅበረ ቅዱሳን አድሮ ገና በልጅነቱ ሲዋጋው የነበረው ሰይጣን መንፈሱ ታወከበትና መምህሩን ከትምህርት ከበታው ለማባረር ግድግዳ መቧጠጥ ጀመረ።
መጀመሪያ የተጠቀመው ሁሌም የሚያደርገውን የፕሮፓጋንዳ ጦርነት አስቀድሞ ማወጅ ነበረ። ለዚህም ማቅ በሚያስተዳድረውና በፈረንጆቹ 2009 `Owned by mahebere kiduasan` የሚል ቃልን ለጥቂት ቀናት ከለጠፈበት በኃላ ያወረደው ደጀ ሰለም የተባለው የመአት፣ የክስ እና የነቀፋ ብሎጉ  ላይ ኮሌጁ የትምህርትህን አቁም ጥያቄ ከማቅረቡ ከወር በፊት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪውን አባረረ በማለት መምህሩ ጨርሶ የማያውቃቸውን የፈጠራ ታሪኮች በመደርደርሰፊ ሪፖርታዥ ሰራ። በዚህ ጊዜ መምህሩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አድሮ ማኅበሩን እንቅልፍ አሳጥጦ እያንቀሳቀሰ ያለው የክስና የአሳዳጅነት መንፈስ አሁንም እንደተከተለው አወቀና የሚገለጥበትን ጊዜ በጸሎት መጠበቅ ጀመረ።
ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም ላይ ተባረረ በማለት ካስነገረ ከአንድ ወር በኃላም ይኼን ለማስፈጸም ወደ ኮሌጁ ሄዱ በሰራው ሴራ መምህር አሰግድ ወደ ኮሌጁ ቅጥር ጊቢ እንዳይገባ የሚል ትዕዛዝ በኮሌጁ ዲን በኩል ለጥበቃዎች ተላለፈ። መምህሩም በሕጋዊ መስመር የገባሁ ተማሪ ስለሆንኩ በሕጋዊ መንገድ ካልሆነ በቀር እንዳትገባ በሚል የቃል ትዕዛዝ ትምህርቴን አላቆምም በማለቱ ከአንድ ሣምንት በኃላ በወረቀት ታግደሃል ተባለ። እሱም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲመለከተው የሕግ ክፍተት እንዳለበት ስለተረዳ ኮሌጁን ከሰሰ። የክስ ወረቀት ለኮሌጁ እንደደረሰ ያወቀው ማኅበረ ቅዱሳን አላማዬ ግብ ሳይመታ ሊቀር ነው በማለት የኮሌጁን ዲን ጉዳዩን ለኔ ጣሉት ብሎ ደስታ በርሔ የተባለ የአመራር አባሉን የኮሌጁ ጠበቃ አድርጎ በማቆም ከዚህ በፊት በፈጠራ ወሬ እንዲታገድ ያደረገው ተማሪ ትምህርቱን እንዳይቀጥል ለማድረግ የሀሰት ማስረጃዎችን በማደራጀት መከራከር ጀመረ። ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲንቀሳቀስ ሲያዝ ወዲያውኑም መምህር አሰግድ ሣህሉ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለስ በማዘዙ መሞህሩ ትምህርቱን ቀጥሎ እንዲከራከር ተደረገ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ በሐምሌ 7 ቀን 2003 .. ለመምህር አሰግድ በመፍረድ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፈ።

 ውሳኔ
-       ተከሣሽ ከሳሽን ከትምህርት ገበታቸው ያገዳቸው አለአግባብ ነው፤
-       በመሆኑም ከሣሽ በምስክሮቻቸው በተረጋገጠው መሠረት የጀመሩትን ትምህርት በማታው ክፍለ ጊዜ ይቀጥሉ ሲል /ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፤
-       ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ከሣሽ ዝርዝር የማቅረብ መብታቸው ተጠብቋል።
ይህ ውሳኔ ሲሰማ የኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞችአሳሳቱን ሲሉ ሌላው የኮሌጁ ማኅበረሰብ ይልቁንም መምህራኑና ተማሪዎች ለመምህሩ በመፈረዱ ደስታቸውን መግለጽ ቢጀምሩም በማኅበረ ቅዱሳን መንደር ያለው ሰይጣን ግን መንፈሱ የሚረካው ሰው በመግደል፣ በማባረርና በሀሰት በመወንጀል በመሆኑ እጅጉን ተበሳጭቶ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አለ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ተመልክቶ ይግባኝ የሚያስጠይቅ አይደለም የስር ፍርድ ቤትም ውሳኔ ትክክል ነው በማለት መዝገቡን ይዘጋል። ይህ ውሳኔ ማቅን ጨርቅዋን አስጥሎ አሳበዳትና ክሱን የተረታሁት መምህሩን በከንቱ ከስሼ ነው ከማለት ይልቅ እንዴት እሸነፋለሁ እንደገና አቤት ማለት አለብኝ ብላ ተነሳች።  ማኅበርዋ እንዴት አቤት ብል ለድል ያበቃኛል እያለች ላለፉት 5 ወራት ስታሴር ቆይታ
ጊዜው እየሄደባትናየመምህሩም መመረቂያ እየደረሰ ስለመጣ በስተመጨረሻም ደረስኩበት ያለችውን የኮሌጁን ህልውና የሚያጠፋ አቤቱታ አቀረበች።
ይህ አቤቱታ እንዴት እንደቀረበ ለማጣራት የበኩላችንን ጥረት አድርገን ነበር። ከትንሳኤ በኃላ ደስታ በርሄ(የማቅ ጠበቃ) ማንያዘዋል(የማኅበረ ቅዱሳን ነገር ሰሪ) እና ዘውዴ(የያረጋል የጭን ገረድ) ሆነው አቡነ ጢሞቲዎስ ቤት ሄደው ጤንነታቸውን ለውጥ እንዳለው በመጠየቅ ጀምረው ብጹዕ አባታችን እርስዎ ከኮሌጁ ከጠፉ በኃላ እኮ ብዙ ነገር ተበላሸ። አስተዳደሩ ጉዳዬ ብሎ ስለማይሰራ እርስዎን የከሰሰው ልጅ  ሊመረቅ ነው።መምህራኑም የኛ ናቸው የምንላቸው ሳይቀሩ `A` እየሰጡት ይገኛሉ። ይህ ተርም ካለቀ መመረቁ ነውና ትምህርት እንዲያቋርጥ ይዘዙ እርስዎ በሚመሩት ግቢ ሕግም ሆነ ፍርድ ቤት ምን አገባው? ከእርስዎ በላይ ማን አለ? በግቢዎ እንደፈለጉ ይሁኑ እኛም የሚደረገውን እናደርጋለን ሲሉዋቸው እሳቸውም ነገሩ ብዙም ባይዋጥላቸውም የሚደረገው ነገር አጓጉቷቸውየሚባለውን ሁሉ ለመስማትና ለመፈጸም ልባቸውን አዘግጅተው ቁጭ አሉ።አቡነ ጢሞቲዎስ እንደ ካቶሊኮች ፖፕ ንግግሬ ዶግማ ነው ብለው በሚናገሩት ንግግር ይታወቃሉ። ታድያ እነዚህ ሰዎችም የሊቀ ጳጳሱን ደካማ ጎን በመረዳት አባታችን ቃልዎን ይጠብቁ ነገሩን አይርሱ እያሉ ሲዘበዝቡዋቸው እሳቸውም ዶግማቸውን ሊያጸኑ ተነሱ። ከዛም የኮሌጁን የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችንበመጥራት በአስቸኳይ ትምህርት እንዲያቋርጥ አድርጉ በማለት ያዛሉ። እነርሱም ልጁ ሕጋዊ ነው። ለምንድን ነው የሚባረረው? አስከዛሬ ድረስም መስሎን የተታለልነው ይበቃናል። በማለት እምቢ አናባርርም ይላሉ። እሳቸውምበቃ ሊመረቅ!! እኔ እያለሁ ሊመረቅ!” ብለው ሲጠይቁአዎን አባታችን ይመረቃል።ብለው መለሱላቸው።ይህማ አይደረግም በሉ አሁን ግቢ እንዳይገባ አድርጉበማለት ሲቆጡ እነርሱም በአንድነትአይ እኛ እንደዛ አናደርግም ከፈለጉ እርስዎ በራስዎት ፊርማ እንዳይገባ ያድረጉ እንጂ እኛ የሰውን ሕጋዊ መብት አንነካምበማለት እምቢኝ አሉ። እሺ ይከሰስም ቢባሉ ሳይስማሙ ቀሩ።
አብር አብር፣ ግፋ ግፋ፣ ግደል ግደል በሚል የዛር ፈረስ የሚመራው ማኅበረ ቅዱሳን የኮሌጁ አስተዳደር ባይስማማበትም አቡነ ጢሞቲዎስን ይዞ ሰበሩ እንዲቀጥል አደርጎዋል።
ይህ የከስ አቤቱታ ሰበር እንደ ቀረበ ሲሰማ ምን ብለው አቤት ብለው ይሆን የሚለው ጥያቄ የተማሪውን ስሜት በመያዙ የተማሪዎቹ ካውንስል ጉዳዩንና ለማወቅና የአቤቱታ ወረቀቱን ለማየት ጉጉት አደረበት። የካውንስሉ አባለት የይግባኝ ወረቀቱ እጃቸው ገብቶ ሲመለከቱትጉዳዩ የአንድ የቤተክርስቲያን ልጅ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኮሌጁና በዚህ ተቋም እየተማሩና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የቤተክርስቲያን ልጆች ሕልውና ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ ስላገኙት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቤት ለማለት ወሰኑ። አቤቱታቸውን ሲያቀርቡም ክሱ የኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞቹ በማያውቁት ሁኔታ በማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ ተቀነባብሮ የቀረበ ክስ መሆኑ ታውቋል፡፡
የኮሌጁ የተማሪዎች ካውንስል ተማሪውን በጉዳዩ ላይ ሰብስቦ ያነጋገረ ሲሆን ጉዳዩ የሁሉንም ተማሪ ህልውና የሚነካና ከላይ የጠቀስነው በተራቁጥር 2.1 ላይ ያለውና በተራ ቁጥር 2.4 ላይ የተጠቀሰው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ለኮሌጁ ከተወሰነ የኮሌጁ ተማሪዎች ህልውና እንደ ቀይ ሽብር ጊዜ በሰዎች እጅ ላይ ስለሚሆን ከምንም ነገር በላይ አንገብጋቢ ችግር ሆኖ እንደታያቸው ለመገንዘብ ተችሏል።
ማኅበረ ቅዱሳን በአባሉ በደስታ በርሔ አማካኝነት ይህን ክስ ሲያዘጋጅ ረጅም አቅዶ ረጅም አልሞ የኮሌጁን ተማሪዎች ህልውና በቁጥጥር ስር ለማድረግና ከዚህ ኮሌጅ የሚወጡ ተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እየቀጠሉት ያለውን የማስትሬትና የዶክትሬት ዲግሪ ዋጋ ለማሳጣትና ከአሁን በኋላም ተማሪዎቹ በሌላ የትምህርት ተቋም ምንም አይነት ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ አስቦ ነው።
መተዳደሪያ ደንቡና የቀረበው አቤቱታ
የኮሌጁ አቤቱታ ኮሌጁ ምንም አይነት ሕጋዊ መሰረት የለውም ሕጋዊ አቋሙ ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነሰ ነው። ሲል ያቀረበውን አቤቱታ የኮሌጁ መተዳደራ ደንብ ውድቅ ያደርገዋል።1954 . ጀምሮ ኮሌጁ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፋካልቲዎች አንዱ ሆኖ ከመንግሥት በሚመደብለት በጀት ሲተዳደር በሺህ የሚቆጠሩ ምሁራንን ሲያስመርቅ ከቆየ…” ይህ ጽሁፍ እንደሚያስረዳው ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋክልቲዎች እንደ አንዱ እንደ ነበር እና ዩንቨርሲቲውም እንደ አካሉ ቆጥሮ ሕልውናውን እንደተቀበለ ነው። ምንም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ኮሌጁ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አካል ባይሆንም ዩንቨርሲቲው ህልውናውን ተቀብሎ ለኮሌጁ ተማሪዎች ዲግሪና ዲፕሎማ እውቅና ሰጥቶ ተማሪዎችን በማስትሬትና በዶክትሬት እያስተማረ ይገኛል። ይህ ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴርም በኩል እውቅና እንዳለው ያስረዳል። ምክንያቱም ያለትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ፈቃድ ዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል አይችልም እና ነው። ማህበረ ቅዱሳን በጠበቃው በደስታ በርሄ አማካኝነት በኮሌጁ ስም ይህን አቤቱታ ከማሰገባቱ በፊት ትምህርት ሚኒስቴርን እንደለመደው በኮሌጁ ስምየሰጠኸኝን ህልውና ሽረህ ተማሪዎቼን አንተ ከምታስተዳድራቸው ተቋማት አባርረህ ሜዳ ላይ ልትጥለኝ ይገባልማለት ነበረበት። መቼም ይሄን ስታነቡ ወይኔ አላሰብንበትም ነበር እንጂ እናደርገው ነበር ማለታችሁ አይቀርም።
በኮሌጁ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 ላይ የኮሌጁ ዓላማዎች በሚለው ስር ኮሌጁ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡ብሎ 5.1 ላይ
5.1. “ለቤተ ክርስቲኒቱ ተስማሚ የሆነ፣ ለሀገር ክብር፣ ለወገን ጥቅም የሚረዳ፣ ለዕድገትና ብልጽግናዋ የሚበጅ እምነትና ሥርዓትዋን የሚያራምድ ትምህርት እንዲካሄድ ማድረግ፤የሚል ቃል አለ
ይህ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ያለው ንኡስ አንቀጽ በአቤቱታው 2.4 ላይ ከቀረበው ጋር በመሰረታዊ ሀሳብ ይለያል። ኮሌጁ የሚፈልገው ተማሪ ቤተክርስቲያኑን አገሩንና ወገኑን የሚጠቅም ትውልድ እንዲወጣ ሲሆን አቤቱታው ደግሞ እንዴት ተደርጎ አላማችን አጭር ነው። ሰፋ አድርጋችሁ አትዩብን የምን ሀገር የምን ወገንብቻበሚል ቃል ገለጽንላችሁ እኮ የሚል ነው።
በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 16የኮሌጁ ዲን ሥልጣንና ተግባር ከሚለው ስር 16.1.1 ላይቦርዱ በሚፈቅደው መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ውጭ አገር ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋሞች ጋር አስፈላጊ የአካዳሚክ ስምምነቶችን ማድረግ፣የሚለው ኮሌጁ ያለህጋዊ አቋም ይህን ማድረግ እንደማይችል ያስረዳል። ምክንያቱም ህጋዊነት ሳይኖር ሕጋዊ ስምምነት ማድረግ የለምና።
የኮሌጁን ሕጋዊ አቋም ማሳጣት የደስታ በርሄ መሰረታዊ የክርክር መንገድ ስለሆነ ኮሌጁ ሊከሰስ አይችልም የሚል አንድምታን ለመፍጠር የፈለገ ስለሆነ ከመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ ህጋዊነቱን የሚያሳዩ ክፍሎችን እያወጣን የጠበቃውን መሰረታዊ የሕግ ዕውቀት ችግር ማሳየቱን እንቀጥላላን።
ሌላው አቤቱታው ከመተዳደሪያ ደንቡ ጋር ያለውን ከፍተኛ ልዩነት የሚያሳየውና አቤቱታውን ፍሬ ቢስ የሚያደርገው በኮሌጁ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6 ላይ ያለው ስለ ኮሌጁ ተግባርና ኃላፊነት የሚያወራው ክፍል ነው አንቀጹን እንዳለ እንመልከተው።
አንቀጽ 6
ተግባርና ኃላፊነት
ኮሌጁ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
6.1. ቤተ ክርስቲያኒቱ ለምትፈጽመው መንፈሳዊና ሥጋዊ ተግባር በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርትና በዘመናዊ እውቀት የበለፀጉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ኮሌጁ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ ከስራው ሂደት ጋር የሚስማሙ መብቶች ግዴታና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
6.2. በየደረጃው ተመድበው ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና የወንጌል ልዑካን መተካት የሚችሉ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሞያዎች ተሰማርተው በማገልገል ላይ የሚገኙት አገልጋዮች ወደፊት ለተተኪነት የሚያስችል ከፍተኛ የነገረ መለኮትንና የወንጌል መምህራንን ማዘጋጀት፣ በሰርተፊኬት በዲፕሎማና በዲግሪ ማስመረቅ፡፡
ይህ አንቀጽ አቤቱታውን ፍሬ ቢስ አድርጎ ምናልባትም ጠበቃውን ደስታ በርሄን ወደ ሕግ ትምህርት ቤት እንደገና የሚመልስ ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው?
ደስታ በአቤቱታው “…የሚሰጠው የትምህርት ዓይነትም ሆነ ብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት አይደለም፡፡ በመሆኑም በስሙ ሊከሰሰም ሆነ ሊፈረድበት አይችልም፡፡ በሕግ ‹‹ሰው›› የሚለውን መስፈረትም አያሟላምና፡፡የሚለውን ቃል ለመከራከርያው እንደ ዋና ሀሳብ አድርጎ ያቀረበ መሆኑን ለሚገነዘብ ሰው እንዲህ የደፈረው ምን አይነት ማስተማመኛ በኮሌጁ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ቢያገኝ ነው ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ያኔ ደግሞ ከመተዳደሪያ ደንቡ ላይ “…ኮሌጁ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ…” የሚለውን ሲያነብ ከአንድ አመት በላይ ጥብቅና የቆመለትን ተቋም መተዳደሪያ ደንብ እንኳ አንብቦ የማያውቅ ጠበቃ የሥራ ፈቃዱ መነጠቅ አለበት ቢል ማን ይቃመወዋል? ደስታ ደስ የምታሰኝ ሰው ነህ። በገዛ እጅህ እራስህን ጠምዝዘህ ስለጣልክ እና ተስፋ የጣለችብህን ባለዛርዋን ማኅበርህን ስላሳፈርክ እናመሰሰግንሀለን።  እነዳንተ አይነቱን ሰው ሲያይ ነው ያገሬ ሰው እንዘን እንፈር የሚለው።

ይህ አቤቱታ በሰበር ሰሚው ተቀባይነት አግኝቶ ለኮሌጁ ቢፈረድለት የሚያስከትላቸው ችግሮች
1.      ኮሌጁ ህልውናውን በመካዱ የኮሌጁ ተማሪዎች የሚኖራቸውን ተቀባይነት ያጣሉ። በዚህም የተነሳ የኮሌጁ ተማሪዎች በሌላ የትምህርት ተቋም ትምህርታቸውን ለመቀጠልም ሆነ ዲግሪና ዲፕሎማቸውን አቅርበው ሥራ ለመወዳደር ያላቸውን እድል ያሳጣል።
2.     ከዚህ በኃላ የኮሌጁ ተማሪን ማኅበሯ እንደለመደችው ከግቢው ለማባረር ብትፈልግ ያለምንም ተጨማሪ ምክንያት የአይንህ ቀለም አላማረኝም በማለት ለማባረር የደርግን ነጻ እርምጃ የመሰለ መብት በኮሌጁስም ታገኛለች።

ለግንዛቤ እንዲረዳ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ለመምህር አሰግድ ሣህሉ የወሰነውንና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያጸደቀውን ውሳኔ እንዳለ አቅርበነዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
መናገሻ ምድብ /ብሄር ችሎት
ሐምሌ 07 ቀን 2003 .
ዳኛ ፍቅርተ ተፈሪ
ከሣሽ /  አሰግድ ሣህሉ       
ተከሣሽ በኢ/////የቅ///ኮሌጅ መዝባቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሠጥቷል፡፡
ፍርድ
ከሣሽ ታህሳስ 27 ቀን 2003 . በተፃፈ ክስ ተከሣሽ 2003 . የትምህርት ዘመን በዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ማሟላት ያለብኝ ማስረጃ አሟልቼ በቀን ፕሮግራም ኮሌሎች ተማሪዎች ጋር ትምህርቴን እየተከታተልኩ እገኝ ነበር፣ ተከሣሽ ግን በተመዘገብኩበት ሰዓት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማውጣት ትምህርቴን ባግባቡ እንዳልከታተል የተለያዩ መሠናክሎችን ሲፈጥርብኝ ቆይቷል፤ ከዚህ በኋላ ደግሞ በቁጥር 42/05/04/03 በታህሣስ 14 ቀን 2003 . በተፃፈ ደብዳቤ ለብዙ ቀናት በትምህርት ገበታ ላይ ሳትገኝ ቀርተሃል፣ ከደብርህ ያቀረብከው ማስረጃም ትክክል አይደለም በማለት ትምህርቴን እንዳቋርጥ ውሳኔ ሠጥቷል፡፡ ነገር ግን የተባለውን ማስረጃ ትክክልኛ ማስረጃ ሲሆን ከትምህርት ቀረህ የተባለውም ደብዳቤውን እስከወጣ ድረስ በነበረው አንድ ሳምንት ውስጥ ወደ ትምህርት ቤት እንዳትገባ በመባሌ እና ከህዳር 8-20 ድረስም በትምህርት ቤቱ በነበረው አድማ የመማር ማስተማር ሂደቱ ስለተቋረጠ እንጀዲ ትምህርቱን ባለመፈለጌ አይደለም፤ ስለዚህ ባጠቃላይ የተከሣሽ ድርጊት አግባብ ስላልሆነ ተከሣሽ ህጋዊ የወሰደው እርምጃ ህጋዊ አይደለም እንዲወሠንልኝ፤ ማስረጃዬን ውድ በማድረግ የሰጠው ውሳኔም ተሠርዞልኝ ትምህርቴን እቀናል ዘንድ ውሳኔ እዲሠጥልኝ እጠይቃለለሁ ያለ ሲሆን ወጪና ኪሣራዬ ይታሠብልኝ ሲሉ አመልክተዋል፤ ማስረጃም አያይዘውል፡፡
ተከሣሽም ለዚህ ክስ በጥር 27 ቀን 2003 . በተፃፈ መልስ ክርክሩን አቅርቧል፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩ የሃይማኖት ክርክር የያዘ ስለሆነ /ቤቱ አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የለውም ሲል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን የፍሬ ነገር ክርኩን በተመለከተም ከሣሽ ቤተ ክርስቲያኗ የማትቀበለውን ትምህርት የሚያራምዱ መሆናቸው በደብረ ይባበየ አዲስ ያሬድ ቤተክርስቲያን //ቤት አቤቱታ ቀርቦባቸውፀ ቤተክርስቲያኗም ይህን በማረገገጧፀ ከሣሽ በማታለል የቀበና መድሃኚዐለም ሸበኻጙ ጉባኤ አባል ነን በማለት ያቀረቡት ማስረጃ በደብሩ አስተዳዳሪ የተሠረዘ በመሆኑና ከሣሽም መተዳደሪያ ደንቡ ከሚፈቅደው ውጭ ከሶስት ቀናት በላይ ለአስራቀ አምስት ቀናት በትምህርት ገበታ ላይ ሳይገኙ በመቅረታቸው ከትምህርት እንዲሠናበቱ ተደርጓል። በመሆኑም የከሣሽ ክስ ከበቂ ኪሣራ ጋራ ውድቅ ተደርጎልን ልንሠናበት ይገባል ሲል ተከራክሯልፀ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫም አያይዟል።
በግራ ቀኙ መካከል ያለው የክርክርወ ሁኔታ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፡ /ቤቱም የፍርድ ቤቱ ስልጣን አያደለም በሚል በከሣሽ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መርምሮ መገቢት 24 ቀን 2003 ዓፀን በዋከው ችሎት /ቤቱ ጉዳዩን አይቶ የመወሠን ስልጣን አለው ሲል መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ ብይን ሠጥቷል። በመሆኑም ይህን ጉዳይ በዚሁ በማለፍ ውሳኔ ሊያገኙ ያገዳቸው ይገባቸዋል ያላቸውን 1/ ተከሣሽ ከሳሽን ከትምህርት ገበታቸው ያገዳቸው ባግባቡ ነው አይደለም? 2/ ከሣሽ ትምህርታቸውን ቀጥለው እንዲማሩ ለወይገባል አይገባም? የሚሉትን በመያዝ መዝገቡን እንደሚጀከተለው መርምሮታል።
የመጀመሪያውብ በተነከጀተ በናስረጃነት ከቀረበውና በከተከሣሽ በታህሣስ 14 ቀን 2003 . ከተጻፈው የስንብት ደብዳቤ ለመረዳት የተቻለው ተከሣሽ ከሣሽን ትምህርት እንዲያቛርጡ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ለብዙ ቀናት በትምህርት ገበታ ላይ ባለመገኘት እና ከደብራቸው ትክክለኛ ማስረጃ ባለማደቅረባቸው የሚሉትን ምክንያቶች በመጥቀስ ነው። ምንም እንኳ ለውሣኔው መሠረት የሆኑት ምክንያቶች እነዚህ ጉዳዮች በመሆናቸው በደብዳቤው ላይ ቢገለጽም ተከሣሽ በሠጠው የጽሑፍ መልስ ላይ ከሣሽ የኮሌጁ ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን የማትቀበለውን ትምህርት የሚያራምዱ ናቸው የሚል ክርክር በማቅረቡ ምክንያት /ቤቱ ከቀረቡት ማስረጃዎች በተጨማሪ በዚህ ጉዳይ ላይም ጭምር ምስክሮችን ስምቷል።። ከተከሣሽ ምስክሮች ውስጥ የመጀመራው አንድ ተማሪ የሃይማኖት ችግር አለበት ብሎ የመጨረሻውን ውሣኔ ይሚሠጠው አካል ቅዱስ ስኖዶሱ ሲሆን ከሣሽ የሃይማኖት ችግር አለባቸው ብሎ ይህ አካል የሠጠው ውሳኔ ግን የለም ሲሉ መስክሮዋል።። በሌላ በኩል የተከሣሽ የራሱ ሁለተኛ ምስክር በዋና ጥያቄ ላይ ከሣሽ ከቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖት ተቃራኒ በሆነ መልኩ የፕሮቴስታንት ትምህርት ሲያስተምሩ ተደርሶባቸዋል ሲሉ የምስክርነት ቃላቸውን የሠጡ ቢሆንም በከሣሹ ለቀረበላቸው መስቀለኛ ጥያቄ መልስ ሲሠጡ ግን ከሣሽ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ሲከተሉም ሆነ ሲያስተምር እኔ አላየሁም ሲሉ አስመዝግበዋል። ከነዚህ የምስክሮች ቃልም መረዳት የተቻለው ይህ የተከሣሽ ክርክር እራሱ ባቀረባቸው ምስክሮች የተስተባለ እንደመሆኑ መጠን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ነው።
ተከሣሽ ከሣሽን ከትምህርት ለማገድ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ወደ ተጠቐሱት ምክኒያቶች ስንመለስ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ምንም እንኳ ተከሣሽ ከሣሹ ለረጅም ጊዜ ከትምህርት ቀርተዋል ቢልም ይህን የሚያረጋግጥ አንዳችም የሠነድ ማስረጃ አላቀረበም። በዚህ ረገድ የግራ ቀኝ ምስክሮች ከመረመርም ከሣሽ ከት/ ገበታ የቀሩት አንድም በኮሌጁ ጥያቄ የድጋፍ ደብዳቤ አምጡ በተባሉበት ወቅት በነበረው ክርክር ሌላም ደግሞ በትምህርት ቤቱ በነበረው የተማሪዎች አድማ ምክናት ትምህርት ተቋርጦ በነበረበት ሰዓት ስለመሆኑ በከሣሽ ምስክሮች በሚገባ የተመሠከረ ሲሆን ይህ የምስክሮች ቃል ግን በተከሣሹ ምስክሮች አልተስተባበለም። እንዲያውም የመጀመሪያው የተከሳሽ ምስክር ራሳቸው በመማር ማስተመሩ ሂደት ላይ ችግር ተፈጥሮ የነበረ በመሆኑ ምክንያት ትምህርት ተዘግቶ እንደነበር ጠቁመዋል። ስለዚህ የግራ ቀኙ ምስክሮች ከተያዘው ጉዳይ አንጻር ሲመዘን ከሣሽ ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ በሚያደርግ መልኩ ትምሀርት እየተሠጠ ባለበት ወቅት በራሳቸው ችግር ምክንያት የቀሩ ወይም ትምህርቱን ያልተከታተሉ አለመሆኑን ሚዛን በሚደፋ መልኩ የሚያስረዳ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከሣሽ በዚህ ረገድ ከሣሽን ከትምህርት ለማገድ የሠጠውን ምክንያት /ቤቱ ተቀባይነት የሌለው ሆኖ አግኝቶታል።
ሌላው ተከሣሽ የጠቀሰው ምክንያት ለሁለተኛ ደረጃ ሲመረመር ደግሞ ከሣሹ ከደብራቸው ትክክለኛ ማስረጃ አላቀረቡም የሚል ነው። ይህ ትክክል አይደለም በሚል የተጠቀሠው ማስረጃ በደ..200/88/03 በህዳር 6 ቀን 2003 . የተጻፈው መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም ደብዳቤ ከሣሹ በደብራቸው ተገቢውን የአባልነት ክፍያ እየከፈሉና የቤተክርስቲያኗ አባል ሆነው እንደሚገኙ የሚገልጽ ነው። ይህን ማስረጃ በማቅረባቸው ምክንያትም ትምህርት ጀምረው እየተከታተሉ የነበረ መሆኑ እሙን ነው።። ተከሣሽም ማስረጃውን ተቀብሎ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከፈቀደላቸው በኋላ ምክኒያት የለም።። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ተከሣሽ ያነሣው ተነስቷል የሚል ነው።። ይህን ሁኔታ የሚገልጸውንና በከሣሽ የቀረበውን የሠነድ ማስረጃም /በደ..417/666/03 ታህሳስ 17 ቀን 2003 . የተጻፈ/ /ቤቱ የመረመረ ሲሆን በአንድ በኩል ይህ ደብዳቤ በደብሩ አስተዳዳሪ የተጻፈው ተከሣሹ ከሣሽን ከትምህርት በማገድ ደብዳቤውን ሲጽፍ /ከታህሣስ 14 ቀን 2003 ./ በኋላ በመሆኑ ምክንያት የማገዱ ውሳኔ መሠረት ነው ብሎ መገመት ስለማይቻል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ በደብሩ የተጻፈው ደብዳቤ እራሱ ምንም አይነት ምክንያት የማይገልጽ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ እንዲሁ በዘፈቀደ በግለሰቦች ወይም በስራ ኃላፊዎች በሚጻፍ ደብዳቤ የአንድን ሰው የመማር መብት መገደቡ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ምክንያት በዚህ ረገድ የቀረበውን የተከሣሽን ክርክርም /ቤቱ ባለመቀበል ውድቅ አድርጎታል። ስለዚህ ተከሣሽ ከሳሽን ከትምህርት ገበታቸው ያገዳቸው በአግባቡ አይደለም ሲል /ቤቱ ፍርድ ሰጥቷል።።
ሁለተኛውን በተመለከተ ያው ከላይ በዝርዝር እንደተመለከተው የተከሳሽ ውሳኔ አግባብ አይደለም ስለተባለ ከሳሽ /ታቸውን ቀጥለው ሊማሩ ይገባል። በመሆኑም ቀርበው የተሰሙት የከሻስ ምስክሮች አንዱም አብረን የተመዘገብን ቢሆንም በማታ እንጂ በቀን መማር አትችሉም ሲሉን ማታ መማር ባለመቻሌ አቋርጫለው ሲሉ በገለጹትና ሌላው ከሳሽ የቀን መማር አይችሉም ተብለው የማታ እየተማሩ እንደነበር ነው የማቀው ሲሉ በመሰከሩት መሠረት ከሳሽ በዚሁ ሽፍት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይቀጥሉ ሲል /ቤቱ ፍርድ ሰጥቷል።
ውሳኔ
-       ተከሣሽ ከሳሽን ከትምህርት ገበታቸው ያገዳቸው አለአግባብ ነው፤
o   በመሆኑም ከሣሽ በምስክሮቻቸው በተረጋገጠው መሠረት የጀመሩትን ትምህርት በማታው ክፍለ ጊዜ ይቀጥሉ ሲል /ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፤
o   ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ከሣሽ ዝርዝር የማቅረብ መብታቸው ተጠብቋል።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።