ምንጭ፤ዓውደ ምሕረት
ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው የፖለቲካ ድርጅት ዘርፈ ብዙ የአሰራር መንገዶች አሉት። አሰራሩ የማፊያነት ባሕርይ ስላለው የሚሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ያደርጋል። አላማውን የሚያስፈጽምበት እስከመሰለው ድረስ አዋጭ ብሎ የሚያምንበትን መንገድ ይጠቀማል። መንፈሳዊ ባሕርይ ስለሌለው ልምድን ከመንፈስ ቅዱስ፤ በጸሎት ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን አሠርር እየገመገመ ይጠቅመኛል የሚለውን መንገዶች ሁሉ ይጠቀማል።
ለዛሬ ስለሦስቱ ሴሎቹ እና ስለሴል መሪዎቹ እናቀርባለን።
አሉላ ጥላሁን
አሉላ ዋነኛ ስራው ግልጹንም ስውሩንም ሚዲያ መቆጣጠርና መምራት ነው። ቱሪስት የነበረውን ቡድን ይመራል። ኤፍሬም እሸቴ የከፈታትን ደጀ ሰላምን ይመራል ይቆጣጠራል። ሪፖርተሮችዋን በደንብ ያንቀሳቅሳል። እነ ሱራፌልን፤ ጳውሎስ፤ መረዋን ሌሎችንም ይመራል። ለጥንቃቄ እንዲረዳ በእነርሱ ስር የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን አይደለችም ብለው እንዲያምኑ የሚያደርግ የተለያየ ዘዴዎችን ይፈጥራል። ያስጠናል። አንዳንዴም ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይበዛ በልዝቡ ወረፍ ያደርጋል። ከዛም ዛሬስ እኛም አልቀረልንም ብለው እንዲያስወሩ ያደርጋል። በዚህም ተሳክቶለታል። አንዳንዶቹ ወሬ አቀባዮች ምለው ተገዝተው ደጀ ሰላም የማቅ አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው። ሱራፌል ወደ አሜሪካ በሄደ ጊዜ እሱም ከማኅበሩ ዋና ጸሀፊ ከሙሉጌታ ጋር በመቃቃሩ ደጀ ሰላም ተቀዛቅዛ እንደነበር ይታወሳል።
ከምርጫ 97 በኋላ ቅንጅት ለምን ተቀባይነት አገኘ ብላ ማኅበሯ ጥናት ስታደርግ ተቀባይነት ያገኘበት መንገድ ጠንካራ መሪዎች ስላሉት ወይም የተሻለ የፖለቲካ መስመር አሊያም ልብ የሚያደርስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስላለው ሳይሆን ጋዜጦችን በሙሉ ደጋፊ አድርጎ ማቆም በመቻሉ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመደረሱ ማኅበሯም ሀሳብዋን ወደ ህዝቡ ለማድረስ የግል ሚዲያዎችን ከማቋቋም ጀምሮ አባላትዋን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ዐምደኛ በማድረግ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመራል፤ ይቆጣጠራል።
አዲስ ነገር በማኅበሩ ፈንድ አድራጊነት በማኅበሩ ሰዎች በነመስፍንና ዓቢይ ሲቋቋም እሱ ኮፒ ኢዲተር ዳንኤል ክብረት አምደኛ፤ ኤፍሬም ሪፖርተር ሆነው በአብዛኛው የማኅበሩ አባላት የሚገኙበትና እንቅስቃሴውን በሙላት የሚቆጣጠሩበት ጋዜጣ እንደነበረች አይዘነጋም። ግን እነ መስፍን እንኳን የሆነ የተጠረጠረ ነገር ሁሉ የሚያስደነግጣቸውና እንደ ልጆች ኩኩሉ ጨዋታ ገና ቁጥር ሳይጀመር መደበቂያ የሚፈልጉ በመሆናቸው ጋዜጣዋ መክና ቀርታለች። አሉላ ከእነርሱ የተሻለ ሰብዕናም ድፍረትም ያለው በመሆኑ ሁሉ ሲፈረጥጡ እሱ ግን እዚሁ ቀርቷል።
ጋዜጣዋ በ2001 የቤተክህነት ግርግር የአባ ሳሙኤልን የሌለ ሰብዕና በመገንባትና የቅዱስነታቸው የአቡነ ጳውሎስን ገጽታ ደግሞ በማኮሰስ የተሰጣትን ተልዕኮ በሚገባ ተወጥታለች። ምስጢር ቢሆን ከጉዳቱ ጥቅሙ የሚያመዝነውን የሲኖዶስ ስብሰባን ከአዲስ ነገር ጋዜጣ ጀምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲዘገብ በማድረክ የአባቶችን ገመናና መጠነኛ አለመግባባት በማስፋት እንዲዘገብ በማድረግ የአንበሳ ድርሻውን ይይዛል።
አሁንም ቢሆን ባለው ቀረቤታ ምክንያት ለሚዲያው የተለያዩ ወሬዎችን በማቀበል እየሰራ ያለው እሱ ነው። አሁን እንኳ ሰፊ ገበያ ባላት ፍትህ ጋዜጣ የሚወጡትን ቤተክርስቲያን ጉዳዮች ወሬ ይኸው ብሎ የሚሰጠው እሱ ነው። አምና ጀምረውት በነበረው የሚዲያ ሰርክል የመፍጠር እንቅስቃሴ ዋና አስተባባሪው አሉላ ነበር። የሚድያ ሰርክሉ አላማ ቤተክርስቲያንን በሚመለከት የሃይማኖት ጉዳይ ነውና መረጃ ከኛ ብቻ ውሰዱ እኛን ብቻ እመኑ ከሌላ ከማንም ዜና አትቀበሉ በማለት የማሳመን ስራ ይሰራ የነበረው አሉላ ነው። ሚዲያ ውስጥ ስላለና ከዚህም የተነሳ ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ ጨርሶ ያላነጋገራቸው ጋዜጠኞች አሉ። በዚህ አካሄድ ግን አብዛኛዎቹን ጋዜጠኞችና ጋዜጦች በማሳመን ተሳክቶለት ነበር። እንደባህሪያቸው በገንዘብም በማግባባትም የተያዙ ጋዜጠኞች አሉ። አሁን አሁን አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች እያፈነገጡ ይገኛሉ።
ባለፈው አመት ዳንኤል የጻፈው ጽሁፍ ደጀ ሰላም ላይ እንዲወጣ በማድረጉ ከሙሉጌታ ጋር ያለው ግንኙነት የተቀዛቀዘ ነው። የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ ሙሉጌታም ከአሉላ ጋር ስር የሰደደ ጸብ ውስጥ መግባቱ የሚያስከትለውን ችግር ስለሚያውቅ በሱ ቦታ ላይ የሚተካ አስተማማኝ ሰው እስኪያዘጋጅ ቀን እየጠበቀለት ይገኛል።
ገብርሄር እንድትጀመር በወዳጆቹ በኩል ሀሳቡን አስነስቶ ደጀ ሰላምን ለመተካት ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም። አንድ አድርገንንም በግልገል ስሜታውያን አባላት ያስጀመረ ሲሆን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እያየለ በመሄዱ ቁጥጥሩ ሙሉ በሙሉ በአሉላ እጅ ወድቋል። ለጊዜውም ከአንዳንድ ወሬዎች በቀር ሙሉ በሙሉ የደጀ ሰላምን ዘገባ ኮፒ እንድታደርግ ታዛለች።
ማንያዘዋል አበበ፤
ማንያዘዋል ደግሞ የሚመራው የኮሌጅ ተማሪዎችንና ለማኅበሩ ያደሩ ጳጳሳትን ነው። የሥላሴ ኮሌጅ ምሩቃን ኅብረት ሊቀመንበር በመሆኑ ተማሪዎችን በቅርብ የማግኘት ዕድል ስላለውና ከአቡነ ሳሙኤል ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስላለው ሁለቱንም ለመምራት ዕድል ሰጥቶታል።
ማንያዘዋል መንፈሳዊነትንና መንፈሳዊ ባህሪያትን በአባቶቻችን የአርበኝበት መንገድ ለማሳካት የሚፈልግ ሰው ነው። በእጅጉ ኢትዮጵያዊ፤ በእጅጉ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ ያምናል። እነዚህን የሚቃወሙትን ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ሰዎች ከፊቱ ለማስወገድ እስከ መግደል ድረስ የሚደርስ ጭከና አለው። በደብረ ብርሃን ከተማ በሙሉ ወንጌል ቸርች ህዝቡን አስተባብሮ ያደረሰው ጭፍጨፋ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ነው። ድቁና እንኳ የሌለው ማንያዘዋል ሥላሴ ኮሌጅ የገባው በደብረ ብርሃን ከተማ በእሱ መሪነት በደረሰው ጭፍጨፋ በፖሊስ ስለሚፈለግ ከዓይን እንዲርቅ ለማድረግ ነበር።
በአሁኑ ሰዓት ለእርሱ ትልቁ ግቡ አቡነ ጳውሎስን ከስልጣን ማውረድ ነው። ለእሳቸው ያለው ጥላቻ ወደር የሌለው ነው። ሳይደክምም ሳይታክትምም ይኼ ነገር እንዲሳካ ጥረት ያደርጋል። ላመነበት ነገር ጽኑ በመሆኑ የማኅበሩ አመራሮች ከሱ ጋር ያላቸው አቀራረብ ጥንቃቄ የተሞላ ነው። እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው እንደሚባለው ቀረብ አደርገው ኃላፊነት እየሰጡ ብዙ ሚስጢሮች እንዳያውቅ ደግሞም እንዳይገባው አድርገው ገፋ እያደረጉ በጥንቃቄ የያዙት ሰው ነው።
የኮሌጅ ተማሪ እያለ ሁልጊዜ ፈተና ሲደርስ ይታመም ነበር ይባላል። የሚታመመው ግን እውነተኛ ህመም ሳይሆን አሞታል ተብሎ እንደልቡ እንዲወራጭና ፈተና ላይ አድርጎት የሚገባው ጋቢ ላይ የሚሰፋትን አጠሪራ በቀላሉ ለማንበብ እንዲረዳው ነው። እንዲህ እያደረገ አምስት አመት ማሳለፉን ተማሪ ሁሉ ያውቃል። እንዲያውም አንድ ተማሪ «ማኔና ህመሙ» የሚል ግጥም ጽፎ አጠሪራውን እንዴት እንደሚጠቀምበት በሚያስቅ መንገድ ገልጾ እንደነበር ይነገራል። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ስለሆነ ማንያዘዋል ስለዚህች ግጥም ምንም ሳያውቅ ይኖራል።
ጨካኝ፤ ክፉና በአላማው ጽኑ ነው እንጂ አስተዋይ ስላልሆነ የሚያወራውን አያውቅም። ከአንድ ወር በፊት እንኳ የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሰብስቦ “እኔ እኮ ለዚህ ግቢ የማልሆነው የለም፤ ደጀ ሰላም ላይ ስለዚህ ግቢ ተጽፎ በሁለት ሰዓት ውስጥ ያስጠፋሁ ሰው ነኝ” አለ አሉ። አይ ሞኞ እግረ መንገድህን ደጀ ሰላምን ማን እንደሚያዘጋጅ ጠቆምክ እኮ!! አሉላ ይኼን ሰምተሃል?
ዳንኤል ክብረት፤
ዳንኤል ክብረት በጳውሎስና ትዝታው አለመግባባት ምክንያት ለሁለት የተከፈለው የሰባኪያን ህብረት አንዱን ይመራል። ልጁ ተንኮለኛ መሰሪና ምን ማድረግ እንዳለበት አርቆ የሚያስብ ነው። ከፖለቲካ ጋር የሚያነካካ በሚመስለው ነገር በሙላት አይሳተፍም። አዲስ ነገር ጋዜጣ ይጀመር ሲባል በመሰረታዊ ሀሳቡ ቢስማማም ከአምደኝነት የዘለለ ሚና እንዲኖረው አልፈለገም። ጋዜጣው ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር ጠልቆ መግባት ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ያውቃልና። ነገሮችን ቀለል አድርጎ የመጻፍ ችሎታው ቢያስመሰግነውም ለራሱ በሰጣቸው የወግ ጸሀፊነትና የቤተክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪነትን ማዕረግ
ይወቀሳል። በቅርቡ አለማየሁ ገላጋይ የሚባል ሀያሲ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ወግና የወግ ጸሀፊዎችን በገመገመመበት ጽሁፉ ዳንኤል የወግ ጸሀፊነት ማዕረግ የማይገባው ወግ ምን እንደሆነ እንኳ ያልገባው ሁሌ ራሱን ትክክል ማድረግና ኢትዮጵያዊያንን መውቀስ ሙያው የሆነ ሰው ነው ብሎታል።