ጌታቸው ዶኒ አስቸጋሪና ለቤተክርስቲያን የማይመች ሰው መሆኑን እናውቃለን። አጥማቂ ነኝ እያለ ቅብዓ ቅዱስና እምነት ነው፤ እያለ አፈር እንደሚሸጥም ይታወቃል። በሽሮ ሜዳ ሥላሴ፣ በቃሊቲ ማርያምና በአቃቂ መድኃኔ ዓለም በሺናሻ ቅጠል ብዙዎችን ሲያጮህ የነበረ ሰው ነው። ሌላም ሌላም ነገር.....! ሰውዬው ለቤተክርስቲያን ሸክምና እንቅፋት ከመሆን ባለፈ መፍትሄ መሆን የሚችል ሰው አይደለም። ደጀ ብርሃን ብሎግም ከሰውዬው ጠባይ የተነሳ በባቦ ጋያ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ምስቅልቅል ከመፍጠር አይመለስም ብሎ ስለሚገምት በዓላማና በአቋም ባንመሳሰልም የቤተክርስቲያን ችግር የእኛም ችግር ስለሆነ ከአንድ አድርገን ብሎግ ላይ የወጣውን መረጃ እንዳለ አቅርበነዋል።
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 19 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የባቦጋያ መድሀኒአለም
ቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ይገኛል ፤ ጌታቸው ዶኒ እንዳሰበው ነገሮች እየሄዱ አለመሆናቸውን ሲረዳ
የቤተክርስትያኒቱን ቄሰ ገበዝ ትላንት አመሻሽ ላይ የመቅደሱን ቁልፍ ካለመጡ ብሎ ጠይቋቸው ነበር ፤ እርሳቸውም ‹‹አንተ ማነህና
ነው የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ የምሰጥ ›› በማለት እምቢ ሲሉት ጉልበት ተጠቅሞ ቁልፉን እጁ ለማስገባት ሙከራ አድርጎ ነበር ፤ ቄሰ ገበዙ የመቅደሱን ቁልፍ አልሰጥም በማለት ለአካባቢው ክርስትያኖች
ስልክ ደውለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስትያኖቹ የተሰበሰቡ ሲሆኑ ከደቂቃዎች በኋላ ጌታቸው ‹‹አመጽ ለማስነሳት ሰዎች ተሰብስበዋል›› ብሎ በደወለላቸው ፖሊሶች አማካኝነት በጊዜው የነበሩትን 16 ክርስትኖችን
እስር ቤት ሊያስገቧቸው ችለዋል ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ሶቶች ጎልማሶችና
፤ ወጣቶች ይገኙበታል ፤ የእነዚህ ንጹሀን ክርስትያኖች ተቃውሞ ‹‹ጌታቸው ዶኒ የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ ለምን ይቀበላል ? ቁልፉን ተቀብሎ ከዚህ በፊት ሲናገር
እንደነበረው የባቦጋያን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ለመዝጋት የሚያደርገውን ተግባር እንቃወማለን ፤ ›› በማለታቸው ነው ለእስር
የበቁት፡፡
በአሁኑ
ሰዓት እስር ቤት ሄዶ ታሳሪዎችን መጠየቅ በራሱ ያሳስራል ፤ ጌታቸው ዶኒ ሀሳብ አንድም ጽላቱን በማውጣት ቤተክርስትያኑ እንዳይቀደስበት
ለማድረግ ሲሆን ያለበለዚያ የቤተክርስትያኒቱን በሮች ሁላ በመቆለፍ ካህናት እንዳያገለግሉ ለማድረግ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከክልሉ መንግስት መልስ ያጡት ምዕመናን ለጠቅላይ
ሚኒስትሩ ቢሮ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ገልጸናል ፤ ይህን ነገር የሰሙት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት እና የክልሉ ፖሊስ ደብዳቤውን ይዘው አዲስ አበባ ድረስ በማምጣት ያስገቡትን ሰዎች
ለመያዝ በተጠናከረ ሁኔታ እየፈለጓቸው መሆኑን ሰምተናል ፤ ይህን የሰሙትም ራሳቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ከአካባቢው ማራቃቸውን ለማወቅ
ችለናል ፡፡ እንዴት ሰው መብቱን ስለጠየቀ ለመታሰር ይታደናል ? ይህ ሁሉ ነገር የቤተክህነቱ ችግረ ነው ፤ ራሱ የቤተክርስትያኒቱን
ቦታ መጠበቅ ቢያቅተው እንዴት ምዕመኑ እዳይጠይቅ በማድረግ ጌታቸውን የመሰለ ማፊያ ሰው መፍትሄ ያመጣል ብሎ ይልካል ፤ ቢያንስ ቦታው ማስከበር ቢያቅተው ይህን
ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ላይ እንቅፋት ሊሆንባቸው አይገባም ነበር ፤
ጌታቸው ዶኒ ከምዕመኑ የከረረ ተቃውሞ ሲደርስበት የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ቤተክርስትያኑን አዘጋዋለሁ ታቦቱንም አወጣዋለሁ
እያለ ሲደነፋ ተሰምቷል ፤ እኛ ግን የምንሰጋው የቤቱ ባለቤት መድሀኒአለም ቤቱን ሊያዘጋ ሲንቀሳቀስ የእርሱን
አንደበት እንዳይዘጋው ነው ፡፡ የዛሬ ሳምንት አካባቢም ይህን ጥያቄ ያነሱ 6 ወጣቶች እስር ቤት መክረማቸውን ለማወቅ ችለናል ፤
ይህ ጉዳይ እንደ ፕሮቴስታንት ሰዎችን ከቤተክርስትያኒቱ ራስ ላይ
ለመቀመጥ የሚያደርጉት ሩጫን ያመላክታል ፤ ሁሉንም ነገር በአንድ ጉልበተኛ ሰው እጅ ስር ለማስገባት አጥብቀው እየሰሩ ነው ፤ የቤተክርስትያናችን ራስ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ይህንም
ጉዳይ ቤተክህነቱ አስቸኳይ መፍትሄ ካልሰጠው ነገሩ መልኩን እዳይቀይር ስጋት አለን ፤ የማንም ቦዘኔ እየመጣ ቤተክርስትያናችን ላይ
ሊፈነጭ አይገባውም ፤ አቡነ ጳውሎስም ጉዳዩን በደንብ ያውቁታል የህዝቡም ፊርማ እና መልዕክት ደርሷችዋል ፤ ዝምታን ለምን እንደመረጡ
እኛ አናውቅም ፤ በመልካም አስተዳደር እጦት ምዕመኑ መከራን መሸከም የለበትም ፤ ችግሮች ተጠንተው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል ፡፡
አሁን ተስፋችን ከቤተክህነቱ እየተሟጠጠ ይገኛል ፤ መንግስት መፍትሄ
ይስጠን ፤ የቤተክርስትያን ችግር የህዝብ ችግር ነው ፤ የህዝብ ችግር ደግሞ የመንግስት ችግር ሊሆንና መፍትሄ ሊሻን ይገባዋል ፡፡
ፈተናችን ዛሬ ደህና ነው ሲባል ነገ እየባሰ እያስቸገረን ይገኛል ፤ ለዚህ ሁሉ ችግር የአንበሳውን ድርሻ ሊወስዱ የሚገባቸው ጠቅላይ
ቤተክህነትና አቡነ ጳውሎስ ናቸው ፤ እኛም መረጃዎችን በጊዜያቸው እናንተው ዘንድ እናደርሳለን ፤