Saturday, April 28, 2012

ደጀ ሰላም ብሎግ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ሲል ህገ መንግሥቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁሉም ሃይማኖቶች ሀገር ናት ይላል! የደሴቲቱ ገዢስ ማኅበረ ቅዱሳን ይሆን?

 ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ካልን እስላሞቹና ሌሎቹ ወደየት ይድረሱ?
ደጀ ሰላም ብሎግ- ህገ መንግሥት፣ የጠ/ሚኒስትር መግለጫ፣ ገለመሌ አይሰራም የሚል ይመስላል፤ ይህንን የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት መሆኗን ከሁለት ዓመት በፊት ዘግቦ ነበር። ሌሎች ሃይማኖቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉና ሊኖሩ እንደሚገባ አምኖ ባለመቀበል ሀገሪቱ የአንዲት ሃይማኖት ደሴት ናት ማለት ምን ማለት ነው? ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ብቻ ናት እንደማይል ይታወቃል። እነዚህኞቹ ግን የክርስቲያን ብቻ ደሴት ነን እንዲል በመንፈሳዊ ታዛ ተጠልለው ይቀሰቅሱታል። ሰለፊ/ወሀቢ የሚባለው ደግሞ በሌላኛው ጽንፍ በኢትዮጵያ የሙስሊም መንግሥት መቆም ይገባዋል ይላል። ማሸበር የሚባለውስ ከዚህ ወዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን የቲ-ሸርት ጫወታ የማኅበረ ቅዱሳን ሌላኛው አፍ እንደሆነ በሚነገርለት ከደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ያገኘነው ስለሆነ ያንብቡትና ሚዛናዊ ግምትዎን ይውሰዱ።

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 17/2010):- በዓለ ከተራ ሰኞ በመላ ኢትዮጵያ ታቦታተ ሕጉ ከየመንበራቸው ወጥተው ይከበራል። በሀገራችን ዋና ከተማ በአዲስ አበባ በዐቢይነት በጃን-ሜዳ ሲከበር፣ በመላው ሀገሪቱ ደግሞ ታቦታተ-ሕጉ ወደ ጥምቀተ-ባሕር ወደሚፈጸምባቸው ውሃዎች ይወርዳሉ። ከተራን ማክበር አዲስ አይደለም። ነገር ግን አምና በተከበረው “የከተራ” በዓል ላይ የታየው የሕዝቡ አከባበር፣ ሥነ ሥርዓቱና በጎ አርአያው ተጠቃሽ በመሆኑ ልናስታውሰው ወደድን። ወጣቶች አንድ ዓይነት ካናቴራ (ቲ-ሸርቶች) አሰርተው በመልበስ ራሳቸው የሕዝባቸውና የበዓላቸው አስተናባሪ ሆነው የታዩበት ሁኔታ ሁሉንም ያስደመመ ነበር። ከመንግሥት እስከ ቤተ ክህነት ባለሥልጣናት፣ ከኦርቶዶክሳውያን እስከ ሌሎች እምነት ተከታዮች ድረስ መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱም የሚከተሉትን መዘገባችን ይታወሳል።






የአባቶቻችንን ርስት ምን ያህል እንፈልገዋለን?
(በብርሃናዊት)

በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ: የተለያዩ ኢትዮጵያውያን "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" እና "የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም" የሚሉ ጽሑፎች የታተሙበትን ቲሸርቶች ለብሰው በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ሳይ: ሁለት ዓይነት ስሜት ተሰማኝ::

1. የመጀመርያው ሕዝበ-ክርስቲያኑ ለእምነቱና የእምነት ሥርዓቱን በነጻነት ለማካሄዱ ምን ያህል ተቆርቋሪ እንደሆነና: ሙሉ ለሙሉ የእምነቱን ጉዳይ ችላ እንዳላለው: ምናልባትም እንደማይለውም ጭምር የተረዳሁበት ስለሆነ: አዎንታዊ ገጽታው ታይቶኛል::

2. ሁለተኛው ስሜቴ ግን: ሕዝበ-ክርቲያኑ ስሜቱ እንደሻከረና: በትንሹም በትልቁም ሊገነፍል የሚችል ስሜታዊነትን እንዲያዳብር በጽንፈኞች መደረጉን ሳይ የፈጠረኝ ስሜት ነው:: በእውነቱ መልካሙን መንፈሳዊነት የሚያደፈርስና የሚሠርቅ: የጨቅጫቃ መናፍቃንና የተንኳሽ ጽንፈኞች ፍላጻ የኢትዮጵያን ሕዝበ ክርስቲያን ወግቶ እስከዛሬ ሳይገድለው በመቅረቱ ጥበበ-እግዚአብሔርን እንዳደንቅ ተገድጃለሁ:: ሰአሊ ለነ ቅድስት የምንላት ድንግል ማርያም አሁንም በእኛ ተስፋ አልቆረጠችም::

ነገር ግን: አንድ ነገር ታሰበኝ:: ማለትም የአባቶቻችን ርስት ማለት ምን ማለት ነው? የት ነው ያለው? ለመኖር ከእኛ የሚፈልገው ምንድነው? 'ርስቴ ነው' ስንል ምን ማለታችን ነው? 'አልሰጥህም' ስንልስ ማንን ነው? ላለመስጠታችን መገለጫው ምንድነው? የምር አንሰጥም? እንፈልገዋለን?

እዚህ ላይ በዝርዝር እያንዳንዳችን ብንነጋገር ልዩነት ይኖረን ይሆናል::

ከመልስ ይልቅ ጥያቄዎችን ልጻፍና እስቲ በአእምሮዋችን እናመላልሰው?

የአባቶቼ ርስት የት ነው ያለው? ኢትዮጵያ ወንዞችና ተራሮች ላይ? ጋራው ሸንተረሩ ላይ? የቤተክርስቲያን አጥር ውስጥ? የቤተክርስቲያን ቅድስተ-ቅዱሳን ውስጥ? ታቦቱ ላይ? መስቀሉ ላይ? የቄሶቻችን ጥምጥም ላይ? መጻሕፍቶቻችን ውስጥ? የሃይማኖት ዶግማችንን የምንገልጽባቸው ጸሎት መጻሕፍቶች ላይ? የት ነው ያለው?

የአባቶቼ ርስት ለመኖር ምኔን ይፈልጋል? ጡንቻዬን? ብዛቴን? ፖለቲካዊ ኃይሌን? የኢኮኖሚ ዕድገቴን? የወዳጅ ሀገሮችን እርዳታ? ወኔዬን? ከሃይማኖቴ ውጪ ካሉት ሰዎች ጋር ተላትሜ ለክብሬ ስል ለመሞት ያለኝን ቁርጠኝነት? ወይስ ምኔን ይፈልጋል?

የአባቶቼ ርስት የእኔ ርስት የሚሆነው እንዴት ነው? የአባቶቼ ርስት ነው ስላልኩት? አባቶቼ ይኖሩ የነበሩበት ቦታ አዘውትሬ ስለምሄድ? አባቶቼ የተከሉትን አብያተክርስቲያናትና ገዳማት እስካሁን ካሉበት ሳይነቃነቁ አካላዊ ይዘታቸው እንዲጠበቁ በመርዳት? የአባቶቼ ርስት ስል አብርሃም አባት አለን እንደሚሉት አይሁድ ወይስ የአብርሀምን እምነትና ምግባር እየፈጸምኩ?

የአባቶቼን ርስት የማልሰጠውስ ለማነው? ለሌላ ሃይማኖት? ለሌላ ሀገር? የኔ ሃይማኖት ሰዎች የአባቶቼን ርስት ይዘውልኛል? ለእኔስ በትክክል አስረክበውኛል? አባቶቼ እንደአባቶቼ ናቸው? ወይስ እነሱም በየአጋጣሚው እንደአይሁድ አብርሃም አባት አለን እያሉ ነው? የአባቴን ርስት የሚወስዱብኝ ከቤተክርስቲያን ውጪ ያሉት ናቸውን? ጦርና ጎራዴ ይዘው በግዘፍ የሚመጡብኝ ናችውን? ወይስ በረቂቅ የሚመጡ ደግሞ ሌሎች ብዙ አሉ? ስንት ስንት አካፈልኩ ለእያንዳንዳቸው? ለረቂቃኑም ለግዙፋኑም? ለቤት ውስጦቹም: ከቤት ውጪ ላሉትም?

የአባቶቼንስ ርስት በርግጥ እፈልገዋለሁ? ለምን? ልኮራበት? ለቱሪዝም? ለማንነት መገለጫና ለታይታ? ለታሪክ ማሟሟቂያ? ለኢኮኖሚ ዕድገት? በዓመት አንዴ ከአለም የእረፍት ጊዜ ወስጄ ለማሳልፍበት ክብረ በዓል? ወይስ ከእግዚአብሔር ጋር ቀን በቀን: ደቂቃ በደቂቃ ሕይወት አድርጌ ልኖርበት? ለመንግሥቱ ልበቃበት? የርስቱ ርስትነት ለመኖርያ ነው ወይስ ለጊዜያዊ ተያዥነት? ሌላ ትርፍ ለማግኘት የብድር ማስያዣ ነው ወይስ የምበላው የምጠጣው በርሱም የምኖርበት እውነተና ሀብትና ሕይወት?

ሁላችንም አተኩረን ራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልገናል::

በርግጥም የአባቶቻችን ርስት ያስፈልገናል! ላንሰጠውም መሐላችንን ከየራሳችንና ከእግዚአብሔር ጋር ማጽናት አለብን::

ሰላም!
የዘንድሮ ጥምቀት እና “የክርስቲያን ደሴት አርማ” ጉዳይ

“ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ” የሚባልለት፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ አከባበሩ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የማይረሳን፣ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን እንኩዋን ሳይቀሩ በባህላዊ ትርጉሙ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጡት የጌታችን የጥምቀት በዓል ዘንድሮ በተለየ መልኩ ተከብሮ አልፎዋል። በተለይም “ያዙኝ ልቀቁኝ” የሚለው የአክራሪ እስልምና ለከት ያጣ እንቅስቃሴ ያሳሰባቸው ምእመናን፣ ከልጅ እስከ አዋቂ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ የተለየዩ “መፈክር መሰል” አርማዎችን በቲ-ሸርቶች ላይ አትመውና ለብሰው ታይተዋል። ለምሳሌ “ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት” እና “የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም”የሚሉትን ፎቶግራፎች ማውጣታችን ይታወሳል።

ይህንን እንዳወጣን ብዙም ሳይቆይ የተላኩልን መልእክቶች የሚከተሉት ናቸው።
Anonymous said...
You will be regreating that day when the day will open the door to those who tolerate you for so long....Allah is the Greates do not forget that Barak HUSSEIN Obama is on the way ...
January 20, 2009
Anonymous said...
አያ ! እናንተ አክራሪና ሞገደኞች ! መቸም ሃገር ማለትና ሃይማኖት ማለት 1 ቀንም በትኪክል ተርጉማችሁት አታውቁም ! ኦርቶዶክስ እንደሆነ ለመሞት በማጣጣር ላይ ባለበት የመጨረሻ እድሜዉ ላይ ይገኛል ለዚህም ነው ዚምብዋቤ የኔ ናት እንዳለው ሙጋቤ ኢትዮፕያ የኛ ብቻ ማለት የጀመራችሁትና ቲ-ሸርት ላይ መለጠፍና በየ ቸርቹ ትምህርት ቀርቶ ፉከራ የበዛው !! እዩኝ እዩኝ ከበዛ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ እኛ ግን ምንም እንክዋን አብላጫ ያለን ብንሆንም ሃገራችን የጋራችን ናት እንላለን ፣እምነት ለሌለው እንክዋን ሃገሩ ደሴቱ ናት ፣ለናንተም ደሴት ናት ፣ለኛም ደሴት ናት ! ትምክህት የትም አላደረሳችሁም ! የትም አላደረሰንም ፣ለሃገር የምታስቡ ከሆነ ቀልብ ግዙ፡፡ ድሮስ የቄስ መንጋ ሆዱን ይሙላ እንጂ ምን ቀልብ አለው ! አልላህ ዪምራችሁ ፣እኛንም ይምራን፡፡አሜን
ኢትዮፕያዊያን ሙስሊሞች ሆይ ዛሬ በቅናተኞችና በስግብግቦች ጦርነት ታውጆብሃል ፣አንተ ግን ሃይማኖትህ እንደሚያዘው ለሰላም በርተተህ ስራ !!
January 21, 2009
Anonymous said...
Ethiopia always stretches Her hand unto God!

Muslims, heretics, and others have tried their best to destroy Ethiopia's Christianity. They couldn't. It has been a long time since they strated trying. They have succesfully accomplished their missions everywhere else. But they couldn't do it in Ethiopia. This indicates that they can't do it at all. And that it is not God's will!!

Glory to the Father, the Son and the Holy Spirit, One God Amen!

A proud Ethiopian Christian!!

ብዙ ጊዜ በደጀ ሰላም የሙስሊሙ ነገሮችን ወደ ጽንፍ መውሰድ ሀገሪቱ ላይ የሚጋርጠው አደጋ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመናል። ይህ ክርስቲአኑን የመግፋትና ሳይፈልግ ራሱን ወደ መከላከል እንዲሄድ ማድረግ ደግ እንዳልሆነም ብዙ ክርስቲያኖች ተናግረዋል። አሁን የሚታየው የክርስቲያኖች “ዓይንን መግለጥ” ነገ የማይመልሱት ነገር እንዳያመጣባቸው ሙስሊም ጸሐፍያንና ሰባክያን የተገራ አንደበት ወደ መጠቀሙ እንዲያዘነብሉ እንመክራቸዋለን።