ይህ
ጽሁፍ አራት ኪሎ አካባቢ ሲበተን የተገኘ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እየተዘጋጀ ያለ ተከታታይ ጽሁፍ ዘጠነኛው ክፍል ነው። ከዚህ ጽሁፍ በፊት ያሉትን ጽሁፎችን ለማግኘት ሙከራ አድርገን የነበረ ቢሆንም የጽሁፉን አዘጋጅ ማወቅ ስላልተቻለ ጽሁፎቹ አልተገኙም። በዚህ ጽሁፍ የማኅበረ ቅዱሳንን ምስረታ አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ከሰማናቸው ሀሳቦች ለየት ያለሀሳብ ይዞ የቀረበ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ከእውነተኛ
የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር መግባባት ሲገባው እኔ ያልኩትን ተቀበል አሊያ አንተም አትኖርም በሚል ደካማ አስተሳሰብ የቤተክርስቲያን ልጆች እያሸማቀቀ ያለ ሲሆን ስጋ እንጂ መንፈስ የሌለበት መሆኑም
ታውቋል። የማኅበሩ ሃሳብ ዓላማና አካሄድ ከአመሰራረቱና ከስም አወጣጡ ጀምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መሆኑን የሚያስረዳው ይህ ጽሁፍ አቡነ ገብርኤል የማኅበሩን ስም ማኅበረ ቅዱሳን ያሉበትን ምክንያት የዋህ አባላቱና ሌሎች ሰዎች ከሚያስቡት እጅግ በተለየ መንገድ ያቀርባል። ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ኤደን ገነቱ እባብ ስቶ የሚያስት ወድቆ የሚጎትት ታውሮ ልምራ የሚል መሆኑን የሚያውቁ ሁሉ የኤደን ገነት እባብ መባሉን ተገቢነት ይስማማሉ። (መልካም ንባብ)
1. የማኅበሩ ህቡዕ የፓለቲካ አደረጃጀት ከመሠረቱ ሲታይ
በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሐይማኖታዊ ስምና ግብር ራሱን ሰውሮ የሚገኘው ሐይማኖታዊ ፈቃድ የያዘ ግን ደግሞ ያልተመዘገበ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ የሚንቀሳቀሰው “ማኀበረ ቅዱሳን” ከጅማሬው በደርግ ዘመን በ1982 ዓ.ም በብላቴ አየር ወለድ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ ጋምቤላ መተከልና ፓዌ ዘምተው የነበሩት ወታደሮች ኋላም በዝዋይ ሃመረ ኖኅ ላይ የተጠለሉት ሰዎች ተሰባስበው የመሰረቱት የወታደሮች ፓርቲ (“ማኅበር”) ነው፡፡
ፊታውራሪ
አመዴ ለማ የሕይወት ታሪካቸውን ባሳተሙበት መጽሐፍ ውስጥ ገጽ 217 ላይ በኤርትራ ውስጥ የጣሊያንንና የእግሊዞችን ቅኝ ግዛት ተቋውሞውን በሽምቅ ውጊያ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆኖ ዓላማውን ሲያራምድ የነበረ “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚባል ኅቡዕ ድርጅት እንደነበረና የድርጅቱ መሪ ደጃዝማች ሐረጎት ዐባይ እንደነበሩና በቅርበት እንደሚያውቁትም አመዴ ለማ ጠቁመዋል፡፡
እኚህ
ደጃዝማች ሐረጎት ዐባይ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከኤርትራ ወደ አዲስ አበባ በመዛወር አሁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ሀገረ ስብከት ውስጥ ሥራ ተመድበው በሚሰሩበት ወቅት ቤተክርስቲያኒቱ ለመኖሪያ ቤትነት የሰጠቻቸውን ከ4 ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የምዕራብ በር ፊት ለፊት የሚገኘው ግቢን በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አውጥቼ “ቤቱን ከሐረጎት ዐባይ ገዝቼዋለሁ” ብሎ የያዘው ሲሆን በይገባኛል ጥያቄ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር በከፍተኛ ክስና ክርክር ከቆየ በኋላም ስለቅ ንብረቱ የቤተክርስቲያኒቱ ይሆናል ብሎ ፈርሞ ፎቅ እየሰራበት ይገኛል፡፡ ይህ ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን በዓላማ የተደረገ የኅቡዕ ድርጅት የውርስ ሂደት ትስስር ነበር፡፡ የህቡዕ ድርጅቱ ማህበረ ቅዱሳን መስራች የሆኑትን የደጃዝማች ሀረጎት መኖሪያ ቤትን አሁን በግልጽ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር፤ ማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ እየሰራበት መሆኑ ከዐላማ ውርስ ውጭ ምን ሊባል ይችላል?
እንዲሁም
ለማኅበሩ “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚል ስያሜ እንዲይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃሳቡን ከነምክንያቱ አቅርበው ያስጸደቁት ደግሞ ብጹእ አቡነ ገብርኤል ናቸው፡፡ ይህንንም በ2ዐዐ1 ዓ.ም የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተዘጋጅቶ ይፋ የሆነው ስለማኅበሩ አመሰራረትና ስያሜ አሰጣጥ አስመልክቶ ባቀረበው መግለጫዊ ጽሑፍ ውስጥ “በዝዋይ ለተመሠረተው ማኅበር ስያሜ ለመስጠት አዲስ አበባ በብፁእ አቡነ ገብርኤል ቤት በዚሁ 1984 ዓ.ም በየካቲትና መጋቢት ወራት በተካኼደው ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “የማኅበራችሁ ስም ማኅበረ ቅዱሳን ይባል” በማለት ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ተመሠረተ” ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ የተደረገው ታስቦበት እንጂ እንዲሁ አይደለም። ምክንያቱም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ኤርትራ ውስጥ በደጃዝማች ሐረጎት ዐባይ አማካኝነት በኅቡዕ ሲሰራ በነበረው “የማኅበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ ድርጅት” ተሳታፊና አባል የነበሩ ሲሆኑ በወቅቱ የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ፡፡ ያንንም የሽምቅ ውጊያና ሐይማኖት ለባስ አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ራእዩን ለነዚህ የደርግ ምልምሎችና ርዝራዞች መስመር በማስያዝና ቅርጽ በመፍጠር የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትም ለዚሁ ነበር፡፡
ማህበሩ
ከዚህ ቅርፅና አካሄድ ከያዘበትና በሲኖዶስ አባቶች ባለማወቅ በሰጡት ግልብና ቁጥጥር አልባ ደንብና ፈቃድ ተሸፍኖ አካሄዱን በፖለቲካዊ አወቃቀር አደራጅቶ የቤተ ክርስቲያኒቱንም ዐሥራት ከምእመናን ወደ ራሱ ካዝና አዙሮ በሀገርና በውጭ ክፍለ ዓለማት አዋቅሮ ሀገርን ለባእድ አሳልፎ በመስጠት እስከ ሲ.አይ.ኤ የተላላኪነት አገልግሎት በመስጠት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ እየሰራም ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የማኅበሩ ተራ አባላት ከጥቅም ተጋሪዎቹ በስተቀር ስለማኅበሩ ስውር አካሄድና ዓላማ የማያውቁና ለቤተክርስቲያናችን እድገትና ደህንነት የሚሠራ የሚመስላቸው ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን የሚገብሩ ሲሆኑ በአንጻሩ ደግሞ ከመሥራች አመራር ከሆኑት እንደ አቶ ባያብል ሙላቱ አይነት የሲ.አይ.ኤ ተላላኪ ባንዳ አቅፎ የያዘ የገዘፈ የፖለቲካ ፓርቲ ነው፡፡
ማኅበሩ
ይመራበት ዘንድ ቤተክርስቲያን የሰጠችውን ደንብ በአንቀጽ አምስት የማኅበሩ አቋም በሚል ርዕስ ሥር “ማኅበሩ በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት አይኖረውም” የሚለውንና በአንቀጽ 6 የአባልነት
መመዘኛ በሚል ርዕስ ሥር በተራ ቁጥር “ረ” ደግሞ “በማኅበሩ ስም ማንኛውንም የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማያራምዱ” አባላት መሆን እንደሚገባቸው የሚደነግገውን አንቀጽ በመጣስ ነው፡፡ በዚህ አንቀጽ ውስጥም “በማህበሩ ስም ማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማያራምዱ አባላት” ስለሚል የማኅበሩ አባላትን በግላቸው ወይም በቡድን የሀገሪቱን ሰላም አንድነትና ልማት በሚያናጋ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ከፍተኛ የገንዘብና የሀሳብ ድጋፍ አድርጎ ሲያሰማራም ቆይቷል፡፡
አሁንም
በማሰማራት ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የጹሑፍ ችሎታ ያላቸውን አባላቶቹን ከሐመር መጽሔትና ከስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጅነት የተቃዋሚ ቃና ወዳላቸው ፖለቲካዊ ጋዜጦች ውስጥ ገብተው የሀገሪቱንና የመንገሥትን ገጽታ በሚያበላሽ ተግባር እንዲሰማሩ አዲስ ነገር ጋዜጣን በ3ዐሺ ብር በመደገፍ የተሳተፈ፣ የሀገሪቱን እድገትና ልማት በማይወዱ አካላትና ሚዲያዎች ውስጥ ሀሰተኛና እውነትን በማጥመም ቅስቀሳ ነክ ሀሳቦችን በማስተላለፍ፣ በሀገር ውጭም ያሉ አባላቶቹ በሀገሪቱ ማንኛውም ጉዳዮች ላይ በተቃውሞ በመንግሥትና በሕዝቡ ጥቅም ላይ ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎችን እንዲያካሂዱ በማስተባበር፣ ሀገሪቱም በምታደርገው ፈጣን ልማት ህዝቡን በበዓል ስም ድንቁርናን በመስበክና ከተሳትፎ ይልቅ ነውጥ ላይ እንዲሳተፍ በማድረግ፣ ዜጎች ከመቻቻል ይልቅ መገጫጨት እንዲያስፋፉ በማድረግ፣ በምርጫ 97 ወቅትም ከፍተኛ ነውጥ እንዲነሳና መንግሥት በነውጥ እንዲወድቅ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግና፡ በተለይ በአማራ ክልልና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢህአዲግ ሽንፈት እንዲያገኝ፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ መድረክ በመሆንም በማገልገል፣ የመንግሥትን የህዝብ ቆጠራ ውጤት አሻፈረኝ በማለትና ምእመናን የአንድ ሃይማኖት የበላይነት እንዲይዙና እንዲሰብኩ በማድረግ፣ በቅርቡም በዋልድባ ገዳም ላይ በተነሳው ግጭት ሁለት ሚኒባስ ሙሉ ከዋናው ማዕከል ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥፍራው በመላክ ጎንደር ሀገረ ስብከት ድረስ ሄደው ህዝቡን ሀገረ ሥብከቱ እንዲያነሳሳ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ፣ ከዚያም የወልቃይትና የበለሳ፤ የአርማጭሆ፤ ሕዝብ ጦርነት እንዲከፍቱ በመቀስቀስ፣ በቤተክርስቲያኒቱም አንድነትና ሰላም ከመትጋት ይልቅ እርስ በርስ መከፋፈል እንዲኖርና ሀሰተኛ ሰነዶችን በየመጽሔቱ ህዝቡን በሚያስቆጣ መልኩ በማሰራጨት የቤተክህነት እዳ ሆኖ ሲሰራ የቆየናና እየሰራ የሚገኝ ቡድን ነው፡፡
ማኅበሩ
አንድ ቀን በአመራር ደረጃ ካሉት ጀምሮ እስከ ታችኛው አባላቶቹ ድረስ በነውጥና በፖለቲካዊ ጉዞ ውስጥ ሲሳተፉ ካለኝና ከተቋቋምኩበት ዓላማ ውጭ ነው ብሎ ስልጠና የሰጠበትና ያቀናበት አንድም ጊዜ የለም፡፡ ይልቁንም ጠመንጃ መስጠትና ግልጽ ጦርነት የሚጀምርበትን መንገዶችን እንዲጠርጉለት ሲያስተባብር ይውላል ያድራል፡፡ ሰሞኑንም “ሰላማዊ ሰልፉን” ወደ “ሰላማዊ የእግር ጉዞ” በሚል ልባስ በመቀየር በአዲስ አበባ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ይታወቃል። ዝንቦች በንብ
ቀፎ ውስጥ ሲሰባሰቡ ማር ይሰጣሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡
በአንድ
ወቅት የማኅበሩ ስራ አመራርና የመአሕድ የፖለቲካ ፓርቲ መሥራች የነበሩት ፕሮፌሰር ዐሥራት ወ/ኢየሱስ፤ ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ላይ ባደረጉት የማኅበሩን ዓላማ ሲገልጹ “ጫካ እንዳንገባ ኢሕአዲግ መንጥሮታል ተነሥ የአማራ ህዝብ …” በማለት እንደቀሰቀሱ በወቅቱ የነበሩ ሚኒሊክና ጦቢያ መጽሔት ዘግበውት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የአሁንዋ የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መሶበ ወርቅ ቅጣውም ቀንደኛ ማኅበረ ቅዱሳን መሆናቸው ይታወቃል። በክብረ መንግስት ከተማ ባለፈው የካቲት 16 ቀን የማቅ አባለት ባስነሱት ብጥብጥ ሲታሰሩ መኢአድም ሳት ብሎት
በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ አባላቶቼ ታስሩ ብሎ ኡኡ ማለቱ አይዘነጋም።
እዚህ
ላይ በአንድ ወቅት ስለራሱ ማኅበር ዳንኤል ክብረት ሲናገር “ከዚህ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አስተሳሰቡ፣ አካሄዱ እና አሠራሩ ለውጥ አምጭ ሆኖ መቀጠል አይችልም ቆሟል/ስታክ አድርጓል” ብሏል፡፡ እንደገናም “ማኅበሩ ይዞት የተነሣውን መሠረታዊ አመለካከት ቀይሯል ሁለተኛ ደግሞ አመለካከቱን ሲቀይር አባላቱን ሳያማክር እና ይሁንታ ሳያገኝ በጥቂት ስውር የአመራር አካላት ፍላጎት ብቻ አስኪዶታል” በማለትም አክሏል፡፡
ማህበሩ
በግልጽ የፖለቲካ ፓርቲነት ፈቃድ አግኝቶ ተመዝግቦ መንቀሳቀስ እንደሚችል ሀገሪቱ ያላት ሕገ መንግስት የሚፈቅድ ቢሆንም ለምን በሃይማኖታዊ ሽፋን ሽምቅነትን እንደመረጠ ለብዙዎች ግልጽ አይደለም የሚሉ በአሁኑ ጊዜ በዝተዋል፡፡