በመላው ዓለም የእውነትን ወንጌል በማዳረስ የሚታወቁት አባ ወ/ትንሣዔ እና በውብ ድምጿ «ታሪኬን ቀያሪ» እያለች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትነት በዜማ ስትመሰክር የቆየችው ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በሚኒሶታ ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ አገልግሎታቸውን አበረከቱ። ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት አባ ወ/ትንሣዔን ተሐድሶ እና መናፍቅ፤ ዘማሪት ዘርፌንም ከእነ ምርትነሽ ጋር አንድ ላይ ፕሮቴስታንታዊ ኃይሎች የሚላቸውን ሰዎች ለመጨፍለቅ ባዘጋጀው የስም ማጥፋት ሙቀጫው፤ሲወቅጣቸው መቆየቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ አባ ወ/ትንሣዔም ወንጌልን ሰብከዋል፤ ዘማሪት ዘርፌም «ታሪኬን ቀያሪ» እያለች ስትዘምር ውላለች። ይህንኑ ዜና ዘሐበሻ ጋዜጣ ዘግቦታል።
(ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ)
በሕዝብ ዘንድ በስብከታቸው እጅግ ተወዳጅ የሆኑት አባ ወልደትንሣኤ እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ታላቅ መንፈሳዊ ፕሮግራም (መርሃ ግብር) አዘጋጁ። ሴንት ፖል ሚኒሶታ የሚገኘው ቅዱስ ዑራዔል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ በላከው መግለጫው እንዳስታወቀው ዘማሪቷና ሰባኪው በሚኒሶታ ለ3 ተከታታይ ቀናት ትልቅ መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል።
አርብ ሰኔ 22 (ጁን 29) ከምሽቱ 6 ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት ፣ ቅዳሜ ሰኔ 23 (ጁን 30) ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ ምሽቱ 7 ሰዓት እንዲሁም እሁድ ሰኔ 24 (ጁላይ 1) ከጠዋቱ 7 ሰዓት እስከ ረፋዱ 11:30 በሚደረጉት መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች ላይ የሚኒሶታና አካባቢው የሆኑ በሙሉ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበው የቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ መዝሙሮቿን በማቅረብ ከም ዕመናን ጋር ትዘምራለች፤ እንዲሁም አባ ወልደትንሣኤ ስብከታቸውን ያቀርባሉ።
ዘማሪት ዘርፌ ወደ ሚኒሶታ በሕዝብ ጥያቄ መሠረት ለ2ኛ ጊዜ የምትመጣ ሲታወቅ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመጣ ምእመናኑ በደስታ ተቀብሏት ነበር። አባ ወልደትንሣኤም እንዲሁ በተለያዩ ዓለማት እየተዟዟሩ የሚያገለግሉ ሲሆኑ በሚኒሶታ በተደጋጋሚ በመምጣት የ እግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
ዘማሪት ዘርፌ በሕይወት ታሪኳ ዙሪያ የተሠራው ;ፓራሜራ ፊልም ብዙ ምእመናንን እምባ እንዳራጨ ይታወቃል።
የቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አድራሻ
ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክ በሴንት ፖል ሚኒሶታ
1144 Earl St, Saint Paul, MN 55106
ስልክ ቁጥራቸው የሚከተለው ነው 651.771.7129
*******************************************************
ማስገንዘቢያ፤
አቶ ፍቅር ለይኩን በአባ ሰላማ ድረ ገጽ ላይ ላወጣው ጽሁፍ ደጀብርሃን ብሎግ መልስ መስጠቷ ይታወሳል። በዚሁ መልስ ላይ አቶ ፍቅር ለይኩን እነ ደጀሰላም ብሎግ ያሻቸውን ሰለፈለጉት ሰው ማንነት ሲጽፉ አንድም ቀን የምክር ይሁን የማስተማር መልእክቱን ሳይሰጥ ቆይቶ አባ ሰላማንና ሌሎች ድረገጾች በመረጃ አስደግፈው ለሚያወጧቸው ጽሁፎች ትክክል አይደላችሁም ሲል በጽሁፉ ለማስጠንቀቅ መፈለጉን በመተቸት በሰጠነው መልሳችን ላይ አስረጂ እንዲሆነን የግርጌ ሊንክ ፊደል [ ለ ] ላይ መረጃ አስቀምጠን ነበር። ይሁን እንጂ የመረጃውን ሊንክ አንባቢ እንዳያገኘው ወዲያውኑ እንዲደመሰስ ተደርጓል። እኛም መረጃውን ጉግል ሰርቨር ከሚሰበስበው ኢንዴክስ ከተመዘገበውን ካቼ በመፈለግና በመቅዳት በራሳችን ሆስት ሰርቨር መረጃውን ለማስቀመጥ ችለናል።አንባቢዎችም መረጃውን በቀድሞው ሊንካችን ማግኘት ይችላሉ። በዚሁ አጋጣሚ ለአቶ ለይኩን በመረጃ ዘመን የተሰወረና የማይገለጥ የለም፤ ለማለት እንወዳለን። [ ለ ] በመጫን ያረጋግጡ!!