የግብጽ ኮፕቲክ ፓትርያርክ ታዋድሮስ 2ኛ በዓባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያናቸው የሽምግልና ሚና እንድትጫወት በመሐመድ ሞርሲ አልተጠየኩም አሉ»

 የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበራትን የብዙ ዘመናት የበላይነትና የጠነከረ ቅርርብ መሠረት አድርገው በፖፕ ታዋድሮስ 2ኛ በኩል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ግፊት ለማድረግና የግጭት መነሻ እንዳይሆን ጫና እንዲያሳድሩ በመሐመድ ሙርሲ በኩል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል የሚል ሰፊ ዘገባ ይዘው የወጡትን የግብጽ ጋዜጦች መነሻ በማድረግ የፓትርያርኩ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥቷል። አናዶሉ የተባለው የዜና ወኪልም በቀጥታ ፖፕ ታዋድሮስ ጉዳዩን ያውቁት እንደሆነ በስልክ አነጋግሮአቸው በሰጡት ምላሽ  እንደገለጹት «የግብጽ ጋዜጦች ይህንን ዜና ከየት እንዳገኙት አላውቅም፤ ለእኔ በግሌ ከፕሬዚዳንት ሞርሲ በኩል  የኢትዮጵያን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ጋር የሽምግልና ድርድር እንዳደርግ የጠየቁኝ ምንም ዓይነት ነገር የለም» በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

  የፓትርያርኩ ጽ/ቤት ለዜና ወኪሉ በተጨማሪ እንደገለጸው ጥያቄው ቢቀርብላቸው የኮፕት ቤተ ክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ለመሥራት ምንም ቅሬታ የሌላት ቢሆንም መታወቅ ያለበት ነገር ግን፤  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ መንግሥት የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣን ውስጥ ምንም ድርሻ የሌላት መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ በመግለጫው ተመልክቷል። ለግብጽና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ጥቅምና ሰላም በሚበጅ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነን፤ ይህንን በተመለከተም የኢትዮጵያው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሐምሌ 19/2013 ግብጽ በሚመጡበት ወቅት ስለግድቡ ጉዳይ እናነሳላቸዋለን በማለት ጽ/ቤቱ ያለውን ሃሳብ በተጨማሪ አስረድቷል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀድሞ በነበራት ተደማጭነት በመንግሥት ላይ የምታሳድረው ተጽእኖ ባለመኖሩ በግድቡ ጉዳይ ላይ የጎላ ሚና ይኖራታል ተብሎ አይጠበቅም ሲል በዜና ዘገባው ላይ «አናዶሉ» የዜና ወኪል ያገኘውን ማብራሪያ መነሻ አድርጎ የራሱን ትንታኔ በመስጠት ስለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የወቅቱ አቅም እስከየት ድረስ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል።
     ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደርግን የውድቀት ቀን ተጠግቶ ግንቦት 20 የመፍሰሻ አቅጣጫው መለወጡ ስለተነገረው ታላቁ ኅዳሴ ግድብ የግብጽ ሚዲያዎች የጩኸትና የጦርነት ዜማ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። የጃማአ አል ኢስላሚያ ሙፍቲ የሆኑት ሼክ አብደል አክሄር ሐማድ ለተከታዮቻቸው ባሰሙት ንግግር እንደተጠቆሙት «ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ አቅጣጫ መቀየሯ በግብጽ ሕዝብ ላይ ጦርነት እንዳወጀች ያህል ይቆጠራል» በማለት ጠጣር መልዕክት አስተላልፈዋል። «አል አረቢያ» ለተሰኘው ቴሌቪዥን ጣቢያም በቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ንግግር «የኢትዮጵያን ድርጊት የግብጽ መንግሥት በትዕግስትና በዝምታ ሊመለከተው አይገባም፤ የኢትዮጵያ ድርጊት በግብጽ ላይ የተፈጸመ የጦርነት አዋጅ ነው፤ ይህንን ድርጊት በፍጹም አንታገስም፤ በሽምግልና  ብቻ የሚፈታ ጉዳይ ስላልሆነ መብታችንን በኃይል እስከማስከበር መሄዳችን የግድ ወደሚል ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው» በማለት አቋማቸውን ለአድማጭ፤ ተመልካቹ በግልጽ ተናግረዋል። ግብጾች የሚጠብቀንን ግዴታ ሳንዘነጋ የዲፕሎማሲውን ጉዳይ ጎን ለጎን በማካሄድ ትኩረት መስጠት ይገባናል ማለታቸውም ተወስቷል።
    በሌላ በኩልም በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ወቅት የግብጽ ጦር አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሞሐመድ አሊ ቢላል እንዳስገነዘቡት ግብጽ በዓባይ ግድብ ላይ የጥቃት እርምጃ ብትወሰድ  ቀጣናውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚቀይረው ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የጋራ ጥቅም ያላት ቻይናና የግብጽ ባላንጣ የሆነችው እስራኤልን ወደጉዳዩ እንዲገቡ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግብጽ በምትወስደው  የጥቃት እርምጃ ምንም ትርፍ አታገኝም ሲሉ ለአል አረቢያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ የረቡዕ 30/ 5/2013 ዕለት ስርጭት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
      የሰሞኑ የግብጽ ሚዲያዎች እያራገቡ የሚገኙበትን ዘገባ ስንቃኝ  ጦር፤ ጦር የሚሸት መንፈስን ባዘለ መልኩ መሆኑ  ምናልባትም አንዳንዶቹ ለኢትዮጵያ ባላቸው ዝቅተኛ ግምትና  ለራሳቸው ጥቅም አብልጦ የማሰብ ራስ ወዳድነት ሲሆን አንዳንዶቹም በከፍተኛ ፖለቲከኞች በኩል ሆን ተብሎ በማስፈራሪያ ሰበብ  የሚሰራጭና የግብጽ እርምጃ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ለኢትዮጵያ መንግሥት መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። 
በዚህም ተባለ በዚያ «አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ያደርጋል ድስትን ጥዶ ማልቀስ» እንዳይሆን  አንዴ የገቡበትን ሥራ ቀድሞ ባልጀመርነው ኖሮ ከማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከዲፕሎማሲው ጎን ለጎን ራሱን ማዘጋጀት ይገባዋል እንላለን። መንግሥት ልቡን ሰፊና እጁን ረጅም አድርጎ በፖለቲካ ያኮረፉትን በመጥራት በሀገር የጋራ ጉዳይ ላይ ማግባባት ወደሚችል የግል ሁኔታ ለመግባት የመድብለ ፓርቲውን ሥርዓት በር ከፈት ማድረግ አለበት።  እንደኢትዮጵያ ባለና ውጥንቅጡ በወጣ አመለካከት ውስጥ ልማት ብቻውን ሀገር አይገነባም። አሸባሪ የተባለ ማንም ተነስቶ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ቢል አያስገርምም። ባራቅነውና በረገምነው ቁጥር መራቁ ባህሪያዊ ነውና። አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን በልማት ዜማ የማዳፈን ጉዳይ አኩራፊ ማበራከቱና ለጠላት በር መክፈቱ አይቀሬ ይሆናል። ግብጾች ራሳቸው መሥራት ያልቻሉትን የውጪ ሥራ በሌሎች እጅ ከማሰራት ይመለሳሉ ማለት የዋህነት ነው። 
ዓለማችን በአየር ለውጥ የተነሳ ሙቀቷ እየጨመረና በረሃማነትም እየተስፋፋ እንደመሄዱ መጠን አንድ ዓባይን ብቻ በተስፋ የምትጠብቅ ግብጽ በሆነ አጋጣሚ አንድ ክረምት ዝናብ በበቂ ባይጥልና ወንዙ ጎድሎ በትነት መጠኑን ከቀድሞው ቢቀንስባት ወደአጥፍቶ መጥፋት አትገባም ማለት አይቻልም። ረጅም እሳቤ ያለው እቅድ ለዓባይ የዛሬው ግድብ አስፈላጊው ነው እንላለን። 
እንዲያውም ስለዓባይ የተነገረው  የግብጽ ሸክም የሚራገፍበት ዘመን ደርሶም ይሆን? የሚል የትንቢት ጥያቄም እናነሳለን።
«ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።  በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም። ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ» 
ኢሳ 19፤ 4-8
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 4 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
May 31, 2013 at 6:44 PM

…አገሬዓርማነውየነጻነትዋንጫ
በቀይየተጌጠባረንጓዴብጫ።
እሾህነውአገሬ፣
በጀግናውልጅአጥንትየተከሰከሰ
ጠላትያሳፈረአጥቂንየመለሰ።
... አገሬታቦትነውመቅደስየሃይማኖት
ዘመንየፈተነውበጠበልበጸሎት።
ለምለምነውአገሬ፣
ውበትነውአገሬ፣
ገነትነውአገሬ።
… ብሞትእሄዳለሁከመሬትብገባ
እዚያነውአፈሩየማማያባባ።
ስሳብእሔዳለሁቢሰበርምእግሬ
አለብኝቀጠሮከትውልድአገሬ።
አለብኝቀጠሮ
ከትውልድአገሬካሳደገኝጓሮ…፡፡
~ገብረክርስቶስደስታ፡፡

Anonymous
May 31, 2013 at 7:19 PM

The disturbing thing is the Islamist regime continues getting big loans and U.S. military aid. With Egypt threatening Nile riparian countries like Ethiopia, things would even go worse. The ignorant world remains indifferent; the hypocritical, despicable main stream mediais usually determined to be “even-handed” or to ignore the extent of the situation, preferring to seek alleged abuses and human rights violations in other, near-by countries like Ethiopia. In the coming days, they will start perpetuating a massive fraud, talking trash, spewing venomous lies and leveling false accusations towards Ethiopia, concerning the construction of the Renaissance Dam.

History about to repeat itself?

In the historically crucial years of 1875 – 1876, Khedive Ismail of Egypt invaded Ethiopia without much success. This was the time when Egypt was suffering because of food shortage after the annual Nile River flood failed. Economic crisis hits Egypt, its total foreign debt came to £94,000,000. Seriously concerned with the country’s financial situation, Ismail asked for British help in fiscal reform. Britain responded by sending Steven Cave, a member of Parliament, to investigate. Cave judged Egypt to be solvent on the basis of its resources and said that all the country needed to get back on its feet was time and the proper servicing of the debts. Cave recommended the establishment of a control commission over Egypt’s finances to approve all future loans. A year earlier, Khedive Ismail sold 176,000 Suez Canal shares to the British government

In order to divert attention from Egypt’s state of confusion and disorderliness, Europe and America encouraged Egypt to invade Ethiopia – by arming the Muslim Khedive Ismael’s army and sending mercenaries alongside the Egyptian army to fight against the Orthodox Christian country of Ethiopia. But, Ismael’s Egyptian forces were again defeated by Emperor Yohannes IV of Ethiopia. The battle at Gura involved 12,000 well-equipped Egyptians, hundreds of European, almost fifty American, and several Ottoman mercenary officers. Of the 6,000 Egyptians that took part in the battle, 4,000 were either killed, wounded or captured (and then killed).

The humiliating defeat of Egypt and its allies followed by their cowardice murder of Ethiopian leaders like Emperor Yohannes. This hatred, of course, was driven by a shame-based Muslim culture that is deeply humiliated by Arab weakness and Ethiopian strength. During the Crimean War, troops from the same Egyptian army fought admirably in southern Russia (Orthodox Christian State) and a decade later, also performed well fighting in the army of Napoleon III in Mexico. Yet, this same army suffered disastrous defeats in the 1870s during Western-powered campaigns in Ethiopia. Losing a war is a traumatic experience for any country, and it often leads to an internal revolution and scapegoating.

In 1876, Egypt was punished not only by the Ethiopian army, but also by mother nature. In the next consecutive years Egypt was repeatedly struck by food shortage because the annual Nile River flood failed. In 1878, England and France gain cabinet seats and control over Egyptian finances. The food shortage, the whole chaos and military fiasco eventually lead later to the British occupation of Egypt.ewnet new deje brhan«ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ። በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም። ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ»
ኢሳ 19፤ 4-8

Anonymous
May 31, 2013 at 7:23 PM

Over the past couple of years everyone has become curious to know why the Western World go over to ally with those forces who later become their own enemies. US defense minister, Hagel was recently in Egypt to try and preserve military ties with the Muslim Brotherhood-led gov’t U.S.-Ethiopian relations were established in 1903

U.S.-Egyptian relations were established in 1922

Ethiopia and Ethiopians never been hostile to Western nations

Egypt’s Muslim brotherhood is the root source of Islamic terrorism

Anonymous
June 4, 2013 at 9:15 AM

it is not related with the above..but...የኢትዮጵያውያን የ15ኛው ክፍለ ዘመን ገዳማት በሊባኖስ ተገኙ

የጽሑፍ መጠን ኢሜይል DISQUS_COMMENTS
шаблоны RocketTheme
Форум вебмастеров

• በዋሻው የተገኙት የግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ማረጋገጫ ሆነዋል

ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በ15ኛው ክፍለ ዘመን በሊባኖስ ቀዲሻ ሸለቆ (Holy Valley) ይገለገሉባቸው የነበሩ አራት ገዳማት ከግእዝ ጽሑፍና ሥዕሎች ጋር ተገኙ፡፡

ኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲና ካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ ባዘጋጁት የግእዝና የሱርስጥ (የሶርያ ቋንቋ) ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት አብዶ በድዊ፣ በገዳማቱ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ጽሑፍና የቅዱሳንና የመስቀል ሥዕሎች መገኘታቸው ገዳማቱ የኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ያሳያሉ ብለዋል፡፡

‹‹አሕባሽ›› የሚል መጠርያ የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን መነኮሳት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንና በ15ኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ሊባኖስ ተራራዎች በተለያዩ አጥቢያዎች የኖሩ ናቸው፡፡ ገዳማቱም ማር ያዕቆብ በኢሕደን (Ehden)፣ ማር ጊዮርጊስ በሐድቺት (Hadchite)፣ ዴር ኤል ፍራዲስ እና ማር አስያ ናቸው፡፡

ጂኢአርኤስኤል የተሰኘ የጥናት ቡድን እ.ኤ.አ በ1991 የግእዝ የድንጋይ ላይ ጽሑፍና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥዕሎች ማግኘቱን ሊባኖሳዊው አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡

መነኮሳቱ በደብረ ሊባኖስ እንዴት ሊገኙ እንደቻሉ የተለያዩ መላምቶች እንዳሉ ያወሱት አጥኚው፣ አንዱ በእምነት የሚመስሏቸውን የግብፅ ኮፕቲኮችን የወንጌል መልዕክተኛነትን ለማገዝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

መነኮሳቱ ሊባኖስ ተራራ (ደብረ ሊባኖስ) የደረሱት በ1470 እና 1488 መካከል መሆኑን በሥፍራው የነበሩትን የማሮናይት እምነት ተከታዮችን በስብከታቸው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መለወጣቸው ይነገራል፡፡ ከነዚህም አንዱ በኋላ ላይ የያዕቆባውያን ፓትርያርክ የሆኑት የብቆፋው ኖኅ (Nouh of Bqoufa) ይገኙበታል፡፡

በአካባቢው አጠራር ኢትዮጵያውያንን ለመጥራት በሚጠቀሙበት አሕባሽ የሚጠሩት ኢትዮጵያውያን በ15ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከደረሰባቸው ጥቃት የሸሹ ደቂቀ እስጢፋኖስ መሆናቸውን ተመራማሪዎች እንደደረሱበት አብዶ በድዊ ተናግረዋል፡፡

‹‹በርካቶች እንደሚያምኑት፣ ከነዚህም መካከል ኢቫ ዊታኮውስኪ (Eva Witakowsky) እንደሚሉት መነኮሳቱ @@@@ደቂቀ እስጢፋኖስ@@@@ ናቸው፡፡ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ወገኖቻቸው ከደረሰባቸው ፍጅት አምልጠው ኢየሩሳሌም፣ ቆጵሮስ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያና አርመን ድረስም የተሰደዱ ናቸው፡፡ ሊባኖስ እንደደረሱ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል በተለያዩ አጥቢያዎች ቀዲሻ (ቅዱስ) ብለው በሰየሙት ቦታ መኖር ጀምረዋል፡፡››

የግድግዳ ላይ ሥዕሎችና የግእዝ ጽሑፍ ከሱርስት ቋንቋ ጽሑፍ ጋር የተገኙት በማር አስያ፣ ማር ጊዮርጊስና ማር ዮሃና ገዳማት መሆኑን ያወሱት አቅራቢው፣ ከተገኙት ሥዕሎች አንዱ የፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል ላሊበላ ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ካለው ጋር ይመሳሰላል ብለዋል፡፡ በማር ሙሳ አልሐበሺ ያለውም ጋይንት ቤተልሔም (ደቡብ ጎንደር) ካለው ጋር ተመሳስሎ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡

የግእዝ ጽሑፉ ከፊሉ የጠፋ ሲሆን፣ ያሉትን የግእዝ ቃላት የቋንቋው ፕሮፌሰሮች ባደረጉት ጥናት ኃይለ ቃሉ ጸሎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹መሐረነ እስከ ለዓለመ ዓለም አሜን›› (ለዓለም እስከ ዘለዓለም ማረን አሜን) ይላል፡፡

በጉዳዩ ላይ ቀጣይ ጥናት እንደሚደረግበትም አብዶ በድዊ ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

አስኮ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካዊ የምርምርና የሥልጠና ማዕከል ከግንቦት 19-22፤ 2005 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው የግእዝና የሱርስጥ ጥናቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ከኢትዮጵያ ሌላ ከሩቅ ምሥራቅ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የመጡ ምሁራን 25 ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger