*የዘመኑ ምዕራፍ*
(by dejebirhan)
ከህይወት ጎዳና – ወጥቶ ከመንገዱ
ከወደላይ ትቶ - የምድሩን መውደዱ
ነፍስያውን ሽጦ - ውረድ መዋረዱ
ነፍሱን ከሞት ገደል - ሰቅሎ በፈቃዱ።
እረፍት የለሽ ኀፍረት - ተከትሎት ኋላ
ከጥልቁ ሰጠመ – ሞኝ ሆኖ ተላላ
ብራሪው በረረ - ጥልማሞት አጠላ
በሀጢአት ፓራሹት – በበደል ዣንጥላ።
አረፈ በማለፍ - አለፈ በማረፍ
ሲብከነከን ኖሮ - ሲበርና ሲከንፍ
ኑረቱ ጨለመ - አንዳችም ሳያተርፍ
እስከዚያው ነበረ - የዘመኑ ምዕራፍ።