ሰበር ዜና – ለዕጩ ፓትርያርክነት የተመረጡት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!


ከዚህ ቀደም ስንል እንደቆየነው ከብዙ እጩዎች መካከል አምስቱን የመለያው መስፈርት ግልጽ ባለመሆኑ የአስመራጭ ኮሚቴው መልካም ፈቃደኝነት የሚወስነው እንደሚሆን በነበረን ግምት መሠረት ለ6ኛ ፓትርያርክነት የታጩትን አምስት ጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴው ለይቶ ለቋሚ ሲኖዶስ ማቅረቡ ተሰምቷል። በዚህ መካከል ሌላ አዲስ ክስተት እስካልተፈጠረ ድረስ የአባ ሳሙኤልና የአባ ገብርኤል እጩ ሆኖ የመቅረብ ነገር ውድቅ ሆኗል። በእርግጥም የጭለማው ቡድን ተብሎ የሚጠራው ክፍል የትግሉን ድል እያጣጣመ ወደሚገኝበት እርከን ተሸጋግሯል። በሌላ መልኩም ጥላወጊ የሆነው  ያ ክፉ ማኅበርም የስኬት ደረጃውን አሳድጓል ማለት ይቻላል። ከእንግዲህ የሚኖረው ወሳኙ ፍልሚያ በጥላ ወጊው ማኅበርና በጭለማው ቡድን መካከል ይሆናል ማለት ነው። ያ ማለት ደግሞ በሁለት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ወደሚደረግ ውድድር ተሸጋግሯል ማለት ነው። የሰልፉን ብርታት አይተን ግምታችንን ስንወስድ ሌሎቹ እጩዎች ለማሟያነት የቀረቡ ናቸው። ምናልባትም የእነ ኤልያስ አብርሃ ፓርቲ የሆነው የጭለማው ቡድን  ሥልጣንን መከታ አድርጎና ከኋላ የድጋፍ ኃይሉን አስታኮ ያንን ጥላ ወጊ ማኅበር ሊያሸንፍ እንደሚችል አስቀድሞ መገመት ይቻላል። ረጂም እጅ እንደገባም ዘግይቶ የወጡ መረጃዎች ይናገራሉ። በምርጫው ውስጥ የሰዎች ምርጫ እንጂ የመንፈስ ቅዱስ አሠራር በጭራሽ የለም።

                                                                                                                          

        የእጩዎች የምርጫ ሂደት ሐራ ዘተዋሕዶ እንዲህ ዘግቦታል።

  •     ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
  •     ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
  •     የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
  •     ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ /ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-

1)  ብፁዕ አቡነ ማትያስበኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ

2)  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስየወላይታ ዳውሮ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3)  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍየባሌ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4)  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልየከፋ ሸካ ቤንች ማጂ /ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

5)  ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕየሰሜን ጎንደር /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡


የአስመራጭ ኮሚቴው አጣርቶ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸውና የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አራቱ በኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ዕጩዎች ውስጥ ያልተጠበቁ አባቶች ሊታዩ እንደሚችሉም አስቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡
ነገር ግን በብዙ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ድምፅ የተጠቆሙትና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አንቀጽ 5 የተዘረዘረውን የዕጩ ፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላሉ ተብለው የታሰቡት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል (9000 ያህል ጠቅላላ ጠቋሚዎች 7200 አግኝተዋል)
እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከዕጩዎቹ ሳይካተቱ መቅረታቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላትን መስገረሙ አልቀረም፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቀድሞም ከዕጩዎች ዝርዝር እንዳይጨመሩ በአንዳንድ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና በተለይም ‹‹መንግሥት የሚፈልጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን እናስመርጣለን›› በማለት በመራጮች ላይ ሽብርና ስጋት ሲፈጥሩ በሰነበቱት÷ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ / እጅጋየሁ በየነ፣ መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ፣ / አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ እና / ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ቡድን ከፍተኛ ጫና ሲፈጠር መሰንበቱ ተዘግቧል፡፡
ኮሚቴው ዕጩዎቹን የለየበትን ሂደት ወደፊት በዝርዝር ለማወቅ የሚጠበቅ ቢኾንም ስለ ተግባርና ሓላፊነቱን አስመልክቶ÷ በአንቀጽ 6/ጥቆማ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከካህናትና ምእመናን እየተቀበለ እንደሚሠራ፤ በአንቀጽ 6/የዕጩዎችን ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ 15 ቀናት ይፋ በማድረግ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንደሚቀበል፤ በአንቀጽ 6/በተቀበላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች መሠረት ዕጩዎቹን ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ መርምሮና አጣርቶ የሚቀበለውን ከተቀበለ፣ የማይቀበለውንም ከጣለ በኋላ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ እንደሚያሳውቅ በግልጽ የተደነገገ በመኾኑ ቀጣይ አካሄዱ ከእኒህ በተጨባጭ መሸራረፍ ከጀመሩ አናቅጽ አኳያ የሚመዘን ይኾናል፡፡
ሐራዊ ምንጮች ከወዲሁ ስለኹኔታው ለመረዳት ባደረጉት ጥረት ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው ጥርጣሬ ያላቸው ሲኾን ከዚህም በመነሣት ውሳኔውን በፊርማቸው ስለማረጋገጣቸውም አበክረው ይጠይቃሉ፡፡
‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› የሚለው ሰሞንኛ አባባል ቋጠሮው ሊፈታ እነኾ ቀኑ ቀርቧል፡፡

Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 3 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
February 22, 2013 at 2:34 PM

Zare ke-aba selama were tefana ke-haratewahido wesedachu
yewere dirk metachu aydel, Enante bizu taweralachu Egziabher gin sirawun zim bilo yiseral.. Esu yefekedew yihun. 1 erigitegna yemihonibet neger, ke-echuwochu manachewum bimeretu enanten ke-betechristian endemiyatefulign betam erigitegna negn. Lemenafikan botam werem yelenm.. Egziabher yewededewun Yaskemt, Atsirare betechristianinm yatifaln
Amen

ewnetu yigelet
February 22, 2013 at 3:20 PM

Yenante echu paster maneberu?

Anonymous
February 22, 2013 at 6:01 PM

እንኳን ደስ አለህ። ቡድንህ አሸነፈልህ። የጨለማው ቡድን እኮ ሲረዝም እነ ሰረቀን፥ በጋሻውን፥ ኅይለጊዮርጊስን እና የመሳሰሉትን የሙስና አለቆች ከጴንጤ ተላላኪ ጥቅመኞች የያዘ ነው እኮ። ዛሬ ወዴት መሸሽ ነው።ከጋለሞታዋ ተጣላችሁ እንዴ? ጋለሞታዋ በቂ አልከፈለቻችሁም ወይስ በአቡነ ማቲያስ አልተስማማችሁም? ለመሆኑ እሳቸው ሲሾሙ እንፈነጫለን ብላችሁ ታስባላችሁ? ይቺን አስተራየን ጠይቀው በደንብ ይነግርሃል።

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger