Tuesday, April 30, 2013

አባ አብርሃም በአሜሪካ ያለውን የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ


http://awdemihreet.blogspot.com/) በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት /ቤት ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን /ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን /ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን /ቤት አላስረክብም በማለት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያልቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡

በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለምን ተዘዋወርኩ በሚል ሂሳብ የሲኖዶሱን ውሳኔ አላከብርም ቁልፍም አላስረክብም በማለት የመጀመሪያው የሆኑት አባ አብርሃም ቁልፍ ላለመስረከብ እና የሲኖዶሱን ውሳኔ ላለማክበር እንደ ምክንያት የሚያቀርቡዋቸው ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ካረፉም በኃላ በተተኪው ፓትርያርክ በአቡነ ማትያስ ጊዜም ቋሚ ሲኖዶሱ ሕገ ወጥነታቸውን ጠቅሶ ቁልፍ እንዲያረክቡ መወሰኑ በፊትም ሆነ አቡን የቤተክርሰቲያንን ውሳኔ ተጋፍተው በሙሉ ስጋዊ አቋም ላይ ያነበሩትም ሆነ ያሉት አባ አብርሃም መሆናቸውን ስለሚገልጽ ውሳኔው አባ አብርሃምን ትልቅ ኃፍረት ያከናነበ  ሆኗል፡፡
የአባ አብርሃም የልብ ወዳጅ  የሆኑት እና እንደ አባ አብርሃም  ሁሉ በተለይ ለማኅበረ ቅዱሳንቅዱስአባት የሆኑት አባ ኤዎስጣቲዎስ የሲኖዱሱን ውሳኔ ተጋፍተው እምቢኝ አሻፈረኝ በማለት በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት ሚናው ያልለየ ሽፍትነት ጀምረው የነበረ ቢሆንም መጨረሻቸው ግን ውርደት መሆኑን ሰሞኑን ከሚማሩነት ትምህርት ቤት የተባረሩበት ምክንያት አስረጅ ሆኗል፡፡ አባ አብርሃምም ከአባ ኤዎስጣቴዎስ የተሻለ ሰብዕና ባይኖራቸውም ዘግይተውም ቢሆን የሲኖዶሱን ውሳኔ በከፊል ለማክበር መወሰናቸው እንዲህ ካለው ውርደት ሸሽጓቸዋል፡፡ አሁንም ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ለማከበር ካልወሰኑ እና ሀገረ ስብከቱን ያስወረሩትን የድርጭት መንጋ አስወግደው ቁልፉን ለአቡነ ፋኑኤል ካላስረከቡ እሳቸውም ቀጣይ ውርደት እንደሚገጥማቸው ብዙዎች የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡
አባ አብርሃም ከተነሱ በኋላ የሲኖዶሱን ውሳኔ እና የደብዳቤ ልውውጦች የሚዳስሰውን ዝርዝር ታሪክ ወደፊት እናቀርባለን፡፡