የሰላምና የአንድነት ኮሚቴው መግለጫ አወጣ!የሰላምና የአንድነት ኮሚቴው ሁለቱንም ሲኖዶሶች  አነጋግሮ የመጨረሻ ግብ ላይ ለመድረስ የመቻሉ ነገር በሚደረገው ምርጫ ምክንያት መስተጓጎሉ ይታወቃል። የውጪው ሲኖዶስ መብት ይጠብቃል ተብሎ የታሰበውን ያህል የተጨበጠ ነገር ባለመኖሩ በቀጣይም  ይደረጋል የሚባለው ድርድር እዚህ ግባ የሚባል ነገር እንደማያስገኝ ይገመታል። ፓትርያርኩ ይመለሱ የሚለው መከራከሪያ አይመለሱም በሚል አራት ነጥብ ተዘግቶ አዲስ ምርጫ ላይ ተገብቷልና። ከእንግዲህስ? አብሮ ለመሥራት? ወይስ ምን?
ለማንኛውም የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ አዲስ መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫውን ሙሉ መልእክት  ለማንበብ፤    ( እዚህ ላይ ይጫኑ )

Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 2 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
February 20, 2013 at 5:19 AM

በትናንትናው እለት (ከመልአእ ብሥራት ከቨርጂኒያ) በሚል አንድ ትልቅ ታሪካዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አንብቤ ዛሬ ስመለስበት ግን አንስታቺሁታል። መነሳት የማይገባው እውነተኛውን ገጽታ የሚያሳይ በመሆኑና እኔም ሁኔታውን በቅርብ ስለማውቀው ነው። ብትችሉ እንደገና ብታስነብቡ መልካም ነው። ምናልባት ተቆጪ ስለአለባችሁ ላታወጡት ስለምትችሉ በሌላ ብሎጎች እንዲወጣ ይደረጋል። ወደ እርቁ ጉዳት ሲመጣ ደግሞ ራሱን የቻለ ችግር ያለው ነው አስታራቂ ከታባሉት በጣም ጥቂቶቹ መልካም ቢሆኑም አብዛኛዎቹ ግን የራስ አጀንዳ ይዘው የሚጓዙ በመሆናቸው የተነሳ የትም ሊደርስ እንደማይችል ከጅምሩ የታወቀ ነበረ። አንዱም ትልቅ ችግር የነበረው ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በውክልና የመጡት አባቶች ግልጽ የሆነ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም ሳይሆን እንዲሁ በቅዱስ ሲኖዶስ በመወሰኑ ብቻ የመጡ ስለነበረ በውግዘት የተለያዩ ሆነው ሳለ እንዲሁ በአንድ ቤተ መቅደስ ተቀላቀሉ። በተለይ ከኢትዮጵያ የሚጡት አባቶች ምእመናን እንዳያነጋግሩ ነጻነት በአንዱአለም(ዲያቆን)ተነፍጎአቸው ከሆቴላቸው እንዳይወጡ እንኳ ቁጥጥር ይደረግ እንደነበረ የአደባባይ ምሥጢር ነበረ ይህን የምለው በዳላስ በተደረገው ስብስባ ነው።
የቤተ ክርስቲያን እርቅ እንደ ዓለማዊ ስብስባ በየሆቴሉ መደረጉ አንዱ ስሕተት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድርድር ነው። በመጀመሪያ ለመሆኑ ከማ ጋር ነው ጥሉ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ያለባቸው ኮብላዮች እንጅ ለዚህ ድርድር የሚያስፈልግው አንድም ነገር አይታይበትም። እርቁ ስለ ሥልጣን ነው ከተባለ ደግሞ ከመንግሥት ጋር ይሆን እንደሆነ እንጂ ሌላ አካል አይመለከተውም። በውስጡ ውዥንብር የሞላበት በመሆኑ ለእርቁ ታስቦ ሳይሆን በዚሁ አሳበው የራሳቸውን ምኞት ለማሳካት በተለይ በገለልተኝነት የነበረው የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከስደተኞች የጳጳሳት ማኅበር ለመቀላቀል ጥረት እየተደረገ መሆኑን በአለፈው ቅዳሜ በተደረገው ትንንቅ አይተነዋል ይህም የተጠነሰሰው በአንዱ ዓለም (ዲያቆን) ሲሆን ይህም ከአንዳንድ ፖሊቲከኞችና ከወንዙ ተወላጆች ጋር ሕብረት በመፍጠር ነበረ። የእርቁ ፊታውራሪ እሱ መሆኑ ባይካድም አብዛኛው አካሄዱ በዚህ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ለእውነት የቆመ ለማለት ፍጹም አይቻልም። እርቅም አስፈላጊ ነው ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ይጠቅማል ከተባለም ከዚህም ከዚያም መልካም አዛውንቶች በሥነ ሥርዓት ተመርጠው ቢቀጥል ይሻል እንደሆነ ነው እንጂ በተቀረ ግን ኢትዮጵይ ያለው ም እመን ብሎግ ብዙም ስለማያነብ የጳጳሳት ጉዳይ የሚያሳስበው አይደለምና እዚህ ላለው ግን መደበሪያው ስለሆነ እናንተ ቀጥሉበት ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል።

Anonymous
February 20, 2013 at 11:05 AM

ውድ ወንድማችን፤ /መልዓከ ብሥራት/ በሚል ሰው ስም የተጻፈውን ጽሁፍ «ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችም» በሚል ርእስ ስር ስለተጻፈ እንዲመለከቱት ተጋብዘዋል። በተሳትፎ ግን ይቀጥሉ!

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger