ካለፈው የቀጠለ………………………………………
ሌላው
በዘመናችን የተደረገ ነው። በካምቦዲያ ውስጥ
ኬሜን ሩዥ የተባለው ኮሚኒስታዊ ድርጅት ሥልጣኑን ይዞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የገዛ ወገኖቹን በገደለበት ወቅት ነው። በዚያን ወቅት
በሀገሪቱ እየተፈለጉና እየታደኑ ይገደሉ የነበሩት አሉ
የሚባሉት የሀገሪቱ ምሑራን ነበሩ። በካምቦዲያ መማር ወንጀል ነበር። ለመማር መጣጣር የሚያስቀጣ ነበር። የነሞዛርትን ረቂቅ ሙዚቃ ያሰማምሩ የነበሩ እጆች የምዕራባውያንን ባሕል ልታመጡ
ነው ተብለው ተቆረጡት። የታሪክ መዛግብትን
የሚመረምሩ ዓይኖች በአብዮቱ ላይ ታሴራላችሁ ተብለው እንዲጠፉ ተደረጉ። ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ተወረወሩ። ማወቅ ወንጀል የሆነበት ወቅት ነበርና።
ያ
ጊዜ ተመልሶ የመጣ የመሰለበት ወቅት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን አምጥቶልናል። ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ማስቀባት፤ ቢቻል የሆነ የሚከሰስበት ነገር መፈለግ ቤተክርስቲያን መናፍቅ ትበለውም፤ አትበለውም በእነርሱ ጥቁር መዝገብ መናፍቅ እንደሆነ ማወጅ ማሳደምና እንዲባረር ማድረግ ቀዳሚው ነገር ነው። ከሳሽ ማኅበረ
ቅዱሳን፤ ምስክር ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፈራጅ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሕግ አስፈጻሚ ማኅበረ ቅዱሳን በሆነበት ሁኔታ ጉዳይህ
አሰቃቂ ፍጻሜ ያገኛል። ከእሱ ከተስማማህ ትድናለህ፤ ካልተስማማህ
ትጠፋለህ።ለዚህ
አስዛኝ ሁኔታ ምሳሌ ምሳሌ የሚሆነን በአንድ ወቅት ማኅበሩ በሚያወጣው ጋዜጣ ላይ የከፍተኛ የቴዎሎጂ ኮሌጅን፤ ከምክትል ዲኑ ጀምሮ የኮሌጁን ዋና ጸሐፊ፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግዕዝ መምሕር፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግእዝ መምህር፤በኮሌጁ የቤተክርስቲያን
ታሪክ መምህር፤ የኮሌጁን ሥራ መሪና የእንግሊዝኛ መምህር ፤ ስድስት ተማሪዎችን ጨምሮ ተሐድሶዎች
ናቸው ብሎ አውጥቷል። ይህም የኮሌጁን
ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ወደ ቅድስት ሥላሴ የተዛወሩ ሦስት አስተማሪዎች ተሐድሶ ማለቱን ሳይጨምር ነው። ይህ ጸሐፊ
እስከሚያታውሰው ኮሌጁ ያሉት አስተማሪዎች ከስምንት እስከ አሥር ቢሆኑ ነው። ስለሆነም በማኅበረ
ቅዱሳን ሚዛን ኮሌጁ ካሉት አስተማሪዎች ዘጠና በመቶዎች መናፍቃን ነበሩ ማለት ነው።
ይህን
ታሪክ ስጽፍ በስሜታዊነት ቢሆን አትፈረዱብኝ ። ልቤ እየደማ
ነውና የምጽፈው። ወደማን አቤት ይባላል? ወደ ማንስ ይኬዳል ? እግዚአብሔር እንዲፈርድ ከመጥራት ሌላ ማን ይባላል ?
"ለመሆኑ የእነዚህ
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም አደባባይ የወጣው ቤተ ክርስቲያን መክራበት ነው ? ለምናቸው አልቅሳላቸው እባካችሁ ልጆቼ ስህተት አግኜባችኋለሁና ተመለሱ ብላቸው ነው ? በፍጹም ! ብጹዓን
ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን የእነዚህን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተከሰሱብትን ምክንያት አያውቁም ። ወንጀሉን የሚያነቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ ላይ ነው። ከዚያም በየቤታቸው እነዚህን ካላባረራችሁልን የሚል ማስፈራራያ ይመጣላቸዋል።
ለመሆኑ
ይህ ሁሉ እወጃ «ጳጳሳቱ ተሐድሶ
ሆኑ» ቤተ ክርስቲያኒቱ ከነበራት ኮሌጅ
ውስጥ ከዲኑ ጀምሮ እስከ አስተማሪዎቹ ድረስ ተሀድሶ ሆነዋል ብሎ ማወጅ ማንን ነው የሚጠቅመው ? ለማነው የልብ ልብ የሚሰጠው ? የቤታችንን ጉድ ጓዳችን ይዘን ድብቅ አድርገን ተዋቅሰናል? ተላቅሰናል? ኧረ ቤተ ክርስቲያን ትምከርበት! ኧረ ለቤተ
ክርስቲያን የምታስቡ ቆም ብለን እንወያይበት! የበደለ ቢኖር
እንኳን አሁን ማኅበረ ቅዱሳን በሚያደርገው ዘመቻ ንስሐ ይገባል ወይ? ይህ እኮ
በሕዘብ ላይ የተነጣጠረ ጠላትነት ነው። ለመሆኑ ይህን
ያህል ሰው የለንም ወይ ? ይህን ያህል አገር ተፈትቷል ወይ ? ተከሳሽ በሌለበት ከሳሽ እንዴት ያፈርዳል?
ኧረ
ለመሆኑ «የቅባት ማቅለጫዎች» የጎጃም ሊቃውንት በስመ ቅባት ማንም ወፍ ዘራሽ ሲሳለቅባቸው ምን አሉ ይሆን ? የሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ፤ የሰማእቱ የቴዎፍሎስ፤ የሊቁ የድሜጥሮስ አጽም እንዴት አለ ይሆን ? ስንቱ ሊቅ በጥንቃቄ የነገረ መለኮት ኃይለ ቃላትን ሳያማታ ምሥጢር ሳያፈልስ ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጋር በጥንቃቄ እየመተከረበት ሲመልስ የነበረውን ጉዳይ እነዚህ ወጣቶች
የሚመልሱት ቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት አጥታ ነው ?
ማኅበረ
ቅዱሳን ፍላጎቱ አውድማው እንዲህ እንዲሆንለት ነው። የትናንቶቹ አቶዎች ዛሬ ቄስ ተብለው ከዚያም አልፈው ራሳቸውን መምህር አሰኝተው በድግሪ ያጡትን ገንዘብ በቤተክርስቲያን ተጠግተው፤ በፖሊቲካ ያጡትን ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን ጓሮ በኩል ማግኘት እንዲችሉ፤ ቤተክርስቲያን ወልዳ ያሳደገቻቸውን ገለል እንዲሉ ምድረግ ነበረባቸው። እነዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች አንዳንዶቹ በማኅበሩ ግፊት ከቤተ ክርስቲያን ከተባረሩ በኋላ በሠሩት ሥራ ተጸጽተው ቤተክርስቲያናቸውን ለበደሉት በደል ፤ ለሰደቧት ስድብ
፤ለሌሎች መሳሳት ምክንያት ለመሆናቸው በሙሉ ንስሐ ገብተው ተጸጽተው ቤተክርስቲያናቸውን ቢጠይቁ ያ ለማኅበረ ቅዱሳን የሞት ሞት ነው። ምክንያቱም ለነርሱ የእነዚህ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አደባባዮች መታየት ለሕልውናቸው አስጊ ነው። ብሩ ፎቅ ቤት መሥራቱ ሊቀር ነው። እውነት ሊገለጥ ነው። እንዲህ ያሉትን አስተማሪዎች የት አፍናችሁ፤
አስቀምጣችሁ ነበር ሊባሉ ነው። ስለዚህ ከዚህ
ይልቅ እንደምንም ብሎ ማሳደድ አውሬ እንዲበላው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ሲጠፉላቸው ደግሞ በአውሬ የተበሉት ራሳቸው ናቸው። ወደ ጴንጤ የሄዱት ራሳቸው ናቸው ብሎ ማላዘን ይሄ ነው ልማዳቸው። «በወልድ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ የሚለውን ለውጠው «በማኅበረ ቅዱሳን የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው» ብለው ያመኑ ይመስል ዛሬ በማኅበረ ቅዱሳን እስካመነ ድረስ ከሃዲ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን የሚዘርፍ ቢሆን ዘማዊ ቢሆን ግድ የለውም። የማኅበሩን ኅልውና እስካልነካ ድረስ አይነካም።
ማኅበረ
ቅዱሳን ሃይማኖተ አበው ከተዘጋለትና ሥልጣኑን ካደላደለ በኋላ ተሐድሶ የሚለውን ቃል አስፍቶ ማናቸውም በቅድስት ሥላሴ የሰንበት ትምህርት ቤት የአዘማመር ስልት የሚዘምሩ በሙሉ ተሐድሶ ናቸው በማለት አዲስ አንድምታ አበጀለት። መንበር ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ በስጦታ በተሰጠው ኦርጋኖን በግርማዊነታቸው ትእዛዝ በሰለጠኑ የቤተክርስቲያኗ ልጆች በነ ዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜነህ በተዘጋጀው መዝሙር የሚጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ሴቶች ቆመው የዘመሩበት ቦታ ነው።
የቅድስት
ሥላሴ መዝሙራት መንፈስን የሚመስጡ የግጥማቸው ስልት ሥርዓትን የጠበቀ ካቴድራሉ ባሉት ምሑራን እየተመረመረ የሚወጡ ስለነበር በአብዛኛው ወጣቶች ዘንድ ተወዳጅነት ነበራቸው :: በዚህም ምክንያት ለብዙ ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ከቤተክርስቲያናቸው እምነትና ሥርዓት ጋር መተዋወቅ ምክንያት ሆኗቸው ነበር ::
እንግዲህ
ማኅበረ ቅዱሳን በጊዜው ባገኘው ኃይል ተጠቅሞ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴን የአዘማመር ስልት ይከተሉ የነበሩትና በአዲስ አበባ በልደታ ለማርያም በቅድስት ሥላሴ፤ በሳሪስ አቦ፤ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ በሐረር በስድስቱም አብያተ ክርስቲያናት በአማሬሳ፤ በሒርና ፤በአሰበ ተፈሪ፤
በድሬዳዋ በቅድስት ማርያም፤ በጊዮርጊስ፤ በደብረ ማርቆስ፤ በናዝሬት የሚገኙ የሰንበቱ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንዲዘጉ አስደረገ። ወጣቶቹንም ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡና በቤተ ክርስቲያን እንዳይሰበሰቡ አሳገደ። ከዚያም የራሱን ድርጅት በየቤተክርስቲያኑ ተከለ።
በአሁን
ወቅት ከቤተክርስቲያን ስለተባረሩ ወጣቶች ማኅበረ ወጣቶች ማኅበረ ቅዱሳን የሚያወጣቸው ዘገባዎች ፍጹም ሐስትን የተመሉ ናቸው :: ስለ እነዚህ ልጆች ያለው እውነታ የሚከተለው ነው።
1ኛ
. ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ አቤቱታም፤ ክስም ለደብር አስተዳዳሪዎችም፤ ሆነ ለሀገር ስብከት ሥራ አስኪያጆቸ ያቀርብ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው።
2ኛ
. እነዚህ ልጆች ከመባረራቸው በፊት በኦርጋን የቅድስት ሥላሴን መዝሙር አትዘምሩ ከሚል ውጪ የተከሰሱበት የክህደት ትምህርት የለም። በየትኛውም ሥፍራ
ጉዳያቸው በስብሰባ አልታየም ።
3ኛ
. ከቤተክርስቲያን ከተባረሩ በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ፤ እንዳያስቀድሱ፤ ቢወልዱ ክርስትና እንዳያስነሱ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪዎች ሰለታገዱ ትንሽ ጊዜ በአዳራሽ፤ በየቤታቸው እየተሰባሰቡ እርስ በእርሳቸው ቢጽናኑም ከማኅበራዊ ኑሮ ግፊት፤ ከፕሮቴስታንቱ ዓለም ማባበልና ከማኅበረ ቅዱሳን
የጥላቻና ደብድቡልኝ፤ አባሩልኝ የሚል ጥላቻ ጩኸት በስተቀር በፍቅር የሚመልሳቸው ስላላገኙ ጠፍተው የቀሩ ናቸው። አንዳንዶቹም የከዳቻቸው ደጅ፤ የወረወረቻቸው እናት ቤተ ክርስቲያናቸው መስላቸው የግለሰቦችን ኃጢአት እና የቤተ ክርስቲያን ቅድስና መለየት አቅቷቸው የቤተክርስቲያን ጠላቶች ሆኑ። አንዳንዶቹም አጥፍተን ከሆነ ይቅርታ ይደረግልን ቢሉ ማኅበረ ቅዱሳን ግብረ አበሮቹን አሰማርቶ አስደበድባቸው። አንዳንዶቹንም በፖሊቲካ አስከሰሰ፤
አንዳንዶቹንም አሰገደለ። በድሬዳዋ የሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር አባል ይዞ የነበረውና የሀገር ልብሱን ለብሶ ጭራውን ይዞ የእመቤታችንን በዓል አከብራልሁ ብሎ ወጥቶ ተሀድሶ ነው ተብሎ በማኅበረ ቅዱሳን አባላት የተገደለው ወንድማችን «አዳም» ከእነዚህ ስማቸውን
ከማላውቀው አእላፋት ወጣቶች አንዱ ነው። የእነዚህን ደም የሚጠየቀው ማን ይሆን ? ይህ ሁሉ ሲሆን ወደ የት እንደሚሄዱ ግራ የገባቸውን ወጣቶች በግልጥ ያገኘው የፕሮቴስታንቱ ዓለም ወደ
የራሱ ጎራ በመውሰድ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ናችሁ፤ ስለዚህ ነው
ያባረሯችሁ እያለ መስበክ
ጀመረ :: በአንዳንድ ከተሞችም ከየቤተ ክርስቲያኑ፤ በማኅበረ ቅዱሳን የተባረሩትና ሰብሳቢ አጥተው የተበተኑትን ወጣቶች ለመንጠቅ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች እርስ በእርሳቸው ከፍተኛ፤ የመረረ ግጭት
ውስጥ ገብተው ነበር። ለእኔ ለእኔ በማለት
ለንጥቅያ ሲሮጡና በተለይም ደግሞ ዳግመኛ ወደ ቤተክርስስቲያናቸው እንዳይመለሱ እንደገና በማጥመቅ የእነርሱ
ታማኝ ተከታዮች በማድረግ ለዘላለም ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ለይተዋቸዋል ።
ሐረር
ጥንታውያን ከሚባሉት የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ ከመሆኑዋ በላይ እንደ አሜሪካዋ ቦስተን ለብዙ ሥልጣኔዎች የመጀመሪያዋ በር ከፋችም ናት። የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የተወለዱበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን በዚያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ ትኩረት ይሰጡ ነበር። በከተማዋ የሚመደቡት የቤተክርስቲያናችን
ሊቃውንትና ሊቃነ ጳጳሳት በእውቀታቸውና በትምህርታቸው ከፍተኛ ተደናቂነት ያላቸው ነበሩ። ለዚህም ምስክር
ይሆን ዘንድ በሊቀ ጳጳስነት ሀገረ ስብከቱን የመሩት ኢትዮጵያዊ ሰማእት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን መጥቀስ ይቻላል። ከለውጡ በኋላ የቀደመውን የወንጌል አገልግሎት እንዲቀጥል ለማድረግ ሌት ተቀን የሚለፉ የቤተክርስቲያን አባቶች አልጠፉም ነበር። ከእነዚህም አንዱ የአደሬ ጢቆ መካነ ሥላሴ ደብር አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ሰላም ጴጥሮስ አዘነ ናቸው። ሌት ተቀን ለጸሎትና ለአገልግሎት የማይደክሙት እንደ መላእክት ስሉጥ የሆኑት ኦርቶዶክሳዊው ሊቅ መልአከ ሰላም ጴጥሮስ አዘነ እያንዳንዱን የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት በተግባር የሚያሳዩ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት ናቸው። ተንባላት በከበቡአት ምድር ሰዓታቱን
ቆመው፤ ስብሐተ ነግሁን
፤ ጾመ ድጓውን አድርሶ ፤ውሎ ቅዳሴው
አስቀድሶ ማታ ምሕላውን፤ የመንፈስ ቅዱስ
ልጆቹን አስተምሮ ፤ውዳሴ ማሪያምን
በዜማ አድርሶ ፤ ለጥቂት ስዓታት
እረፍት በኋላ እንደገና
ስዓታት ለመቆም የሚነሳው ስንቱ ነው ? መልአከ ሰላም ጴጥሮስ እንዲህ ያሉ ታላቅ አባት ናቸው። እኒህ አባት ወጣቱ ሃይማኖቱን አጽንቶ እንዲይዝና ከሌሎች የእምነት ክፍሎች ተጽእኖ የጸዳ እንዲሆን ከፍተኛ ትግል ያደርጉ ነበር። አገልግሎታቸው ፍሬ አፍርቶ በተለይ በ 1980 ዓ .ም . ጀምሮ ወጣቶች በብዛት በአጸደ ቤተክርስቲያን መሰብሰብ ጀመሩ። የእርሳቸውን አርአያነት ተከትለው በተለይ ወጣቶች ማታ በሠርክ ጸሎት ላይ ጠዋት በኪዳን ቤተክርስቲያኒቱን አጣበው «መሓረነ አብ»
ሲሉ መቋሚያ ሲያቀብሉ፤ ቤተ ክርስቲያን ሲያጸዱ፤ መመልከት ምንኛ የሚያሰደስት ነበር።
ይህ
በመካነ ሥላሴ የተጀመረው ወደ አጸደ ቤተክርስቲያን የመመለስ እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ በሌሎችም አድባራት ቀጠለ። በመሆኑም በደብረ
ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን፤ በቅዱስ ሚካኤል
፤ በተክለ
ሃይማኖት፤ በአቦከር ደብረ
ጸሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስና በስተኋላ በተተከለው በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባቶች እና እናቶች ይሰበሰቡ ጀመር።
በሐረር
ከተማ የነበረው እንቅስቃሴ እጅግ ከሚያስቆጣቸውና ከሚያናዳድቻቸው መካከል በዚያ አካባቢ የሚገኙ ፕሮቴስታንቶች ነበሩ። ምክንያቱም ወደ
እነርሱ አዳራሽ ማንም ሰው አይሄድም ነበር። በየቦታው የማታ ጉባኤ ሳይጀመር ሐረር በየቤተከርስቲያኑ ታላቅ ጉባኤ ነበር። ፕሮቴስታንቱን ስላናደደው «'አስተማሪዎቻቸው የእኛ አባላት
ናቸው» እያሉ ማስወራት
ጀመሩ። ባሳለፍኳቸው የአገልግሎትና
የስደት ዓመታት እንዳስተዋልኳቸው ፕሮቴስታንቶች ታዋቂ የሆኑና ህዝቡን የሚያስተምሩ
አንደበተ ርቱእ የሆኑ የቤተክርስቲያንን መምህራን በህዝባችን ለማስጠላት የሚጠቀሙበት በዚህ ዓይነት መንገድ ነው። በሐረር ግን ማኅበረ ቅዱሳን መጥቶ የሃሳባቸውን እሰኪያሟላላቸው ድረስ አልተሳካላቸውም ነበር።
የሐረር ሰንበት
ትምህርት ቤቶች ተሐድሶ መባል !
ይቀጥላል……………………..