Friday, April 27, 2012

የአቡነ ገብርኤል ቡድን አጉራ ዘለል ሰባክያንን በድጋሚ በመጋበዝ ከሲኖዶስ ውጪ መንቀሳቀሱን ቀጥሎበታል


 ዘሪሁን ሙላቱ እና ፋንቱ ወልዴ እንደተጋበዙ ውስጥ ዐዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

"ማኅበረ ቅዱሳን" የሀዋሳ ንዑስ ማዕከል አስተባባሪነት በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል ስም ከሚያዘያ 19 እስከ 21/ 2004 . እና ከግንቦት 3 እስከ 5/2004 . የሚቆዩ ሁለት ጉባዔያት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡
የአቡነ ገብርኤል ሀገረ ስብከት ከየካቲት 25 እስከ የካቲት 27/2004 በሕገ ወጥነት ያካሄደው ጉባዔ እንዳይካሄድ የካቲት 22 ቀን 2004 . በቁጥር 221/54/2004 በወጣ ደብዳቤ የዕግድ ደብዳቤ ቢታዘዝም፣ ትዕዛዙን ባለመቀበል፣ የኢትዮጵያ ሲኖዶስን ህልውና የማይቀበለውን መምህር ዘበነ ለማን፣ ዳንኤል ክብረትንና ምሕረተአብ አሰፋን በመጋበዝ ፍጹም ለማኅበረ ቅዱሳን የወገነ ድራማን ተጫውቷል፡፡
አሁንም፣ መምህር ዘበነ ለማን በድጋሚ በመጥራት፣ ፋንቱ ወልዴን ከአሜሪካ፣ ጎረምሳውን ዘሪሁን ሙላቱንና ዘማሪ ይልማ ኃይሉን በመጋበዝ ፍጹም የሆነውን ማኅበረ ቅዱሳናዊ ግዛት ለማስፋፋት ደፋ ቀና በመባል ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡
 ይሁን እንጂ፣ አዘጋጆቹ የአገልጋዮቹን ማንነት የደበቁ ሲሆን፣ የጉባዔው መሪ ቃል (አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጌታ፣ አንዲት ጥምቀት)ያያዘው ትልልቅ ባነር በከተማይቱ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ከተሰቀለ በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር አንድ ሀገር፣ አንድ ሃይማኖት የሚል ኢሕገመንግሥታዊ መፈክር ያለባቸው ቲሸርቶችን የለበሱ አንዳንድ ወጣቶች አሉ ካሉ በኋላ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከአክራሪነት አቋሙ እንዲታቀብ ከሰጡት ማስጠንቀቂያ ጋር ተያይዞ የተደናገጡት አባላቱ ከየባነሩ፣ በየባጃጁ ከለጠፏቸው ፖስተሮችና ከየበራሪ ወረቀቶቹ "አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጌታ፣ አንዲት ጥምቀት" የሚለውን ጥቅስ በመፋቅና የሰቀላቸውን ባነሮች በማውረድ ሥራ መጠመዱን ታዛቢዎቻችን  ገልጸዋል፡፡
ቀድሞም ቢሆን ከወንጌሉ ቃል ጋር በተግባር የሌለው "ማኅበረ ቅዱሳን" የወንጌሉን ጥቅሶች ለመቅደድና ለመሰረዝ መሯሯጡ ብዙም አላሰደነቀም፡፡  ይሁን እንጂ ቃሉ ለክርስቲያኖች ትክክልና የማይለወጥ፣ ሲሆን ትርጉሙም፣ ሰዎች በፍቅርና በዕምነት አንድ ጌታን አምነውና ተጠምቀው አንድ ሃይማኖት ይኖራቸዋል የሚል ነው፡፡ ሆኖም በአስተሳሰቡ ኃይልና ጉልበትን፣ ጽንፈኝነትንና ፖለቲከኛነትን የያዘው "ማኅበረ ቅዱሳን" የተነቃበት መሆኑን ሲረዳ የጌታን ቃል በመካድ ጥቅሶቹን ለመፋቅ መገደዱ ታውቋል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ሕጋዊ ለመምሰልና ለማምታታት መጋቢት 28 ቀን 2004 . በቁጥር 733/5/53/2004 ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ፣ ዓባይነህ ካሤ (የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል) ዘማሪ ይልማ ኃይሉ፣ ዘማሪት መቅደስ እና ዘማሪ ፈቃዱ አማረ ከሚያዝያ 19 እስከ ሚያዘያ 21/2004 . ለሚካሄደው ጉባዔ እንዲሁም፣ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ፣ / ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ እና / ባህሩ ተፈራ እንዲመደቡለት ጠይቋል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ሽፋን ሊመጡ የታሰቡት ፋንቱ ወልዴ፣ ዘበነ ለማና ዘሪሁን ሙላቱ ናቸው ተብሏል፡፡
ዓላማው በተሰደዱት ምዕመናን ላይ የማንቋሸሽ ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት እስከሆነ ድረስ በቅድስና ቦታ ርኩሰት፣ በእውነት ቦታ ሐሰት በመዝራት የሚገኝ ኪሣራ እንጂ ጸሎቱም የማያርግ ፖለቲካዊ ነው ተብሎለታል።
 ምንጭ፣dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
(በደጀ ብርሃን የተጨመረ) 
ብጹእ አቡነ ገብርኤል በሃዋሳ ሰላም አሰፍናለሁ፤ እርቅና ፍቅርን አንግሳለሁ ሲሉ እንደነበር ይታወቃል። ምን ያህል ተሳክቶላቸው ይሆን? እንደሚሰማው ስለማኅበረ ቅዱሳን ደስታ ሲባል ብጹእነታቸው የገፏቸው  ምእመናንና ምእመናት ግን ተስፋ ባለመቁረጥ በየቤታቸው ምህላና ጸሎት እንዳላቋረጡ ነው። ይህን ማኅበር ከምእመናን ጉባዔ በላይ መደገፍ ትርፉ አሸባሪ መባል ስለሆነ የተሰደዱትን ምእመናን በይቅርታና በእርቅ ቢጠሯቸው ትልቅ ሥራ ነበር እንላለን። ያልበላቸውን የሚያክና እንቅልፍ ሲወስዳቸው የአባቶችን ቦታ ተረክቦ ዓላማውን የሚፈጽመው ማኅበር የዛሬ ዓመት ገደማ በግንቦት 1-15/2003  «ስምዓ ጽድቅ» በተባለ ልሳኑ ይህንን ቃለ መጠይቅ አቅርቦላቸው ነበር።( እዚህ ላይ ይጫኑ )