Thursday, April 26, 2012

«የማኅበረ ቅዱሳን ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው!»



/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com
ጥብቅ ማሳሰቢያ:
በቅድሚያ ጽሑፉን ለምታነቡ ወንዶችንም ሴቶችም የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ሰላም ይሁን! እያልኩ በጽሑፉ ከተካተቱ እውነታዎችና ከጽሑፉ ከፊል ይዘት የተነሳ ጽሑፉ ከጸሐፊው መልእክት ዓላማና ከመልእክቱም ግብ ውጭ ሌላ አንድምታ እንዳይዝና እንዳይሰጠው ይህን ጥብቅ የሆነ ወንድማዊ ማስጠንቀቂያ ለመጻፍ ግድ ብለዋል:: ጸሐፊው በስራ ክቡርነት ያምናሉ: በየትኛውም የስራ መስክ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰብና ለሀገር የሚተርፉት ዜጎችንም የላቀ ክብር አላቸው:: ክብር ስለማያውቅ: ሰላሙን አጥቶ በሰላማዊያን ዜጎች የህይወት ጎዳና ላይ እየቆመ እሾክና አሜከላ ስለሚዘራ: እርግማን ቀለብ ስለሆነለት: የራሱ ያለሆነውን በማጭበርበርና በማደናገር የራሱ በማድረግ የሚታወቀው እልል ያለ ህጋዊ ሽፍታ ማህበርና አባላቶቹ ብቻ ላይ ያነጣጠረ እውነታ መሆኑን ተገንዝባችሁ ጽሑፍን በቅንነት ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ::
ምንም ዛሬ ደግሞ እንደገና ትኩስ ሆኖ ማወያያ ቢሆንም "ማህበረ ቅዱሳን" ከተመታ: ቅስሙ ከተሰበረና ተናዳፊ አንደበቱ ከተመነገለ ከራርመዋል:: ቢሆንም ግን የተመታ: ሞትን የማይቀርለት እባብ በቀላሉ አይገላገልምና ዛሬም ወዲያ ወዲህ በማለት መወራጨቱ አልቀረም:: ይህ በዚህ ሲባል በዚያ: ወድያ ሲባል ወዲህ: ከዚያ ሲታይ ከዚህ እየሆነና እያለ አልያዝ አልጨበጥ በማለት በመሸበት ቁጥር መልኩንና አድራሻውን እየለዋወጠ በሚፈበርካቸውና በሚለቃቸው የማደናገሪያ ወሬዎች በጥቂቶች ዘንድ ብዥታ እየፈጠረ በመምጣቱ ስለራሱ በራሱ ሰዎችና ዓላማውን በሚጋሩ አጨብጫቢዎች በኩል በእጅ አዙር ስለ ማህበሩና የማህበሩ አባላት መልካምነትና ብቃት ነጠላ ዜማ ለቆ ስሙልኝ! አልሰማችሁም ወይ! እያለ ይገኛል:: ከእነዚህ መካከልም የማህበሩ አባላት የትምህርት ደረጃና ብቃት የሚገልጽ መፈክር ማለት “የተማሩ ናቸው!” እየተባለ ማስተጋባት ይገኝበታል::

በመጀመሪያ ደረጃ የጽሐፉ መልእክት ለአንባቢያን ግልጽ ይሆን ዘንድ ማህበሩ አይደለም ከተራ ምእመን ቤተ-ክርስቲያን መንጋዬን ይጠብቁልኛል: በፈረሰ በኩል ይቆሙልኛል ብላ ከፍተኛ ወጪ አውጥታ ካስተማራቻቸውና ከምታስተምራቸው መምህራን ደቀመዛሙርት በአጠቃላይ ከካህናቶችዋ በመላ ሳይቀር የተሻልኩ ነኝ በማለት የሚመጻደቅባቸው ሦስት ዓበይት ነጥቦችን ላስቀምጥ
ይኸውም÷
አንደኛ: አስኳላ (በዘመናዊ ትምህርት) ከእኛ በላይ ላሳር የተማርን የተመራመርን አዋቂዎች ነን! ባዮች ናቸው::
ሁለተኛ: ማህበሩ (አባላቱ) በቅድስና ህይወት/በስነ ምግባር “እኛን ያላየ በአብርሃም ይደነቃል” ባዮችም ናቸው::
ሦስተኛ: “በማህበሩ ውስጥ ካህናት ዲያቆናት ሰባኪያን አሉ” በማለት በውስጠ ታዋቂነት መልእክቱ እኛም ካህናት ነን ባዮች ናቸው::
በአንድ ወቅት ትዕቢታቸው አድጎባቸው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅጽር ግቢ በጠሩት ጉባኤ ላይ አፋቸው ሞልተው “ጋዜጣችን ስምዓ ጽድቅ የተሻለ ስርጭትና ይዘትም ስላለው የዜና ቤተ-ክርስቲያን ቦታ ተክቶ ይሰራ ዘንድ ይፈቀድልን” ሲሉ መናገራቸውን አስታውሳለሁ:: ታድያ ይህ የሚያመላክተው ማህበሩ እንደ ሌሎች የጥልቁ መልእክተኞች የእኩይ ምግባር ደቂቆች(አልቃይዳና አልሽባብ)  በኢ/ት/ኦ/ተ/ቤ/ያን የቀበረው ፈንጅ እግዚአብሔር ለክፉ ቀን ቅባቱን በላያቸው ባፈሰሰባቸው ዓመጻንና ክፋትን ለባህሪያቸው በማስማማቸው የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች የሚይዘው የሚጨብጠው እስኪያጣ ድረስ ነገሩ ሁሉ ነፋስን የመከተል እስኪሆንበትም ድረስ አከሸፉበት እንጂ ለማን ራርቶ? ቢሆንለት ኖሮማ እንጀራው ነው!! የሆኖ ሆኖ ማህበሩ እንደ እስትራቴጂ በእጅ አዙር ስለ ራሱና ስለ አባላቱ እያስተጋባው የሚገኘው ጭንቀት የወለደው መፈክር ስንመለስ እንዲህ ይመስላል::
በቅድሚያ ግን እውቀትና መሃይምነት በአሜሪካን አገር ምን መልክ እንዳለውና ምን እንደሚመስልም ጥቂት ልበላችሁ:: በአሜሪካን ሀገር "መሃይም" በሁለት ነው የሚከፈለው አንደኛው ሌጣ ዜጋ (የማይጽፍና የማያነብ) እንደማለት ሲሆን ሁለተኛው የመሃይም ዓይነት ደግሞ ዓይን እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ የአብርሃም በግ ዓይነት ይሉታል:: እንግዲህ ይህ ማለት ምንም እንኳን ከመጣበት ሀገር "የተማረ" ተብሎ የሚፈረጅ ባለ ዲግሪ ቢሆንም በሀገሪትዋ ሲስተም የማይበላ የማይጠጣ: ተግባራዊ የሆነ ትምህርት የሌለው በወረቀት ተንጠልጥሎ የቀረው እንደማለት ነው:: በዚህ ጎራ ብዙሐኑ እኛን (ኢትዮጵያዊያን) ጨምሮ የሦስተኛው ዓለም ዜጎች ናቸው:: ልብ ይበሉ! ከ85 ከመቶ በላይ ያልተማረ ዜጋ በያዘች ምድር ላይ “የተማርኩ ነኝ!” ሲል ደረቱን እየደቃ መለከት እየነፋ የሚፏንን መውጫ መግቢያ ያሳጣን የማህበረ ቅዱሳን አባላት ክፍላቸው ከዚህ ምድብ መሆኑ ነው::
በአሁን ሰዓት "የተማሩ የተመራመሩ የማህበረ ቅዱሳን" አባላት በታላቅዋ ሀገረ አሜሪካ ምን ይመስላሉ ያልን እንደሆነ ሐቁ እንደሚከተለው ነው:: ምድሪትዋ ማንም ሰው ከየትም ይምጣ ከየት ምንም ይሁን ምን ለሰው ልጆች በሙሉ የስራ ዕድል የምትሰጥ የላብክን ዋጋ የምታገኝባት የለውጥና የዕድገት ሀገር ለመሆንዋ አያጠያይቅም:: ታድያ እንዲህ ሲባል ዘሎ የሚገባበት ምንም ዓይነት የስራ መስክ አለመኖሩንም ሳይዘነጋ ነው:: ለእያንዳንዱ የስራ መስክ በሀገሪትዋ ተዘጋጅቶ የሚሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ማለፍ ይጠበቅበታል:: እንግዲህ ማነቆው ያለው እዚህ ላይ ነው ሁለት እግር አለኝ ብለው ሁለት ዛፍ ሲንጠላጠሉ ከሁሉ ያልሆኑ የማህበሩ አባላት የሀገር ቤቱ “ዳኛ” “ኢንጅነር” “የሂሳብ ባለሞያ” “ዶክተር” እዚህ የምርመራ ኬላ ላይ መታወቂያቸው በድንገት ይቀየርና በለስ የቀናው ቢጢዎቻቸውን እየደለሉ በጸሐፊነት በቀዳሽነት እየተባለ ቤተ-ክርስቲያን ላይ ተሰግስጎ ለእግዚአብሔር ቤት የሚገባውን ገንዘብ እየመዘበረ ቤተ-ክርስቲያንን ሲያውክ የምእመናን ሰላም ሲነሳና ሲያበጣብጥ ይኖራል በተረፈ ደግሞ በታክሲ ስራ ላይ ተጠምዶ የሰው ሰው ሲያመላልስ: በታላላቅ መጋዘኖች ክርታስን ሲወስድና ሲመልስ: በየመናፈሻውና መዝናኛው ስፍራ የወደቀውን ሲልቅም: የአሳማ ሲጋ ሲቆርጥ: በየነዳጅ ማድያውና የመኪና ማቆሚያ ስፍራ የተበተነው ባለ ዲግሪ ማን ሆኖ?
ለምሳሌ ያክል በኔቫዳ ግዛት ላስቬግስ ከተማ ያየሁትንና የታዘብኩትን ላካፍላችሁ (ይህ ምስክርነት እውነተኛ ነው):: በከተማው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የማህበሩ አባላት የሚገኙባት ቤተ-ክርስቲያን ስርዓተ ቅዳሴውን የሚከናወነው በዕለተ ሰንበት መሆኑ ቀርቶ በዕለተ ሐሙስ ነው:: ምን ነው ቢሉ በዕለተ ሰንበት ሰው ሁሉ (የማህበሩ አባላት) ስራ ስለሚገቡና በአንጻሩ ደግሞ በዕለተ ሐሙስ በብዛት የታክሲ ሰራተኛ: የሆቴል ሰራተኛ: የነዳጅ ማድያ ሰራተኛ: የካዚኖ (ቁማር) ቤት ሰራተኛ: የመኪና ማቆሚያ/"ፓርኪንግ" ሰራተኛ ዕረፍት ስለሚሆን ነጩን ነጠላ ለብሶ ለነገርና ለክፋት የሚሰባሰበው በዕለተ ሐሙስ ነው:: ጸሐፊው የካንጋሮ እጅና የማህበረ ቅዱሳን ዲግሪ አንድ ነው ያሉበት ምክንያትም ይህ ነው:: ምን ነው ካንጋሮማ ቢያጥርም ነፋሱን ትቀስፍበት የለም ወይ ቢሉ ማህበሩና አባላቱ እንደሆነም አለን የሚሉት ዲግሪ 85 በመቶ ያልተማረውን ማህበረሰብ ለማጭበርበር ጠቅሞታል ተጠቅሞበታልም ይሆናል መልሴ::
ፊተኞችን ኋለኞች ኋለኞችን ፊተኞች ማድረግ የሚችልበት:
የሌለውን እንዳለው የሚጠራ:
የተናቀውን የሰው ዓይን እያየ ጆሮውም እየሰማ ነፍሱን በከበረ ሰረገላ ላይ የሚያኖር:
የጠራውን ባሪያ የማይረሳ የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ አምላክ ይባረክ!!
ዛሬም እጄ በጠላቶቼ ደንደስ ላይ ነች!
Posted from http://awdemihret.blogspot.com