እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ ( ክፍል ስድስት )

 ክፍል ስድስት (የጽሁፉ ባለቤቶች ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)
(www.answering-islam.org)

ሙሶሊኒና የሳውዲው የግመሎች ግዢ
 
በግንቦቱ ስምምነት መሰረት የሳውዲና የጣሊያኖች ግንኙነት በጣም እየተቀጣጠለ ሄደ፤ በዚያው ወር የጣሊያን ወኪል የሆነውና በጣሊያን የወታደራዊ ስለላ ውስጥ የሌተናንት ኮሎኔልነት ማዕረግ ያለውሴልሶ ዖዴሎባለቤቱና ሴት ልጃቸው ጅዳ ደረሱ፡፡ እርሱም እራሱን የተለያዩ የጣሊያን የንግድ ድርጅቶች ወኪል እንደሆነ አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱም ወዲያውኑ የጅዳ ሕይወት ማዕከል ሆነና ከምሁራን እንዲሁም ከያሲን ጋር ጥብቅ ወዳጅነትን መሰረተ፡፡ በሐምሌም ወር ዖዴሎና ያሲን በኤርትራ ውስጥ እየተከማቸ ላለው የጣሊያን ሰራዊት አስፈላጊ ስለሆኑት 12,000 ግመሎች ለጣሊያን የመግዛት ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡ሴልሶ ዖዴሎምከመደበኛ ዋጋቸው ሦስት እጥፍ እንደሚከፍል ሐሳብን አቀረበ፡፡ ዓለም አቀፉ ውጥረት እየተፋፋመ ነበርና ሳውዲ አረቢያ ከመቼውም በላይ ከሙሶሊኒ ጋር ባደረገችው ድርድር ብሪቴንን የሚያስቆጣና በመካከላቸው ማለትም በብሪቴንና በጣሊያን ጦርነት ያስከትላል በማለት በጣም ተጨንቃለች፡፡ በዚህም ምክንያት ከሳውዲ የጦር ወታደር እንዳይመለመል አግዳለች፣ ይሁን እንጂ ሌሎች ነገሮች የምግብ ግዢዎችና ግመሎች ግዢዎች ላይ ምንም ችግር አልነበረም፡፡
በዖዴሎም አማካኝነት ለጣሊያኖች አትክልቶች ይሸጡላቸው ነበር፣ ምፅዋ ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ከጥቅም ውጭ ይሆኑ የነበረ ቢሆንም፡፡ አሁን የጣሊያን ጦር መሳሪያዎች የሚፈልጉት ግመሎችን ነበር፤ ለጦርነት የሚደረገው ዝግጅት እንደቀጠለ ከባድ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ማጓጓዝ በጣም ችግር እንደነበረ በጣም ግልፅ እየሆነ መጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ ተራራዎች አካባቢዎች መሳሪያዎችን ለማጓጓዝና አስፈላጊ ነገሮችን ለማግኘት የጣሊያን ሰራዊት በግመሎች ላይ መደገፍ ነበረበት፡፡ በእርግጥ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላም እንኳን የተረጋገጠው ነገር የግመሎች አስፈላጊነት ነበር፡፡

በሐምሌ ወር ኢብን ሳውድ በየወሩ 300 ግመሎች በዖዴሎ በኩል እንዲሸጥ ቀስ በቀስ የተደረገውን ስምምነት አፀደቀው፡፡ ነገር ግን ሼክ ያሲን ተጨማሪ ግመሎች እንዲሸጡ በጣም ይገፋፋ ነበር፡፡ ከጣሊያን ጋር የሚደረገውን ድርድር እንዲጠናከር የሚያደርጉት እርሱና ሐምዛ ነበሩ እርሱም በግሉ ከግመሎች ሽያጭ ድርድር የሚያገኘው ጥቅም ነበር፣ ያሲን በመጨረሻ ዖዴሎን ከኢብን ሳውድ ጋር ያገናኛው ሲሆን 12,000 ግመሎቹ ግዢ እንዲከናወን ተደርጓል፣ በግዢውም 7 ፓውንድ ለመንግስት ግምጃ ቤት፣ 7 ፓውንድ ለባለግመሎቹ የናጅድ ጎሳዎች እና 1 ፓውንድ ለያሲን እንደ ደላላ እንዲከፈል ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢብን ሳውድ ብሪቲሾችን በጣም ፈርቶ ስለነበር ሽያጩን በተመለከተ እንደ ፀረ ብሪቲሽ ያዩት መሆንና አለመሆኑን እንዲያጣራ ያሲንን ወክሎትም ነበር፡፡ ብሪቲሾችም ቀደም ብሎ ኢትዮጵያን ለመሰዋት ባቀዱት ስልት መሰረት ምንም ግድ እንደሌላቸው ሲገልፁ ኢብን ሳውድም ጦርነቱ በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል ስለሆነ በሽያጩ ምንም ግድ እንደሌለው አሳይቶ ነበር፡፡
የብሪቲሾች መልስ ለኢብን ሳውድ ጣሊያን ስለሚያደርገው የጦር እንቅስቃሴ ምንም ችግር እንደሌለባቸውና በግመሎች ሽያጩም እንዳይጨነቅ ሲያደርጉ፤ ጣሊያንም ኢትዮጵያን ለመያዝ ለሚያደርገው ዘመቻ ሰፊ ዕድልን ሰጥተውታል፡፡ ስለዚህም ብሪቲሽና ፈረንሳይ ለኢብን ሳውድ ምክራቸው ጣሊያኖችን በትህትና እንዲይዛቸውና የግመል ሽያጭ ድርድሩ ምንም ሊያሳስበው እንደማይገባ ነበር፡፡ በእርግጥ እዚህ ላይ እራሳቸው ያወጡት አንድ ምስጢር ጣሊያን ከሱዳን ግመልን ሲገዛ ዝም እንዳሉትም በመጠቆም ነው፡፡ በመስከረም 20 32 ገፅ የግመሎች መግዛት ስምምነት ተዘጋጅቶ በሁለቱ አገሮች መካከል ተፈርሞ የግመል ግዢው ቀጥሏል፡፡ ሙሶሊኒ እንዲህ ዓይነቱን ትብብር ከሳውዲ ማግኘቱ ኢትዮጵያን ለመውረር ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ የጦር የበላይነትን እንዲቀዳጅ አድርጎታል፡፡
ኢትዮጵያን አሳፍሮ ፋሽስትን መርዳት
 በጥቅምት 3 1935 ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ወረሩ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ አድዋን ያዙ ነገር ግን 1896 ጦርነት ላይ ድል ለተደረጉት በቀልን ለማድረግ ያቀዱት ዓላማ ወዲያውኑ አልተሳካላቸውም ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ በተጠቀሰው በኃይለስላሴ ጉግሳ ክዳት የተነሳ የኢትዮጵያ ጦር በፍጥነት ተፍረክርኮ ነበር፣ የሽምቅ ተዋጊዎች ጣሊያኖችን ብዙም ስላላራመዷቸው መቀሌን የያዙት ህዳር 8 ቀን ነበር፡፡ ይህን እንጂ ብዙ ጦርነቶች እየተካሄዱ እያሉ የኃይለስላሴ መንግስት አሁንም የዲፕሎማቲካዊ እንቅስቃሴውን ጎን ለጎን በማካሄድ ሌሎች ልዑካንን ወደ ሳውዲ ላከ እነዚህም ብላታ አየለ ገብሩና ወጣቱ ሳይድ መሃመድ ማህዲ ነበሩ ሁለቱም በፈረንሳይ የተማሩና አረብኛንም በጥራት የሚናገሩ ነበሩ፡፡ ጉዟቸውም ከሳውዲ ጋር የወዳጅነት ስምምነት ለመፈራረምና በሳውዲ ከተማም በጂዳ ውስጥ አምባሳደር ቢሮ ለመክፈት ነበር፣ ልክ እንደቀድሞዎቹ ልዑካን እነዚህም የህዳርን ወር ሙሉ እስከ ታህሳስ 24 ድረስ ለብዙ ቀናት ያለምንም ምላሽ ሲጉላሉ ቆይተው ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል፡፡ ከጅዳም ታህሳስ 29 ሲነሱ ምንም የስምምነት ደብዳቤ አልያዙም ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን የመንግስታቱ ህብረት በወቅቱ አባል ለነበረችው ለኢትዮጵያ ምን አድርጓል? ከነበረው ዓለም አቀፍ ውጥረት የተነሳ ምንም ነገር አልተደረገላትም፡፡ በወቅቱም የመንግስታቱ ድርጅት አባል ያልነበረችው ሳውዲ አረቢያ በነፃነት ግመሎችን ለወራሪው ለማቅረብም ችላ ነበር፡፡ በታህሳስና በጥር 1936 ሐምዛ እንደዘገበው ጣሊያኖች ለአንድ ግመል አስከ 100 ፓውንድ ድረስ ለመክፈል ዝግጁዎች ነበሩ ብሎ ነው፡፡ ከየካቲት 1936 በኋላ ጣሊያኖች የጦር የበላይነትን ይዘው በጦርነቱ ላይ ድልን ለማግኘት የቻሉት በግመሎቹ አማካኝነት ብቻ ነበር፡፡  
በዚህ ሁሉ ወቅት ሳውዲዎች ገለልተኞች እንደሆኑ ቢናገሩም ጦርነቱ በከፊል የሙስሊም ሳውዲና የክርስትያን ኢትዮጵያ የነበረ መሆኑን ለማንም ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ይህንን የምናየው ሳውዲዎች ለኢትዮጵያ ልዑካን በተደጋጋሚ ካሳዩት መጥፎ አመለካከትና የጥላቻ ምላሽ እንዲሁም ከፋሽስት ጣሊያን ጋር ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከመስማማታቸው እውነታ ላይ ነው፡፡
በውጤቱ ሙሶሊኒ በጣም ተደስቶ ኢብን ሳውድንና አማካሪዎቹን ከልብ አመስግኗል፡፡ የሳውዲ ህዝብ ስለ ኢትዮጵያ መከበብ ምን ይል ነበር? ጋዜጦቻቸውስ? ይህ ጥያቄ ድብልቅ መልስ ያለው ይሆናል የሳውዲ ሕዝብ መንግስቱን ከመደገፍ ሌላ ምን ሊያደርግ ይችላል ተብሎ ቢታሰብም የኢትዮጵያ መከበብ ላይ ሳውዲ ባደረገችው ድጋፍ አንዳንዶች ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጦቻቸው ይሰጡ የነበረው የተቃረነ ነገርን ነበር፡፡
የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ከአጠቃላይ አካሄዱና ከታሪካዊ እውነታው እንደተገመገመው የዋሃቢው ሳውዲ መንግስትና የክርስትያን ኢትዮጵያ ጦርነት እንደነበር መናገር ስህተት አይመስልም፡፡ ከፕሮፌሰር ኤርሊች ታሪካዊ ጽሑፍ የምንገነዘባቸው ነጥቦች:
ሳውዲ የኢትዮጵያን ጥያቄ ችላ ብላ ለሙሶሊኒ እርዳታ ማድረጓ፤
የጣሊያን መንግስት ጦርነቱን ባደረገበት ወቅት 70,000 የሙስሊም ወታደሮች መጠቀሙ፤
ሙሶሊኒ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ውስጥ የእስላም ነፃ አውጭ ሆኖ እራሱን ማቅረቡ፤
ለዘመናዊ የጣሊያን የጦር መሳሪያው ማጓጓዣና የጦር የበላይነት ለመያዙ 12,000 ግመሎችን ከሳውዲ በሳውዲው ንጉስ የበላይ ተቆጣጣሪነት ጣሊያን መግዛቱና መጠቀሙ ናቸው፡፡
በዚህ ሁሉ ውስጥ የኃይለስላሴ መንግስት በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሙስሊሞች ለማስተባባር እንዲያውም አዲስየኢትዮጵያ መንግስት ሞዴልመቀረፁን በማስተዋወቅ የተቻለውን ዲፕሎማቲካዊ እንቅስቃሴ ቢያደርግም የዋሃቢዝም ደጋፊዎች ከጣሊያን ወገን በመሆን አገሪቱን ለጠላት በመስጠት አገሪቱን ተዋግተው እንደነበር በታሪኩ ውስጥ ፍጥጥ ያለ እውነታ ነው፡፡
ከዚህ በላይ የቀረበው የፕሮፌሰር ኤርሊች ታሪካዊ እውነተኛና ገለልተኛ ዘገባ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለያዩና መሰረታዊ ጥያቄዎችን ማስነሳት አለበት፡፡ ለሚነሱትም ጥያቄዎች መንደርደሪያ ይሆኑ ዘንድ የሚከተሉት የማጠቃለያ ሐሳቦች ይጤኑ ዘንድ ያስፈልጋል እነዚህም፡-•ታሪክ የሚያሳየው በየጊዜው የተነሱ የኢትዮጵያ ንጉሶችና መሪዎች ከሙስሊም አገሮች ጋር ወዳጅነት እንመስርት ወይንም እንተባበር ጥያቄ ሲያነሱ በግልፅና በተዘዋዋሪ ይጠየቁ የነበሩት ሃይማኖት እንዲቀይሩ የነበረ መሆኑ፡፡
ጥንት ለጎንደሩ ንጉስ ፋሲለደስ በየመኖችና ቆይቶም በሱዳኖች ለአፄ ዮሐንስ የቀረቡት ጥያቄዎች ሁሉእንደ ነጃሺ እስላምብትሆኑ ከጎናችሁ እንቆማለን የሚል የነበረ መሆኑ፡፡
በሳውዲ የሚመራው የዋሃቢዝም እንቅስቃሴ ባለፈው ምዕተ ዓመት በጣሊያኖች አማካኝነት ከዚያም ቀደም ብሎ በኦቶማን ቱርክ ድጋፍ የተነሳው ግራኝ መሐመድ አገሪቱን የእስላም አገር ለማድረግ ከፍተኛ ትግል አድርጎ የነበረ መሆኑን፡፡
ጣሊያንም እራሱ በኢትዮጵያ የእስልምና ጠባቂ ነኝ ብሎ ጦር ይዞ ሲመጣ በአገሪቱ ውስጥ የነበሩትን እውነተኛ ዜጋዎች በማስጨፍጨፍ ትብብር ድጋፍ አብሮም መሰለፍ ላይ የተሰማሩት ሁሉ ሙስሊሞች የነበሩ መሆናቸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ መንግስት የሚመራው የዋሃቢዝም እንቅስቃሴ እና የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎችና ድጋፎች ታሪካዊ ጥልቅ አመጣጥ ያላቸው መሆኑ ናቸው፡፡
የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆ ፖለቲከኞች ወይንም የሆነ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎች አይደለንም ነገር ግን እንደማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ የአገራችን ጉዳይ ያሳስበናል፡፡ ይህንን በተመለከተ የአንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦችና ጋዜጠኞች እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች የሃይማኖት ነፃነት ተደፍሯል በሚል ሰበብ የሚሰጡት አስተያየት ያስገርመናል፡፡
ስለዚህም በእነዚህ ታሪካዊ ጽሑፎች አማካኝነት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታሪክ ምን ይመስል እንደነበረ ለማሳየት እንሞክራለን ዋናው ዓላማችንም የምናደርገውን አስተውለን እንድናደርግናየጠላቴ ጠላት ወደጄ ነውየሚል የተሳሳተ ድጋፍ ውስጥ እንዳንገባ ነው፡፡ በመሆኑም የአሁኑ የሙስሊሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው ምንድነው? በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ ያለው መንግስት ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እየገባ ነውን? ወይንስ አገሪቱ በሰላም የሁሉም አገር ሆና እንድትኖር የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው?
ጎረቤቷን ኢትዮጵያን ለጣሊያን ወረራ አሳልፋ የሰጠችው ሳውዲ አረቢያ አሁንስ ምን እያደረገች ነው? ባላፈው የካቲት 27 በወጣው ሱዳን ቲሪቡን ላይ የቀረበው የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለስልጣን ንግግር www.ethiomedia.com/addis/5677.html ምክንያቱ ምንድነው? ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን እስላም አገር ለማድረግ አሁንም የማትፈነቅለው ድንጋይ የላትም፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ቁጥር የሌላቸው መስጊዶች በማሰራት፣ የቁርአን ማእከሎችና ሌሎች ማዕከሎችን በተለያዩ ቦታዎች በማቋቋም፣ እስልምና በአገሪቱ ውስጥ የብዙው ሕዝብ እምነት እንደሆነ ተደርጎ የተቀናበረ ቅስቀሳ በማሰራጨትና በዚህም በዚያም ትሞክራለች፡፡ ይህ ሁሉ አልሳካ ስላለ ወደ መንግስት ፍንቀላ ይህም አልሳካ ካለ በሱዳንና በግብፅ በኩል ኢትዮጵያን ለመውጋት አትመለስም! በዚህ ሁሉ የሳውዲ መንግስት ዓላማ ምንድነው? በኢትዮጵያ ውስጥ የተጨቆኑትን እስላሞች ነፃ ለማውጣት? ወይንስ በካኣባ ላይ ተነግሯል የሚባለው የጥንቱ ትንቢት  እንዳይፈፀም ሊኖር የሚችለውን ፍርሃት ለማጥፋት? ወይንስ የመጀመሪያ የእስላም ንጉስ ነጃሺን ገድላለች ተብላ በውሸት የተወነጀለችውን ክርስትያን ትባል የነበረውን ኢትዮጵያን ለመበቀል ነውን? ለነዚህ ጥያቄዎች መጪው የወደፊት ጊዜ የሚያሳየን ቢሆንም ያለፈው ታሪክም የሚነግረን ብዙ ምስጢር አለ፡፡
በመሆኑም በሚቀጥለው ጊዜ የዋሃቢ እንቅስቃሴና ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ላይ በፕሮፌሰር ኤርሊች መጽሐፍ ላይ የተመሰረተውን እውነተኛ ታሪካዊ ዘገባ እንመለከታለን፡፡
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 1 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
April 24, 2013 at 2:41 PM

melkam new bere hoy bere hoy entnun ayteh gedelun satay....le tekawami poletikeghoch new

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger