የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በአቡነ መርቆሪዎስ ወደሚመራው ሲኖዶስ ተቀላቀለ

 (የጽሁፍ ምንጭ፤ ዘሐበሻ)
የዳላሱ ርዕሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ዛሬ ባካሄደው ምርጫ መሰረት በአቡኑ መርቆሪዎስ ወደ ሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ ተቀላቀለ።
ላለፉት 21 ዓመታት በገለልተኝነት የቆየው የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ምዕመናኑ አባት ይኑረን፣ በገለልተኛነት መቆየት ይቅርብን በሚል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ዛሬ ምርጫው ተጠናቆ በተደረገው ቆጠራ;
- 140 ሰዎች በ4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ሚመራው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲጠቃለል
- 2 ሰዎች በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲጠቃለል;
- 85 ምዕመናን በገለልተኝነት እንዲቀጥል ድምጽ የሰጡ መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በአሜሪካ ከቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አብያተ ክርስቲያናት በትልቅነቱ ትልቅ የሆነውና በቀዳሚነቱም የሚጠቀሰው የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ስደተኛው ሲኖዶስን ተጠቃሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን አሜሪካ በገለልተኝነት የቆዩ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በቅርብ ቀናት በ4ኛው ፓትርያርክ ወደሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ ይጠቃለላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው
Share this article :

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger