Friday, June 29, 2012

የፍቅር ለይኩን አላማ ማኅበረ ቅዱሳንን መታደግ ወይስ እውነትን መዋጋት?

                               ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት
ፍቅር ለይኩንን በግሌ በጣም አደንቀዋለሁ። በማንኛውም ርዕስ ጽሁፍ ሲጽፍ ነገሮችን በሚያይበት ዕይታ በእጅጉ እመሰጣለሁ። አገር ውስጥ ያሉ መጽሔቶች ለምን አምድ እንደማይሰጡት ሁሌም ግራ ይገባኛል። አገሩን እና ቤተክርስቲያንን የሚወድበትን ፍቅር ያንንም የሚገልጽበትን መንገድም አደንቃለሁ። ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን ጋር ሲደርስ ሚዛናዊነቱን ሚዛን ያሳጠበት ምክንያት እየደነቀኝ ግን መልስ ልሰጠው ተገድጃለሁ። በመጀመሪያ አባ ሰላማ ላይ በጻፈው ጽኁፍ ካለኝ ከበሬታ አንጻር በዝምታ ላልፈው ብፈልግም ለደጀ ብርሃን የሰጠው የመልስ መልስ ግን ያለመናገር መብቴን ስለገፈፈው በጽኁፉ ላይ ያሉትን ሚዛን ያጣባቸውን ነገሮች ለመተቸት ተገድጃለሁ።
ላለፉት ስድስት አመታት አቡነ ጳውሎስ በዘረኝበት በሌብነት በተሃድሶነት ተጠርጥረው ሲሰደቡ አቡነ ገሪማ አቡነ ፋኑኤል አቡነ ሳዊሮስ ያለስማቸው ስም እየተሰጣቸው ሲሰደቡ ዲያቆን አሰግድ በሀሰት በከፍተኛ ደረጃ ስሙ ሲጠፋ ወንጌል ሰበክ ተብሎ ፓስተር ሲባል መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ለምን እውነትን አገለገልክ ተብሎ በከፍተኛ ደረጃ የስነ ምግባር ጉድለት በተቀነባበረ ካሴት ካደ ሲባል አባ ሰረቀብርሃን በህጋዊ መንገድ ሂዱ ባሉ በጠላትነት ተፈርጀው ሲብጠለጠሉ እነ አእመረ፣ ሀይለጊዮርጊስ፣ ኑብረዕድ ኤልያስ፣ ዲያቆን ትዝታው፣ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል፣ በሪሁን፣ ተረፈ፣ ያሬድ፣ ታሪኩ……በተለያዩ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች በከፍተኛ ደረጃ ሲብጠለጠሉ እንደ ተራራ የተቆለለው ትዕግስትህ ምነው አውደ ምህረትና አባ ሰላማ በጻፉት ጽሁፍ ጊዜ እንደ ገለባ ክምር ተበታተነ?

በመጀመሪያ አባ ሰላማ ላይ ላወጣኸው ጽኁፍ ለተሠጡህ ጠንካራ አስታየቶች በሰጠኸው ምላሽ እንጀምር “…የመጻፋችን ዓላማ እርስ በርስ ለመተናነጽና ለመማማር እስከሆነ ድረስ መልካም ነው እላለሁ፡፡” በማለት ጀምረሀል ፍቅር እስኪ እንደገና አባ ሰላማ ላይ ያወጣኸውን ጽሁፍ ተመልከተው በርግጥ እሱ ጽሁፍ የመመካከርና የመማማር ለዛ ነበረው? ስድብ ያልከውን ነገር በስድብ ከማወራረድ በቀር ምን አይነት ምክር ጠቅሰሃል? የጻፍከው መቅሰፍት አዘል ማስፈራሪያ መሆኑንስ ትስተዋለህ?  ጽሁፍህ ላይ “…እየተገለጸ ያለው ገመና ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው።…” በማለትህ ግን ሳናመሰግንህ አናልፍህም። አንተም ቢሆን ያልሆኑትን ተባሉ አላልክምና እና ነው። በበኩላችን በጻፍነው ነገር አናፍርም ሀሰትን ላለመጸፍ እንጠነቀቃለን።
ለገመናቸው ሲሉ ግን የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማጥቃትና ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚተጉትን አባቶችንና የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን ብሎጎቻቸው ሊገነቡላቸው የሚፈልጉትን የሐሰት ገጽታ ከመናድና ትክክለኛ ማንነታቸውን ከመግለጽ ግን ወደ ኃላ እንልም። እነዚህ ሰዎች ስለ ራሳቸው ኃጢአት እየተጸጸቱ ንስሀ ከመግባት ባለፈ ንጹሀንን እያሳደዱ ሊገነቡ የሚፈልጉትን ከንቱ ዝና የመግለጽና መንፈሳዊ ሰው መስለው ሌሎችን ለመቃወም የሞራል ብቃቱና መንፈሳዊነቱ እንደሌላቸው እውነትን ለሚፈልጉ አንባቢዎቻችን የማሳየት ግዴታ አለብን።
በአስተያየትህ ላይ “እንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ እኔ የማንንም ግለሰብም ሆነ ብሎግ ስም አልጠቀስኩም፡፡” ብለህ መጻፍህ በጉዳዩ ላይ ሚዛናዊነት እንደጎደልህ ያሳያል። ሌላ አስተያየት ሰጪ በምላሽህ አዝኖ “ሁሉንም ብሎጎች ሳይሆን የጠቀስከው አባ ሰላማን እና አውደ ምህረትን ብቻ ነው። ምሳሌዎችህን በጥንቃቄ ተመልከታቸው። ቀውስ ጦስ ማን ላይ የወጣ ጽሁፍ ነው? የጉድ ሙዳይ ማን ላይ የወጣ ጽሁፍ ነው? ሁሉንም ለመውቀስ ብትፈልግ ሳይሳደቡ ውለው ከማያድሩት ከደጀ ሰላምና ከአንድ አድርገን የሚጠቀስ ምሳሌ አጣህ? ቢያንስ እንድንረዳህ ስህተትህን እመን።” ያለውን ሀሳብ አኔም እጋራለሁ። በኛ በኩል አቡነ አብርሃምን የጉድ ሙዳይ ማለታችንን አናፍርበትም ስለ እሳቸው ጉድ አይደለም ሙሉ ታሪኩን ገና መቅድሙንም አልጻፍነው። ሲጀመር መቼ የተዋህዶ ልጅ ሆኑና ነው። ለእሳቸው እኮ የቤተክርስቲያን ልጆች መወገዝ በጣም ተራ ነገር ነው። የሚመኙት ጠቅላላ ቤተክርስቲያኒቱን ማውገዝ ነው። ሲቀጥል እንዲህ እና እንዲያ ተብለው የሚጠቀሱ እንኳን ከጳጳስ ከአንድ ምዕመንም የማይጠበቁ በርካታ ጉዶች አሉባቸው። በቤተ ክህነት አካባቢ እሳቸው ሲገቡ ጳጳሳቱ  ቀስ እያሉ “ሙዳየ መና ዘጉድ ሙዳየ መና” እያሉ የሚዘምሩላቸው ማንነታቸውን በሚገቡ ስለተገነዘቡ ይመስለኛል።
 ስለአባ ሳሙኤል ስለጻፍነው ጽኁፍ ስትጽፍም እንዲህ ብለሀል “…አባ ሳሙኤልና ሚጡ ተለዋውጠውታል የተባለው ለጆሮ የሚቀፍ ንግግርን በዝርዝር መዘገብ በምን መልኩ መንፈሳዊ ለዛ ያለው ለቤተ ክርስቲያን ህልውና የቆመ ጹሑፍ ሊሆን እንደሚችል አንባቢ ይፍረደው…” ፍቅር እንዴት አድርገህ እንዳነበብከው አናውቅም እንጂ እኛ ግን ሚጡ የተናገረችውን ጸያፍ ንግግር … አድርገን ነው ያለፍነው ለምን አልገለጻችሁትም ከሆነ እና ምን እንዳለች ማወቅ ከፈለክ ግን ሁሌም በጽሁፍ ስር በምትገልጸው ኢሜልህ እንልክልሀን። ነገሩን ከ10 በላይ ምስክሮች እንዳዩት ስለምናውቅና የማኅበረ ቅዱሳን መሳሪያ የሆኑበት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናችን ነው ያለን ሰው ከእነርሱ በቀር ማንም የሚያውቀው በሌለ ፍጹም ስህተት በሆነ ልዩ የውግዘት ሀሳብ ለማውገዝ የደፈሩ ሰው መንፈሳዊነቱ ቢጎል ሰብዓዊነቱ እንኳ ያጡበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ ደግሞ ጥፊው ለሳቸውም ለአይዞህ ባያቸው ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንም የእግዚአብሔር ፍርድ መሆኑን እናምናለን፡፡
አስተውለኸው ከሆነ አባ ሰላማ ላይ ከቀረቡት ጽሁፍ ሁሉ በሬሽዎ ሲሰላ ያንተን ጽኁፍ ያህል ብዙ ተቃማዊ ያስተናገደ ጸሀፊ የለም ለምን ይመስልሀል? ምክንያቱም በከፍተኛ ደረጃ ሚዛናዊነት ስላጣህ ነው።
የጳጳሳትን ገመና የምንከድነው እኛ አይደለንም። ወይም እያስፈራራ ያልኩዋችሁን ፈጽሙ አሊያ…የሚለው ማኅበረ ቅዱሳንን አይደለም። እነርሱን ገመና የሚከድነው እውነተኛ ንስሀና ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ክብር መኖር ነው። እስከመውለድ ድረስ የገለጡትን ገመና እንዴት አርገን ነው የምንሸፍነው? ልጁን ለካደ ጳጳስ ጌታውን እንደማይክድ ምን ዋስትና አለን? እያደረጉት ያለውንስ ይሄንን አይደለምን?
ፍቅር አንተ ተንጠራርተህ መንካት የፈለከው የማኅበረ ቅዱሳን ተቃዋሚ ብሎጎችን ብቻ ነው። አይንህን ጨፍነህ እንኳን ብታይ በጭላንጭል ውስጥ ከቶውን ልታጣቸው የማትችላቸውንና አንተም ብትሆን  ውሸትነታቸውን ልትመሰክርላቸው የምትችላቸውን በርካታ የስም ማጥፋት ዘገባዎችን የሚያወጡ የማቅ ብሎጎችን በዝምታ አልፈህ የእነርሱን ተቃማዊሞች ግን እወቁልኝ በሚል መንፈስ ስማቸውን ተራ በተራ እየዘረዘርክ ማሻቀልህ አሳዝኖናል። ጽኁፍህ ሰው ምንም ሚዛናዊ ቢሆን ሁሌም በቀላሉ የሚነካ ስስ ብልት እንዳለው  ያሳየ ጽኁፍ ነው። 

 
የዶ/ር ፈቃደን ተረት መጥቀስህ ፈገግ ቢያሰኘንም ምን ብለህ ልትሰድበን እንደፈለክ ስለገባን ግን ተሳስተሃል እንልሀለን። የማቅ ብሎጎችም ሆነ ማኅበሩ ደፍረው ሊቃወሙዋቸው ያልቻሉዋቸውንና የእኛ ብቻ ሚስጢሮች ብለው የሚመጻደቁበት ብርቱ ሚስጢራቸውን አስነብበናል። አሁንም ቢሆን ጊዜና ሁኔታ የምንጠብቅለት በርካታ የማኅበሩ ሚስጢሮች በእጃችን አሉ፡፡ አብዛኛዎቹን ሚስጢሮች የምናገኛቸው ደግሞ ከዛው ከማኅበሩ  ቢሮ መሆኑን ስንገልጽልህ ደስታ ይሰማናል። ስለዚህ የገባንን ገለጽን እንጂ የማናውቀውን አላወራንም።
አንተም ብትሆን መቸም ቢሆን በቀላሉ ሊገባህ የማይችል የከፋ አካሄድ ማኅበሩ እንዳለው እናውቃለን። ምናልባት ሲደርስብህ ይገባህ ይሆናል። ማኅበረ ቅዱሳንን “የፈረደበት” ስትል ሀዘንህን ገልጸህለታል። አዛኝ መንፈስ እንዳለህ ማወቁ መልካም ነው። ግን ሀዘንህን በትክክለኛ ቦታ የምትጠቀምበት ቢሆን ኖሮ ጥፋቱ የማኅበሩ አባል ብቻ አለመሆን ሆኖ በማህበረ ቅዱሳን በትር ከቤተክርስቲያን ለተባረረው ወገን ታዝን ነበር።
ጥፋቱ ማኅበረ ቅዱሳንን አለመደገፍ ሆኖ ከስራ የተፈናቀለውን የቤተክርስቲያን ልጅ ታዝንለት ነበር። ሀዘንህ አላማ ያለው ቢሆን ኖሮ ጥፋታቸው ወንጌል መስበክ ሆኖ ከፍተኛ ማሳደድና ወከባ እየተፈጠረባቸው ላሉት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ታዝን ነበር። ለአሳዳጁ ለአስጨናቂውና ለነብሰ ገዳዩ ማኅበር ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ ባለ ሁኔታ ግን ማዘንህ ሕይወትህን ሙሉ ልትታገልለት የፈቀድከውን ፍትህን ያዛባብሀል። ቢያንስ ለነጻነት ለእውነትና ለፍቅር አላማ አድርገህ የምትጽፍላቸውን ማንዴላን ያስረሳሀል።  
ይህ ጸሀፊ በአንተ ቅር የተሰኘው የማኅበረ ቅዱሳን ተቃዋሚ የሆኑ ብሎጎችን ስለወቀስክ አይደለም። ነገር ግን እድሉ እያለህ፣ ምንጭ ሳታጣ፣ የምትለው ሳያንስህ፣ አላማቸውም እየገባህ ሆን ብለህ የማኅበረ ቅዱሳንን ብሎጎች ለመውቀስ አለመፈለግህ ነው።
ይህን እንደተመራማሪነትህና እንደታሪክ አጥኚነትህ ምን ትለው ይሆን? በዚህ ጸሀፊ እምነት ከመጀመሪያው ይልቅ የሁለተኛው ጽሁፍህ ስህተት ይከፋል። ምክንያቱም የመጀመሪያው ስሜትህን ሲሆን የጻፍከው ሁለተኛው ደግሞ ራስን በጭፍኑ መከላከል ነው። እውነት የደጀ ብርሃን ጽሁፍ አንተ በተቸኸው መንገድ የወረደ ተብሎ የሚተች ነው? አንባቢ ይፈርዳል። ደጀ ብርሃን አንተን በገለጸበት መንገድ ሙሉ በሙሉ ባልስማማም  መልስ መስጠቱ ግን ተገቢ ነው እላለሁ። አንዲያውም እንዲያ ባለ ፍጥነትና መልስ መስጠታቸው በራሱ ያስመሰግናቸዋል።
ከማህበረ ቅዱሳን የተሻለ ሥራ መስራት ለምን አቃታችሁ? ስትል ለጻፍከው ብዙ የምልህ ነበረኝ ግን እንዲህ ያለ ጥያቄ እንድትጠይቅ ያደረገህ ማቅን በሚገባ አለማወቅህ መሆኑን ስለማውቅ አጠር አድርጌ እነግርሃለሁ።
በመጀመሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ማንም ሰው ከሱ ሌላ ስራ እንዲሰራ አይፈልግም ገና ስራ ለመስራት የሚነሳ ሰው ሲያዩ ያደረባቸው መንፈስ ስራህን በኛ በኩል አድረገው አለበለዚያ አቁመው ይልሃል። እንቢ እኔ ባመንኩበትና ቤተክርስቲያንን በሚጠቅም መንገድ እሰራለሁ ስትላቸው ወዲያው ስም አውጥተው ያሳድዱሀል። የባንክ ሰራተኞችን ማኀበር ያን የመሰለ በገዳማት ላይና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ሥራ እየሰራ ሳለ ሽባ ያደረጉት አካሄዱ የማኅበሩ ቅዱሳንን ስራ በዜሮ የሚያባዛው እንደሆነ ስለገባቸው ነው።
ህዝብን ወደ ቤተክርስታን በመመለስ በኩል እነ መጋቢ ሀዲስ በጋሻውና ሌሎች ሰባኪዎች ማኅበረ ቅዱሳን በሃያ አመት ከሰራው ሥራ በተሻለ በሁለት አመት ውስጥ እንደሰሩ አንተም ምስክር ልትሆን ትችላለህ ግን የወላደላቸው ነገር ተሀድሶ ተብሎ መሳደድ ነው። በማን ካልክ ደግሞ አንተ ስራ ሰራ ብለህ ልታወራለት በመደድከው ማኅበር ነው። ስራ መስራት የሚገለጸው ገንዘብ በመሰብሰብ ሳይሆን ሰዎችን ወደ ቤተክርስቲያን በማምጣት ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ለእግዚአብሔር የሚገደው የሚድነው ነፍስ ብዛት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በጠንካራ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን አብዛኛዎቹን የሰራተኛ ጉባኤ አቅሙ ስላልቻለ አፍርሷል። ከሁሉም በላይ ግን የሚያስቆጨው በራጉኤል ቤተክርስቲያን እሁድ አሁድ ጠዋት የነበረው ጉባኤ ነው። ጉባኤ ሲደምቅ ሰው ወደ እግዚአብሔር ሲጠጋ ስጋት የሚይዛቸው ማኅበረ ቅዱሳኖች ጉባኤውን እኛ ካልያዝነው ብለው ከተረከቡት በኋላ አንድ አመት እንኳ ማሰቀጠል አቅቶዋቸው ፈርሷል።
ቤተክርስቲያኒቱ በአስር አመት ውስት ስምነት ሚሊየን ህዝብ አጥታለች ይህ ለምን ሆነ ብሎ ማስተካከያ ከመውሰድ ይልቅ ማኅበሩ አሁንም 20 ሚሊየን ተሀድሶ አለ እያለ እያስወራ እነርሱን ለማባረር ቋምጦል። ይህን ስራ ካልከው እንጃ? ለኛ ግን ጥፋት ነው።
ባለፉት አመታት እነ መጋቢ ሀዲስ በጋሻው በስፋት በሚያገለግሉበት ጊዜ ከተማው ሁሉ ከመዝሙር ውጭ ሌላ ነገር የማይሰማበት ሆኖ ነበር። ሁሉን ቧጠው ሁሉን ግጠው አገልግሎት ካስቆሙዋቸው በኋላ ያለውን ነገር አዲስ አበባ ካለህ የምታየው ነው። ስራ መስራት አይደለም የቸገረው እጅ ሲላወስ ካልቆረጥኩ እያለ የሚያስቸግር ክፉ መንፈስ ማቅ መኖሩ እንጂ።
በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ላይ የወረደው የወንጌል ድርቅ የተከሰተው አንተ ሥራ ሠራ በምትለው በማኅበረ ቅዱሳን ሥራ መሆኑን አትክደውም። በየሀገረ ስብከቱ በርካታ የቤተክርስቲያን ልጆች እየተገፉ ያሉት አንተ ሠራተኛ በምትለው ማቅ እጅ መሆኑንን አትስተውም።
በዋልድባ ጉዳይ ሊያገኘው ከፈለገው ፖለቲካዊ ትርፍ በመለስ አሜሪካን አገር በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦ የውሀ ሽታ ያደረገው ይኸው ክፉ አይንካብኝ እያልከው ያለው ማኅበር ነው።
ማቅ ሥራ ሰራሁ ይላል፡፡ ግን የሚሰራው የራሱን ስራ ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን ግን አልሰራላትም፡፡ ተቸገረች ብሎ በህጋዊ መንገድ አልቅሶላት ከሚሰበስበው ገንዘብ 10% እንኳ አይሰጥም፡፡  በስምዋ ለምኖ የሰርቪስ ቻርጅ ያህል እንኳ አይሰጣትም፡፡ እውነተኞች ከሆኑ ለምን ሰጪውን ከገዳሙ ጋር አያገናኙም? በራሳቸው ተነሳሽነት ተደራጅተው ቤተክርሰቲያንን ቅንነት እያገለገሉ ያሉ ማኅበራትን እንኳ ብሩን ለኛ ስጡን አሊያ ከመስመር ውጡ እያሉ እንዴት እንደሚያዋክቡ ህያው ምስክር ነን፡፡
ለምን ልርዳ የሚለውን ባለሀብት ቀጥታ ከገዳሙ ጋር አያገናኝም? ኦዲት ላይ ለምን ይፈራል? ለምን የራሱን ደረሰኝ ይጠቀማል? ለምን በህጋዊው የቤተክህነት ደረሰኝ ሞዴል 30 አይጠቀምም? ህግ እንዳያውቀው ኦዲት እንዳያውቀው ገቢው እንዳይታወቅ  አይደለምን? በአለም ህግ እንደሚታወቀው ገቢያቸውን ሕግ እንዳያውቅባቸው የሚፈልጉት አደንዛዥ እጽ ነጋዴዎች፣ ህገ ወጥ  መሳሪያ ነጋዴዎችና እነርሱን የሚመስሉ ሕገወጥ ግለሰቦችና ድርጅቶች ብቻ ናቸው፡፡
ማህበሩ ወገኑ ወዴት ቢሆን ነው በቤተክርሰቲን ስም በገዳማትዋ ስም የሚሰበስበውን ገንዘብ አትወቁብኝ የሚለው? የቤተክርስቲያን ባለሙያዎችን ለምን የማኅበሩ አስተዳደር ላይ አያስቀምጥም? ማኅበሩ የሚፈልገው ሙያቸውን ተጠቅሞ መጣል ብቻ ነው? አካሄዱ ያልተመቻቸው አደራረጉ ያልጣማቸው ጥቂት ልባም የማኅበሩ አባላት ይሔ ነገር ይስተካከል ሲሉ የሚደርስባቸው ወከባ ማሳደድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ምንጩ ምንድን ነው? ይህንን እያደረገ ያለ ማኅበር ደግሞ ሥራ ሰራ የሚባለው እንዴት ነው?
“የፈረደበት” ማኅበረ ቅዱሳን ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንደሌለው እናውቃለን፡፡ አንተስ መልስ ይኖርህ ይሆን ፍቅር? አይመስለኝም፡፡
ፍቅርም ቢሆን በሌሎች ጽኁፎችህ የነበረህን ሚዛናዊነት ዚህ ጋር ስትደርስ እንዴት እንዳጣኸው ግራ ቢገባንም አሁንም ቢሆን ሁሉንም ብሎጎች የራስህን ጽኁፎች ጨምሮ በትክከለኛ የጥናት ሰው ሰብዕና መተቸት እንደምትጀምር ተስፋ አለን።
የሕይወት አላማህ ከስሜታዊነት ርቀህ እውነትን ማገልገል እነደሆነ ታስታውቃለህ፡፡ ግን የሕይወት አላማም ቢሆን በስሜታዊነት የሚሸፈንበት ጊዜ እንዳለ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያለህ አመለካከት ያረጋግጥልናል፡፡ የሁልጊዜም አላማህ ለእውነት መቆም ቢሆን ኖሮ በሚዛናዊነት ሁሉንም ብሎጎች ትተች ነበር። እንዲያውም ወኔህና ምክንያታዊነትህ ራስህን የመውቀስ ጀግንነትን ካደለህ ራስህንም ጭምር ተችተህ ጻፍ። ያኔ ቢያንስ ላንተ ያለን ከበሬታ በእጥፍ ይጨምራል፡፡
በመጨረሻም ለፍቅርም ይሁን ለሌሎች አንባቢዎቻችን መግለጽ የምንፈልገው ይህ ነገር ወደን ፈቅደን የገባንበት አይደለም። ማኅበረ ቅዱሳን በተለያየ ብሎጎቹ እና እነ ዕንቁን ጨምሮ በህጋዊነት ስም ያቋቋማቸው ሕጋዊ ህቡዕ መጽሄቶቹ ካለፉት ስድስት አመታት በላይ እየፈጠረ ያለው ውዥንብር ብዙ ሰዎችን እያሳተ ስለመጣ ህዝቡ ሁሉንም አቅጣጫ አይቶ ወደ እውነቱ እንዲያደላ ለማድረግ ነው። ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፈው በቤተክርሰቲያን ላይ እየፈጠራቸው ያለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምን እንደሚመስሉ ለህዝቡ ማሳየት ስለሚኖርብን ነው።
ነገር ግን የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች እነ ደጀ ሰላም አንድ አድርገን እና ሌሎችም የወንድሞችንና የአባቶችን ስም ከማኅበረ ቅዱሳን ጥቅም አንጻር እያዩ ማጥፋትን ካቆሙ እኛ ደግሞ እውነትም ቢሆን ምንም ላለማለት ቃል እንገባለን። ማቅ በብሎጎቹ የጠላውን ሰው ስም በሀሰት እያጠፋ ህዝብን ማሳት እስካላቆመ ድረስ እኛም ስለ ማኅበረ ቅዱሳንና ስለሌሎች የጉድ ሙዳዮች የምናውቀውንና እውነት የሆነውን ነገር ከመግለጽ ወደ ኃላ አንልም።
በመጨረሻም በእብራይስጥም በአማርኛም ሁሌም የምትመኝልን ሰላም ላንተም ይድረስህ እላለሁ፡፡