ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላል የሀገሬ ሰው። እኔ ማርያም ነኝ የምትል ጠላት የሰለጠነባት ሴት አንድ ሰሞን ሀገር ስታምስ ሰምተን እጅግ ተገርመን ነበር። ይበልጥ ያስደነቀን ነገር የአጋንንት መጫወቻ ሆና ሳለ ፤ እኔ ማርያም ነኝ ማለቷ ሳይሆን፤ ማርያም ናት ብለው አብረው በመከተል እንባቸውን እንደጅረት የሚያፈሱ የክፉው መንፈስ አባላትን ማየት በመቻላችን ነበር። አሁን ደግሞ ኢየሱስን ወለድኩ እያለች ህጻን ልጅ አስከትላ /ሎቱ ስብሐት/ ቃለ ጽርፈትን እያስተጋባችና ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ኑና ተፈወሱ ስትል መገኘቷ ተዘግቧል።
ጣሪያውን ቀዳ እንደምትወጣ ብትናገርም ከአፍ በዘለለ ምንም ማድረግ ሳትችል ፖሊስ ቀፍድዶ ጣቢያ ሲወረውራት ማምለጥ ሳትችል ቀርታለች። ከታች ያለውን ዘገባ «ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ» ላይ ያገኘነውን ዜና አካፍለናችኋል። መልካም ንባብ!
ጣሪያውን ቀዳ እንደምትወጣ ብትናገርም ከአፍ በዘለለ ምንም ማድረግ ሳትችል ፖሊስ ቀፍድዶ ጣቢያ ሲወረውራት ማምለጥ ሳትችል ቀርታለች። ከታች ያለውን ዘገባ «ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ» ላይ ያገኘነውን ዜና አካፍለናችኋል። መልካም ንባብ!
በደብረሊባኖስ
በቁጥጥር ሥር ውላለች :: የያዘችውን ህፃን “ኢየሱስ ነው” ብላለች።
ሦስት
ልጆቼን የወለድኩት በመንፈስ ቅዱስ ነው በሚል ተከታዮች በማፍራት ለፈፀመችው የማታለል ወንጀል እና ተከታይዋ የነበረችውን ትዕግስት አበራ፣ ምንነቱ ያልታወቀ ባእድ ነገር በማጠጣት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ ተከስሳ ፍ/ቤት የቀረበችው ወ/ሮ ትዕግስት ብርሃኑ፤ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለቷ ክሷን እንድትከላከል ተወስኖ ምስክሮቿን ያሰማች ሲሆን ጥፋተኛ ነች
አይደለችም የሚለውን ለመበየን ፍ/ቤት ለነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡
ተከሳሿ
የዋስትና መብቷን አስጠብቃ ከእስር ከወጣች በኋላ ድንግል ማርያም ነኝ በማለት ሠላሳ ተከታዮቿን ይዛ ደብረሊባኖስ በመሄድ አብሮአት ያለውን አቶ ወ/ገብርኤል የተባለ ግለሰብ፤ “እሱ ገብርኤል ነው ፤ ብታምኑ ትድናላችሁ ባታምኑ ትቀሠፋላችሁ” በማለት ቅስቀሳ ስታደርግ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ወ/ሮ ትዕግስት በተጨማሪም የያዘችውን ህፃን ልጅ “እየሱስ ነው፤ ንኩት ትፈወሳላችሁ” በማለት ሁከት በመፍጠሯ፣ የአካባቢው ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላትና በደብረ ጽጌ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ ታውቋል፡፡ ተከሳሿ ማረሚያ ቤት ከገባች በኋላም “በተአምር ጣሪያ ቀድጄ እወጣለሁ፤ የሚይዘኝ የለም፤ መንፈሴ ከተቆጣ ሁላችሁም ትሞታላችሁ” እያለች በእስረኞች ላይ ሽብር እየፈጠረች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡