Tuesday, February 19, 2013

የፓትርያርክ ጥቆማው ስልታዊ ነበር፤ የመጨረሻው ምርጫም የማቅ ጥበብ የተሞላበት ይሆን ይሆናል!?

የፓትርያርክ ምርጫው ዘመቻ እየገፋ ሲመጣ የማቅ ስውር ብሎጎችና በስሙ የሚጠራው ድረ ገጽ ጭምር የሚያወጧቸው ዘገባዎች የተጠኑና መጠናቸውም የቀነሰ ሆኗል። «እርቅ ይቅደም፤ ሲኖዶሱ አንድ ይሁን» የሚለውንም ጩኸት በልክ አድርገውታል። በወቅቱ ይህንን ድምጽ ማስጮህ ያስፈለገበት ምክንያት  ማኅበረ ቅዱሳን በፓትርያርክ ምርጫው ውስጥ  እንደሌለበት አንድ እጁን በማሳየት በአንድ እጁ ደግሞ ወደ ምርጫው  ለመግባት የመሸጋገሪያ ስልት አድርጎ በመጠቀም ነበር።  ይህንንም በአንድ በኩል አባላቶቹን በአስመራጭነት ሰግስጎ በመክተት በሌላ መልኩ ደግሞ የፓትርያርክ ምርጫውን እንደሚቃወም መስሎ የመታየት ስልቱ አስቀድሞ ጥናት የተወሰደበት ስልት ነው። ይህ ስልት ደግሞ በትክክል ሰርቷል። ምርጫውን እንቃወማለን ብሎ በመጮህ ብዙዎችን አጃጅሏል ፤ በጀርባው ደግሞ አባላቶቹንም በአስመራጭነት በመሰየም የተሳካ ስራ ሰርቷል። አሁን የቀረው ነገር የሚፈልገውን እጩ በመጠቆም፤ በካርድ ምርጫው ሽፋን የሚፈልገውን ፓትርያርክ አድርጎ ማስቀመጥ ነው። ይህንንም ስልት በተጠና መንገድ እያስኬደው እንደሚገኝ መረጃዎችና እንቅስቃሴዎች ይጠቁሙናል።

 ከአስመራጭ ኮሚቴዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የወሰደው ማቅ ነው።
  1. ባያብል ሙላቴ የተባለው ሰው ዊኪሊክስ ሳይቀር የመሰከረለት የማኅበረ ቅዱሳን አባልና በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል እርቅ መምጣት እንደማይችል  በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ሲያቀብል የኖረና ቀንደኛ የአባ ጳውሎስ ተቃዋሚ ነው። በወቅቱ አባ ሳሙኤል ከሟቹ ፓትርያርክ ጋር ውዝግብ ውስጥ ስለገቡ ብቻ ደጋፊያቸው መስሎ በመቅረብ እሳት ሲያነድ የቆየ አስመሳይ ሲሆን ዛሬም አባ ሳሙኤል እንደሚመረጡ በማስመሰል እያጃጃለ ቁማሩን ይቆምራል 
  2.   ፋንታሁን ሙጬ፤ ይህ ሰው ከኦስትሪያ  ካቶሊክ ኮሌጅ ከተባረረ በኋላ / የመባረሩ ምክንያት ሰፊ ነው/ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ የተሾመ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ካህናትን  በጉቦና በዘረኝነት በሽታ ሥጋቸውን  ጨርሶ አጥንታቸውን እየጋጠ ባለበት ሰዓት ፈጀን፤ ጨረሰን ብለው እሪ በማለታቸው ከቦታው የተነሳ ርኅራኄ ያልፈጠረበት ሰው ነው።  ከአባ ጳውሎስ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት የነበረው ሲሆን ከባል አልቦዋ ሴት ጋር ትስስሩ የጠነከረ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን በስልት የሚመለከት መሰሪ ሰው ነው።  
  3.    ዓለማየሁ ተስፋዬ፤ ይህ ሰው ተንኮለኛና እንቅስቃሴውን እንደቀንድ አውጣ ከሰንኮፉ ሳያርቅ ብቅ ጥልቅ እያደረገ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሚና የተጫወተ አደገኛ ጸረ ትግሬ ነው። «ቃሌ» በሚባለውና በብርቱኳን ሚደቅሳ ስም በተመሠረተው  የፓልቶክ  ውስጥ ተባባሪ ባለቤት /Admin/ ሆኖ የሚያገለግል የሽማግሌ ውሸታም ነው። የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅትን ጥሩ አድርጎ የጋጠ አድመኛና ዘረኛ  እንደሆነም በሰውየው የተማረሩ ሰዎች እንባ ቀረሽ እሮሮ ያሰማሉ።
  4. ጸባቴ ገብረ መስቀል ውቤ /ሙሽራው ይሉታል በቅርብ የሚያውቁት/  መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገ/ጻድቅና ዲ/ን ኄኖክ ዐሥራት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ እንደሌላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። /በእነዚህ ሰዎች ዙሪያ ያገኘናቸውን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው/


እንግዲህ እነዚህ ናቸው የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ የሚባሉት። አስመራጮች ራሳቸው በምእመናኑ የተመሰከረላቸው ታማኞች፤ ቅኖች፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው መሆናቸው ከሕይወት ታሪካቸው ተነስቶ ምስክርነት ሳይሰጣቸው ፓትርያርክ ያስመርጣሉ ቢባል በሕዝቡ ላይ ማላጋጥ፤ በእግዚአብሔር አሠራር ላይ ማሾፍ፤ በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ላይ ጋሬጣ መትከል ይሆናል። ይህን ሁሉ ሸርና ደባ የሚሰራው ያ  ቅዱሳኑን እወክላለሁ የሚለው ማኅበር ነው። እንደምንሰማው ከሆነ አባ ማቴዎስን / የሸዋ ሰው/ ለማስመረጥ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በተጠባባቂነት ደግሞ ትውልደ ትግራይ የሆኑትን አባ ሉቃስን በመሸፈኛነት በመጠቀም ዘረኛ እያለ የሚጠራውን መንግሥት ለማሞኘት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የሰንበት ትምህርት ቤት አካል ነኝ ይል የነበረው ይህ ነጋዴ ቡድን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ምንም መዋቅር በሌለው ሁኔታ መኖሩ ሳያንስ ሚሊየነር የመሆኑ ምስጢር ሌላ ሳይሆን ቤተ ክህነቱን በሲኖዶስ በኩል መቆጣጠር እንደሆነ እስከዛሬ የተጓዘባቸውን መንገዶች እየለፈለፍን ሰሚ ሳናገኝ እነሆ የዓላማውን ፍጻሜ ለመጨበጥ ከጫፍ ደርሷል።

ማኅበረ ቅዱሳን የሰንበት ት/ቤት አካል ነው የሚባለው ሽፍን ስሙ ለጊዜው ይቆየንና በፓትርያርክ አስመራጭነትና በድምጽ ሰጪነት እንደ አንድ ትልቅ ተቋም ተቆጥሮ ይህንን ያህል መብት ያገኘው በምን ሂሳብ ነው? ብለን ብንጠይቅ ሥልጣን፤ ገንዘብና እውቀት ካለህ ያቀድክበት ትደርሳለህ ከሚል ስንኩል እሳቤ የተነሳ ነው።

  «Money is just a tool, but when this tool in the wrong hands it becomes a weapon of control and abuse»

«ገንዘብ የመገልገያ መሣሪያ ነው፤ ነገር ግን ይህ መሣሪያ በጥፋት እጆች ውስጥ ሲገባ የጦር መሣሪያ ሆኖ ሁሉን ለመቆጣጠርና ሕገ ወጥ ድርጊት  ለመፈጸም ያገለግላል» የሚባለውም ለዚህ ነው። ከዚህም የተነሳ ገንዘብ የተባለው መሣሪያ ከብላቴ ጦር ካምፕ አንስቶ በናዝሬትና በዝዋይ ተጉዞ እስከደብረ ብርሃን ድረስ በተሰባሰቡ፤ የተለያዩ  ነገር ግን አንድ ዓላማ ባስተሳሰራቸው ሰዎች እጅ ወደቀና ዛሬ ያንን የድኩም ቤተ ክህነትን አስተዳደር ለመቆጣጠሪያ አገልግሎት ሊውል የጥፋት መሣሪያ ሆኖ ይገኛል።

ከዚህም የተነሳ የማኅበረ ቅዱሳንን የፓትርያርክ ምርጫ ተቃውሞን ማላገጥ ትተን እውነት እውነቱን ስንናገር የፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የመሆኑ ነገር ፊት ለፊት የሚታይ ሐቅ ነው። ጥቆማ ተቀባይ ሆኖ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ሆኖ ደግሞ ጥቆማውን እንዴት መቀበል እንዳለበትና እንዴት አበጥሮ እርሱ ያቀደውን ዓላማ ማሳካት እንደሚችል እያወቀ ብቅ በማለት በአስመራጭ ኮሚቴ መግለጫ ሽፋን  ጸሎት፤ ግብዓት፤ የኅብረት ጥቆማ፤ ምናምን እያለ የማምታታት ድራማውን ይተውናል። አሁን እየተፋጠነ ያለው ሥራ 5 /አምስት/ ሰዎችን በማቅረብ ቢቻል የማይፈለጉትን 2/ ሁለቱን/ እጩዎች በሲኖዶስ እንዲቀሩ ማስደረግ 3/ ሦስት/ ብቻ እንዲቀርቡ ማስወሰን ነው። ይህ እንኳን ባይሳካ በሚቀርቡ 5 /እጩዎች/  ላይ የድምጽ ሰጪዎችን ቁጥር ከ800 ወደ ላይ ከፍ በማስደረግ እንደቀንደኛ ተሳታፊነቱ በካርድ ጫወታው ጥበብ  የሚያታልላቸውንና አስጊ ናቸው የተባሉትን አባ ሳሙኤልን ጠልፎ መጣል ነው።

በየሚዲያው የሚሰማው የአባ ሳሙኤል ቀጣይ ፓትርያርክነት በአብዛኛው መነሻው ከማኅበረ ቅዱሳን ስልታዊ የትወና ድራማዎች ቢሮ እንደማስታወቂያ የሚለቀቁ ነጠላ ዜማዎች ናቸው። ይህም አባ ሳሙኤል በመንግሥት ይደገፋሉ በማሰኘት ውጥረቱን እያረገበ የራሱን ግብ እየሄደ ባለበት ትክክለኛ ስልታዊ ጉዞው ማስፈጸም መቻል ነው።

በዚህም መሠረት የሆነ አዲስ ክስተት እስካልተፈጠረ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን በትክክለኛ የእቅዱ ምሕዋር ላይ እየተሽከረከረ ነው።  መንግሥት ምን አገባኝ ብሎ ነገሩን ሁሉ ትቶላቸው ነው ወይስ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ይሆን? የገዢውን መንግሥት ሁኔታ ባናውቅም የቤተ ክህነቱ መንግሥት የማቅ ጉዞ ግን ያለችግር ባሰበው መንገድ እየሄደ እንደሆነ እንረዳለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ቀንና ሌሊት እየተፈራረቀ ሲሆን የምርጫውን መከር ለመሰብሰብ የቀሩት ቀናቶች ብቻ ናቸው።

የፓትርያርክ ጥቆማው ስልታዊ ነበር፤ የመጨረሻው  ምርጫም የማቅ ጥበብ የተሞላበት ይሆን ይሆናል!?