ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ቀድሞ
መልአከ አሚን አባ ዘካርያስ ይባሉ ነበር፡፡ በብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት አንብሮተ እድ ግንቦት 3ዐ ቀን
1979 ዓ.ም፣ እንደ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ታሪከ የቀሳፊውንና ተልእኮውን በሚገባ ባለመፈጸሙ መብረር የተሳነውን
መልአክ ስም ወስደው «አቡነ ቀውስጦስ» ተብለው ተሾሙ፡፡ አባ ቀውስጦስ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ የሚስማማቸው ሸዋ
ነክ ነገር ብቻ ነው፡፡ ከቅዱሳን ሸዋ፣ ከቤተ ክርስቲያን አለቃ የሸዋ ተወላጅ፣ ዲያቆን ሲሾሙ የሸዋ ተወላጅ በአጭሩ
ዘረኝነት የተጠናወታቸው ከጳጳስነት ይልቅ ያገር ሽማግሌነት የሚስማማቸው አባት ናቸው፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር
ያወዳጃቸውም በዋናነት ሸዋነት መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡
የአቡነ
ቀውስጦስ ዘረኝነት ጐልቶ የታየው ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ለማሳነጽ፣ ታቦት ለመቅረጽ፣ ገድል ለማጻፍ
ባደረጉት ጥረት ነው፡፡ በጣልያን ወረራ በ1928 ዓ.ም የተገደሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና የጐሬው ሊቀ ጳጳስ አቡነ
ሚካኤል ለአንድ አይነት አላማ ሞተው ሳለ አቡነ ጴጥሮስ ብቻ እንዲታሰቡ መሯሯጣቸው ለምን ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱን
በቀላሉ ማግኘት ይችላል፤ የአገር ልጅነት፡፡ አቡነ ሚካኤል ግን የሸዋ ተወላጅ ስላልሆኑ አስተዋሽ አጥተው የረባ
መታሰቢያ ሳይኖራቸው እስካሁን አለ፡፡
የከፋ ዘረኝነት እና ፖለቲካ (በ1997 ዓ.ም ይግባኝ ለክርስቶስ ብለው ያሳተሙትን ይመለከቷል) የተጠናወታቸው አቡነ ቀውስጦስ ከግብር ልጆጃቸው የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በመሆን የሸዋ
ተወላጅ ለሆኑት ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ብለው አሠርተው አስመርቀዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን
ምረቃ እለት የወጣው “ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ” የተሠኘው መጽሔት ገፅ 53 ላይ ይህን የአቡነ ቀውስጦስን
የዘረኝነት ሥራ የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጅ ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በቅኔው እንዲህ አጋልጦታል፡-
ሚካኤል ለይንበር በጥቃ ገቦሁ
ለበአለ ቤት ጴጥሮስ ወያስምኮ ውስተ ቤቱ
እስመ ለሚካኤል በምድር ዘመደ ሥጋ አልቦቱ
በውስተ ጐሬ ውእቱ ንብረቱ
እንዘ አኃዊሁ ወአዝማዲሁ
መላዕክተ ሰማይ ኩሎሙ ወመንግሥተ ሰማይ ሐይመቱ
ቅኔውን ያቀረበው መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል በዚሁ መጽሔት የተረጐመው እንደሚከተለው
ነው፡፡ “አቡነ ጴጥሮስ በአዲስ አበባ አቡነ ሚካኤል በጎሬ በሃይማኖታቸውና በሀገር ወዳድነታቸው ምክንያት በኢጣሊያ
ፋሽስት በግፍ የተረሸኑት በአንድ ወቅትና በአንደ አላማ ሆኖ ሳለ ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራላቸው
ለአቡነ ሚካኤል ግን ሳይሠራላቸው በመቅረቱ ቤት አልባ ጎሬ ውስጥ ስለሚኖሩና በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም
በመጠራታቸው ቤተሰባቸው የሰማይ መላእክት፣ ቤታቸውም መንግሥተ ሰማይ በመሆኑ በምድር የሥጋ ዘመድ ስለሌላቸው አቡነ
ጴጥሮስ በተሠራላቸው ቤተክርስቲያን እንዲያስጠጓቸው የሚጠቁም ኅብረ ቅኔ ሲሆን፣ ተጋድሎ ያልለያያቸው ሁለቱን አባቶች
መለያየት እንደማይገባና ተለያይተው መኖራቸውን ወንጌል እንደማይፈቅድ የሚያብራራ የሚጠቁም ነው” ይላል ቅኔ
አቅራቢው ሲተረጉመው፡፡
ፍፁም
የዘረኝነት ተግባር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እና በቀኖናዋ ላይ እያካሔዱ ያሉትን ዘረኛውን አቡነ ቀውስጦስን ባህሪ
የገለጸው ይህ መጽሔት በሀላፊነት ሲታተምስ ይህ ለምን አልታየም? አቋም የለሽ ሆኖና የራሱን እይታ ሳያክል በማህበረ
ቅዱሳን ክስ ላይ ፊርማውን አኑሮ የማኅበረ ቅዱሳን ታዛዥና ተገዢ የሆነውና የቤተክርስቲያንን ልጆች እንዲወገዙ
ያደረገው “የሊቃውንት ጉባኤ” የእስካሁን እንዳይበቃን በአገር ፍቅር ሰማዕት ለሆኑት ለአቡነ ጴጥሮስ፣ ለክርስቶስ
ወንጌል እንደሞቱ ተቆጥሮ “ሰማዕት” መባላቸው ሳያንስ ገድል እየጻፈላቸው መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ መቼም ቢሆን አቡነ ጴጥሮስ ከአሁኖቹ ጳጳሳት የተሻሉ ለአገራቸው እንኳን ሰማዕት እስከመሆን የደረሱ ታላቅ አባት በመሆናቸው በዚህ ተግባራቸው ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን ከቅዱሳን አንዱ ተብለው ገድል ሊጻፍላቸው፣ ታቦት ሊቀረጽላቸው፣ መልክ ሊደረስላቸው፣ የበዓል ቀን ሊመደብላቸው፣ ማኅሌት ሊቆምላቸው ከዚያ … ሊሆን ግን አይገባም፡፡ ለነገሩ ብዙው ሰው በቅርብ ስለሚያውቃቸው በአገር ወዳድነት ካልሆነ በቀር እርሳቸውን የወንጌል አርበኛ አድርጎ መንፈሳዊ ሰማዕት የሚያሰኛቸው ነገር የለም፡፡ ለሀገራችን የሆኑትን ነገር እያደነቅን ለሀገር ፍቅርና ለወንጌል አውነት መሰዋት ልዩነት ያለው ነገር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ አንድ የሚያውቋቸው የእድሜ ባለጸጋ ለአቡነ ጴጥሮስ በስማቸው ቤተክርስቲያን እየታነጸ መሆኑን ሰምተው “አብረናቸው ጠጅ የጠጣነው ሰዎች እስክናልፍክ እንኳ ቢጠብቁ ምናለበት …” ብለው የተናገሩት የሚረሳ አይደለም፡፡
ዳንኤል ክብረት የልብ ወዳጆቹ ከነበሩት ከባያብል ሙላቱና ከብርሃን አድማስ ጋር መቃብሬ ላይ አትቁም አልቆምም ወደሚል የከረረ ጸብ ያደረሳቸው ለአቡነ ጴጥሮስ ጽላት ይቀረጽ በሚለው ጉዳይ በተነሳ አለመግባባት ተጀምሮ ኃላ ላይ ዳንኤልን ከልብ ወዳጆቹ ለመነጠል አጋጣሚ ሲፈልግ በነበረው ዋና ጸሐፊው ሙሉጌታ ክፍተቱን ከማስፋት በበቂ ሁኔታ በመንቀሳቀሱ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡
ከመንፈሳዊነት ይልቅ ዘረኝነት የሚያጠቃቸው እኚህ አባት የማቅ የበላይ ጠባቂ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡