ጉባዔ አርድእት የተሰኘ የአገልግሎት ጉባዔ በቤተክርስቲያኒቱ
እውቅና ምሁር ሠራተኞች እንደተመሰረተ ይሰማል። እንደ ደጀ ብርሃን ብሎግ እምነት በቤተክርስቲያኒቱ
ውስጥ ከጥንታዊው የጽዋ ማኅበራት ውጪ ምንም ዓይነት የተደራጀ ማኅበርም
ይሁን ጉባዔ እንዲኖር የማንፈልግ ቢሆንም እኛን የገረመንና የደነቀን
ነገር ማኅበረ ቅዱሳን እሱ ራሱ እንደማኅበር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እየነገደና እያጭበረበረ የቆየ ሆኖ ሳለ ጉባዔ አርድእት የሚባል
ስብስብ ሊደራጅ መሆኑን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ጨርቁን አስጥሎ እንዲበር ያደረገው ነገር አስገራሚ ሆኖብናል።
የጉባዔ አርድእት ህልውና እውን መሆን ማኅበረ
ቅዱሳን ያሰጋኛል ከሚል የፍርሃት፤ የጭንቀትና የቅንዓት ዓላማ ተነስቶ ጉባዔውን ቶሎ ማዳፈንና ግብዓተ ሞቱን ማፋጠን በሚል እብደት
ውስጥ መግባቱን የሚያሳየው እንቅስቃሴ ማኅበሩ በራሱ ምን ዓይነት ማኅበር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው። በአጭር ቃል ማኅበረ
ቅዱሳን እያለ ያለው በማኅበር ደረጃ ከእኔ በስተቀር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ፈጽሞ አይታሰብም፤ የኔ የመተዳደሪያ ሕገ መንግሥት
ተፎካካሪ የሚያገኘው በመቃብሬ ላይ ነው የሚል አንጀኛ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ተደራጅቻለሁ፤
የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ትውፊት አስከብራለሁ፤ ሕግና ስርዓቷን አከብራለሁ፤ ከዚህም በላይ በእግዚአብሔር እተማመናለሁ የሚል
ከሆነ የሌላ ማኅበር ወይም ጉባዔ መቋቋም ስጋት የሚሆንበት ለምንድነው?
አዎ! ድሮውንም ቢሆን ማኅበሩ አጭበርባሪ፤ አስመሳይ፤ ነጋዴና ከሳሽ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ አቻ የሚሆነውን ወይም ከሱ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ምንም ዓይነት ተቋም እንዲመሰረት ስለማይፈልግ ነው። ይህንንም ባላቋረጠ የማጥፋት እንቅስቃሴው በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
አዎ! ድሮውንም ቢሆን ማኅበሩ አጭበርባሪ፤ አስመሳይ፤ ነጋዴና ከሳሽ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ አቻ የሚሆነውን ወይም ከሱ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ምንም ዓይነት ተቋም እንዲመሰረት ስለማይፈልግ ነው። ይህንንም ባላቋረጠ የማጥፋት እንቅስቃሴው በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
የውስጥ አዋቂዎችን መረጃ በመጠቀም ዓውደ ምሕረት
ብሎግ ማኅበሩ እያደረገ ያለውን የጥፋት ዘመቻና ለዘመቻው ግብ መምታት እየተጓዘ ያለበትንም ርቀት ሁሉ በመዘገብ ለመረጃ መረብ አቅርባ ይህንኑ መረጃ እኛም ማሰራጨታችን ይታወሳል። ከወጣው መረጃ ላይ ከርእሳችን ጋር የሄደውን ቃል ከታች ለማሳያነት በጥቂቱ እናቅርብ።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ
የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ
ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ
እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ
ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ለዚሁ የጉባዔ አርድእት እግድ ለማፋጠን ደግሞ ማቅ የአቶ ተስፋዬ ውብሸትንና እስክንድር ገ/ክርስቶስን ጀርባ ለጭነት መከራየቱንና ግለሰቦቹም ለተሰጣቸው የማኅበሩ ጭነት ጀርባቸውን
ለማከራየት መስማማታቸውን ተገልጿል። ለዚሁም የበጎ ፈቃድ ተጫኝነትና ጉዳዩን
ለማስፈጸም ለሚሰማሩ ሁሉ እንደየሸክም መጠናቸው ጉርሻ የሚሆን 2 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ከነጋዴው ድርጅት በተመደበላቸው
መሰረት የሰማነው መረጃ መቼ እንደሚፈጸም ስንጠባበቅ የቆየን ሲሆን «ዓውደ
ምሕረት» ጉዳዩ ፍጻሜ ለማግኘቱ ጠቋሚው ነገር ወዲያውኑ በደጀ ሰላም ብሎግ ላይ እንደሚውልና ጽሁፉም ተዘጋጅቶ የአባ ሕዝቅኤል ፊርማ
ብቻ እንደሚጠበቅ እንዲህ ብላን ነበር።
የእግዱን ደብዳቤ በቶሎ እንዲጽፉ አቡነ ፊሊጶስና አቡነ ሕዝቅኤል እየተወተወቱ ሲሆን ደጀ ሰላምም
ዜናውን ሰርታ ጨርሳ ለመልቀቅ ደብዳቤው እየጠበቀች መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ያሉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ከተወሰነ ጳጰሳት በቀር
ለአብዛኛዎቹ ጳጳሳት በነብስ ወከፍ 50,000 ሺህ ብር ይደርሳቸዋል የተባለለት የእጅ መንሻ ብር ጳጳሳቱን አየር ዳባሽ ውሳኔ ያስወስናቸው
ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የዓውደ ምሕረትን የመረጃ ፍልፈላ አስገራሚ ያደረገው ሐምሌ
30/ 2004 ዓ/ም መረጃው ኢንተርኔት ላይ ከዋለ በኋላ ይህንኑ መረጃ ተከትሎ ደጀ ሰላም ብሎግ አስቀድሞ እንደተነገረባት የአባ ሕዝቅኤልን እግድ ደብዳቤ
ይዛ ነሐሴ 5/ 2004 ዓ/ም ብቅ ማለቷ ነበር። ዓውደ ምሕረት ብሎግ
የዚህን መሰሪ ማኅበር መረጃ ፈልፍላ በማውጣቷና መረጃውም በተጻፈው መሰረት እውን ሆኖ መታየቱን በማረጋገጣችን ልናመሰግናት እንወዳለን።
ይበል የሚያሰኝ ነው!
ውድ አንባቢያንን
ማስገንዘብ የምንፈልገው ነገር፤ እኛን የሚያሳስበን የጉባዔ አርድእት መኖር፤ አለመኖር ጉዳይ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ግን አንድ
የማይፈልገውን ሰው ወይም ማኅበር ለማጥፋት እስከ መጨረሻው የክፋት ጥግ ድረስ ከመሄድ የማይመለስ መሆኑን ከበቂ በላይ አረጋጋጭ
መሆኑን እንድትረዱልን ነው።
የሲኖዶስ ጉባዔ ሊቃረብ ሲል ብጹእ ወቅዱስ ፓትርያርኩ
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ገለጹ የሚል ዜና ይሰሩና ጉባዔው ካለፈ በኋላ ደግሞ ወደቀደመ እርግማናቸውና የማዋረድ
ተግባራቸው እንደሚመለሱ ሁሉ ደጀ ሰላም ብሎግ የጉባዔ አርድእትን እግድ ባወጣችበት ዜና ፓትርያርኩን ጥሩ አድርጋ ጎሽማለች። ድሮም
ፓትርያርኩን ለማዋረድ የማታቅማማ የማቅ የስድብ አፍ መሆኗ ቢታወቅም ያሁኑን ግን ልዩ የሚያደርገው ፓትርያርኩ ለጉባዔ አርድእት
ህልውና ተግተው የሚሰሩት እሳቸው ናቸው ከሚል ንዴትና ብስጭት የመነጨ መሆኑ ልብ ይሏል?
እንዲህ ስትል የንዴት ትንፋሿን ተንፍሳለች።
እንዲህ ስትል የንዴት ትንፋሿን ተንፍሳለች።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 5/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 11/ 2012/ READ THIS
ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት መጽናትና ለአስተዳደራዊ አንድነቷ መጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ውሳኔዎች መጠናቀቁን ተከትሎ÷ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነናዊ አሠራር ለማጠናከርና ቡድናዊ ጥቅሞቹን ለማሳካት ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ፈቃድ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ በመጥራት ኅቡእ እንቀስቃሴ ሲያካሂድ የቆየው ቡድን በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ታገደ፡፡
ደጀ ሰላም ሆይ! እኛ ከመታገዱ በፊት እግዱ በአባ ሕዝቅኤል ፊርማ እንደሚወጣና አንቺም ይህንኑ መረጃ መረብ ላይ ለማውጣት አሰፍስፈሽ እንደምትጠባበቂ ሰምተናል። አሁን ልዩ የሚያደርገው የተነገረብሽን አንቺው መመስከርሽና ማረጋገጫ መስጠትሽ ነው!!
ደጀ ሰላም ሆይ! እኛ ከመታገዱ በፊት እግዱ በአባ ሕዝቅኤል ፊርማ እንደሚወጣና አንቺም ይህንኑ መረጃ መረብ ላይ ለማውጣት አሰፍስፈሽ እንደምትጠባበቂ ሰምተናል። አሁን ልዩ የሚያደርገው የተነገረብሽን አንቺው መመስከርሽና ማረጋገጫ መስጠትሽ ነው!!
ሌላው አስገራሚው ነገር አቶ ተስፋዬና አቶ ገ/ክርስቶስ የተባሉት የማኅበሩ ሸክም የማይከብዳቸው አሳዛኝ ፍጥረቶች
ነገር ነው። በእርግጥ ጀርባውን ለጭነት አስቀድሞ ላስለመደ ሰው ጉዳዩ ባይከብደውም ኅሊና ላለው ግን ይዘገንናል። ሸክማችሁን ስናይ
እናዝንላችኋለንና እባካችሁ ሰው ሁኑ ምክራችን ነው።
ሲጠቃለል መረጃው አስቀድሞ መገኘቱና፤ የመረጃው
ፍጻሜ ደግሞ በደጀ ሰላም ላይ እንደሚወጣ መገለጹን በተግባር ሆኖ ስናየው ስለማኅበረ ቅዱሳን መሰሪነት ከምንም በላይ አረጋጋጭ ሆኖልናል።
የደጀ ሰላምንም ማንነት ግልጽ አድርጓል።
እነዚህ የጥፋት ኃይሎች ባሉበት ቤተክርስቲያን
ውስጥ ሰላም ይኖራል ብሎ ማሰብ፤ ራስ ሆድ መሆን ጀምሯል ማለት ነው።