Showing posts with label መረጃ. Show all posts
Showing posts with label መረጃ. Show all posts

Monday, April 6, 2015

አስነዋሪው የአሸናፊ መኮንን ንስሐ አልቦ ተግባር

(ሲሳይ ንዳው ለድሬ ቲዩብ ከላከው የደረሰን መረጃ)

ግብረ-ሰዶማዊው ዲያቆን

ቅዱሳት መጽሐፍትን ስንመለከት የእምነት አባቶችን የሕይወት አደራ ያላንዳች ሽፋን፤ ድክመታቸውንም ይሁን ብርታታቸውን እየገለጡ፤ ምስክርነታቸውን ለእኛ አስቀርተው ያስተምሩናል፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍት ስለ አብርሃም ሲዘግቡ፡- ልጁ ይስሐቅን በእምነት በእግዚአብሔር ፊት ይሰዋ ዘንድ እስከ መጨረሻው ደቂቃ የታመነ ‹‹የእምነት ሰው›› መሆኑን ብቻ አስረድተው አላለፉም፤ ይልቁንም የተስፋው ቃል የዘገየ የመሰለው አብርሃም ከእግዚአብሔር ፈቃድ አፈንግጦ ከሚስቱ ሳራ ውጭ ከአጋር ጋር ተኝቶ ‹‹እስማኤልን›› እንደወለደ አስፍረውልናል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ምን ያህል የእምነት ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ‹‹እንደ ልቤ›› ቢባልም፣ የወዳጁን ሚስት በመድፈሩ የወደቀውን ታላቅ አወዳደቅ ሳይደብቁ መጽሐፍቱ ዘግበውልናል፡፡ ከዚህም የተነሳ የእምነት አባቶቻችንን ብርታትና ድካም ተመልክተን ለሕይወታችን የሚበጀውን ትምህርት እንድንቀስምና ምንም ነውርና ነቀፋ የሌለውን ኢየሱስን ግን በማየት ከፊታችን ያለውን ሩጫ እንድንሮጥ፤የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ እንዲህ ሲል አመለከተን፡- ‹‹እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።›› ዕብ 12፡-1-2፡፡

   ዛሬም በእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ ስር ተጠልሎ፤ ‹‹የግብረ-ሰዶማዊነቱን›› ጥም እየቆረጠ ስላለው ‹‹ዲያቆን አሸናፊ መኮነን›› ማንነት በአደባባይ ለሕዝብ ሁሉ መግለጥ ምን ያህል ተገቢ ነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሳምንታት የፈጀ ሙግት ከራሴ ጋር አድርጌያለሁ። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሥራ እሰራለሁ እያለ የኃጢአትን ኑሮን እያቀላጠፈ ያለን አጭበርባሪ ማንነት መግለጽ ለክርስቲያኖች ጥቅም ሲባል አስፈላጊነቱን አምኜበታለሁ። የዲያቆን አሸናፊ መኮነን ግብረ-ሰዶማዊነት በተመለከተ ‹‹ይህ መልዕክት››ለሕዝቡ ሁሉ እንዲሰራጭ የፈለኩበት ምክንያት ምን እንደሆነ በግልጽ በማስረዳት፤ የዲያቆኑን ማንነት በማስረጃዎች መግለጥ እጀምራለሁ፡-

1ኛ/ የወንድም የእህቶችን ምክር አልሰማም በማለት ይሄን ዘግናኝ ዓመጻ በገዛ ሰውነቱ ላይ ሾሞ በመቀጠሉ፤
2ኛ/ ሰዶማዊ መሆኑን ‹‹በአዞ እንባም›› ቢሆን ካመነ በኋላ፣ በምን ተፍረት ዳግም ተመልሶ‹‹በአንድ አፍ ሁለት ምላስ›› እንዲሉ አበው ‹‹እኔ ግብረ-ሰዶማዊ አይደለሁም›› ሲል በመዋሸቱ፤
3ኛ/ ሰዶማዊው ዲያቆን እድሉን ተጠቅሞ ንስሐ ከመግባት ይልቅ ወደ ልቡ ይመሰለስ ዘንድ የሚመክሩ ሰዎችን ‹‹በቅናት ተነሳስተውብኝ እንጂ እኔስ ግብረ-ሰዶማዊ አይደለሁም በሐሰት ስሜን እያጠፉብኝ ነው›› ሲል በመክሰሱ፤
4ኛ/ ሰዶማዊው ዲያቆን አሸናፊ መኮነን በእግዚአብሔር ቃል ተከልሎ ነውሩን በማስፋፋት ሥራ ላይ በመጠመዱ፤
5ኛ/ አበው ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› እንዲሉ የእነዚህ የግብረ-ሰዶማውያን ዓመጻ ሥር ሰዶ፤ ወደፊት ሐገርን ጎድቶ ትውልዱን ሳያበላሽ ከአሁኑ በእንጭጩ ሳለ ‹‹እርቃኑን በአደባባይ ገልጦ ማሳየቱ›› እጅግ መልካም በመሆኑ፤
6ኛ/ ስለ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን ግብረ-ሰዶማዊነት የተሳሳተ መረጃ ላላቸውና በአንድም በሌላመንገድ ከእርሱ የዓመጻ ግብር ሥር ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች ግልጽ ማስረጃ ለመስጠትና እራሳቸውን ከኃጢአትም ከወንጀልም እንዲለዩለመምከር፤
7ኛ/ ግብረ-ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ ህግ የተወገዘና በወንጀለኞች የመቅጫ ሕግ መሰረት ከፍተኛ ቅጣት ከሚያሰጡ አደገኛ ወንጀሎች መካከል አንዱ መሆኑን ተከትሎ፡- ይሄን ጉድ ደጋግሞ ለወገን ራሱን እንዲጠብቅ ማሳወቁ ሐገራ ዊግዴታዬ መሆኑን በማስተዋል የዲያቆን አሸናፊ መኮነንን ግብረ-ሰዶማዊነት በማስረጃዎች ለመግለጥ ተገደናል፡፡
10ኛ/ ግብረ-ሰዶማዊነት በእግዚአብሔር ቃል በከፍተኛ ደረጃ ኃጢአትነት የተፈረጀ በመሆኑ

ግብረሰዶማዊነት ምንም አይነት ማመቻመች ሳይደረግበት የተወገዘና እንዲያውም የአእምሮ መለወጥ ወይም የተፈጠረበትን ዓላማ መሳት ውጤትመሆኑ ስለተገለጸ የዲያቆን አሸናፊ መኮነንን ‹‹የግብረ-ሰዶማዊነት ቅሌት›› በማስረጃነት እያወጣን የምንገልጥበት ምንጫችን፡- እርሱ በሥራ አስኪያጅነት የሚመራበት‹‹የቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎትን›› የመሰረቱት አባላት ባለባቸው ኃላፊነትና ግዴታ መሰረት ማሕበሩን የለቀቁበት ጉዳይምን እንደሆነ ‹‹ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ለሐይማኖት ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት በቀን 28/11/2006 ዓመተ ምህረት ያስገቡትን ባለ አራት ገጽ የስንብት ደብዳቤን›› እየጠቀስን የምናወጣ በመሆኑ፤ የነገሩን ሐቀኝነት ልብ ይሏል፡፡
በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስተር በፋይል ቁጥር 0096 በሕዳር 16 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት በወጣው የወንጌል አገልግሎት ፈቃድ መሰረት የተቋቋመው ‹‹ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት›› ዋና ዓላማው ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ በመመስከር ላይ ያጠነጠነ ቢሆንም፤ እነዚህ በቁጥር ስድስት የሆኑት የድርጅቱ መስራቾች ማህበሩን በይፋ የለቀቁበት ምክንያት፡- በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ አጸያፊ በሆነው ዓመጻ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን ግብረ ሰዶማዊ በመሆኑ ነበር (በደብዳቤው ገጽ 2፤ አንቀጽ 5 ላይ ይመለከቷል)፡፡
በመጀመርያ የዲያቆኑን ሰዶማዊነት ከስድስት ወራት በፊት በወሬ ደረጃ የሰሙት የወንጌል አገልግሎቱ መስራቾች፤ እየዋለ ሲያድር የወሬው ነገር ስር መስደዱናብሎም በኢንትርኔት በልዩ ልዩ ማስረጃዎች ዜናው መታወጁን ተከትሎ ስለተፈጠረባቸው ድንጋጤ እንዲህ ሲሉ በደብዳቤያቸው ሰይመውታል፡-‹‹ከሁለት ወር በፊት ወዲህ ግን ይህ ነገር ከወሬነት አልፎ ተጨባጭ ማስረጃዎች ሲገኝበት፤ ነገሩ ፈጠረብን ድንጋጤ በወቅቱ ይህንእውነት ለሰማንና ላረጋገጥን ወንድሞችና እህቶች ከቁጥጥራችን በላይ ሆኖብን ነበር፡፡›› በድብዳቤያቸው ገጽ 2 አንቀጽ 4 ያገኙታል፡፡በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደምብ መግቢያ ቁጥር 3 ላይ፡- ‹‹የወንጌልን አገልግሎት በመስጠት፣ የክርስቶስ ምሳሌ በመሆን መንግስትና ሕዝባችን የሚጠበቅብንን የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት›› የሚለውን መሰረታዊ ሐሳብ በመጻረር ዲያቆን አሸናፊ መኮነን ነውረኛ የሶዶማዊነቱንጥም ይቆርጥ ዘንድ የጥቃት ሙከራ ያደረሰባቸው የማህበሩ ሰዎች እንዳሉ በደብዳቤው ገጽ 2፤ አንቀጽ 5 ላይ እንዲህ ሰፍሯል፡-‹‹ነገሩ ምንም አስቸጋሪ ቢሆንም እንደ መንፈሳዊ ሰው ተረጋግተን፤ ለማየት በመሞከር በተናጠል ምስክርነቶቻቸውን ከሰጡን የተወሰኑየግብረ ሰዶም ጥቃት ሙከራ ከደረሰባቸው ጋር እና ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር በመሆን በአጠቃላይ አስራ አንድ ሰዎች ያሉበትስብሰባ ተቀመጥን ...›› ማለቱን ይመለከቷል፡፡ አስራ አንድ (11) በመሆን ስብሰባውን ካደረጉ በኋላ፡- በተፈጠረው ጉዳይ ላይእንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል አንዱ የአንዱን ሸክም መሸከም አለበትና ስለ ወንድም አሸናፊ መኮነን ‹‹ግበረ-ሰዶማዊነት›› በትጋት በእግዚአብሄርፊት አስቀድሞ መጸለይ እንዳለበት በማመንና በመጨረሻም ዲያቆን አሸናፊን በአካል ለመነጋገር ይወሰናል፡፡

በመጀመሪያ አካባቢ ነገሩ የሚፈለገውን ውጤት ይዞ እየሄደ እንደነበር የሚገልጸው ደብዳቤው ዲያቆኑ ሰዶማዊ መሆኑን በማመኑ ለንስሐም ራሱን ዝግጁ በማድረጉንስሃ እንዲገባና እና አንዲመለስ ጥረት ከማድረግ ባለፈ የተፈጠረ ነገር አልነበረም። ‹‹ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ለሐይማኖት ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት›› የገባው ደብዳቤ ዲያቆን አሸናፊ ግብረ-ሰዶማዊ መሆኑን እንዳመነ እንዲህ ሲል አስምሮበታል፡- ‹‹አንድ ወንድም በደረሰውመረጃ መሰረት አጣርቶ ባገኛቸው መረጃዎች ተመርኩዞ፤ ዲያቆን አሸናፊን አነጋግሮታል፤ ዲያቆኑም ድርጊቱን መፈጸሙንና መጸጸቱን ገልጾነበር፡፡ ዲያቆን አሸናፊ በዚሁ ዕለት ጉዳዩን ለሚያውቁ ወንድሞች የይቅርታ መልዕክት በሞባይላቸው ልኳል፡፡ አንዳንዶችንም በአካልጠርቶ ይቅርታ ተይቋል፡፡›› በማለት በገጽ 2፤ አንቀጽ 5 ላይ ይናገራል፡፡ በዲያቆን አሸናፊ መኮነን በግዳጅ የግብረ-ሰዶም ጥቃትሙከራ ያደረሰባቸው ወንድሞች የእርሱን የይቅርታ መልእክት ስለሰሙ በአካል ‹‹ይቅርታውን›› ሊያደምጡ በነጋታው ቀጠሮ በስልክ ተነጋግረውቢይዙም፤ አሸናፊ ግን ወደ ክፍለ ሐገር እንደሄደ በስልክ ሜሴጅ አሳውቋቸው ሳያገኙት ይቀራሉ፡፡ በእዚህ ድርጊቱ ልባቸው ያዘንባቸውናሌሎች የጥቃቱ ሙከራ ያልደረሰባቸውን ወገኖች በመጨመር ‹‹የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ›› የሆነውን ወንድም የሽጥላ ብርሃኑን ቢሮ ድረስበመሄድ ‹‹ዲያቆን አሸናፊ መኮነን በግዳጅ ላደረሰባቸው ግብረ-ሰዶማዊ የጥቃት ሙከራ›› ሊያናግሩት እንደሚፈልጉ በጽኑ አስረድተውትይለያያሉ፡፡ ይህ ከሆነ በኃላ የተፈጠረውን ሁናቴ ደብዳቤው እንዲህ ሲል ይተርካል፡- ‹‹አነጋግረውት ከወጡ በኃላ (ወንድም የሽጥላን)በግምት በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ዲያቆን አሸናፊ እራሱ ደውሎ ‹‹ያለሁበት ቦታ ኑ›› በማለቱ በወቅቱ ሦስት ሙከራው የተደረገባቸውና ሌሎች ሦስት ወንድሞች በአንድነትሆነው ዲያቆን አሸናፊ ወዳለበት ሄደው በጉዳዩ ላይ ተነጋግረው፤ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን ያደረገውን ድርጊት በማመኑ እና እግራቸውላይ ወድቆ ‹‹ማሩኝ›› በማለቱ፤ ንስሃ እንዲገባ እና የንስሃን ፍሬ እንዲያሳይ ተነጋግረውበቀጣይ ለመገናኘት ተስማምተው ይለያያሉ፡፡ ከእነዚህ ለምስክርነት ከተገኙ ወንድሞች መካከል አንዱ የጠቅላላ ጉባኤ መስራች አባልየሆነ ወንድም ነው፡፡›› ገጽ 3 አንቀጽ 1 ላይ ሰፍሯል፡፡

እንግዲህ ካላይእንዳየነው ‹‹በቀን 28/11/2006ዓ/ም ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት መስራች አባላት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ለሐይማኖትጉዳዮች ዳይሮክቶሬት›› ባስገቡት ባለ አራት ገጽ የስንበት ደብዳቤ ላይ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን ግብረ-ሰዶማዊ መሆኑን፣ በዚህምግብረ-ሰዶማዊነቱ ሳያበቃ በተለያዩ ወንድሞች ላይ አስገድዶ የግብረ-ሰዶም ጥቃት ማድረሱን፣ ይህም ድርጊቱ ሲወራ ቢቆይም እየዋለሲያድር ግን አስደንጋጭ ማስረጃዎች እንደተገኙበት፣ በግልጽም ስለ ግብረ-ሰዶማዊነቱ በማስረጃዎች ጥያቄ እንደቀረበለት እርሱም ግብረ-ሰዶማዊመሆኑ፣ በዚህም ጥማቱ ተነሳስቶ ጥቃት ለማድረስ በጽዎታ እሱን መሰል በሆኑ ወገኖች ላይ ሙከራ እንዳደረገ በጸጸት ማመኑንና እንዲሁምማሩኝ ሲል እንደተማጸናቸው፤ ይሄንንም ነገር ላወቁ ወንድሞች በአካልም በስልክም ይቅርታውን እንዳቀረበ ይናገራል፡፡ ታዲያ ይህ መሆኑባልከፋ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን እጅግ አጸያፊ ዓመጻ ሥር መሆኑን አምኖ ወደ ንስሃ ገብቶ ይመለሳል፣ የንስሃንም ፍሬ አሳይቶ ሕይወቱንበእግዚአብሔር እጅ ያኖራል ተብሎ ሲጠበቅ፤ እርሱ ግን ባልተጠበቀው መንገድ ‹‹ሥም የማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል›› እያለ የሞትሽረቱን ግብረ-ሰዶማዊነቱን ለመደበቅ ማስወራት ጀመረ፡፡ በዚህም የሞኛ ሞኝ ሥራው ያታለላቸውን ሰዎች በመሰብሰብ ‹‹እኔ ግብረ-ሰዶማዊአይደለሁም ነገር ግን የእኔን ስም ለማጥፋት ተብሎ ነው የሚወራብኝ›› ማለቱን ተያያዘው፡፡ ይህን ነገሩን ሰምተው የተታለሉና በአንድምበሌላ መንገድ በጥቅማጥቅም ከተሳሰሩት ሰዎች ጋር በጥምረት ‹‹የአይደለሁም›› ትግሉን አሁንም ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ታዲያ ግን! ዲያቆንአሸናፊን ምን ነካው? የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- ‹‹ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።›› ምሳ 28፡-13፡፡ ወንድም አሸናፊ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ በአጸያፊ ርኩሰትና ዓመጻ ሥር መሆኑ ሳያንሰው፤ ኃጢአቱን ለመደበቅ የገዛ አዕምሮውን አስቶ ‹‹ንስሃ ግባወደ እግዚአብሔርም ተመለስ ሲሉ በጾም በጸሎት የተጉለትን›› ወንድም እህቶቹን ስሜን ለማጥፋት ነው ሲል መደመጡ፤ በርግጥም ምንያህል በርኩሳን መናፍስት ጥላ ስር ስለማደሩ ምስክር ነው፡፡ ዲያቆን አሸናፊ አሁንም ቢሆን ‹‹ኃጢአቱን አምኖ በንስሃ ወደ እግዚአብሔርመመለስ፣ ፍሬንም አፍርቶ መገኘት እንጂ፤ ኃጢአቱን መሰወር የለበትም፤ ይህ ካልሆነ ግን የእግዚአብሄር ቃል ‹‹‹‹ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።›› እንደሚል ፍሬ የሌለበት ተክል፣ ውሃ የሌለበት ደመና ሆኖ ሞቱን ይጠብቃልና፡፡ በባህላችንም ይሁን በሕግበተለይም በእግዚአብሔር ቃል እጅግ የተወገዘውን ርኩሰት ተሸክሞ ግብዝ ሆኖ በመንፈሳዊ ሽፋን ተሸፋፍኖ እራስን ሲያስቱ መኖር፤ ብርሃንየበራለት ሰው ሕይወት ሳይሆን ያልዳነ ሰው ማንነትና መለያ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ እንዲሲል ገለጠው፡-‹‹ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙትአጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።›› በማለት የእግዚአሔርን ፍቅር፣ አባትነት፣ ሁሉን ቻይነት፣ ምህረት ርህራሄውን እያወቁ ነገር ግን ያወቁትን እግዚአብሔርን እንደሚገባው የማያመልኩትና የማያመሰግኑት ሰዎች፣ ምን ያህል በአስተሳሰባቸው ከንቱና በልባቸውም ጨለማ መሆናቸውንይናገራል ሮሜ1፡-20-21፡፡ ዛሬም በወንድም አሸናፊ የምናው እግዚአብሔርን አውቃለሁ ብሎ የወንድ ዳሌና ሽንጥ ሲናፍቅ መኖሩ በአሳቡከንቱ በልቡም ጨለማ የመላ መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔርን እያወቁት እንደ እግዚአሔርነቱ መጠን ስላላከበሩት ሰዎችሲናገር በመጨረሻ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስላገኛቸው ርግማን እንዲህ ሲል ገለጠው፡- ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔርለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውምለባሕርያቸው የሚገባውንሥራ ለባሕርያቸው በማይገባውለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውንሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸውተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔርየማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡›› ሮሜ 1፡-26-28፡፡ እንግዲህበአሸናፊም ያየነው ይሄኑ ቃል ነው፡፡ እግዚአብሔርን አውቃለሁ፣ ክርስቶስን እሰብካለሁ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል፣እያለ በግብዝነት በዓመጻ እየኖረ በሕያው አምላክ በእግዚአሔር ላይ ሲዘባበት ለክፉ አዕምሮ ምኞት ተላልፎ ተጣለ፡፡

ወንድ ድመት ከወንድ ድመት ጋር አብሮ ዕለት ዕለት ሲሴስን ያየ ሰው አለን? ሴት ላም ከሴት ባልንጀራዋ ላም ጋር አብራ ስትዳራ በግልሙትናም ስትባዝን የሰማ አለን? ወይስ ወንድ አንበሳ ከወንድ የአንበሳ ደቦል ጋር በፍቅር ተሳስሮ ሲሴስን የተመለከተ አለን? ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ መስጠት፤ አዕምሮ እያለው የእንስሳ እንስሳ መሆን ማለት እንዲህ ነው፡፡ መጽሐፍ እንደሚል፡- ‹‹ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።›› መዝሙር 49፡-12፡፡ ዲያቆን አሸናፊ መኮነን እነሆ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነቱከእንስሳ ብሶ አዕምሮ ያለው ግና የእንስሳ እንስሳ ሲሆን የወንድ ዳሌና ሽንጥ ናፋቂ፣ እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ ዓለም የዘረጋውንስርዓተ-ተዋልዶን ስቶ ይገኛል፡፡ አሁንም ቢሆን በንስሃ መውደቅ ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንጂ ከዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያወጣ ዘንድ በእውነት ፍጹም ብቃት አለው፡- ‹‹የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።›› 1ዮሐ 1-7፡፡ ከኃጢአት ‹‹ሁሉ›› ያነጻን ዘንድ የታመነ ጻድቃችንነውና አምላካችን፡፡
በአንድም በሌላ መንገድ የዲያቆን አሸናፊ መኮነንን ግብረ-ሰዶማዊነት አምናችሁም ይሁንሳታውቁ አብራችሁት ላላችሁ ወገኖች፤ እነሆ በእግዚአብሔር ቃል እንጂ አንዳች በስንፈት ቃላት ወደ እናንተ አንመጣምና አድምጡን?በጌታችንንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሕዝብ በእውነትይሄን ጉድ ምን የሚል ይመስላችኋል? አዕምሮአቸው የሳተባቸው ጥቁሩን ነጭ፣ ብርሃኑን ጨለማ፣ የሚሉ የአሮጌው ሰው ወኪሎችን አያስተውልምን?ለገንዘብና ለሆዳቸው ሲሉ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን የመረጡ ዓይን እያላቸው የማያዩ ታላላቅ ዕውራንን አይመለከትምን? እንግዲህ እናንተ ከማን ወገን ናችሁ? ከእግዚአብሔር ወይስ ከዲያብሎስ? ሕብረታችሁ ማንን ገለጠ? በቃለ እግዚአብሔር ላይ ልባቸውን አስገዝተው አንዳች እንኳ ከቃሉ ፈቀቅ ለማይሉና ለማያመቻምቹ እንዲህ እንላለን፡- አዕምሮው የሳተበት ግብረ-ሰዶማዊን ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ በሉት እንጂ ከእርሱ ጋር አንዳች እንኳ አትተባበሩ!! የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- ‹‹በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም ፈቀቅ በል ተዋትም። ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ካላሰናከሉም እንቅልፋቸውይወገዳልና። የኃጢአትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።›› ምሳሌ 4፡-14-17፡፡ በመሆኑምትውልድ የማይረሳው የታሪክ ስህተትን ፈጽማችሁ የታሪክ ተወቃሽ ሆናችሁ ከምታልፉ አሁኑኑ ወደ ልባችሁ ተመለሱ!!
በመጨረሻምበዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሳዊ መንግስታችን የምናስተላልፈው፡- ‹‹በቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት ድርጅትውስጥ በግብረ-ሰዶማዊነት ወንጀል፤ በዲያቆን አሸናፊ መኮነን ስለሚሰራው ዓመጻ አስፈላጊውን የማጣራትና የመመርመር ስራ ተካሂዶ ተገቢውንሕጋዊ እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ነው›› መልዕክታችን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፡፡›› እንደሚል በተጨማሪ ማስረጃዎች እመለሳለሁ ኤፌሶን 5፡-11!!
እግዚአብሔር የሰዶማዊውን አሸናፊ መኮንን ልብ ይመልስልን!!

Tuesday, March 24, 2015

ቤተ ክርስቲያን ግን እያሽቆለቆለች፤ አስተዳደሯ እየሞተ ነው። እየገደላት ያለው ማነው?


  በቤተ ክርስቲያን ድክመትና የቁልቁሊት ጉዞ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ከውስጥ የሚነሳው ሽኩቻ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ከኬልቄዶን ጉባዔ አንስቶ በየዘመናቱ ሂደት በየክፍልፋይ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሲታይ የቆየው መለያየትና መናቆር መነሻው በመንፈሳዊ ሥልጣን ላይ በሚቀመጡ መሪዎችና ሊቅ ነን በሚሉ ሹመኞች እንደሆነ ብዙ ዋቢ ማቅረብ ይቻላል። ተመሪው ሕዝብም በሚናቆሩ መሪዎች ሁለት ወገን ቆሞ ለአንዱ ወገን አሸናፊነት የቤተክርስቲያኒቱን ግድግዳ እየነቀለ የማፍረሱን ሂደት ማፋጠኑ ሌላው ጉዳት ነው። ሥልጣኑ መንፈሳዊ ሆኖ ሳለ ሽኩቻው ወደሥጋዊ ሕይወት በማድላቱ በመደማመጥ መፍትሄ ለማምጣት ባለመቻሉ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እየተዳከመች በመሄድ ላይ ትገኛለች። በዚያው አንጻር ያሉባትን ተግዳሮቶችና ጊዜውን የዋጀ ክህሎት ያለው ብቁ አመራር በመፍጠር ስላልተቻለ ችግሩ እንዳለ ሊቆይ ችሏል። በዓለም ላይ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዷ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም አንዷ የችግሩ ሰላባ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን መካድ አይቻልም።


   የሩቁን ትተን የራሷን ቤተ ክርስቲያን ላዕላይ መዋቅር ራሷ መምራት ከጀመረችበት ከ1950ቹ አንስቶ ብንመለከት ችግሮች እየገዘፉ እንጂ እንየቀነሱ አለመሄዳቸው አስገራሚ ነው። በተለይም ከአፄው ስርወ መንግሥት መውደቅ ጀምሮ አሁን እስካለው እስከ ዘመነ ኢህአዴግ ድረስ ቤተክርስቲያን በአስተዳደሯ ተዳክማ፤ በተከታዮቿ አሽቆልቁላ መሄዷገሃዳዊ እውነት ነው። ጳጳሳቶቿ ፓትርያርካቸውን ከሰው በላው ደርግ ጋር ወግነው የበሉት ሥልጣን እናገኛለን ብለው ካልሆነ ስለእውነትና ስለቤተ ክርስቲያን ዝም ማለታቸው ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ደርግ ፓትርያርክ ሲሾምላቸው አሜን ብለው መቀበላቸው ሥጋዊ ፍርሃት አሸንፏቸው ካልሆነ በስተቀር ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ስለክርስቶስ ወንጌል ግድ ብሏቸው ሊሆን አይችልም። እንዲያም ሆኖ ከነፈሰው ጋር የሚነፍሱት ጳጳሳት «ብፁዕ ወቅዱስ» ሲሉ በነበሩት ፓትርያርክ ላይ ሌላ ፓትርያርክ ለመሾም ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ወደምርጫ የገቡት ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገት ተጨንቀው አለመሆኑንም አስረግጦ መናገር ይቻላል።


   በዘመነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፕትርክና የተሻለ አስተዳደርና የልማት ምልክቶች የታየበት ጊዜ ቢሆንም ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት ባለመኖሩ የሰውና የሀብት ብክነቱ ግን ወደር ያልተገኘለት ሆኖ አልፏል።  በሌላ መልኩም ከታዩት ስህተቶች ውስጥ ደግሞ ወደመንፈሳዊ ሥልጣን እንዲመጡ የተደረጉት ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ለለውጥ ሳይሆን ለውድቀት በር የከፈተ መሆኑ ሌላው ጉዳይ ነው። እንኳን ለሊቀ ለሊቀጳሳትነት ይቅርና ለደላላነት የማይመጥኑ ሰዎች በአፈፋ በገፈፋ መሾማቸው በአሳፋሪነቱ ወደር የለውም። ጳጳሳቱ የታወቀና ያልታወቀ የግል ኃጢአታቸው በአደባባይ የተነበበት እንዲሁም በዘረኝነት፤ በጎጠኝነት፤ በአፍቅሮ ንዋይ ፤ በሥልጣን ጥመኝነት፤ በአድመኝነት ራሳቸውን በተግባር ያሳወቁበት ጊዜ መሆኑ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ድክመት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን መሸፈን ከእውነታው ማፈግፈግ ይሆናል። 


  እነዚሁ ጳጳስ የተባሉት ሰዎች ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር አብ’ረው ለነውራቸው መሸፈኛ ያገኙ መስሏቸው ቤተክርስቲያኒቱን ሲያምሱ መገኘታቸው ለወንጌል አገልግሎት መዳከምና  እረኛ አልቦ የሆኑ ተከታዮቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲኮበልሉ የሆነበትም ዘመን ነበር። አስቀድሞ በተደረገ ፖለቲካዊ ምርጫ ወደፓትርያርክነት የመጡት አባ ማትያስም ከነበረው የተሻለ አስተዳደር ለመፍጠር ይቅርና የነበረውን ለማስቀጠል አለመቻላቸው ሌላው የቀጣይ ውድቀት አንዱ ማሳያ ነው።
የመሻሻል ምልክት የሌለውንና የጅምላ ሹመኞቹን የጳጳሳት ጉባዔ በርዕሰ መንበርነት የሚመሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንዴት አድርገው ቤተክርስቲያኒቱን ወደአንድ የአመራር ከፍታ ሊያሳድጉ ይችላሉ? በጭራሽ አይችሉም! ምክንያቱም ፓትርያርክ ከመሆናቸው በፊት ያልነበራቸውን ችሎታ ዛሬ ከወዴት ያገኙታል? በብዙ ሚዛን አሁን ካለበት ሁኔታ የተሻለ የነበረውን የአቡነ ጳውሎስን አስተዳደር በምኒልክና አስኳል ጋዜጣ ላይ በመተቸት ይታወቁ የነበሩት አቡነ ማትያስ የሥልጣኑ ሉል እጃቸው ላይ ሲወድቅ ወሬውን በተግባር ከማሳየት ይልቅ ለባለጉዳዮች «ተኝቷል በሉልኝ» በማለት በር ዘግተው መደበቅን ምርጫቸው ማድረጋቸው በሰፊው ይወራል።


  ከዚህ በፊት በዚሁ መካነ ጦማር ላይ የሙስና ታሪኩን በቅጽል ስሙ ያወጣነውና ማኅበረ ካህናቱ «ኑረዲን» የሚሉት(ንቡረእድ) ማንም እንዳይገባ በሩን ዘግቶ ለፓትርያርኩ የብቃት ጉድለት ተጨማሪ ድርሻ የወሰደ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በሩ ቢከፈትስ ፓትርያርኩ መፍትሄ የመስጠት ብቃት አላቸው ወይ? ብለው የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው።  አንድ ሰሞን ትኩስ በሚሆንና ቆይቶ በሚባረድ ስሜት ውስጥ ሆነው ፈታኝ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍታት አይቻልም። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ትኩስም፤ በራድም በመሆን የለውጥ ሰው መሆን አይችሉም። አንዱን መያዝ የግድ ይላል። በር እየዘጉ መደበቅም ችግሮቹንና ሸክሙን ከሚያበዛ በስተቀር እንከኖችን ሊሰውር የሚችል የምትሃት መንገድ አይደለም። መደበቅን እንደምርጫ ከወሰዱ ደግሞ ሲመተ ፓትርያርኩን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ሰጥተው ወደገዳም መሄድ ይሻላል።


 ሌላው የቤተ ክርስቲያኒቱ የአመራር ጉድለት «ቋሚ» የሚባለው ነገር ቋሚ ያልሆነው ተለዋዋጭ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው። ጳጳሳት ስለሚገኙት ብቻ «ቋሚ» ሊባል አይችልም። በየ3 ወሩ በሚደረግ መለዋወጥ «ቋሚ» የሆነ አመራር ሊሰጥ የሚችለው በምን መለኪያ ነው? የሲኖዶስ ውሳኔዎች አፈጻጸም የሚዘገዩት ወይም ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በውዝፍ እየተተወ የሚቀረው 3 ወራት ለሥራ በቂ ጊዜ ባለመሆኑ የተነሳ እንደሆነም መዘንጋት የሌለበት ነጥብ ነው። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚቆይና ቋሚ ሊያሰኝ የሚችል ሥራ መፈጸም የሚችል የቋሚ ሲኖዶስ ያስፈልጋል። በየ3 ወራት መቀያየር ያስፈለገው ጳጳሳቱ ከአዲስ አበባ ውጪ መቆየቱ ስለሚሰለቻቸው እንደእረፍት ጊዜ የመለዋወጫ መንገድ የወሰዱበት ዘዴ ሊሆን ይችላል እንጂ ሥራ ለመስራት አይደለም። ለዚያውም መሥራት የማይችሉ ሠራተኞች አድርገው አድርገን ከቆጠርናቸው ነው።  ከራሱና ከዘር ጉዳይወጥቶ የቤተ ክርስቲያን ችግር ግድ የሚለው ጳጳስ ከቶውኑ አለን? እነ አባ ማቴዎስ አሁን ባሉበት ሥልጣን እየሰሩ ያለው ሲታይ ለፓትርያርክነት መወዳደራቸው በራሱ ቤተ ክርስቲያኒቱን ራስ ዳሽንን ከሚያክል የተራራ ሸክም ገላገላት የሚያሰኝ ነው። ዛሬ ካሉት ጳጳሳት መካከል ጵጵስና ከመሾማቸው በፊት የጵጵስና የክብር ልብስ በማሰፋት በጉጉት ሲጠባበቁ የቆዩ እንደነበሩ እናውቃለን። አንዳንዶቹም ጳጳስ ሳይሆኑ በፊት የጵጵስናውን ድስት አጥልቀው ፎቶ ተነስተውም ታይተዋል። ዘመቻና ዲናር የሲመት መስፈርት በመሆኑ የተነሳ የተሻለ የአስተዳደር ለውጥ አልታየም፤ ወደፊትም አይታይምም። አንድ ጳጳስ፤ «በኛ ጊዜ ይሄን ያህል ገንዘብ ያስከፍል ነበር» ሲሉ ሰምተን አፍረንባቸዋል።


  ከዚህ በታች የምንመለከተው ፎቶ ግራፍም የዚያ የሹመት ስካር ውጤት ነው። አባ ገ/ሚካኤል ይባላል። ከዚህ በፊት በቃሲም ሥላሴ ሰባኬ ወንጌል ነበር። ከዚያም ኬንያ ከተላከ በኋላ ፈርጥጦ ከአፈንጋጩ ሲኖዶስ የተቀላቀለ ነው። አሁን ደግሞ ሳይሾም በፊት የሲመት አራራውን እየተወጣው ይገኛል። ነገ ደግሞ ወይም በፈርጣጩ ሲኖዶስ አለያም በዘመቻ መልክ በሀገር ቤቱ ልማት የለሽ ሲኖዶስ ሊሾም ይችል ይሆናል።

 ጳጳስ ከሆኑት መካከልም እንደዚሁ ሲያደርጉ የነበሩ ተሹመው ታይተዋል። ነገ ስላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም። የጵጵስናውን ሹመት በተስፋ የሚጠባበቁትም ልብሱ ብል እስኪበላው ድረስ አሰፍተው ጥቅምትና ግንቦትን በህልም ይቋምጣሉ።


ቤተ ክርስቲያን ግን እያሽቆለቆለች፤ አስተዳደሯ እየሞተ ነው። እየገደላት ያለው ማነው?

Sunday, November 30, 2014

በምድር ላይ በክፉው መንፈስ ተነድተው ሕዝብን ያሳሳቱ አሰተኛ ክርስቶሶች (ክፍል 4 )

ላዝሎ ቶት(1938-2012) 

በትውልዱ ሀንጋሪ፤ በዜግነት አውስትራሊያዊ የሆነ ሰው ነው። በትውልድ ሀገሩ በጂኦሎጂ ትምህርት ዲፕሎማ የነበረው ቢሆንም የእንግሊዝኛ ቋንቋው ደካማ ስለነበርና የሙያ ክህሎቱም ተቀባይነት ባለማግኘቱ አውስትራሊያ እንደገባ ሀንጋሪ በተማረው ሙያ መስራት አልቻለም። በኋላም በአንድ ሳሙና ፋብሪካ በቀን ሰራተኝነት ተቀጥሮ ጥቂት ከቆየ በኋላ በ1971 ዓ/ም ወደኢጣሊያ አቅንቷል።  ጣልያን እንደደረሰም እኔ «ኢየሱስ» ነኝ እያለ ለመስበክ ቢሞክርም ጣሊያንኛ ባለመቻሉ ስብከቱን ያዳመጠው አልነበረም። ከሮማው ካቶሊክ ፖፕ ጳውሎስ 6ኛ ለመገናኘትና የራሱን ማንነት ሊገልጽላቸው እንደሚፈልግ ደብዳቤ ጽፎላቸው ደብዳቤው ከፖፑ ሳይደርስ መንገድ ላይ ቢቀርበትም በሌላ መንገድ ለመገናኘት ያልተሳካ ሙከራም አድርጓል። ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ተስፋ ያልቆረጠው «ቶት» የመጨረሻ ሙከራውን ለማድረግ በ33ኛው ዓመት ዕድሜው ግንቦት 21 ቀን 1972 ዓ/ም ጂኦሎጂስቶች በተለይ የሚጠቀሙበትን ትንሽ መዶሻ ከፍ አድርጎ በመያዝና በአደባባይ እየጮኸ «እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ ሞቼም ነበር፤ ሕያው ነኝ» እያለ ይረብሽ ጀመር። ከዚያም ወደ ቫቲካን ሲቲ በመግባት በሚካኤል አንጄሎ የተሰራውን ቅርጽ ማለትም ኢየሱስ ከመስቀል ላይ ወርዶ በእናቱ በማርያም እቅፍ ላይ ሆኖ ከአንገቱ ዘንበል ብሎ የሚታየውን ምስል በያዘው መዶሻ መደብደብ ጀመረ። በድብደባውም የማርያምን ምስል ቀኝ ክንድ፤ የአንድ ዓይን ክፍሏንና አፍንጫዋን ሰብሮ ጥሏል።


 በቦታው ከነበሩ ጎብኚዎች አንዱ የሆነው ቦብ ካሲሊ የተባለ ሰው ቶት ላይ ተጠምጥሞ በመያዝ ሊያስጥለው ችሏል። ቶት በቁጥጥር ስር ውሎ ህክምና ሲደረግለት የአእምሮ በሽተኛ መሆኑ በመረጋገጡ ከጣሊያን ወደአውስትራሊያ በአስቸኳይ እንዲባረር ተደርጓል። አውስትራሊያም እንደደረሰ በተመሳሳይ ድርጊት ላይ በመገኘቱ ከህሙማን ክብካቤ ማዕከል እንዲገባ ተደርጎ ህይወቱ እስካለፈችበት 2012 ዓ/ም ድረስ በዚያው ሲረዳ ቆይቷል።

===============================================================================

ዌይን ቤንት ወይም ማይክል ትራቬሰር (ከ1941- እስካሁን በሕይወት ያለ)

 በ1941 ዓ/ም የተወለደ ሲሆን  በአይዳሆ ሴንትፖይንት ከተማ በምትገኝ «ጌታ የኛ ቅድስና ቤተ ክርስቲያን» መሪ የነበረ ሰው ነው። ቤንት የዚህች ቤተክርስቲያን መሪ ከመሆኑ በፊት «በሰባተኛ ቀን ቤተ ክርስቲያን» ፓስተር ሆኖ ያገለግል ነበር። በ1987 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያኒቱን በይፋ ለቆ ሲወጣ «ሰባተኛ ቀን ቤተ ክርስቲያን የታላቂቱ ጋለሞታ ሴት ልጅ ናት» ብሎ በአደባባይ ተናግሮ ነበር። ይህንን ለማለት ያበቃውን ምክንያት ግን በወቅቱ አልተናገረም።  ከዚያም ወደ አይዳሆ በማምራት ጥቂት ጊዜ በአባልነት ከቆየ በኋላ በ2000 ዓ/ም «ጌታ የኛ ቅድስና» በተባለችውና አነስተኛ ቁጥር በያዘችው ቤተ ክርስቲያን መሪ  ለመሆን ቻለ። በዚያው ዓመት «እግዚአብሔር፤ አንተ ኢየሱስ ነህ ብሎ ተገልጾ ነገረኝ» በማለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት አወጀ። ጥቂት ቆይቶም ከሰባት ደናግላን ጋራ ለወሲብ እንድትተኛ የሚል ትዕዛዝ ስለመጣልኝ ደናግል ልጆቻችሁን እንድትሰጡኝ በማለት ጥያቄውን አቀረበ። ገሚሶቹ የቡድኑ አባላት ሃሳቡን ውድቅ ያደረጉበት ቢሆንም በግላጭ ሴት ልጁን አሳልፎ የሰጠው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ በምስጢር ከደናግላን ጋር ወሲብ መፈጸሙ በኋላ ላይ በፖሊስ በተደረገበት ምርመራ ሊረጋገጥ ችሏል። ቻናል 4 የተባለው የዩኬ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ2007 ዓ/ም ከዌይን ቤንት ጋር ባደረገው ቃል ምልልስ ስለደናግላኑ ወሲብና ከእግዚአብሔር ስለሚመጣለት ትዕዛዛት ተከታታይ ፕሮግራም አስተላልፎ ነበር።(ከቪዲዮዎቹ አንዱን ለማየት እዚህ ይጫኑ)
  የዓለምም መጨረሻ ጥቅምት 31/2007 ዓ/ም እንደሚሆንና ተከታዮቹም ለመነጠቅ እንዲዘጋጁ የተናገረ ቢሆንም ቀኑ ሲደርስ እንዳለው የሆነ ነገር ምንም አልነበረም።  ይልቁንም ቤንት ከልጁ ሚስት፤ ከደናግላን ጋር እንዲሁም ለአቅመ ሄዋን ካልደረሱ ታዳጊዎች ጋር ወሲብ በመፈጸም ወንጀል ተከሶ በ2008 ዓ/ም የ18 ዓመታትን እስራት ተከናንቦ ከርቸሌ ወርዷል። ዌይን ቤንት ከርቸሌ ከወረደ በ2014 ዓ/ም ገና 6ኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን ቢያንስ በአመክሮ ለመፈታት ከእንግዲህ 3 ዓመት ገደማ በዚያው መቆየት ይጠበቅበታል። 

==============================================================================

አሪፊን ሙሐመድ ( 1943- እስካሁን ያለ)

 አሪፊን ሙሐመድ በ1943 ዓ/ም ከሙስሊም ቤተሰብ በማሌዢያ ተወለደ። እድሜው ለአቅመ ህውከት እንደደረሰ በ1980ቹ አጋማሽ  በማላያን ቋንቋ «ካራጃአን ላንጊት» ወይም በእንግሊዝኛው «የሰማይ መንግሥት» የተሰኘ ድርጅት አቋቋመ። በአክራሪ ሙስሊሞች በምትታወቀው ማሌዢያ ውስጥ አሪፊን ሙሐመድ «እኔ አልመሲህ ዒሳ፤ ቡድሃ፤ ሙሐመድ ሺቫ ነኝ» እያለ በመስበክ ተከታዮችን ለማፍራት ጊዜ አልፈጀበትም። በዚህ አድራጎቱ ብርቱ ተቃውሞ ገጠመው። በተደጋጋሚ ሲታሰር፤ ሲፈታ ቆይቶ መንግሥታዊ ስርዓቱን በዓመጽ ለመገልበጥ በመሞከርና ሃይማኖታዊ ብጥብጥን በመፍጠር ወንጀል ተከሶ ድርጅቱ እንዲዘጋ፤ በአባልነት የተሳተፉትም እንዲታሰሩ ሲወሰን አሪፊን ሙሐመድ ሾልኮ አመለጠ። ከአራቱ ሚስቶቹ ሦስቱና ከተከታዮቹም 58 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

 እያንዳንዳቸውም 3000 የማሌዢያን ገንዘብ እንዲከፍሉና ሁለት ዓመት እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት ወሰነባቸው።  የድርጅታቸውም ህንጻና ማንኛውም ንብረት እንዲፈርስ ተደረገ። አሪፊን ሙሐመድ አንዴ ኢየሱስ ነኝ፤ አንዴ ማህዲ ነኝ እያለ ተከታዮቹን ቢያጭበረብርም በማሌዢያ መንግሥት በወንጀል ከሚፈለጉ ሰዎች ቀንደኛው ሲሆን ማሌዢያን ለቆ ከጠፋ በኋላ በታይላንድ ውስጥ ተሸሽጎ እንደሚገኝ ይገመታል።
==================================================================================

ማታዮሺ ሚትሱኣ (1944- እስካሁን በሕይወት ያለ) 

በጃፓን፤ ኦኪናዋ ከተማ በጥር 5/ 1944 ዓ/ም ተወለደ። ከዚያም ለአቅመ ትምህርት እንደደረሰ በመጀመሪያ በተወለደት ቦታ በኋላም በቶኪዮ ቹዋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪውን አግኝቷል። በ1997 ዓ/ም «ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ ኅብረት ፓርቲ» የተባለውን ሃይማኖትንና ፖለቲካን በጥምር የሚያንቀሳቅስ ፓርቲ መሰረተ። እንደሃይማኖት ሥርዓት ዓለም በኔ እንዲገዛ «እኔ ኢየሱስ ነኝ» አለ። እንደፖለቲካ አስተዳደር ደግሞ ዓለም በኔ እንዲመራ «የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ አለ»። የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ባለው ከፍተኛ ጉጉት የርሱ ፓርቲ በተደጋጋሚ በምርጫ ቢወዳደርም  እንኳን ከትልቅ ስልጣን ሊደርስ ቀርቶ የመንደር ምርጫም ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል። በምርጫ የተፎካከሩትን ሰዎች ለዚህ ድርጊታችሁ የምሰጣችሁ ምክር «ራሳችሁን አጥፉ»  ያላቸው ሲሆን ስልጣን ብይዝ ደግሞ ሁሉንም ሰብስቤ እሳት ውስጥ እጨምራቸው ነበር እያለ ሲለፍፍ ተሰምቷል።

== ==============================================================



ጆሴ ሉዊስ ደ ጂሰስ ሚራንዳ ( 1946- 2013) 

 ፖርቶሪኮ ውስጥ ፖንሴ በተባለች ከተማ በ1946 ዓ/ም ተወለደ። ወላጆቹ በጣም ድሃ ስለነበሩ የሴቶችን ቦርሳ መመንተፍ የተለማመደው በልጅነት ዕድሜው ነበር። ገና የ14 ዓመት ዕድሜ ሳለም የሔሮይን አደገኛ ተጠቃሚ እስከመሆን ደርሷል።  ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆይ በፖንሴ ከተማ በነበረችው መጥምቃውያን ቤተ ክርስቲያን ተቀላቀለ። እግዚአብሔር ባደረገልኝ ጥሪና እገዛ ከነበረብኝ ደባል ሱስ ሁሉ ተላቅቄአለሁ አለ።  ጆሴ ሚራንዳ በ1973 ዓ/ም  ሁለት መላዕክት መጥተው በነገሩኝ መሠረት «እኔ ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ ሆኜ በምድር ላይ መገለጤን ነግረውኛል» ብሎ መለፈፉን «ሀ»ብሎ ጀመረ። በማያሚ፤ ፍሎሪዳ የስደት ኑሮውን የቀጠለው ሚራንዳ የ15 ደቂቃ የሬዲዮ ፕሮግራም በማሰራጨት የሱን ኢየሱስነት ይሰብክ ገባ። በስብከት መርሐ ግብሩ «ሚኒስትሮ ግሬሴንዴ  ኤን ግራሲያ» ወይም « በጸጋው የማደግ አገልግሎት» የተሰኘ ድርጅት ከመሰረተ በኋላ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ማስፋፋቱን ቀጠለ። በ35 ስቴቶች በከፈተው ተቋም 287 የሬዲዮ ጣቢያዎችና በእንግሊዝኛና ስፓኒሽ ቋንቋ የሚተላለፍ የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን ስርጭትም እስከማስተላለፍም ደርሷል።
ጆሴ ሚራንዳ አንድ ጊዜ ሐዋርያው ጳውሎስ ነኝ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ ኢየሱስ ነኝ እያለ ከቆየ በኋላ በ2006 ዓ/ም ክህደቱን በማጠናከር ከዛሬ ጀምሮ «እኔ የኢየሱስ ተቃዋሚ ነኝ» ሲል አወጀ።  «Anti Christ» ወይም ተቃዋሚው ስለሆንኩኝ መለያ ምልክቴ በራእይ 13 ላይ የተጠቀሰው«666» ቁጥር ነው በማለቱ  ተከታዮቹ ሁሉ በሰውነታቸው ላይ እንዲነቀሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ተከታዮቹም «666» ቁጥርን በሰውነታቸው ላይ በሰልፍ ተነቀሱት።
የሚራንዳ ወርሃዊ ደመወዝም ልዩ ልዩ ክፍያና አበልን ሳይጨምር 228,000 ዶላር ገደማ ነበር። ሚራንዳ ባደረበት የጉበት ህመም በተወለደ በ67 ዓመቱ በ2013 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ከ2 ሚሊዮን በላይ በሚገመቱ ተከታዮቹም ዘንድ «እንደመልከ ጼዴቅ ለዘለዓለም የሚኖር» ተብሎለታል።
በአንድ ወቅት CNN ካቀረበው የጆሴ 666 ታሪክ የተወሰደ ቪዲዮ ይመልከቱ።





Friday, November 21, 2014

ፍሪማሰንሪ /freemasonry/ ምንድነው?




ከዚህ በፊት በአንድ ጽሁፍ «ስለኤርያ 51» አጭር ምስጢራዊ ጽሁፍ ማስነበባችን ይታወሳል። አሜሪካና ዲሞክራሲ፤ ሥልጣኔና አሜሪካ መሳ ለመሳ ናቸው። እንደዚሁ ሁሉ ሌላው ዓለም ይቅርና የሀገሪቱ ዜጋ የማያውቃቸው ብዙ ምሥጢሮችም ያሉባት ሀገር ናት። ላይ ላዩን በዲሞክራሲው ዕድገት ጫፍ ረግጫለሁ በማለቷና በሥልጣኔውም መጥቄአለሁ እያለች ከመለፈፏ ጀርባ ብዙ ጉድ እንዳዘለች ብዙው ሰው አያውቅም፤ ቢያውቅም ትኩረት አይሰጠውም።  በነገረ መለኮት የበሰሉና የትንቢቱ ፍጻሜ ሰዓት መድረሱን በደንብ ያጠኑ ምሁራን ግን አሜሪካንን «ታላቂቱ ባቢሎን» ይሏታል። ምክንያቱም በአደባባይ ከሚታወቅላት የዲሞክራሲውና የሥልጣኔው እርከን ባሻገር የተሸከመችው ጉድ የት የለሌ ነውና። ሁሉም ነገር ከብረት በጠነከረ ምስጢርና ከምስጢሩ አጠባበቅ ጋር ሕይወት በሚያስከፍል ዋጋ፤ የረቀቀ መዋቅር በተዘረጋበት ሥርዓት የምትመራ ሀገር በመሆኗ እያወቁ ወይም ሳያውቁ ታደነዝዛለች።  በህጋዊ ደረጃ ከ«Church of Satan” አንስቶ እስከመጨረሻው ክሂዶተ እግዚአብሔር  «Atheism” ድረስ በነጻ የሚንቀሳቀሱባትና ለዓለሙ ሁሉ ማዕከል ሆና የምታገለግለዋ አሜሪካ ጾታን በመቀየር እንዲሁም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻንም በመፍቀድ መሪ በመሆን ታገለግላለች።

      ሌላው ቀርቶ በየዓመቱ የሚከበረውን የሀለዊን /Halloween/ በዓል ጥቅምት/31 ቀን ከጫፍ ጫፍ በማክበር አሜሪካንን የሚቀድማት የለም። ለነገሩ «ሀለዊን» የሞቱ ቅዱሳንን ለማሰብ በሚል ይጀመር እንጂ ድርጊቱ የሙት መንፈስ የሆነውን ሰይጣንን ለማሰብ የተሰራ ለመሆኑ የድርጊቱ ክንዋኔ ያስረዳል። የሚያስፈራ ምስልና ቅርጽ፤ ጥርሱ ያገጠጠ፤ ዓይኑ ያፈጠጠ፤ አጽሙ  የተቆጠረ ማስጠሎ ነገር ለብሶ ወይም አጥልቆ  ሰውን በማስደንገጥና በማስፈራራት ቅዱሳንን ማክበር ነው ቢባል እንዴት ሊሆን ይችላል? ለነገሩ ቅዱሳንን ተጠግቶ ይህንን ማድረጉ ራሱን የቻለ ሌላ ምስጢር ስላለው እንጂ ቅዱሳንን ስለሚወክል አይደለም። (የዚህን ምስጢር ፍቺ በዚህ ጽሁፍ ቀጣይ ክፍሎች ለመዳሰስ ይሞከራል) አሜሪካ ለመጨረሻው ዘመን የተዘጋጀችና ለጥፋት ነጋሪት የምትጎስም ሀገር በመሆንዋ ነገሩ ሁሉ እየተበላሸ ሄዷል። ባለፈው ጥቅምት 31/ 2014 ዓ/ም በሚዙሪ፤ ሴንት ሉዊስ ከተማ ዓለም አቀፍ የ«ሀሎዊን» በዓል እንደሚደረግ የተላለፈው የጥሪ ምስል እንደሚያሳየን የጨለማውን ኃይል ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማንን ሊሆን ይችላል? እስኪ ምስሉን አይተው ግምትዎን ይስጡ!!
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነን አሜሪካ ከምታስተናግዳቸው እንግዳ ነገሮች አንዱ ክፍል ስለሆነው ስለ«ፍሪማሰንሪ»/freemasonry/ ውቅያኖስ ታሪክ ጥቂቱን በጭልፋ ልናካችላችሁ ፈልገን ነው። ምክንያቱም የአንድ ዓለም አገዛዝ /One World Order/ እንዴት እየሰራ እንዳለ በማወቅ ከሚመጣው የስህተት መንፈስ እንድንጠበቅ አበክረን ለማስገንዘብ ነው። በዚህ ዙሪያ ምሁራኑ በሀገርኛ ቋንቋ ጽፈው በሰፊው እስኪያስነብቡን ድረስ ለጥንቃቄ እንዲበጅ በጥቂቱ እንዲህ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ!

ፍሪማሰንሪ ምንድነው?

     «ማሰን» የሚለው ቃል ከላቲኑ / machio/ ከሚለው ቃል የተወረሰ ነው።  ትርጉሙም «ድንጋይ ጠራቢ ፈላጭ ወይም ግንበኛ  ማለት ነው።  ቃሉም ከ1155 እ,ኤ,አ ጀምሮ አገልግሎት ላይ ውሏል። freestone-mason ማለት «ነጻ ድንጋይ ጠራቢ፤ ግንበኛ ሰው ማለት ሲሆን ይህም ስያሜ በዚህ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች «free mason» ፍሪማሰን በሚል አኅጽሮት አገልግሎት ላይ እንደዋለ በ1908 ዓ/ም የታተመው የፍሪማሰን ዜና መዋዕል መጽሐፍ ያስረዳል።  የላቲኑን ውርስ ቃል ተከትሎ “free” እና “mason” ከሚለው የእንግሊዝኛ ጥምር ቃላት የተገኘው ይህ ስያሜ ድንጋይ የመጥረብ፤ የመቁረጥና የመገንባትን ድርጊት ሲያመለክት «ፍሪማሰንሪ» /freemasonry/ ይባላል።  ይህም በነጻ ፈቃድ፤ በራስ ውሳኔ ዓለቱን ጠርቦ የማይነቃነቅና የማይናወጥ መሠረት ያለው ግንብ የመገንባት ዓላማ ነው ማለት ነው።  

«ፍሪማሰን» የተባለው ስያሜ በግንበኝነት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች በተናጠል ሲጠሩበት የቆየ ቢሆንም ከ14ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ በአውሮፓ የህንጻ ምህንድስና ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በጥቂት ሰዎች ተደራጅተው ራሳቸውን የመጥራት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ የማሰን የተናጠል እንቅስቃሴ ቀደም ሲል እንደነበረ ቢሆንም ድርጅታዊ ሕግና ፒራሚዳዊ የብቃት የእርከን ደረጃ ወጥቶለት የተመሰረተው በ1717 ዓ/ም በለንደን ከተማ ነው።። በ1731 በአሜሪካ ፤ በ1736 በስኮትላንድ መሰረቱን አስፋፋ። ከዚያም በ1725 በአየር ላንድ እንደተጀመረ ይነገራል።  አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመው በጣም ደርጅቶና ጎልብቶ ዓለም ዐቀፍ ቅርጽ ለመያዝ በቅቷል። 

      ይህ የፍሪማሰን ማኅበር የአውሮፓን የኢንዱስትሪ አብዮት ተጠግቶ የተመሰረተው የህንጻና የምህንድስና ባለሙያዎችን የያዘው እንቅስቃሴ ቅርጹንና መልኩን ለውጦ በሰው አእምሮና አስተሳሰብ ላይ እንደህንጻ የሚያድግ ግብረገብነትን፤ በጎ አድራጎትንና  መልካም ስብእና ያለው ሕብረተሰብን የመፍጠር ዓላማ ባለው መመሪያ ላይ ራሱን በማቆም ሕግና ደንብ አውጥቶ መሥራት መጀመሩን የተጻፈ ታሪኩ ያስረዳል። 

  ምንም እንኳን የፍሪማሰንሪ ማኅበር በኦፊሴል ከአምልኮና ከፖለቲካ አስተሳሰብ ነጻ ነኝ ቢልም በ1723 እና በ1738 ዓም ተሻሽሎ በወጣው የፍሪማሰንሪ ሕገ መንግሥት ላይ እንደተመለከተው የሁሉም ነገር ንድፍ / architect/ ባለቤት «እግዚአብሔር ነው ስለሚል እንቅስቃሴው ሃይማኖት ለበስ እንደሆነ ፍንጭ ከመስጠቱም በላይ ድርጅቱ የራሱ የሆነ ዶግማና መመሪያ ስላለው የእምነት ድርጅት አይደለሁም የሚለው አባባሉ ተቀባይነት እንዳይኖረው አድርጓል።  ድርጅቱ የአንድ ወጥ የሃይማኖት ተቋም ላለመሆኑ እንደመከራከሪያ የሚያቀርበው ጭብጥ የፍሪማሰንሪ አባል ለመሆን  የየትኛውንም ሃይማኖት ተከታይ ወይም የሃይማኖት መጽሐፍ ተቀባይ ወይም የትኛውንም የፖለቲካ መስመር የያዘ ሰው በአባልነት መቀበል መቻሉን በማስረጃነት ያቀርባል።  ድርጅቱ ይህንን ይበል እንጂ አባል የሚሆን ሰው ቀድሞ የነበረውን እምነቱን ይሁን አመለካከቱን እንዲጥል ሳይገደድ የፍሪማሰንን አስተምህሮና ሕግ በተከታታይ ተምሮ በድርጅቱ የረቀቀ አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰጥም ማድረግ በራሱ ቀድሞ የነበረውን የማስቀየር ዘዴ እንደሆነ በተሞክሮ ያዩት ሰዎች በተግባር ያረጋገጡት ሀቅ ነው።

    እንደፍሪማሰንሪ አባባል የጥበቦች ሁሉ /Architect/ የንድፍ ባለቤት እግዚአብሔር ሲሆን ያገኙትን ጥበብ ወደተግባር የሚለውጡት ደግሞ የፍሪማሰንሪ እውቀት የተሰጣቸው ሰዎች ናቸው ይላሉ። ለምሳሌም የኖኅ መርከብ የተሰራቸው በኖኅ የፍሪማሰን እውቀት ነው። የባቢሎን ግንብ ይሁን የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ያለፍሪማሰን እውቀት ፍጻሜ አያገኝም ነበር ባዮች ናቸው። የግብጽ ፒራሚዶች የፍሪማሰን ጥበብ ውጤት ነው። የኖስቲኮች እውቀት፤ የግሪክ ፍልስፍና፤ የፓይታጎረስ ስሌት፤ የዞሮአስተር ትምህርት፤ የቻይና ጥበብ፤ የአልኬሚስቶች ፈጠራ ሁሉ በፍሪማሰን እውቀት ጎልምሶ ወደተግባር የተለወጠ መሆኑን ያምናሉ። 

   ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የፍሪማሰንሪ ድርጅት አባል ሲመለመል የትኛውንም ሃይማኖት የሚከተል ወይም የትኛውንም የሃይማኖት መጽሐፍ የሚቀበል ሰው መሆኑ ችግር የለውም። እንዲተውም አይጠበቅም። ቁምነገሩ አንድ ጊዜ የፍሪማሰንሪ ድርጅት አባል ከሆኑ በኋላ ድርጅቱን መልቀቅ እንደማይቻል ወይም በምክንያት ከለቀቁ ደግሞ የቆዩበትን የድርጅቱን ምስጢር ማውጣት የሞት ዋጋ እንደሚያስከፍል አስቀድሞ ቃለመሃላ ይፈጽማል። ፍሪማሰንሪ በስብከትና በድለላ የአባልነት ምልመላ አያደርግም። አብዛኛው የዚህ ድርጅት አባላት ፕሬዚዳንቶች፤ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፤ ዶክተሮች፤ ፕሮፌሰሮች፤ ጀነራሎች፤ ዳኞች፤ የሴኔትና የምክር ቤት አባላት፤ ቢሊየነሮች፤ ታዋቂ ሰዎችና ከፍተኛ ነጋዴዎች ናቸው። ከአሜሪካ 44 ፕሬዚዳንቶች ውስጥ 14ቱ የፍሪማሰንሪ ድርጅት አባላት እንደነበሩ በግልጽ ሲታወቅ  ከተቀሩትም ውስጥ በምስጢራዊ አባልነት የነበሩ እንዳሉ ይነገራል።

ፍሪማሰንሪ ካሉት 330 (ሠላሳ ሦስት ድግሪ) ማእርጋት አንዱ በሆነው የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ የተወሰኑ ትምህርቶችን አስቀድሞ ከወሰደ በኋላ ወደድግሪ ትምህርቱ ሲገባ ይህንን መሃላ ይፈጽማል።

« ዛሬ የፍሪማሰንሪ አባል ከሆንኩ በኋላ አባል ለሆንኩበት ድርጅት ካልታመንኩ ወይም ብከዳ ወይም ምስጢር ባወጣ በጎሮሮዬ ላይ ስለት ይረፍ፤ ምሳሴ ከስሩ ተነቅሎ ይጣል፤ አጽሜ አመድ ሆኖ ከውቅያኖስ የጥልቁ አሸዋ ውስጥ የተሰወረ ይሁን» ይላል። ለምን?

የፍሪማሰንሪ ዓርማና ሌሎች ምልክቶች ምንድናቸው? ከኢሉሚናቲ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምንድነው? ይህንንና ሌሎች ምስጢሮችን በቀጣይ ክፍል ለማቅረብ እንሞክራለን።

Thursday, October 30, 2014

«የሚያስፈራሩን ከሆነ ወደየገዳማችን እንሄድልዎታለን!» አባ አብርሃም፤ «ወደየትኛው ገዳምዎ? ለመሆኑ ገዳም ያውቃሉ?» ፓትርያርክ ማትያስ


ቅዱስ ፓትርያርኩ ስለማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የፈረጠመ ጡንቻ ሲገልጹ «የፈርዖን አገዛዝ» ነበር ያሉት። ማኅበረ ቅዱሳን የደርግ መንግሥት መውደቅ የወለደውና በዓለት ስንጥቅ መካከል የበቀለ ዛፍ ነው። ዓለቱን አንቆ ይዞ በላዩ ላይ የለመለመ ነገር ግን ከአለቱ መካከል ከወጣ ኅልውና የሌለው ሥር አልባ መሆኑም እርግጥ ነው።  ይህን ሽብልቅ ገብቶ የፈረጠመውን ዛፍ ከማነቃነቅ ባለፈ ከሥሩ ነግሎ ለመጣል ጊዜና ሰው የተገናኙት ዘንድሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና ነው። ዋና ዓላማውም ከመሠሪና ስውር የቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወረራ ብቸኛዋን ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንን መታደግ መሆኑን ቅዱስ ፓትርያርኩ በግልጽ ደጋግመው ተናግረዋል።

 «ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር» እንዲል መጽሐፉ ዘንድሮ ቀኑ ደርሶ ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ በማኅበረ ቅዱሳን እስትንፋስ የሚንቀሳቀሱ ተላላኪ ጳጳሳቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን እጅ ጠምዝዘው ለማስረከብ ደፋ ቀና የሚሉበት ዘመን ግብዓተ መሬቱ እየተፈጸመ ይገኛል። ከትናንት በስቲያ በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የጉድ ሙዳይ የሚባለው ሊቀጳጳስ አባ አብርሃም በአቡነ ጳውሎስ ላይ የለመደ አፉን በአቡነ ማትያስ ላይ በመክፈት «የመንግሥትን ኃይል ተማምነው አያስፈራሩን፤ የሚያስፈራሩን ከሆነ ሲኖዶሱን ለቀንልዎ ወደየገዳማችን እንሄድልዎታለን» ብሎ እስከመናገር የደረሰ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩም ለሱም ይሁን ለቢጤ ወንድሞቹ ራስ ምታት የሆነ ምላሽ በመስጠት ዝም ጭጭ እንዲል አድርገውታል።

«ኧረ ለመሆኑ የእርስዎ ገዳም የት ነው? እስኪ ንገሩኝ የትኛው ገዳም ነው ያገለገሉት?  ደግሞስ እኔ አባ ማትያስ ለእርስዎ አንሼ ነው የመንግሥትን እርዳታ የምጠይቀው? ምነው! ቤተ ክርስቲያን እንደተሸከመችዎ አውቀው አርፈው ቢቀመጡ?!» በማለት የጳጳሱን ጉድ ጫፍ ጫፉን በመናገር አፉን እንዳስያዙት የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

ተመሳሳይ በሽታ የነበረባቸው የማኅበሩ ጳጳሳት የጓደኛቸው ጉድ ፊታቸው ሲነገር በመስማታቸው የተሸማቀቁ ሲሆን አንዳንዶቹ በብስጭት ጉባዔውን ለመረበሽና ለምን ተነካን? የማለት ያህል ሲቁነጠነጡ ታይተዋል። ይሁን እንጂ ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጣቸው ምላሽ «ምን አለፋችሁ? ዘንድሮ ማኅበረ ቅዱሳንን በሕግና በሥርዓት ሳላስገባው አልተወውም!» በማለት ቁርጡን እንደነገሯቸው ተያይዞ የደረሰው ዜና ያስረዳል።
ቀደም ሲል የማኅበሩ ደጋፊ የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ግን የፓትርያርኩን የጠነከረ አቋም ያጤኑ በሚመስል መልኩ ተዐቅቦን መርጠዋል። እነአባ ኤልያስ፤አባ ሉቃስ፤ አባ ቀውስጦስና በእድሜ ገፋ ያሉት ጳጳሳት ጥቂት የታገሉ ቢሆንም ከአባ ገብርኤል በስተቀር ወሎዬዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት ግን ዝምታን መምረጣቸው ተዘግቧል። ምናልባትም «እነዚህ እኮ መንግሥትን ከአንድ ክፍለ ሀገር፤ ወደ ሌላ ክ/ሀገር ማዛወር የቻሉ ናቸው፤ ዛሬ አቤሲዲ ቆጥረውማ ማን ይችላቸዋል?» የተባለው ኃይለ ቃል ሳይከነክናቸው የቀረ አይመስልም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተደረሰበት ውሳኔ እንደሚያሳየው ማኅበረ ቅዱሳን አፈንግጦ ከወጣበት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተመልሶ በሥሩ እንዲተዳደር፤ በቤተ ክህነቱ ሞዴላ ሞዴሎች እንዲጠቀም፤ እስከዛሬ የፈጸመው የገቢና ወጪው አጠቃላይ ሂሳብ በቤተ ክህነት ባለሙያዎች እንዲመረመር፤ አዲስ በሚረቀቀውና ፀድቆ በሚሰጠው የመተዳደሪያ ደንብ በቤተ ክህነቱ ቁጥጥር እንዲንቀሳቀስ፤ ማንኛውንም ሥራ ቤተ ክህነቱን እያስፈቀደ እንዲፈጽም የሚያስገድደው ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑም ተዘግቧል። ድንቅ ውሳኔና ተገቢነቱም ትክክለኛ እንደሆነ አስምረንበታል።

 ድሮም በዚህ ዓይነቱ ልክና ገደብ ባለው አካሄድ ይስራ ከመባሉ ውጪ ይፍረስ፤ ይውደም ያለው  ማንም አልነበረም። ነገር ግን ማኅበሩ ያለውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት ዘለለ መልኩ በአባላት ጳጳሶቹ በኩል እንደሚመቸው አጣሞ በማስቀረጽ መንቀሳቀሱ እንዲገደብ ካለመፈለጉ የተነሳ ወደመላተም አድርሶታል።

የሚደርስበትን ጥላቻና ተቃውሞ ለመሸፈንና በቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ለመሸሸግ በመፈለግ «ሲኖዶሱ ቀርጾ ከሰጠኝ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ አልንቀሳቀስም» እያለ መደዴ አካሄዱን ሕጋዊ ለማስመሰል ይፈልጋል። እንደነአባ የጉድ ሙዳይ አባላቱ የሰጡትን ገደብ አልባ መተዳደሪያ ደንብ በማሞካሸት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈ ለማስመሰል መሞከሩ ራሱን ከሚያታልልበት በስተቀር ማንንም ማሞኘት አይችልም። «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» በሚል ስልት የሚያጨበጭቡለት ጥቂቶች ባይታጡም አብዛኛው የቤተ ክህነት ሰው ዓይንህን ላፈር ካለው ውሎ አድሯል።
ጳጳሳቱ በማኅበረ ቅዱሳን አዚም ነፍዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን አጨብጭበው ለማስረከብ በደረሱበት ሰዓት ፓትርያርክ አባ ማትያስ ደርሰው ልጓም አልባ ሩጫውን ገደብ ሰጥተውታል። ምናልባትም በማኅበሩ ግፍና መከራ የወረደባቸው ማኅበረ ካህናት፤ በኃጢአት ገመናቸውን እየገለበ የሚያሳድዳቸው ማኅበረ መነኮሳትና በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያለቀሱት ልቅሶና ያፈሰሱት እንባ ከመንበረ ጸባዖት ደርሶ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የመጣ ፍርድ ይሆን ይሆናል።
ወደፊትም ማኅበሩ ጊዜ በመግዛት የራሱን ሌላ አማራጭ ለመፍጠር እስትንፋሱን ያሰባስብ ይሆናል እንጂ አሁን በሚሰጠው ሕግና ሥርዓት ይተዳደራል ተብሎ አይጠበቅም። ለሁሉም አሁን የተያዘው የፓትርያርኩ እርምጃ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ዘንድ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያለው ነው።
 ሁላችንም ይበል ብለናል!

Saturday, October 18, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈርሰው በራሱ ተግባር ነው፤ ኢሕአዴግ ላለፉት 22 ዓመታት መቼ ነካው?

ይህን ጽሑፍ በመጋቢት ወር 2006 ዓ/ም በመካነ ጦማራችን ላይ አውጥተነው ነበር።። ዳግመኛ ማውጣት ያስፈለገን ጉዳይ ሰሞኑን በፓትርያርክ አቡነ ማትያስና በማኅበረ ካህናቱ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን በቅኝ ገዢነት የመቆጣጠር ስልቱና ይህንን ስለማስቆም በአንድ ድምጽ የተናገሩትን አቋም በመጻረር የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ ክንፍ የሆኑት አባ ማቴዎስ የሰጡትን  ማስጠንቀቂያ መነሻ በማድረግ ለማስታወስ የምንፈልገው ቁም ነገር ስላለ ነው።
 ዛሬ አባ ማቴዎስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን « እንደአቡነ ጳውሎስ በሞት ይወገዳሉ» በማለት የተናገሩትን ቃል ከስምንት ወራት በፊት ማኅበሩ ራሱ በአሉላ ጥላሁን መካነ ጦማር በኩል ተናግሮት ነበር። ያንኑ የእናስወግዳለን ዛቻ አባ ማቴዎስ ሲደግሙት በቤተ ክህነቱ ውስጥ በተቃርኖ የቆሙ አካሎች ስውር መጠፋፋት እንደሚፈጽሙ ማሳያ ምስክር ነው።  በሌላ መልኩም ማኅበሩ ሊታረም የሚችል አካል ስላይደለ እየታየ ባለው የምድራዊ ሥልጣን ግብግብ ውስጥ ማኅበሩ በያዘው መንገድ ከቀጠለ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር መጥፋቱ የማይቀር መሆኑንም አስረግጠን ገልጸን ነበር። መቅኖ አጥቶና ባክኖ እንዲቀር ባንፈልግም አንዴ «ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ነው፤አንዴ አቡነ ማትያስ ሊበሉኝ ነው» የሚለው ጩኸት የራሱን ሥፍራ ቆም ብሎ እንዳያይ እያደረገው ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ቢጠፋ፤ መጥፋቱ በሌላ በማንም ሳይሆን በራሱ ተግባር መሆኑን ጠቁመን ነበር።
 መልካም ንባብ ይሁንላችሁ!!

ይህ ሕንጻ የማነው? የቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን? የመንበረ ፓትርያርክ? የአስመጪና ላኪ? የበጎ አድራጊ ድርጅት?

 የሀገሬ ሰው «ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል» ይላል። ይህ አባባል ለሰሞነኛው የማኅበረ ቅዱሳን የጅቡ በላኝ ጩኸት ይስማማል። ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ነው ሲል በየግል ጋዜጣው ማስወራቱ 22 ዓመታት ኢህአዴግ በሚመራት ሀገር ውስጥ ያልነበረ ይመስላል። ሲነግድ፤ ሲያስነግድ፤ ሲሸጥ ሲለውጥ፤ከግብርና ታክስ ተከልሎ በሚሊዮኖች ብር ህንጻ ሲገነባ በሀገሪቱ ኢህአዴግ ያላየው ወይም የማያውቀው ይመስላል። ኢህአዴግ ማኅበረ ቅዱሳንን በአስማት ይሁን በምትሃት እስከዛሬ ሳያየው ቆይቶ አሁን ለማየት ዓይኑን ሲከፍት ማኅበረ ቅዱሳንን አገኘውና ሊበላው ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ለምን ፈለገ ሲል ለመጠየቅ የተገደደ ይመስላል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ተግባሬ ከማኅበረ ካህናቱ ጋር አጋጨኝ፤ በማያገባኝ አስተዳደር ውስጥ እጄን ሳስገባ ተገኘሁ እንዳይል ከመሬት ተነስቶ ኢህአዴግ ሊውጠኝ ነው ወደሚል ቅስቀሳ መግባቱን  ከመምረጡ በስተቀር በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን የምርጫ ዘጠና ሰባት ውጤትና ተከትሎ የመጣው ፖለቲካዊ ቀውስ ስንቱን ፓርቲና የተቃዋሚ መሪዎች እየደፈጠጠ ሲያልፍ ማኅበረ ቅዱሳን ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ታዛ ተጠልሎ አልፏል።ኢህአዴግ ቢያጠፋው ኖሮ ያኔ ባጠፋው ነበር። 

ከዚህ በፊት ማኅበሩ እንደጥራጊ አውጥቶ የጣለው ዳንኤል ክብረት ይህን ኢህአዴግ ሊበላኝ ነው የሚለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ዘፈን እንዲህ ሲል በደጀሰላም ብሎግ ላይ አውጥቶ ነበር።
«እኔ እንደምገምተው የማኅበሩ አባላት መንግሥትን እንዲፈሩ እና እንዲጠሉ የሚፈልጉ አካላት በአመራሩ ውስጥ ሳይኖሩ አይ ቀርም፡፡ ምንጊዜም አንዳች ከባድ ነገር ሲነሣ መንግሥት እንዲህ ብሎናል፣ በዚህ ስብሰባው እንዲህ ብሏል፣ ሊዘጋን ነው፣ ሊያስረን ነው፣ ሊጨርሰን ነው ከማለት ያለፈ አንድም ቀን በጎ ነገር ስለ መንግሥት የማያነሡ አካላት አሉ»
 ስለዚህ ከዚህ አባባል ተነስተን ልንል የምንችለው ነገር ይህ መንግሥት ሊበላን ነው የሚለው ዜማ እንደስልት የተያዘና መንግሥት በአባላቱ ዘንድ እንዲጠላ የተዘየደ መሆኑ ነው። ከዚያም ባሻገር መሰሪ ስራውን ለመደበቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ለመሳል የታቀደ ጥበብ ሲሆን ጻድቁ ማኅበረ ቅዱሳንን ኢህአዴግ ሊያጠፋው ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ ሁሉ የዚህን መንግሥት መሠሪነት ተመልከቱ ብሎ ክፉ ስዕል ለመስጠት የተፈለገ ብልጠት ነው።
እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ነጋዴ ድርጅት መሆኑ ማንም ያውቃል። የግል ይሁን የአክሲዮን ማኅበር መሆኑ ያልታወቀና የራሱን ሀብት የፈጠረ ተቋም ስለመሆኑም ስራው ምስክር ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ከንግድ ተቋማቱና ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮቹ ባሻገር የራሱ የሆኑ አባላት ያሉትና የአባልነት መዋጮ የሚሰበስብ ድርጅት ነው። ከዋናው ማዕከል ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቁመት የራሱ የሆነ መዋቅርና  ራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ነገር ግን አደረጃጀቱ በየትኛው የሀገሪቱ  የአደረጃጀት ፈቃድ ላይ እንደቆመ ያልታወቀ መሆኑም እርግጥ ነው። ይህንን የራሱ ተቋማዊ ኅልውና ያለውን ማኅበር በሀብቱ፤ በንግድ ተቋማቱ፤ በመዋቅራዊ አካላቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቆጣጠርና የማዘዝ ምንም ሥልጣን የላትም።  በአንጻሩም ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስር ተሸፋፍኖ እንደመጠለሉ መጠን ቤተ ክርስቲያኒቱ በማኅበሩ ላይ የመቆጣጠርና የማዘዝ ሥልጣን እንዳላት ግምት ያለው በመሆኑ መንግሥት ይህን ድርጅት ነክቶት አያውቅም። ስለዚህ ይህንን ማኅበር ቤተ ክርስቲያኒቱም፤ መንግሥትም ሳይመለከቱት ከሁለት ወገን ቁጥጥር ነጻ ሆኖ 22 ዓመት ዘልቋል። 
 «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲሉ ሆኖ ማኅበሩን ማነህ? ምንድነህ? የት ነህ? ምን አለህ? ምን አገባህ? የሚሉ ካህናትና የአመራር አካላት ተባብረው በመነሳት መጠየቅ ሲጀምሩ ጥቂት ሟሳኞችና አሟሳኞች ወደሚል ሃሳብ ለመውረድ ተገዷል።  በምንም ደረጃ ያሉ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳንን መክሰስ መቻላቸው የማኅበሩን ማንነት ማሳያው ተግባሩ እንጂ ክሱ አይደለም።  እየተከሰሰ ያለው ማኅበር በተግባሩ ያልታወቀ ማኅበር ባለመሆኑ በሟሳኞችና አሟሳኞች የቃላት ጫወታ እየፈጸመ የቆየውን ሸፍጥ ሸፍኖ ማስቀረት አይቻልም።
ማኅበረ ቅዱሳን በተግባር በሌለው ሥልጣንና መብት መናፍቃን ናቸው ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን በራሱ ጥቁር መዝገብ አስፍሮ አስደብድቧል፤ ሰልሏል፤ ስም አጥፍቷል፤ አስፈራርቷል፤ እንዲሰደዱ አድርጓል። ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ስም መጽሔትና መጻሕፍትን፤ ካሴትና ቪዲዮ፤ አልባሳትና ንዋየ ቅድሳትን ከታክስና ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ነግዷል። የማኅበረ ቅዱሳን አቋም የሚቃወሙ ሁሉ ጠላቶቹ ናቸው። የሚደግፉት ደግሞ ጳጳሳቱ ሳይቀሩ ወንጀል ቢኖርባቸው እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ታማኝ አገልጋይ ተደርገው ዜና ይሰራላቸዋል፤ ሙገሳ ይሰጣቸዋል። አባ እስጢፋኖስን ማንሳት ይቻላል። ጠላቶቼ ከሚላቸውና ስማቸውን ሌሊትና ቀን ሲያጠፋቸው ከቆዩት ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ደግሞ የጥላቻ የአፍ መፍቻው ናቸው። ሌሎቹም ፈርተው አንገታቸውን ደፍተውለታል። የተገዳደረውን አንገት ያስደፋል፤ አለያም ቀና ካለ አንገቱን ይሰብራል።  ሌላው ቀርቶ ሲያመሰግናቸው የነበሩትን አዲሱን ፓትርያርክ ጠላቶቼ የሚላቸውን ሰዎች ሲቀጣ በቆየበት መልኩ በስም ማጥፋት ቅጣት ናዳውን እያወረደባቸው ይገኛል። ለራሱ ኅልውና ብቻ የሚጨነቅ፤ ካልመሰለው ደግሞ ሲያወድሳቸው ለነበሩት ሳይቀር ግድ የሌለው ማኅበር ስለመሆኑ ከድርጊቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።  ወትሮውንም ሸፋጭ ነጋዴ ገንዘቡን እንጂ ወዳጅና እውነት በእሱ ዘንድ ዋጋ የሌላቸው ስለሆኑ የሚያስበው ጊዜያዊ ትርፉን ብቻ ነው። በዚህ ዙሪያ ማኅበሩ አሸንቅጥሮ የጣለውና ለተቀበለው የእጅ መንሻ በውጪ እንዳለ የሚለፈልፈው ዳንኤል ክብረት ማኅበሩ ስለግለሰቦችና ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ደንታ ቢስ እንደሆነ ያጋለጠው እንዲህ ሲል ነበር።
«ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው? ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ? በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም፡፡ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሣ ቤተ ክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ፡፡ ማኅበሩ አቡነ ጳውሎስን በተመለከተ የተለየ አቋም መያዝ የጀመረው መቼ ነው? «እርሳቸው ማኅበሩን ሊያፈርሱ ነው» ብሎ መሥጋት ከጀመረ በኋላ፡፡ አባ ሠረቀንም ቢሆንኮ ዛሬ ዛሬ በእምነት ችግር ይከሳቸዋል እንጂ፣ ከእርሳቸው ጋር ያለው ዋናው ችግሩ ማኅበሩ መነካቱ ነው፡፡ አባ ሠረቀ ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይናገራቸውም ነበር፡፡ ባለፈው ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ችግር ሲፈጠር፣ ዝምታን መርጦ የነበረው አመራር የመንግሥት አካላት ከቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት ጋር ሆነው ስለ ማኅበሩ ሲያወያዩት ግን አገር ይያዝልኝ አለ፡፡ የአዋሳ ምእመናንን ችግር በዝምታ ያለፈው አመራር አባ ሠረቀ አንዳች ነገር ተናገሩ ብሎ ድምፁን አሰምቶ ተናገረ፡፡ እነዚህ እና መሰል ሁኔታዎች አመራሩ የሚቆረቁረው ማኅበሩ ሲነካ እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ አለመሆኑን ያመለክታሉ» ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ በላይ ማንንም እንደማይወድ እርግጥ ነው። የራሱን ድክመት ቆም ብሎ በመገምገም ለመስተካከል ከመሞከር ይልቅ አንገቱን በማደንደን ወደ ስድብ፤ ዛቻ፤ ማስፈራራትና ስም ማጥፋት ይሮጣል። ይህም በመሆኑ ማኅበሩ የሚጠፋው በራሱ ተግባር እንጂ በቅንነቱ ወይም በቀናዒነቱ አይደለም። ይህም ማለት ግን ቀናዒና ቅን አባላት የሉትም ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። ቅን አባላቱ ጠማማውን አመራር ማስተካከል የሚችል አቅም የላቸውም። ማኅበሩ ራሱ የሚመራው በቡድናዊ ስልት ስለሆነ በቡድን ይመታሉ፤ በቡድን ይወገዳሉ። 
ማኅበረ ቅዱሳን በፖለቲካው ዙሪያ ከምርጫ 97 በፊትም ሆነ በኋላ ስላለው ሁኔታ መንግሥት በቂ መረጃ እንዳለው ይሰማል። በዚህ ዙሪያ መንግሥት ያለውን መረጃ እስኪያወጣ ድረስ የምንለው ነገር የለም። ነገር ግን ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያምሳት መቆየቱን፤ እጁን እያስገባ ሲኖዶሱን ሳይቀር እንደሚጠመዝዝ እናውቃለን። ማኅበሩ ደፋርና የልብ ልብ የተሰማው አንዳንድ የሲኖዶስ አባላት ተጠግቶ የጉባዔ ሃሳብ በራሱ መንገድ እስከመጠምዘዝ የመድረሱን አቅም እየለካ በመሄዱ ነው። ዛሬ ላይ ያ ነገር የለም። ፓትርያርክ ማትያስ ለዚህ የማኅበሩ ሃሳብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ገና አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥረው ሊያጠፉኝ ነው እያለ ስም ወደማጥፋት ወርዷል። በተቃራኒው ደግሞ ማንም እንደማያጠፋው በሚገልጽ ጀብደኝነቱ ፓትርያርክ ጳውሎስም እንደዚሁ ሊያጠፉኝ ሞክረው እንደማያዋጣቸው አውቀው አጃቸውን ከእኔ ላይ ለማንሳት ተገደዋል በማለት ለፓትርያርክ ማትያስ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ እየሰራ ይገኛል። እጅዎን ከእኔ ላይ የማንሳትን ጉዳይ ችላ ሳይሉ ከቀድሞው ፓትርያርክ ትምህርት ውሰዱ በማለት ማሳሰቢያ እየሰጠ መሆኑ ነው። 
የሚፈራው ከተገኘ ጥሩ ጀብደኝነት ነው፤ ነገር ግን ባለቀ ጊዜ ማላዘን ዋጋ የለውም። ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኒቱ ስንት ችግር ባለባት ሰዓት ራሱ ችግር ፈጣሪ ሆኖ ካለቦታው የተገኘ ማኅበር ስለሆነ ተገቢ ቦታውን መያዝ ካለበት ሰዓቱ አሁን ነው። ማኅበረ ካህናቱና የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር አባላት ጠንክሮ መታገል የሚገባችሁ ወቅት ቢኖር ዛሬ ነው። ማኅበሩ ቁጭ ብሎ አዋጭ የሆነውን መንገድ መቅረጽ ካለበት ቶሎ ብሎ ይህንኑ እንዲፈጽም ምክር እንለግሰዋለን። የአክሲዮን ማኅበር፤ የሃይማኖት ተቋም፤ በጎ አድራጊ ድርጅት ወይም የተሻለ ነው ብሎ የደረሰበትን ውሳኔ ወደተግባር መቀየር ካለበት ቀኑ ሳይመሽ በብርሃኑ ይሆን ዘንድ ልናሳስበው እንወዳለን። ሲሆን ዘንድሮ፤ ካልሆነም በቀጣዩ ዓመት፤ ቢረዝም፤ ቢረዝም አንድ ቀን ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጉያ እንደመዥገር የተጣበቀበት ቀን እንደሚያበቃ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምክንያቱም ማኅበሩና ተግባሩ፤ ካህናቱና አስተዳደሩ መቼም ቢሆን አሁን ባለው መንገድ አብረው መጓዝ አይችሉምና ነው።  ከዚህ ሁሉ ፓትርያርኩም፤ ካህናቱም፤ አመራሮችም፤ መንግሥትም ይህንን ማኅበር ቦታ የማስያዙን ጉዳይ ችላ ሊሉት አይገባም። ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን ነበረች፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖርም ትኖራለች!!!  «ማኅበረ ቅዱሳን ከሌለ ቤተ ክርስቲያን ትጠፋለች» የሚለው ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ነው።

Friday, October 17, 2014

ካሕናቱና ማኅበሩ…እንዴት ተጃመሩ(ተጀማመሩ)???…

 ( በአማን ነጸረ )

 - ልክ የዛሬ አመት በተካሄደው አመታዊው የሰበካ ጠቅላላ ጉባኤ የምዕራብ ሸዋዎቹ አቡነ ሳዊሮስና ስ/አስኪያጆቻቸው “ማኅበሩ በሀገረ ስብከታችን ጣልቃ እየገባ አላሰራን አለ” የሚል ሪፖርት አቀረቡ፡፡ጉባኤው ለሪፖርቱ ያለውን ድጋፍ በእጁ ብቻ ሳይሆን በእግሩ ጭምር መሬት እየደበደበ በድምድምታ ታግዞ ገለጸ፡፡የዚህ ትርጉም ‘መናገር ፈርተን እንጅ በሁላችንም ሀገረ ስብከት ጣልቃ እየገባ ነው’ የሚል ነበር፡፡መፍትሄውም የራሱን የማኅበሩን አካሄድ መፈተሽ ነበር፡፡ማኅበሩ ያደረገው ግን በኅቡዕ ሚዲያዎቹ ጳጳሱንና ስ/አስኪያጆቹን ማብጠልጠል ሆነ፡፡የእነሱ ኃጢኣት የማኅበሩን ጥፋት ይሸፍነው ይመስል ጳጳሱን ‘ሺበሺ’፣መነኩሴውን ‘ዘማዊ’፣ካሕኑን ‘ካንድ በላይ ያገባ’ እያለ በኅቡዕ መዝለፉን ቀጠለ፡፡

2 - በሂሳብ ሙያ 25 አመታት ልምድ አለን ያሉ የጠቅላይ ቤተክሕነቱ ሰዎች ማኅበሩ በቤተክሕነት ስር እስከሆነና ተጠሪነቱም ለኛ እስከሆነ ድረስ በራሳችን ሰዎች ኦዲት ይደረግ፣የራሳችንን ደረሰኝ ይጠቀም የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ጉባኤው አሁንም ድጋፉን ገለጸ፡፡የማኅበሩ ተወካዮች ግን ጉባኤውን ረግጠው ወጡና በተለመዱት ኅቡዕ ሚዲያዎቻቸው የቤተክሕነቱን የአቅም ውሱንነትና የደረሰኞቹን ለሂሳብ አያያዝ ምቹ አለመሆን በመግለጽ ጥያቄውንና ጠያቂዎቹን ለማንኳሰስ ተሽቀዳደሙ፡፡ ‘እንዲህ አይነቱን አሰራር እኮ ማስተካከል የሚቻለው ከአስተዳደሩ በመራቅና እሱን በማራከስ ሳይሆን ውስጥ ገብቶ ራሱን ተቋሙንም አግዞ ከችግሩ ለመውጣት ያብሮነት ተጋድሎ በማድረግ ነው’ ብሎ ለመናገር ይቅርና ይሄን ሀሳብ ማሰብም ኑፋቄ ነው ተባለ፡፡

3 - ቀጠሉና ቤ/ክ ትዘምናለች፤አስተዳደሯ ይስተካከላል የሚል መፈክር አነሱ፡፡መፈክሩ ሁላችንንም አማለለን፡፡በገዳማውያን ጸሎት በመታገዝ 3 ሚሊዮን የፈጀ ጥናት አቅርበናል ‘ወንዶች በጭብጨባ ሴቶች በእልልታ’ ተባልን፡፡ከማኅበራዊ ሚዲያ እስከ ዐለማዊ ጋዜጦችና የዲያስፖራው ሚዲያ ተቀባበለው፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ጥናቱ ለሚመለከተው አካል ደርሶ ገና አልጸደቀም፤ካሕናቱም አልመከሩበትም፡፡ቀጠለ፡፡ካሕናቱና ምዕመናኑ ስለ ጥናቱ ስልጠና ተብሎ አራት ኪሎ ላይ ከተሙ፡፡ጉዳዩ ግን ስልጠና ሳይሆን ራስን መስበኪያና ጥያቄዎችን ማፈኛ ወደ መሆን አዘነበለ፡፡

4 - ከአጥኚው ክፍል ውስጥ ከ12ቱ 8ቱ የማኅበሩ አባላት ሲሆኑ በቋሚ ትክለኛ አገልጋይ ደረጃ ደግሞ አንድ ጸሐፊ መሀላቸው ጣል ተደርጓል፡፡ካሕናቱ እዚህ ላይ ጥያቄ አነሱ “በጥናቱ ውስጥ እኛን የሚወክል ሰው የታለ?” አሉ፡፡ “ጉዳያችሁ ከጥናቱ ጠቀሜታ ነው ወይስ ከአጥኚው?” እየተባለ ትርፍ ንግግርና አፈና ተጀመረ፡፡ነገርየው “እኛ ስለናንተ ጥቅም ስለምናውቅ ባትሳተፉ ምን ቸገራችሁ--እናውቅላችኋለን” በሚል እንደሚተረጎም ማን አስቦት!!እነሱ እንደሆነ ቀናኢነታቸው ከማንም በላይ ነው!!ጥያቄው ቀጥሏል!! “ያጠናችሁት ጥናት የቤ/ክ የበላይ ሕግ በሆነው ቃለዐዋዲ የታቀፉ ነባር የስራ መደቦች ላይ ሽግሽግ የሚያደርግና የተወሰኑ ኃላፊነቶችን ጨምሮ እንደ አዲስ የሚደለድል ስለሆነ ቃለዐዋዲውን ቀድሞ መመሪያው መምጣቱ ከፈረሱ ጋሪው (በሐጋጊዎች አነጋገር against hierarchy of law) ሆነሳ?” ቢባል!! እረ ወዲያ!!ማን ሰምቶ!! አማሳኝ፣ ዘረኛ፣ ተሐድሶ፣ ካድሬ፣ ወያኔ፣ ሌባ፣ ሙሰኛ፣ምንደኛ፣ተላላኪ፣ደደብ፣ምቀኛ፣ሸረኛ…..የስድብ ሜኑ ተደረደረ!!

5 - አሁን ፅዋው ሞላ!!የአድባራትና ገዳማት አለቆችና ፀሐፊዎች መጋረጃውን ገልጠው ወጡ!!በይፋ ተሰባስበው በቤ/ክሕነቱ አዳራሽ አጀንዳቸውን ቀርጸው ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡ገና በጠዋቱ መንገዳቸው ላይ ያለውን ፈተና ተገንዝበውት ነበር፡፡የማኅበሩ ኅቡዕ ሚዲያ የ30 እና 40 አመት አገልግሎታቸውን አፈር አስግጦ ዛሬ እሱ ላይ ጥያቄ ስላነሱ ብቻ ስማቸውን ጭቃ ከመቀባትም አልፎ በራሳቸውና በሚቀርቧቸው ሰዎች ጭምር እንደሚመጣባቸው እንደሚጠብቁ በአደባባይ ተናገሩ፡፡እነ ፋክት መጽሔት፣እነ ‘ቀናኢ ነን’ ብሎጎች የአደባባዩን አቋም “ጥብቅ ምስጢር” እያሉ ቲፎዞ ማንቀሳቀሳቸውን ቀጠሉ፡፡አልገረመንም!!ብሎግን ከግል ኅትመት ሚዲያ አቀናጅቶ በማኅበሩ አካሄድ ጥያቄ ባነሱ ሁሉ መዝመት ከሚሊኒየሙ ማግሥት ጀምሮ እንደ መልካም ትውፊት ስለተያዘ!!

6 - የካሕናቱ በአለቆችና በፀሐፊዎች መያዝ ባሰጋው ማኅበር ቀስቃሽነት ጉዳዩን የምዕመናንን መብት የማስከበር አስመስሎ ከ40 አመት በፊት በሰበካ ጉባኤና በልማት ኮሚቴ እየተመረጠ ከካሕናቱ ጎን ለጎን በቤ/ክ ጉዳይ ውሳኔ ሰጭ የሆነውን ምዕመን ሆድ ለማስባስ ተሞከረ፡፡ “መሬት አንቀጥቅጥ ሰልፍ እንጠራለን፣የአማሳኞችን ገመና እናወጣለን” ተባለ!!ተፎከረ!! ‘እረ ቀስ’ የሚል አልነበረም!! ‘ገመና-ገመና የሚባለው አካሄድ የሚሰራው ሰዎቹ ያጠፉ እለት እለቱን እንዲታረሙና ማስረጃውም ገና ትኩስ እያለ ቢሆን እንጅ ማኅበሩን ሲያነሱ ብቻ ከሆነማ ማኅበሩን ሳያነሱ ስለሚያጠፉት ሰዎች ደንታ የላችሁም፤ስለዚህ እናንተ ቤ/ክ ተጎዳች ምትሉት ማኅበሩ ላይ ጥያቄ ከተነሳ ብቻ ነው’ ያሰኝብናል የሚል ይሉኝታ እንኳ የለም!!ወደ ፊት ብቻ!!በዚህ መሀል ካሕናቱ በጥናቱ ይዘት፣በአጥኚው ስብጥር፣በጥናቱ የስልጠና ሂደት ያላቸውን ቅሬታ በመጠኑ ፈንገጥ ካለና ስሜታዊነት በታከለበት አኳኋን የማኅበረቅዱሳንን ሥም እየጠሩ አስረዱ--ለቅ/ፓትርያርኩ፡፡

7 - ‘የለውጥ አራማጅ ነኝ፣ተነቃናቂ ኃይል አለኝ፣ተወደደም ተጠላም ጥናቱ ሳይሸራረፍ ይተገበራል’ የሚለው ቡድንም በጋዜጣና በብሎግ ተጠራርቶ ፓትርያርኩ ላይ ገብቶ አጀንዳውን አስረዳ፡፡ፓትርያርኩም “ጥናቱ በሊቃውንት ክለሳ ተካሂዶበት ለቤ/ክ በሚበጅ መልኩ ይተገበራል፤ቀደም ሲል የመጡት ካሕናትም ጉዳያቸውን ማስረዳት መብታቸው ቢሆንም ዳኅፀ - ቃል (የምላስ ወለምታ) አድርገዋል” ብለው በአባታዊ መንገድ አስተናገዱ፡፡እዚህ ላይ ጨዋታው ፈረሰ!! ‘ጥናቱ አሁኑኑ’ የሚለው ኃይል የጭቃ ጅራፉን ያጮኸው ጀመር!!ጮኸ-ጮኸ-ጮኸ!!ይሄን ጩኸት ከኋላ ሆኖ ይዘውረው የነበረው ማኅበርም በጩኸቱ ተበረታቶ ነው መሰለኝ መጋረጃውን ገልጦ ወጣና ልሳኔ-የግሌ በሚል ስሜት ሐመር መጽሄቱን መዶሻ፣አቤቱታ አቅራቢዎቹን ካሕናት ደረቅ የማገዶ ግንድ አድርጎ አማሳኝ፣ተሐድሶ…እያለ ፈለጣውን ቀጠለ!!

8 - ካሕናቱ ግን ወይ ፍንክች!!ከነብር ተፋዞ (ተፋጦ) ማን እንቅልፍ ያበዛል!!እስከ በታች ሰራተኛ ወርደው 5ሺህ የሚገመት ፊርማ አሰባሰቡ፣ኮሚቴ አዋቀሩ፣መንግሥት እንዳይገላምጣቸው አሳወቁ (በመንግሥትም ተሰግስግንበታል እየተባለ ማስፈራሪያ ሆኗላ)፣ዐላማቸው ማኅበሩ ቤ/ክ ባሰመረችለት ልክ ከመጓዝ አልፎ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም እንጅ ማኅበሩን ለማፍረስ አንዳች ፍላጎት እንደሌላቸው ተናገሩ፣የተላተምነው አድማሳትን የሚያቋርጥ የሚዲያ መረብ ከዘረጋ አካል ነውና በአስተዳደር ላይ ያላችሁ ራሳችሁን ካላስፈላጊ ምግባርና ከተበላሸ አስተዳደር ጠብቁ፣በተቻለ መጠን አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ ከሚሰጠው የተሐድሶዎች እንቅስቃሴ አጀንዳችንን እንጠብቅ…የሚሉ መርሆዎች ተቀመጡ፡፡

9 - እንቅስቃሴው ከላይኛው የቤተክሕነት አካልም ቀላል የማይባል ድጋፍ አገኘ፡፡በፓ/ኩ ዕለተ - ሲመት የካቲት 24 በተደረጉ ቅኔያት ይሄው ሀሳብ…ወቤቴል አሀቲ ኢትኩን ዝርውተ፣አኃዝ ማኅበራተ፣መዋግደ ብዙኅ ፀጋከ ወአስተናድፍ ሥርዓተ…በሚሉ የሊቃውንት ቅኔያት ተንፀባረቀ፡፡ማኅበሩ ግን ይሄንን ከቅርቡ ያሉ ሊቃውንት ውትወታ ከመስማት ይልቅ ለሚመለከተው መምሪያና ላሉበት ሀገረ ስብከት ሳያሳውቅ የጠረፎቹን እየጠራ “ለማናውቀው ስብሰባ ኃላፊነት አንወስድም” ሲባል….የኛ ቤት እንደምታውቁት…እያለ የአዞ እንባውን መርጨት ጀመረ፡፡ታዲያ ሚዲያው አልሰነፈም!!ጉዳዩን ሲፈልግ ከወያኔ አነሳስ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ከተሐድሶ እንቅስሴ ጋር እያገናኘ ማኅበሩ ራሱን የሚያይበትን ውስጣዊ ዐይን ዐውሮ በትምክሕቱ እንዲጀቦን የውዳሴ ከንቱ ቡልኮ አጎናጸፈው፡፡ “አንድ ለእናቱ” እያሉ የቤተክርስቲያኒቱን የ2ሺህ አመት ታሪክ ለ20 አመቱ ማኅበር አሸክመው አንገዳገዱት፡፡ውስጡን እንዳይመለከት ጋረዱት!!

10 - እናም ይሄው አባላቱ ማኅበሩን የበጎነት እና የክፋት፣የጽድቅና የኩነኔ መለኪያ አድርገው ኮሽ ባለ ቁጥር ፡- ራሳቸውን መድኅን ቅሬታ አቅራቢዎችን ሰቃልያነ - እግዚእ፣ራሳቸውን ድመት ሌላውን አይጥ፣እነሱ ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ ሌላው መናፍቅ፣እነሱ ለነፍስ ያደሩ ሌላው ለሆዱ….እያሉ እያስመሰሉ የልዩነት መስመር ሲያሰምሩ ይውላሉ፡፡የሚበዙት አባላቱም ማኅበራቸውን ከመፈተሸ ይልቅ ዕቡያን ክሶቹን ተቀብው አሜን-አሜን ይላሉ!!ይህ የማኅበሩ ከመዋቅር እና ከማዕከላዊ አስተዳደር የማፈንገጥ ዝንባሌ፣ስሙን ባነሱ የቤ/ክ ልጆች ላይ ሁሉ ከቅ/ሲኖዶስና ከፍርድ ቤት ውሳኔ በፊት የሚያደርገው “የተሐድሶ እና አማሳኝ” የውንጀላ ዘመቻ ለቀሳጥያን ተሐድሶዎችና የእነሱ ልሳናት ለሆኑ ብሎጎች ምን ያህል መንገዱን ጨርቅ እንዳደረገላቸው አልተረዱም!!እነዚህ በቁም ያሉትን፣እነዛ ደግሞ በቅድስና ያረፉትን ክብር በማጉደፍ ምዕመኑ ላይ የእጓለማውታነት ስሜት ለመፍጠር ይታትራሉ!!ከንቱ መታተር!!ፍኖተ ሐኬት--የክፋት መንገድ!!

Wednesday, October 8, 2014

«የማዕተብ ጉዳይ ሰሞነኛ ወሬ»


 
ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ «የኦርቶዶክሱን ክር እናስበጥሳለን» ብለዋል በማለት ማስጮሁን የጀመረው አሉላ ጥላሁን የሚባለውና የማኅበረ ቅዱሳኑ አባል የሚነዳው «ሐራ ተዋሕዶ» መካነ ጦማር ነው።  ድርጅት እንጂ እምነት የሌለው ሁሉ ያንን ተቀብሎ አስተጋባ። በእርግጥ ዶ/ር ሽፈራው ብለውታል? ወይስ አላሉትም? የሚለው ጉዳይ ማረጋገጫ የሚያስፈልገው  ቢሆንም «ራስ ሲመለጥና አፍ ሲያመልጥ አይታወቅም» እንዲሉ ዶ/ሩ ብለው ሊሆን ይችላል ብለን ብንገምት እንኳን ይሄንን ያህል ማስጮህና ማጦዝ ያስፈለገው ለምንድነው? ብለን መጠየቅ ተገቢ ይመስለናል።

1/ ምክንያታዊነቱ፤

    አዲስ ይወጣል በተባለው የሴኩላሪዝም ደንብ በመንግሥት የሥራ ቦታዎች ውስጥ ሃይማኖታዊ የሆኑ ምልክቶች ማለትም ስዕል ማድረግ፤ በጠረጴዛም ይሁን በግድግዳ መስቀል ማንጠልጠል፤ የኮምፒውተር ስክሪን ሴቨር ማድረግ፤ መንፈሳዊ ጥቅሶችን፤ ሂጃብ፤ ኒቃብ፤ ቡርቃና ሌላ ተመሳሳይ ሃይማኖታዊ ምልክቶች እንዳይኖሩ የመከልከል ደንብ እየወጣ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።

  እነዚህ ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እንደፈለጉ መጠቀም ከዚህ ቀደም ባለፉ ሥርዓታት ዘመን ያልነበሩና አዲስ የፈጠራ ልምዶች እርግጥ ነው። ዲሞክራሲ ያሰፈናቸው ወይም ዘመን የፈጠራቸው ናቸው ወይ? ብለን አንከራከርም።  ነገር ግን ሁሉም ሃይማኖት ከማን አንሼ ሰበብ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የሚያደርግ ከሆነ ወይም «እኔን ደስ የማይለኝ ነገር በሥራ ቦታዬ ላይ ተቀምጧል፤ ስለዚህ እንዲወገድ ይደረግልኝ» በማለት ቢቃወም ሰላማዊ የሥራ ሁኔታውን ወደሃይማኖታዊ ንትርክና ጭቅጭቅ ሊቀይር መቻሉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ከዚህ በፊትም ይህ ክሰተት ተፈጽሞ «መብቴ ነው!»  «መብትህ አይደለም!»  ወደሚል አተካራ ማስገባቱን ያጋጣመቸው ሰዎች ሲናገሩ ተደምጧል። 

  ለመሆኑ ደመወዝ ሊከፈለው ውል ፈጽሞ በገባበት የሥራ ቦታ ሃይማኖታዊ ምልክቶችን ማስቀመጥ ለምን አስፈለገ? ነገሩን ስንመለከተው ብዙ ጊዜ ሃይማኖታዊ ምልክቶችን ባልተፈቀደ ቦታም ይሁን ተገቢ ባልሆነ ሥፍራ ለማሳየት የሚፈልጉ ሰዎች «እኔ እበልጣለሁ» ወይም «ሃይማኖቴን በጣም እወዳለሁ» በሚል ስሜት ሌላውን ለማሳነስና እነሱ በእምነታቸው የተሻሉ መሆናቸውን ለማሳየት የሚፈልጉ ሰዎች ይመስሉናል።  የዚህ ተቃራኒ ደግሞ «እኔም አላንስም» በማለት ሌላውን ለመቃወም የራሱን ምልክት በተደራቢነት ለመጠቀም የመፈለጉ አዝማሚያ ወይም «ይነሳልኝ» ሲል ክስ የማቅረቡ ሁኔታ ያለውን የእኔነት ውጥረት ለማርገብና አደብ ለማስያዝ መንግሥት መፈለጉ ከተገቢነቱ አኳያ አያጠያይቅም። በየቦታው እየሄዱ በስመ ስብከት ሰበብ «ኢየሱስ ጌታ ነው» እያሉ የግል ነጻነትን ሳያስፈቅዱ እንሰብካለን ሲሉ ከግለሰብ ጋር የሚጋጩትን ጨምሮ በሃይማኖት ሽፋን የሌላውን መብትና ነጻነት መጋፋት ተገቢ አለመሆኑም ትክክል ነው።

  «እኔ የተሻልኩ ነኝ» በሚል ራስን የማግዘፍና በፈጣሪ ፊት ያለውን ተመራጭነት ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር ምልክትን መደርደር፤ አብዝቶ መናገር ወይም ራስን ለማሳየት መሞከርና የየትኛው ሃይማኖት ተከታይ እንደሆንክ ማስተዋወቅ በእግዚአብሔር ፊት የበለጠ ተወዳጅ መሆንን ሊያሳይ አይችልም። ስለዚህ የትኞቹም ምልክቶች የፊት ማሳያ እንጂ የልባችን ተግባር መግለጫዎች ስላይደሉ አስፈላጊነታቸው ምክንያታዊ አይደሉም። የክርስትና ወይም የእስልምና ምልክት አድርጎ የሚሰርቅ ወይም የሚያመነዝር ትውልድ ምልክት ስላደረገ እንደ እውነተኛ ሰው ሊቆጠር አይችልም። 

«ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና» ሉቃ 16፤15

የሃይማኖታዊ ምልክት ፉክክር የጥፋት መጀመሪያ ነው። አንድ ሰሞን «አንድ እምነት፤ አንዲት ጥምቀት፤ አንድ ጌታ» የሚለውን ጥቅስ በልብስ ላይ አትመው የለበሱ ሰዎችን ለመገዳደር በሚመስል መልኩ «ኢየሱስ፤ መሐመድና ሙሴ የአላህ ነብያት» የሚል ጥቅስ ለብሰው የሚዞሩ ወጣቶችን ማየቴን አልረሳውም። ሃይማኖቱን በተፈቀደለት ቦታና በሥፍራ እንደመጠቀም ከሌላው የተሻለ እውነተኛነት እንዳለው ለማሳወቅ በሚደረግ ሩጫ ጥፋት ለማስከተል መሞከር የነበረውን ሰላም ከማደፍረስ በስተቀር በዚህ አድራጎት የሚታነጽ ማንም የለም።

«እንዲሁ ደግሞ እናንተ መንፈሳዊ ስጦታን በብርቱ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ እንዲበዛላችሁ ፈልጉ» 1ኛ ቆሮ 14፤12

2/ የክር እናስበጥሳለን ፉከራና የተቃውሞ ዘመቻ፤

ከላይ በመግቢያችን ላይ እንደጠቆምነው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ላይ «ሂጃብ እንዳስወለቅን ክርም እናስበጥሳለን» ብለዋል የተባለው ጉዳይ እውነት ነው ወይ?   
«ሃይማኖታዊ ምልክቶችን ከመንግሥት የሥራ ቦታዎች ውስጥ እናስቆማለን፤ ሴኩላር የሆነ የሥራ ቦታ እንፈጥራለን» በሚለው እሳቤ ዙሪያ ከአንገት ላይ ክርም እናስበጥሳለን» የሚለውን ፉከራ በምን መስፈርት እንደተመለከቱት ግልጽ አይደለም። እንደእውነቱ ከሆነ ክር አንገት ላይ ማሰር ሌላውን አማኝ አያውክም። ለጌጥ ብሎ ሀብል ከሚያስር ሰው የተለየ ነገር የለውም። መንግሥት እስከዚህ ድረስ የወረደ ተግባር ይፈጽማል ተብሎ አይታሰብም። ተብሎ ከሆነ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው እንላለን።
 ዶ/ር ሽፈራው ብለዋል ከተባለ በኋላ የገቡበትን አጣብቂኝ ለመከላከል እንደሆነ ለጊዜው ባይገባንም የጉዳዩን ጡዘት በማርገብ ደረጃ  በመንግሥታዊው ሚዲያ «ፋና ብሮድ ካስቲንግ» ቀርበው አላልኩም በማለት አስተባብለዋል። «ቤን» የተባለው አፍቃሬ መንግሥት ድረ ገጽ አዘጋጅም ጥያቄ አቅርቦላቸው አለመናገራቸውን ገልጸዋል። «እንደዚህ አላልንም» ካሉት በላይ የምንጠብቀው ምላሽ አይኖርም።
 ነገር ግን በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሃይማኖታዊ የሆኑ ምልክቶች ሁሉ እንዳይኖሩ እናደርጋለን ተብሎ ከተዘጋጀው ደንብ ውስጥ ከተዘረዙት ሁሉ በአራጋቢዎቹ ዘንድ የዚህ የክር ጉዳይ ብቻዋን ለምን ተነጥላ ወጣች? ነው ጥያቄያችን። ይህንን ጉዳይ አስቀድሞ ያስጮኸው የማኅበረ ቅዱሳኑ «ሐራ ተዋሕዶ» መካነ ጦማር ነው። ሐራ ደግሞ ጅራፏን የምታስጮኸው በማኅበረ ቅዱሳኑ አሉላ ጥላሁን በኩል ነው።

 ብዙ ጊዜ በአፍቃሬ ማኅበሩ ብሎጎች ስማቸው በክፉ የሚወሳው ዓባይ ፀሐዬ፤ ስብሐት ነጋና ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ናቸው።  እነዚህን የፖለቲካ ሹማምንት ማኅበሩና ደጋፊዎቹ የሚቃወሟቸው ማኅበሩ የፖለቲካ ድርጅት ስለሆነ ሳይሆን የማኅበሩን አካሄድ በግልጽ ስለሚቃወሙ ብቻ ነው።  እዚህ ላይ በአንድ ወቅት አቶ ስብሐት ነጋ «ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሸክም» ማለታቸው ሳይዘነጋ ነው። 
በሌላ በኩል ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማኅበር መሆኑም መታለፍ የለበትም። ማኅበሩ  በፓትርያርኩ ላይ ጫና በማሳደር በወዳጆቹ ሊቃነ ጳጳሳት በኩል ማስፈጸም ያቃተውን ቤተ ክርስቲያንን የመረከብ ዓላማ ለጊዜውም ቢሆን የተገታው በሃይማኖት ሽፋን ሀገሪቱን ወደቀውስ መውሰድ ከሚፈልጉ ተቋማት አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው ስለተባለና ስሙ ብዙ ጊዜ ብዙ ጊዜ መነሳቱም አንዱ ምክንያት ነው። በዚህ በኩል ዶ/ር ሽፈራው ብዙ ተጉዘዋል። 

  ማኅበሩ ከአባ እስጢፋኖስ ጀርባ ሆኖ ያረቀቀውና የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የመረከብ ሕግ  ውድቅ ከሆነበት በኋላ የተወረወረበትን ቅዝምዝም ለማሳለፍ ባለፉት ወራቶች አንገቱን ዝቅ አድርጎ ጠብቋል። መጪው ወር የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ይካሄዳል።  በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ውስጥ ያጣውንና ለአባ እስጢፋኖስ መነሳት ምክንያት የሆነው የሕግ ማርቀቅን ጉዳይ ተከትሎ ማኅበሩን አደብ ለማስያዝ በፓትርያርኩ በኩል የቀረቡ ነጥቦች ነበሩ። 

ይህንን ተከትሎ በማኅበሩ ላይ ይጸና ዘንድ ከሚታሰበው ደንብ በፊት ጥቂት ነገር መጫር ሳያስፈልግ አልቀረም። በማኅበሩ ላይ በሴኩላሪዝም ደንብ ስዕልና ጥቅስ በመሥሪያ ቤቶች እንዳይገኙ ከሚከለክለው ጉዳይ ውስጥ ከኦርቶዶክሳውያን አንገት ላይ የሚታሰረውን ክር ነጥሎ በማውጣት ማስጮህ የፈለገው በአማኙ ስስ ስሜት ተጠግቶ ብዙ ተቃዋሚ በማስነሳት አቅጣጫ የማስቀየር ስልት መሆኑ ነው። በዚህም የማኅበሩ አመራር የሆነው አሉላ በተወሰነ መልኩ ተሳክቶለታል። በዶ/ሩ ላይ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሳይቀሩ ተቀባብለው ዘምተውባቸዋል። በዚህም ጫና ይመስላል፤ ዶ/ሩ ሳይወዱ ምላሽ ወደመስጠት የተገደዱት። ብለውም ከሆነ «ካፈርኩ አይመልሰኝ» መሆኑ ነው። ያላሉም ከሆነ አጋጣሚውን ጠብቆ ዱላውን ያሳረፋባቸው ማኅበር ምላሽ በመስጠት የማስገደድ አቅሙን እንዲያዩ አድርጓቸዋል። ወደፊት በማኅበሩ ላይ ተጽዕኖ የማሳደር እስትንፋሳቸውን የመከልከል ዘዴ መሆኑ ነው።  በእርግጥ እንዲያ ከሆነ አያዋጣም።

የሚገርመው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ «ኦርቶዶክሶች ክር የማይበጥሱ ከሆነ እኛም እስላሞቹ ሂጃብ አናወልቅም፤ ቆባችንንም አንጥልም» የሚል ዘመቻ መጀመሩ ነው። ነገሩ አብረን እንጥፋ ነው። «ከኔ ኪስ መታወቂያ ከጠፋ፤ ያንተም መታወቂያ መጥፋት አለበት» ማለት ቅናት እንጂ ጤናማ ክርክር አይደለም። ቡርቃና ኒቃብ ከክር ጋር የሚነጻጸሩት በምን ስሌት እንደሆነ አይገባንም። ትክክልም አይመስለንም። ባለክሮች ስለክር ማሰር ሲጮሁ ባለኒቃቦች ባለክሮችን ተጠግተው ጩኸት አስነሱ። ስለክርም፤ ስለቆብም፤ ስለኒቃብም ማንሳት የማይፈልግ ነጻው ሰው በመንግሥት መሥሪያ ቤት ነጻ ሆኖ እንዴት ይስራ? መልሱ አጭር ነው። ሃይማኖተኞች ሃይማኖታችሁን በተፈቀደላችሁ ቦታ ብቻ ፈጽሙ ነው። ሴኩላሪዝም ማለት ይህ ነው። መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም፤ ሃይማኖታዊ መንግሥትም የለም።

 ነገር ግን ባልተጋነነ መልኩ ሥርዓት ማስያዝ የመንግሥት ድርሻ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሃይማኖታዊ ነገሮችን በጥንቃቄ በመያዝና ከባለጉዳዮቹ ጋር በመነጋገር ማስተካከል እንደሚቻል ጽኑ እምነት አለን። ለምሳሌ ፈረንሳይ ኒቃብና ቡርቃን በሕግ አግዳለች። «ኒቃብ» ዓይን ብቻ የሚታይበት ሲሆን «ቡርቃ» ደግሞ ሙሉ በሙሉ የተሸፋፈነች ሴት አለባበስ ነው። ሳርኮዚ «ለእነዚህ ሰዎች መታወቂያ መስጠት ምን ይጠቅማል?» ሲሉ ጠይቀዋል።
መታወቂያ ማን መሆኑን መለያ ነውና አባባላቸው እውነት ነው። ስለዚህ ክርን ከቡርቃ ጋር ለማስተያየት የምትሞክሩ ጥቂት ተረጋጉ። ከጸጥታ ስጋት አንጻርም ቢያስፈራ አያስገርምም። በ2007 ዓ/ም ያሲን ዑመር የተባለ እንግሊዛዊ አሸባሪ ፈንጂ ታጥቆ እንደሴት ቡርቃ ለብሶ እንደነበር የቢርምንግሃም ፖሊስ ሲያከሽፍበት አይተናል።

  በሌላ በኩል ደግሞ ክር ማሰር የተጀመረው መቼ ነው? ብለን ወደዝርዝር አንገባም። ታሪኩ ረጅም ነው። ነገር ግን «ማዕተብ» ማለት ምልክት ማለት እንደሆነ እንናገራለን። ከክርስቲያንም ኦርቶዶክስ የመሆን ምልክት!
 ክር ማሰር ምልክት እንጂ ሌላ ምንም አይደለም። በአዲስ ኪዳን ስለክር ማሰር የተነገረን ነገር የለም። ማኅበሩ እንደቀድሞ ዋሾዎች የሌለውን ጥቅስ እያቀረበ የወንጌል አስተምህሮ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቢሞክርም ከውሸትነቱ ፈቀቅ ብሎ እውነት ሊሆን አይችልም። ክርስትና እምነት እንጂ ምልክት አይደለም። በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት በማመን የሚኖሩበት ሕይወት ነው። የሚገርመው ደግሞ ሚሊዮኖች ክርና መስቀል አንገታቸው ላይ እያለ የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ይዘርፋሉ፤ ያመነዝራሉ፤ ይሰክራሉ፤ ይሰርቃሉ፤ ይዋሻሉ። የአንገት ላይ ምልክት እንጂ የልብ ላይ ክርስትና የላቸውምና ከዚህ ድርጊታቸው ክር ማሰራቸው በጭራሽ ሊያድናቸው አይችልም።
 እንዲያውም ሥነ ምግባር የሌላቸውን ብዙ ጫት በሊታዎች፤ ሴትኛ አዳሪዎች፤ አመንዝራዎች፤ ሰካራሞች፤ ተሳዳቢዎች፤ ዘፋኞች ሰዎች ልብ ብላችሁ ብታዩ አንገታቸው ላይ ክር ወይም መስቀል ታገኛላችሁ። አንገታቸውን ላይ ምንም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በተመሳሳይ ጥፋት ብናገኛቸው ያላዳናቸው አለማሰራቸው ነው ብንል ምልክቱን አስረው ያጠፉትንስ ለምን አልታደጋቸውም? ብለን መጠየቁ ተገቢ ነው።


  ስለዚህ ከክር ማሰር ጀርባ የራሳቸውን ዓላማ ለማራገብ የሚፈልጉ ቡድኖች ክር ስላሰራችሁ ጻድቅ አትሆኑም፤ ስላላሰራችሁም አትኮነኑም እንላቸዋለን። ክርስትና በክርስቶስ በማመንና የሥጋ ሥራዎችን በመተው የሚጓዙበት ሕይወት እንጂ ክር በማሰር ክርስቲያን መሆንህን ለሰዎች የምታሳይበት የጎዳና ላይ ማስታወቂያ አይደለም። ባለክሮችም እንደባለቡርቃዎቹ ተረጋጉ።
ጥል፤ ክርክር፤ አድመኝነት፤ በወንጌል ቃል ያልሆነ የቃላት ስንጠቃ፤ እውነትን የተቀሙ ሰዎች ተግባር ነው። አንዲቱ ቤተ ክርስቲያን የተከፋፈለችውም በእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ስለተሞላች ነው። የሐራ ተዋሕዶው አሉላ ያልኖረበትን ክርስትና በክር ስር ቢፈልገው አያገኘውም። እንዲያውም ጥፋት በደጁ ታደባለች።
 ክርስትና ስለስዕል ስለመስቀል፤ አንገት ላይ ክር ስለማሰር አይደለም። ክርስቶስን ስለመምሰል እንጂ።
 
«እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥ በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ» 1ኛ ጢሞ 6፤3-5

Thursday, August 14, 2014

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥርዓተ አልበኝነት ነግሷል!

  • የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሲፈራርስ ዝምታው እስከመቼ?
  •  
  •  ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ ጉዳይ ምላሻቸው ምን ይሆን?

ዛሬ ዛሬ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሚለው ቃል ከወረቀት ባለፈ በመሬት ላይ ተፈሚነቱ የሚታየው በጣም በጥቂቱ ነው። በተለይም ቤተ ክርስቲያኒቱ አለኝ በምትለው ማእርገ ክህነት በኩል ዲቁና፤ ቅስና ( ምንኩስና) ቁምስና በሙሉ የሚሰጠው ለማንና መስፈርቱ ምን እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ሥርዓተ የለሽ ሆኖ ይታይበታል። እነ መቶ አለቃ ግርማ ወንድሙ ሳይቀሩ በር የሚዘጋ መስቀል ተሸክመው እያሳለሙ በአጥማቂነት ተሰማርተው ገንዘብ ይሰበስባሉ። ከዚህ በፊት ወደእስራኤል አቅንቶ የነበረው ግርማ ወንድሙ ገና ገንዘብ መሰብሰብ ሲጀምር አንዷን ሴት ሲያጠምቅ ጎረቤቷ ቡዳ ሆና በላቻት በማሰኘቱ፤ ቡዳ ናት የተባለችው ሴት ፍርድ ቤት በስም አጥፊነት ከሳው መጥሪያ ብታመጣበት ሌሊቱኑ ፈርጥጦ ወደኢትዮጵያ ማምለጡን ጉዳዩን በቅርበት ከሚያውቁ ሰምተን ተገርመን ነበር። ባለቤት የሌላትን ቤተ ክርስቲያን እየተዘዋወረ በክፉ መንፈስ የሚበጠብጠው ግርማ አሁን ደግሞ ወደአውሮፓ ዘልቆ በጣሊያን የዘረፋውንና የቡዳ በላሽ ዜማውን እያስነካው ይገኛል። እነባህታዊ ገብረ መስቀል ማርያምን ተገለጸችልኝ እያሉ ህዝቡን ሲያጭበረብሩ እንዳልነበር ብህትውናውን እርግፍ አድርገው ቆንጆ መርጠው ሚስት አግብተው ልጆች ወልደው ማርያም ተገለጸችልኝ፤ ገብርኤልን አየሁት ከሚል ማደናገሪያ ነጻ ወጥተዋል። ከማጭበር በር ይህኛው የተሻለ አማራጭ ይመስለናል።
ይህ ማእርገ ክህነት የሚባለው ሹመት በአንዳንዶች ዘንድ የክብር ዶክትሬት ይመስል ከስም ባለፈና የሕዝቡን ግንባር ከሚገጩበት በስተቀር እንደማኅበረ ቅዱሳን ባሉ ማኅበራት ዘንድም የአገልግሎት ዋጋ የሌለው መሳሪያ ሆኖ ይገኛል። በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን ሲያገለግሉበት አይታይም። የማዕረጉን ስም የሚፈልጉት ክህነት የላቸውም እንዳይባሉና በክህነት ሽፋን በሚገኘው ክብር የመበለቶችን ቤት ለመዝረፍ ስለሚረዳ እንጂ ከመጀመሪያው በድንግልና ጸንተው ለማዕርገ ዲቁና በቅተው «ተንሥኡ፤ ጸልዩ» እያሉ ሲያገለግሉበት ቆይተው፤ በኋላም በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን በተክሊል በድንግልና የጸናች አግብተው አይደለም። ሲጀመር ጀምሮ ዲቁናም ይሁን ቅስና የተቀበሉት ሰዎች ድንግላቸው የፈረሰበትን ጊዜ ራሳቸው በትክክል አያውቁትም። ራሳቸው በድንግልና ሳይቆዩ፤ ድንግልና እንደፈንጣጣ በጠፋበት ዘመን ድንግል አግብተው አይቀስሱም።  በተለይ ወንዶቹ አጭበርባሪዎች፤ ቀሳጮችና መልቴዎች ናቸው። በዚህ ዙሪያ ሀገር ሰፈሩን ሲያዳርሱ የኖሩ የዘመኑ ቀሳውስትና መነኮሳት ነን ባዮች ቅስናን እንደማጭበርበሪያ ይጠቀሙበታል። ቅዱስ በተባለው መቅደስ ገብተው በርኩስናቸው ሕዝቡን ያታልሉበታል። ይህ ዐመፃና ማታለል በሀገር ላይ ጥፋትን፤ በሕዝብ ላይ ቁጣን ማምጣቱ አይቀርም። ማንም እመራበታለሁ ብሎ ላወጣው ለራሱ ሕግ የማይታዘዝ ከሆነ የሚጠፋው በዚያው በራሱ ሕግ ነው።
«ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል» ሮሜ 2፤12
ዛሬ ሁሉም ከዚህ ከራሳቸው የሕግ ክብር ስለወረዱ ማንም ምንንም አይቆጣጠርም። ሥርዓት ፈረሰ፤ ሕግ ተጣሰ የሚል አንድም ስንኳ የለም። «ኩሉ ዐረየ፤ ወኅቡረ ዐለወ» እንዳለው ዳዊት በመዝሙሩ ሁላቸውም ተሳስተዋል፤ ሁላቸውም በዐመጻ ስለተስተካከሉ ዲቁና ሰጪውም ተቀባዩም ከሥርዓት ውጪ ሆነዋል።  ከዚህ በታች የቀረበውም ጽሁፍ ይህንን መሠረት ያደረገ ነው።
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነን «እንበለ አሐዱ ኄር፤ ኢይኀድጋ ለሀገር» ለሀገር እንዲሉ አንድ ተቆርቋሪ ኤርትራዊ ቄስ ከሀገረ እስራኤል-ቴል አቪቭ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለልዩ ልዩ ድረ ገጾች በግልባጭ ሲልክ ለእኛ የደረሰውን ጽሁፍ እንዳለ አቅርበነዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን ሆነች?

በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከመለያየታቸው በስተቀር በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ዛሬም ድረስ አንድ ነን። ሥርዓቱና ሕግጋቱ የተለያየ አይደለም። በማዕረገ ክህነት አሰጣጥ ልዩነት ያለን አይመስለንም።  ነገር ግን እጅግ አሳዝኝና አስገራሚ ነገር ስናይ የምንጠይቀው አጥተናል። በተደረገው ሁኔታ እኛ በእስራኤል የምንገኝ ኤርትራውያን በተደረገው አድራጎት ተጎድተናል። ይኸውም ለሰሚ የሚከብድና ከምናውቃት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ህግጋት ውጪ ማዕረገ ክህነት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ሲሰጥ በማየታችን በጣም አዝነናል። ነገሩን በአጭሩ አስረዳለሁ።
ሰውየው በትግራይ ክፍለሀገር ሰንቃጣ እንደተወለደ አውቀነዋል። ስሙም ሓጎስ አስገዶም ይባላል። በትግራይ ክፍለ ሀገር ይህ ሓጎስ አስገዶም የተባለ ሰውዬ አባ ሰላማ የሚባል ማኅበር አቁሞ ህዝብ ለህዝብ ሲያጋጭ ተይዞ ሶስት አመት ወኅኒ ታስሮ ነበር። በአቡነ መርሐ ክርስቶስ ማኅበሩ በትእዛዝ ፈረሰ። በሲኖዶስም ተወሰነበት። ተስፋ ያልቆረጠው ይህ ሓጎስ አሰገዶም የተባለ ሰውዬው ወደ ሽመልባ የኤትራውያን ስደተኛ ካምፖ በመግባት ባሕታዊ ወልደ ሥላሴ እባለሎህ በማለት ማደናገር ጀመረ።
ባህታዊ ነኝ የሚለው ሓጎስ አስገዶም

በዚያም በእሱ የተጀመረ ረብሻ በሽመልባ ባሉ የኤርትራ ቤተክርስቲያን በመበራከቱ ጥቂት ተከታዮች አስከትሎ በሱዳን አድርጎ ሊቢያ ገባ። ሊቢያ ሲገባም አባ ሰላማ መልዕክት ነግረውኛል ከዛሬ ጀምሮ አንተ ሞኖክሴ ነህ ብለውኛል ብሎ አባ ሳሙኤል ነኝ አለ። ከዚያም ይህ ሓጎስ አስገዶም ከሊቢያ ወደእስራኤል ሀገር ከኤርትራውያን ጋር ገብቶ ኤርትራዊ ነኝ ብሎ የስደተኛ ወረቀት ከወሰደ በኋላ ሳይሞኖክስ አባ ሳሙኤል ተብሎ እየተጠራ ቆየ። አጠምቃለሁ እያለ ሲያታልል፤ ህዝብ ሲያሳብድ፤ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቶ ብዙ ኤትራውያን ደግሞ አንተ ሞኖክሴ አይደለህም፤ ለምን አባ ትባላለህ። ክህነት የለህም ለምን ታሳልማለህ።  ንስሀ ለምን ትሰጣለህ ስንለው የእኔ ክህነት በአባ ሰላማ ፍሬምናጦስ አማላጅነት ከሰማይ ነው የተሰጠኝ፤ የእናንተ ክህነት ግን ከኃጢአተኛ ጳጳስ እጅ የተሰጠ ነው እያለ ሲሳደብ በማየታችን ህዝቡ በዚህ አታላይ ሰው እንዳይታለል ስናስተምር ተናዶ ወደኢየሩሳሌም በመሄድ ከኢትዮጵያ ሊቀጳጳስና አንዳንድ መነኮሳት ጋር በስውር መገናኘቱን ቀጠለ።
ባህታዊ ወልደ ሥላሴ ነኝ እያለ በሽመልባ ሲያታልል

 ከዚያም ከሊቀ ጳጳሱ አባ ዳንኤል ዘንድ ዲቁና ተቀበልኩ አለና በአስማቱ ለሚያታልላቸው ደጋፊዎቹ  ማዕረጉ ሲሰጠው የሚያሳይ ፎቶና ፊልም አሳየ። ትንሽ ቆይቶ ሞኖኮስኩኝ ብሎ እንደቦብ ማርሊ ያሳደገውን ጸጉሩን ቆርጦ ጥቁር ቆብና ቀሚስ አድርጎ መጣ። አንተን አመነኮሰች ቤተ ክርስቲያን? ብለን አዘንን። አለቀስን።
በአባ ሳሙኤል ስም ቄስና መነኩሴ ነኝ አለን ደግሞ

ከሱ ጋር የነበሩና ስናስተምራቸው የተመለሱ ሁለት ዲያቆናት ለመመንኮስ 50 ሺህ ሼቄል ከፍሏል አሉን። ለሊቀ ጳጳሱና ከመነኮሳቱ መካከል አባ ፍስሐና አባ ብርሃና መስቀል የተባሉም ገንዘብ መቀበላቸውን አሁንም ይመሰክራሉ። የሰው ማስረጃ አለን። ሌሎችም መነኮሳት የተቀበሉ አሉ። ይህ አታላይ አባ ሳሙኤል የተባለው ትንሽ ቆይቶ የቅስና ማዕረግ ከአባ ዳንኤል ተሰጠኝ ብሎ በደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሥርዓት በቢዲዮና በፎቶ  ቴልአቪቭ አምጥቶ ለተከታዮቹ አሳየ። ይህ ሁሉ ማስረጃ በእጃችን ይገኛል።
ምንም የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሙያ ለሌለው፤ ዲቁና ሳይኖረው  ለሓገስ አስገዶም ቅስና ሲሰጡት አቡነ ዳንኤል ናቸው

 የዚህ ሁሉ አስተባባሪ አባ ፍስሐ ይባላሉ። አባ ብርሃነ መስቀል የተባሉት፤ አባ ተወልደ የተባሉትም አብረውት አሉ። ገንዘብ የተቀበሉ መኖክሴዎች ዝርዝር በእጃችን አለ። በቁጥር ትንሾች ቢሆኑም የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ጠፋ ብለው የተናገሩ ቢኖሩም የሰማቸው የለም።  ገንዘብ የሁሉንም አፍ ዝም አሰኝቷል።



 እኛ የምናዝነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ሹማምንት በገንዘብ ስልጣነ ክህነት እየሰጡ ለምን ቤተ ክርስቲያንን ያሰድባሉ? የኢየሩሳሌም ገዳም ሞኖክሴዎችስ ለምን በገንዘብ ይደለላሉ? ክህነት እንደዚህ ነው? ሙንኩስናስ እንደዚህ ነው? በበኩላችን ይህን ሰውዬ ያለአግባብ እያታለለ ከኤርትራውያን እጅ የወሰደውን በብዙ መቶ ሺህ ሼቄል ለማስመለስና በህግ ፊት ለማቆም ማስረጃዎቻችንን ይዘናል። እናንተ በሰጣችሁት ክህነት አንታለልም። አንታወክም። ለነገሩ ቤተ ክርስቲያንን አዋርዳችሁታል። ሓጎስ አስገዶም ቄስ ሆነ? ሚስቱንም አምጥቶ አመነኮሰ። አንድ ቤት አንድ ላይ ይኖራሉ። አይ ኦርቶዶክስ፤ እንደዚህ መሆና ያሳዝናል። ሕግ ካለ፤ ዳኛ ካለ ኢየሩሳሌም ያሉ ሞነኮሳትን ከገዳሙ ማባረር ነበር። ለሓጎስ አስገዶም ቅስና የሰጡ ሊቀጳጳሱም መቀጣት ነበረባቸው።
ያሳዝናል። ያሳዝናል። በትክክልም ዘመኑ ተጨርሷል። ክህነትና ሙንኩስና  በገንዘብ ሆነ። ኤሎሄ ኤሎሄ ይባላል።

ለምእመን በገንዘብ ክህነት እንዲያገኝ ያደረጉ አባ ብርሃነ መስቀል የሚባሉት በቀኙ፤ አባ ፍስሐ የሚባሉት አባ ፍስሐ የሚባሉት በግራ በመሀል አቡነ ዳንኤልና ሲሆኑ በደብረ ገነት ቤተመቅደስ ውስጥ ሓጎስ አስገዶም ፤ ወልደሥላሴና አባ ሳሙኤል የተባለው ቅስና ሲቀበል የሚያሳይ ፎቶ። የዚህ ሥርዓት ሙሉ ቪዲዮ በእጃችን አለን።
             
                     ፍትዊ አንገሶም ቴልአቪቭ

Tuesday, July 1, 2014

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ማኅበር አቡነ ዳንኤልን የበደላቸው ነገር የለም!!



( ለዘሐበሻና ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን መካነ ጦማሮች በተለይ የተላከ)

በአባ ሰላማና ደጀ ብርሃን የተሐድሶ መካነ ጦማሮች ለወጣው የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር ለማይጠብቅ ጽሁፍ እናዝናለን!
በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት አቡነ ዳንኤል ከመጡበት ከነሐሴ 2005 ዓ/ም ጀምሮ የገዳሙ ማኅበር ለአንድ ሊቀ ጳጳስ የሚገባውን ክብርና የሥራ ትብብር በማድረግ ሲፈጽም ቆይቷል። ይሁን እንጂ በቆዩበት ለአንድ ዓመት የስራ ሂደታቸው ጉድለት ሲገመገም በዚህ ጽሁፍ ለመዘርዘር የሚከብዱና የሚቀፉ ቃላትን በማውጣትና ተግባራትን በመፈጸም  አባታዊ ደረጃቸውን ለመጠበቅ በጣም የሚቸገሩ እንደነበሩ አይካድም። ይህም ሆኖ  ገዳሙ የራሱን ስምና ደረጃ ለመጠበቅ ሲል ሁሉንም በትዕግስት ተሸክሞ ቆይቷል።
  ችግሮቹ ይሻሻሉ ዘንድ ነገሮችን በትዕግስት መጠበቁ ገዳሙን የሚጎዳ ደረጃ ላይ የሚያስደርስ ሁኔታ በመፈጠሩ በብጹዕነታቸው የተፈጸሙ 10 / አስር/ የስራ ጉድለቶችን በመዘርዘር አጠቃላይ የማኅበሩ አባላት በውሳኔ አሳልፈውና ተፈራርመው ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩን እንዲያጣራና ባለው ስልጣን መሰረት የእርምት እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ ለግንቦት /2006 ዓ/ም የሲኖዶስ ጉባዔ በደብዳቤ ጠይቋል። ደብዳቤው ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ከታየ በኋላ መወሰድ ስለሚችለው ቀጣይ ጉዳይ ውሳኔ የተላለፈ በመሆኑ አፈጻጸሙን ገዳሙ በትዕግስት እየተጠባበቀ ይገኛል።
ይሁን እንጂ የሊቀ ጳጳሱን የማዕርግ ደረጃ በማይጠብቅና የኦርቶዶክሳውያንን የእምነት አቋም በማይከተል መንገድ በሊቀ ጳጳሱ በራሳቸው የተጻፈ ይሁን  ወይም በሌሎች የገዳሙን ስም ለማጉደፍ የቆሸሸ ምግባራቸው እየተከተለ ማንነታቸውን በሚያሳብቅባቸው  ስም አጥፊ ግለሰቦች እጅ እንደተጻፈ ለጊዜው ባልታወቀ መንገድ በተሐድሶ/ፕሮቴስታንታዊ ብሎጎች ላይ ሊቀ ጳጳሱ በረሃብ እየተቀጡ መሆናቸውን የሚገልጽ ጽሁፍ በመውጣቱ በጣም አዝነናል።
«እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራል» እንዲሉ ገዳሙ ተበድሏል ወይስ ሊቀ ጳጳሱ? የሚለው ጉዳይ ወደፊት የሚታይ ሆኖ ገዳሙ  በሊቀጳጳሱ የደረሰበትን የስራ በደል የሚገልጸውን ዝርዝር ጉዳይ እዚህ ጽሁፍ ላይ ቢያወጣ የአባቶችን ደረጃ ማቃለልና  የቤተ ክርስቲያናችንንም  ችግር በራሳችን የስልጣን እርከን መፍታት እንደማንችል የሚቆጠር በመሆኑና ለቤተ ክርስቲያናቸው ክብር ዘወትር የሚቆረቆሩ ምእመናንንና ምእመናትን ልቡና ማሳዘን በመሆኑ ሊቀ ጳጳሱ በተሐድሶ ብሎጎች ላወጡት የተበደልኩ አቤቱታ የምንሰጠው ዝርዝር ነገር አለመኖሩን መግለጽ እንወዳለን።
ስለሆነም  ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ የምናሳውቀው ነገር በተሐድሶ/ፕሮቴስታንታዊ መጦመርያዎች የወጣው ጽሁፍ የተሳሳተና የገዳሙን ስም ለማጉደፍ ተላላኪዎች የፈጸሙት የትስስር ድርጊት እንጂ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚያንጸባርቅ አይደለም። ሊቀ ጳጳስ አባ ዳንኤልን በተመለከተ ለሲኖዶስ በተገለጸ ጽሁፍ ገዳሙ በስራ መግባባት ባለመቻሉ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ የተጠየቀ ስለሆነ የዚያን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ስለምንገኝ ውሳኔውን ወደፊት የምናሳውቅ መሆናችንን በአክብሮት እንገልጻለን።
                                                                 እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ!


Tuesday, May 13, 2014

በውስጡ ቀና መንፈሳዊ አባላት መኖራቸው ብቻ የሃይማኖት ማህበር አያሰኘውም!


(ከወልደገብርኤል ስሁል)
 
የየትኛውም እምነት ተከታዮች መንፈሳዊ ህይወትና የሃይማኖት ቀኖና በሚመለከቱ ጉዳዮች ያሻቸው ማመንና መከተል ይችላሉ፤ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር የሚለውን መርህ አክብረው ሁለቱን ሳያደበላልቁ እስከተጓዙ ድረስ። መጋቢት 1983 “በአቡነ ደርግ” ብላቴ ላይ የተቋቋመው ማ.ቅ. ዋና ዓላማው ጠመንጃ የታጠቀ የቅዱሳን ብርጌድ ሁኖ በማርክሲዝም የተከዳውን አምባገነን መንግስት የማዳን ተልእኮ ይዞ ሲሆን፤ ይህ ካልተቻለም “የብሄራዊ እርቅ መንግስት ይመስረት” በማለት ባቋራጭ የመንግስት ስልጣን ሊጨብጡ ይቋምጡ ለነበሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን (ማርክሲዝም ባዶ ሜዳ ላይ ጥሏቸው በመሄዱ የቆጫቸውና የደርግ ለሞት መቃረብ “ንስሃ” ለመግባት የተገደዱ የደርግ ቀኝ እጆች) በድህረደርግ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መጫወቻ ካርድ ይሆናቸው ዘንድ ተጠፍጥፎ የተሰራ ማህበር ነው። መስራቾቹም የደርግ ደህንነት ያሰባሰባቸው አንዳንድ “ምሁራን”ና “መንፈሳዊ አባቶች” ሲሆኑ በህቡእ እንዲመሩት የተሰየሙትም ከነሱ የተውጣጡ “ታላላቅ ወንድሞች” ናቸው(ለማንም ግልጽ በሆነ ምክኒያት ስማቸውን እዚህ ላይ መጥቀስ ሳያስፈልግ)። ስለዚህ መስራቾቹና ህቡእ መሪዎቹ ፖለቲከኞች ናቸው፤ የተመሰረተበት ዓላማ ደግሞ መንፈሳዊም ሃይማኖታዊም አልነበረም፤ አሁንም አይደለም። በውስጡ ቀና መንፈሳዊ አባላት መኖራቸው ብቻ የሃይማኖት ማህበር አያሰኘውም።

Sunday, May 4, 2014

አንዳንድ ቅዱሳን በጣም ያስቁኛል...፪ (ካለፈው የቀጠለ)


(by Tedy Sih)

ስለማህበረ ቅዱሳን ስውር አመራር የሙሉጌታ ማደናገርያና የዳንኤል እውነታ

ማህበሩን ከጥንስሱና ከአመሰራረቱ ጀምረን በተጨባጭ ለምናውቀው እንጂ ህቡእ ገጹ ለብዙሃኑ አባላት እስከቅርብ ጊዚያት ግልጽ አልነበረም። አሁን ግን ስለማህበሩ ቆም ተብሎ ማሰቢያና ለርኩሰቱ መላ መፈለጊያ ጊዜ መጥቶ በር እያንኳኳ ነው። በቤተክርስቲያኗ ላይ እስካሁን ያደረሳቸውና በሃገርም ደረጃ ሊያደርሳቸው የሚሰናዳባቸው ነገሮች ፈጥጠው ወጥተዋል። የማሀበሩ እኩይ ስነፍጥረት፣ እኩይ ዓላማና እኩይ አካሄድ እርቃኑ እየወጣ ነው። ይህም ሃቅ ዘግይተውም የተቀላቀሉትን ጨምሮ ለአብዝሃኞቹ ቀና አባላቱ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የቤተክርስቲያኗ ምእመናን፣ የልዩ ልዩ እምነት ተከታይ የሆኑት የሃገሪቱ ህዝቦች፣ እንዲሁም መንግስት ከእንቅልፋቸው በቅርቡ እየነቁ መጥተዋል። የማህበሩ ማንነት አጠያያቂ መሆን በጀመረበት በዚህ ወቅትም ከራሷ ከቤተክርስቲያና እና ከማህበሩ ከፍተኛ አመራሮችም እያፈተለኩ የሚወጡት መግለጫዎች ይበልጥ እርቃኑን እያስቀሩት አደገኛ ባህርያቱ ወደ አደባባይ እየተገለጠ መታየት ጀምሯል። ባለፉት ሳምንታት በማህበሩ አመራሮች የተሰጡ መግለጫዎች ላፍታ ብንመልከት እንቆቅልሹን በደንብ ይፈቱልናል። የመምህር ሙሉጌታ ሃይለማርያም ሃሰትና የዲያቆን ዳንኤል ክብረት እውነት ተደምረው ባለፉት ክፍሎች ስለማህበሩ የገለጽኳቸውን ነገሮች እውነትነት ይበልጥ ያረጋግጣሉ።
ማህበሩ ግልጽ ጥያቄዎች በመጡበት ወቅት የማህበሩ ዋና ጸሃፊ መምህር ሙሉጌታ ሃይለማርያም ከድንጋጤ የሚመስል ማብራርያ ሰጥቷል። መምህር ሙሉጌታ እንቁ መጽሄት ጋር ባደረገው አስገራሚ ቃለ ምልልስ ማህበሩ ከተቃውሞ ፖለቲካ ጋር ምንም ንክኪ እንደለለው በማበከር ስጋትና ምጸት በቀላቀለ ችኮላ አብዛሃኞቹ የማሀበሩ አባላት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው ብሏል። ይህንን ለማስረዳት የተጠቀመበት አመክንዮ ደግሞ አባላቶቻችን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጡ ስለሆኑና በነዚህ ስፍራዎች ደግሞ ኢህአዴግ ሁሉንም አባላቱ አድርጎ ስለሚመለምል የኛም አባላት ብዙዎቹ እነሱ ናቸው የሚል ነው።
ቃለምልልሱም ብዙዎቹን የማህበሩ አባላት ከማስቆጣቱም በላይ ከእውነት የራቀ ነበር። ቁጣ የቀሰቀሰውም ይበልጥ ጥያቄዎቸ አስነስቶ ከማህበሩ አባላት ጋር ብቻ የሚነገር ግን ለማህበረሰቡ በግላጭ ለገበያ የማይቀርብ መረጃ እንዲወጣ በር ይከፍታል በሚል ነው። በዚህ መልኩም ህቡእ ገጽታው እንዳይጋለጥ በሚሹት ሁሉ የናሩ ነቀፌታዎች ተሰንዝረዋል። የነቃፊዎቹም ስጋት የማህበሩ አባላት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው በመባሉ አይደለም። አባባሉ ትክክል ስላለመሆኑ ዋና ጸሃፊውና ነቃፊዎቹም ሆኑ ከነሱ ውጭ ያለ ማንኛውም ወገን እንደማያጣው ያውቃሉና። የስጋቱና የቁጣው ምንጭ የማህበሩ አባላት ካላቸው የብሄር ወይም የፖለቲካ ወገንተኝት ተነስቶ ሲዘረዘር ዋና ጸሃፊው በሃሰት የለጠፈው ኢህአዴግነት ሳይሆን ማህበሩ በተልእኮና በገቢር የጨበጠው እውነተኛ ማንነት(ተቃዋሚነት) ስለመሆኑ ከራሱ ከአመራሩ ግልጽ ጥቆማና እማኝነት ተመስርቶ እንዳይታወቅ በመፍራት ነበር። የፈሩት ግን አልቀረም። መምህር ሙሉጌታ በቃለምልልሱ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ስም ጠቅሶ ስላንቋሸሸ ዳንኤል በሰጠው ምላሽ ስውር አመራር እንዳለ ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ ከውስጥ ሰው ይፋ ተደረጓል። ዳንኤልም የምናውቀውን ያክል የማህበሩን ህቡእ ገጽታ ደፍሮ ባያፍረጠርጥም ስለ ስውር አመራሩና ስለ እኩይ ድርጊቶቹ ከውስጥ አዋቂ በሚሰጥ እማኝነት ሰጥቷል።
ዳንኤል አደባባይ ካዋላቸው የማህበረ ቅዱሳን አካሄዶችም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ እነሱንም አጠር አድርጌ በማስቀመጥ ከማህበሩ ፖለቲካዊ ተልእኮ አንጻር ትርጉማቸውን እገልጻለሁ።
ማህበሩ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ግልጽ መረጃ ሳይጨብጥና የት እንደሚያደርሳት ግልጽ ግብ ሳይኖረው ስለ መጓዙ ተናግሯል።
(መጀመሪያውንም በመንፈሳዊ ቤተክርስቲያኗን የሚደግፍ ሃይማኖታዊ ተልእኮ ያልነበረው ስለመሆኑ ይነግረናል። አመራሩም ቤተክርስቲያን ተኮር ስትራቴጂ የሌለውና የፖለቲካ አባቶቹ ጭፍን ፈረስ ስለመሆኑ በማያሻማ ቋንቋ ይመሰክራል።)
አመራሩ ማህበሩ ለቤተክርስቲያኗ አገልግሎት የተመሰረተ ሳይሆን ቤተክርስቲያኗ ለማህበሩ አገልግሎት ወደሚል አመለካከት መዞሩ፣
(አመራሩ ቤተክርስቲያኗን ለህቡእ ተልእኮው መሳካት ሊቆጣጠራት ይፈልጋል እንጂ እሷ የምትፈልገውን አገልግሎት ሊሰጥ አይሻም ። ሲጀምር የሚያገለግላት መስሎ ቢገባም ቀስ በቀስ ለተልእኮው ሊገለገልባት ወደሚያደርግ አቅጣጫ ማምራቱን ያሳየናል።)
ተሃድሶን ለማጋለጥ እንጂ ተሃድሶን እንዲፈጠር ያደረገውን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት ስትራቴጂ የሌለው መሆኑ፣
(ማህበሩ የቤተክርስቲያኗን መሰረታዊ ቀኖናዎች እና አስተምህሮዎች ለመጠበቅም ሆነ ለማስፋፋት የቆመ ስላለመሆኑ ያስረዳናል። ይልቁንም የተሃድሶን አደጋ በተጋነነ ምስል እያቀረበ ብጥብጥ ህውከትና መመሰቃቀል ቤተክርስቲያኗን እንዳይለያት በትጋት እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ያስረዳል።)
የማህበሩ አመራር የእለት ተለት ነገሮችን ለማየት የሚሰበሰብ፣ ማህበሩ ስራውን ትቶ አባላቱን እንደሚሰልል፣ አባላቱ የሚወገዙትና የሚታገዱትም ማህበሩን ከነኩ ወይም የተለየ አቋም ከያዙ እንጂ ለቤተክርስቲያኗ እምነትና አስተምህሮ ወይም ለመንፈሳዊው ምግባር አደጋ ናቸው ተብሎ አለመሆኑ ገልጿል፣
(ማህበሩ በየእለቱ በሚከናወኑ ዓለማዊና ፖለቲካዊ ሂደቶች ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ፣ አባላቱንም ማንነታቸውንና አመለካከታቸው የተለየ እንዳይሆን ሲል በየጊዜው እንደሚከታተል ብሎም ህቡእ ተልእኮውና እንቅስቃሴዎቹ እንዳይታወቁበት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሚስጢራዊ ጉዞ እያካሄደ ስለመሆኑ አስረጅ ነው።)
ማህበሩ ስውር አመራር ያለው መሆኑ፣ ስውሩም አመራር ጥላቻውን የሚገልጽበት ሶስት መንገዶች ያሉት ስትራቴጂ እንዳለው፣ እነሱም ስለሚጠላው ሰው ክፉ በመናገር ስለሚጠላው ሰው የሚያውቀውን ጥሩ ነገር ባለመናገር እና ስለሚጠላው ሰው ተራ ነገር በመናገር የሚገለጹ ስለመሆናቸው፣ ከነዚህ በተጨማሪም ስውር አመራሩ የማስከፋትና የጭር ሲል አልወድም ስትራቴጂ ስለመያዙ አስረድቷል።
(ይህ ደግሞ በነ አቡነ ሺፈራው ተነድፎ ተግባራዊ እየሆነ ያለው የአሁኑን መንግስት ጥላሸት እየቀቡ ተቀባይነት የመንሳትና ድሮ የነበሩትን ሁሉ ቅዱስ አድርጎ የመሳል ስትራቴጂ በማህበሩ ስውር አመራር እንዴት እንደሚተገብረው ይጠቁመናል።ማህበሩ በግልጽ በሚታወቀው አመራሩ ሳይሆን በህቡእ አመራሩ ቁጥጥር ስር መሆኑ ይህም አመራር የጥላቻ ስትራቴጂ እንዳለው፣ ስለሚጠላቸውም ወገኖች( መንግስትንና የቤተክህነትን አመራር) ክፉውን ብቻ በመናገር በጎ ስራቸውን ባለመናገር እና ተራ አሉባልታ ፈጥሮ በማጥላላት የማስጠላት ስልት እንደሚተገብር ይመሰክራል። እውነትና ሃሰት አዛብቶ ጥላቻ ማራመጃ ከማድረጉ በተጨማሪም ጭር ሲል አልወድምን ሆን ብሎ በመከተል በማህበሩ በቤተክርስቲያኗ እና በሃገሪቱ ላይም አጠቃላይ ብጥብጥ በሚፈጥር የዓመፃ መንገድ ላይ መቆሙን ያሳያል።)
ማህበሩ በእውቀትና በተጨባጭ መረጃ ተመስርቶ ስራ ከመስራት ይልቅ በአሉባልታና በስሚ ስሚ እንደሚንቀሳቀስ እቅዶቹን 50 በመቶ ያህሉን እንኳን መስራት ያልቻለና እስካሁንም የባለጉዳይ መስመር እንጂ የሃሳብ መስመር የሌለው መሆኑ፣ የማህበሩ አመራር ተሰብስቦ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች እንደገና ለብቻቸው ተሰብስበው ባሻቸው የሚቀይሩ ታላላቅ ወንድሞች እንዳሉ፣ ከነዚህ አመራሮቹም ውስጥ የማኅበሩ አባላት መንግሥትን እንዲፈሩ እና እንዲጠሉ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው፣ እነሱም ምንጊዜም አንዳች ከባድ ነገር ሲነሣ መንግሥት እንዲህ ብሎናል፣ በዚህ ስብሰባው እንዲህ ብሏል፣ ሊዘጋን ነው፣ ሊያስረን ነው፣ ሊጨርሰን ነው ከማለት ያለፈ አንድም ቀን በጎ ነገር ስለ መንግሥት እንደማያነሡ፣
(ማህበሩ በግልጽ እቅድና በአመክንዮ የተመሰረተ መርህ ከመመራት ይልቅ በአሉባልታና በበሬ ወለደ እንደሚነዳ፣ በግልጽ የሚታወቀው የማህበሩ አመራር የስውር አመራሩ አሻንጉሊት ስለመሆኑና ወሳኝ ወይም አድራጊ ፈጣ የሆነው ስውር አመራሩም በታላላቅ ወንድሞች እጅ እንደተያዘ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል። ከታላላቅ ወንደሞችም መካከል በተለይም የነ ካህን ሽፈራው የድሮ ቀረ ማንዋል እንዴት ባለ ዘዴ ቤተክህነትን እያመሰ እንዳለ በቂ ምስክርነት ይሰጣል። ይህም ዘዴ ማህበሩና አባላቱ የአሁኑን መንግስት እንዲፈሩት፣ ያለተጨባጭ ምክኒያትም እንዲጠሉት እና በመከበብ ስሜት እንዲታጠሩ በማድረግ ለአመጽ እንዲነሳሱ ስለሚቀሰቀሱበት አጠቃላይ ሁኔታ በቂ ጥቆማ ይሰጣል።)
ዲያቆን ዳንኤል የገለጻቸው እነዚህንና ሌሎች በማህበሩ ውስጥ የታመቁ ሚስጥሮች በክፍል አንድና በክፍል ሁለት ባቀረብኳቸው ተከታታይ ጽሁፎቼ የተገለጹትን እውነታዎች ተጨማሪ ማስረጃ ይሰጣሉ። በተለይ የሱ ምስክርነት ክብደት የሚያሰጠውም ከጅምሩ አንስቶ ማህበሩን በይፋ እየመራ የነበረ በመሆኑ ከሱና ከመሰል ወንድሞቹ በላይ ሁነው ታላላቅ ወንድሞች በስውር ለቅዱሳኑ ማህበር ልዩ አመራር እንደሚሰጡ ከሱ በላይ እማኝ መጥራት ስለማይቻል ነው። እርግጥ ችግሮቹን ሙሉ በሙሉ ገላልጦ ባይጽፍም በመምህር ሙሉጌታ አስተያየት ተቆጥቶም ቢሆን ዳንኤል ይህንን ሲጽፍ አጽንኦት የሰጠው ስለስውሩ አመራርና ከቤተክርስቲያን አገልጋይነቱ የሚጻረሩ ፖለቲካዊ ገጾቹ ላይ ነው። ተወደደም ተጠላም ዳንኤል እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ “አውላላ ሜዳ ላይ የተኛውን በሬ፣ ነካክተው ነካክተው አደረጉት አውሬ።” እያለ ተማርሮ ስለማህበረ ቅዱሳን በልቡ ብቻ ይዟቸው የነበሩትን እውነቶች አጋልጧል። ማህበረ ቅዱሳንና የታላላቅ ውነድሞቹ ስውር አመራርም እርቃኑን ወጥቷል። የዳግመ ደርጊዝምና የዳግመ ሞናርኪዝም ፈረስ እንደሆነ ለምናውቀው ብዙ ባያስገርምም ቢያንስ እስካሁን ስለማህበሩ ሃቁን ለማያውቁት ግን የእውነት ብርሃን ፈንጥቆ ጨለማውን ያጋለጠ ምስክርነት ስለመሆኑ አንዳች ጥያቄ የለውም።
በዳንኤል ጽሁፍ የተደሰቱ አባላት ያሉትን ያህል ማህበሩን ለበለጠ አደጋ አሳልፈህ ሰጠህ ብለው የተከፉበትም ብዙ ናቸው። ጽሁፉን ተከትለው በየብሎጎች የወጡት አስተያየቶችም ይህንን ያሳያሉ። አንዳንዶቹ ድረ ገጾችም ጽሁፉን ላፍታ አትመው ካወጡ በኋላ ከገጾቻቸው አንስተውታል። ይህም በማህበሩ የተጠለለው ህቡእ ክንፍ እውነተኛ ማንነት ይፋ እንዳይወጣ የተደረገ ስልት ነው። በተለይ የማህበሩ ታላላቅ ወንድሞች በጣም ተደናግጠው ጉዳዩን ለማዳፈን የቻሉትን ያህል እየተሯሯጡ ነው። ከማዳፈኛ ስልታቸውም መካከል ዳንኤልን በማስፈራራት ወይም በማባበል ይቅርታ እንዲጠይቅ በማድረግ ሁሉም ነገር አማን የሚል ምስል ለምስጠትና ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ይጥራሉ። ለማባበል ከሚመስለው ጥረታቸውም አንዱ ጽሁፉ በዳንኤልና በሙሉጌታ አለመጣጣም የመጣ ችግር እንደሆነ ወይም ማህበሩ እንዴት ተሃድሶዎችን እንደሚዋጋ በሁለቱ አመራሮች የታየ የሃሳብ መለያየት ብቻ እንደሆነ ለመተንተን ሲጥሩ ይስተዋላሉ። ጎን ለጎን ደግሞ ዳንኤል ብዙ ጽሁፎች እንደጻፈ አንዳንዶቹም በብእር ስም እንዳሳተማቸው በመጠቆም ይቅርታ ካልጠየቀ ሚስጥሩን እንደሚዘከዝኩበት ፍንጭ እየሰጡም በአንዳንድ መጽሄቶች ባወጧቸው ጽሁፎች በግልጽ አስፈራርተውታል። በዛቻው ይሁን በማባበሉ ወይም በሁለቱ ተንበርክኮ ዳንኤል ይቅርታ ጠይቆ ከማህበሩ አመራር ጋር እንደታረቀ እየተነገረ ነው።
ይህ ሁሉ ሽር ጉድ ሰሚን ለማደናገር አልያም እርቃኑ የወጣውን የማህበሩ የውስጥ ጉድ ለማዳፈን ካልሆነ በስተቀር ስለማህበሩ እውነተኛ ማንንትም ሆነ በሱ ላይ ዳንኤል የሰጠውን እማኝነት በቅንጣትም የሚለውጥ ነገር አይደለም። እንዲያውም እውነቱን ለማዳፈን ተብሎ የሚደረገው ርብርብ ይበልጥ ጥያቄዎችን እንድናነሳና የማህበሩ የጥፋት ርኩሰት ከተቀደሰው ስፍራ እንዲወጣ አጥብቀን እንድንሻ ያስገድዳል። አዎ! የእግዚአብሄር ቤት የወንበዴዎች ዋሻ አይደለምና ማህበሩን ፈረሳቸው ያደረጉት እርኩሳን መናብርት ባስቸኳይ ይውጡ እንላለን። ይህ እንዲሆንም ከማህበሩ ታላላቅ ወንድሞች መካከል ፖለቲካዊ አመራር በመስጠት ቀንደኞች የሆኑትን በመጥቀስ እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ተቋሞቻቸውን የመንቀሳቀሻ ማእከላት በማድረግ እየፈጸሟቸው ስላሉ ርኩሰቶች ጥቂት በመዘርዘር ወደ ጽሁፌ ማጠቃለያ ልሂድ።...”

( ከመልከፀዴቅ ጽሁፍ/ “የጥፋ ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ሲቆም” ክፍል‐፫/ ተቀንጭቦ የተወሰደ)

Sunday, April 27, 2014

«ኤሪያ 51» በአሜሪካ ውስጥ ያለ ሌላ አሜሪካ!



ይህ ሀገር «Area 51»  ይባላል። ስያሜውን ያገኘው አሜሪካ በ1967 በቬትናም ላይ ወረራ በፈጸመች ጊዜ ከኦኪናዋ እየተነሳ እንዲደደበድብ ትዕዛዝ የተሰጠው የሲአይኤ የምስጢር ኮድ በወቅቱ ኤርያ 51 ይባል ነበር።  የያኔው ትዕዛዝ ተቀባይ የነበረው ሲአይ ኤ ይህንን በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ሌላ አሜሪካ ብዙ ዓመታት ሲሰልል ከቆየ በኋላ በጥንቱ  የቬትናም ኮድ «ኤርያ 51» ሲል ጠራው። በዚሁ መሰረት «Groome Lake» ይባል የነበረው ይህ ቦታ «Area 51» ተብሎ ይጠራ ጀመረ። ኤርያ 51 የሚገኘው በግሩም ሌክ /ግሩም ሐይቅ/ ዳርቻ በኒቫዳ ስቴት ውስጥ ነው። ከላስቬጋስ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ወደኒቫዳ ሲሄዱ በአስቤስቶስ ፋብሪካ ሠራተኞች በተቋቋመችውና በኋላም ጥቂት ጡረተኞች የከተሙባት የራሔል ከተማን ለመጎብኘት የሚሄድ ሰው ወደግራ የሚታጠፍ ቀጥ ያለ ኮረኮች መንገድ ተከትሎ ከሄደ በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ሌላ አሜሪካ የሆነውን  «ኤርያ 51» መግቢያ ያገኛል። ነገር ግን እዚህ አሜሪካ ውስጥ ይገባ ዘንድ ማንም አይፈቀድለትም። 23 በ25 በሆነ  ስኴር ኪሎሜትር ውስጥ ያረፈው «ኤርያ 51» በረቀቁ ካሜራዎች የተተከለለት ማለትም ከየትኛው አቅጣጫ የሚመጣ ሰው የሚናገረውን መጥለፍ የሚችል፤ ቪዲዮ ቀርጾ የማስተላለፍ ብቃት ያለው፤ ምን እንደሚሰራ፤ ምን እያደረገ እንዳለ በመለየት መተንተን የሚችል ሴንሰር የተገጠመበት ክልል ነው። በአደገኛ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍና ቁጥራቸው በማይታወቅ የጥበቃ ፖሊስ መኪና የታጠረው ይህ ሌላው አሜሪካ እስከመኖሩ የታወቀው ከ1960ዎቹ በኋላ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖ በእምቢተኛነቱ ጸንቶ ለማለፍ የፈለገውን ግለሰብ ወይም ቡድን ከጉጉት ዓይን በበለጠ የሚከታተለው ፈጣኑ ጠባቂ ኃይል በመኪና ከተፍ ብሎ ያለምንም ምርመራ የደረሰበትን ሊያጠፋው ይችላል። እጅግ አደገኛና ምስጢራዊ ክልል «ኤርያ 51» እሱ ነው።


 ከ1970ዎቹና 80ዎቹ ወዲህም «ኤርያ 51» የሚባል ቦታ ስለመኖሩ እንጂ «በኤርያ 51» ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚሰራ ምናልባት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ያውቁ እንደሆነ እንጂ ይህ ስፍራ እንኳን ለዓለም ሕዝብ በቅርቡ ላሉት ለራሔል ከተማ ሕዝቦች እንግዳ ሀገር ነው።
«ኤርያ 51» ተብሎ ከመሰየሙ በፊት ግሩም ሐይቅ ዳርቻ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ1942 ዓ/ም አሜሪካ የአውሮፕላን ማረፊያ ነገር ነበራት። ዙሪያውን በተራራ የተከበበውን ይህንን የሀይቅ ዳርቻ ካምፕ በማድረግ በ1955 ዓ/ም ወደምስጢራዊ ተግባር አዛወሩት። ይህ ካምፕ የአሜሪካ አቪየሽን መስሪያ ቤት የማያውቁት የራሱ አውሮፕላኖች አሉት።  ከፔንታጎን ወይም ከመከላከያ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ልዩ ሀገር ነው። ብዙ አሜሪካኖች የዚህን ቦታ ምንነት ለማወቅ ያደረጉት ሙከራ ከተወሰኑ ግምቶችና መላምቶች በስተቀር የተጨበጠ መረጃ ሊያገኙበት አልቻሉም። ሆሊውዶች ደግሞ ይህንን ምስጢራዊ ስፍራ በፈጠራ ታሪክ ሞልተውት «AREA 51» የተባለ ፊልም ሰርተውበታል።
በኤርያ 51 የአየር ክልል አውሮፕላን መብረር አይችልም። በአካባቢው ለመብረር ለአየር ማማ ተቆጣጣሪ ማሳወቅ አለበት። «ኤርያ 51» ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የሚኖሩበት ራሱን የቻለ ከተማ ነው። ምናልባትም የሳይንስ ጠበብቶች ስብስብ ከተማ ይሆናል። የከተማው ዋናው ክፍል በምድር ውስጥና በተራራዎቹ የታችኛው ክፍል ሊሆን እንደሚችል የካርታ ጥናት ባለሙያዎች «ጉግል ማፕ» ን አይተው ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በአንድ ወቅት አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቡድን አካባቢውን ለመሰለል ከረጅም ርቀት ምስል ማስቀረት በሚችሉ ዘመናዊ ካሜራዎች እየታገዘ ቦታውን በቪዲዮ ለመቅረጽ ሞክሮ ነበር። በተወሰነ መልኩ የኤርያ 51 የመብራትና ድምቀትና የቦታ ስፋት መረጃ ለማስቀረት ችሏል። ወደኤርያ 51 የሚገቡ የአውሮፕላን ማመላለሻዎችንም ተመልክቷል። ነገር እነማንን? ከየት? ለምን? የታወቀ ነገር የለም።
ታዲያ «ኤርያ 51» የምን ከተማ ነው?
ከመነሻው በ1942 ዓ/ም የአውሮፕላን ማረፊያ የነበረው ይህ የግሩም ሀይቅ ስፍራ ወደተሻሻለና ምስጢራዊነቱ ወደተጠበቀ ወታደራዊ የምርምር፤ የሙከራና የምርት ጣቢያ ተቀይሯል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ለዚህም የሚጠቀሰው አሜሪካ የታጠቀቻቸውና ማንም ያላገኛቸውን ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች፤ ቦምበር ጄቶች፤ የስለላ መሳሪያዎች፤ ሰው አልባ ድሮን ጭምር የሚመረቱት በዚህ ከተማ ነው የሚል እምነት አላቸው። ምክንያቱም እነዚህ ዘመናዊ የጦር ምርቶች በተለያየ ጊዜ ከዚህ ከኤርያ 51 ውስጥ እየተነሱ በአካባቢውን ትናንሽ ከተሞች ላይ ሲበሩ ታይተዋልና ነው። ይህንንም የሚከታተል የረጅም ርቀት ካሜራዎችን ተክለው የዕለት ዕለቱን የሰማይ እንቅስቃሴ የሚከታተሉ የምርመራ ጋዜጠኞች ለማረጋገጥ መቻላቸው ነው።
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውና ስለኤርያ 51 ምስጢራዊነት ትኩረት የሰጠው ዋናው ምክንያት ግን ሌላ ነው። ከኤርያ 51 የሚወጡና ወደኤርያ 51 የሚገቡ በዚህ ምድር ላይ ያልታዩ አካሎች የመኖራቸው ጉዳይ ነው። እነዚህ በረጅም ርቀት ካሜራዎች የኤርያ 51ን ሰማይ በሌሊት ምን ክስተት እንዳለው ለማየት ባደረጉት ሙከራ የበራሪ አካሎቹን ምስል ለማስቀረት ችለዋል።  በጣም ፈጣንና ልዩ መልክ ያላቸው በራሪ አካሎች በኤርያ 51 ምን ያደርጋሉ? ከማንስ ጋር ይገናኛሉ? ያስነሳው ልዩ ጥያቄ ነው።
በኤርያ 51 ቅርብ ርቀት በኒቫዳ በረሃ ባለችው ራሔል ከተማና አልፎ ተርፎም  130 ኪሎሜትር በምትርቀው በቀለጠው መንደር በቬጋስ ጎዳናዎችና ቤቶች ላይ የእነዚህ የበራሪ አካሎች ምስል ይገኛል። ከዚህ በፊት ታዋቂው ደራሲና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ ስለነዚህ ያልታወቁ አካሎች ታሪክ አስነብበውን እንደነበር አይዘነጋም። እነዚህ በራሪ አካላት በኤርያ 51 ምን ይሰራሉ? አሜሪካ ለደረሰችበት እጅግ የረቀቀ ምድራዊ ጥበብ እነዚህ በራሪ አካላት ድርሻ ይኖራቸው ይሆን? በራሪ አካላሎቹ ወይም UFO የሚባሉት ከየት የሚመጡ አካላት ናቸው?
በራሄል ከተማ የምትገኝ አነስተኛ ምግብ ቤት (የምስሉን ዓይን ይመልከቱ)
የነገረ መለኮት ምሁራን UFO ወይም ያልታወቁ በራሪ አካላት የተባሉት የወደቀው መልአክ ሰራዊት ናቸው ይላሉ። እነዚህ ሰራዊት የሰይጣንን ፈቃድ ለመፈጸም ቃል በገቡ ሀገራት ውስጥ ስራቸውን ይሰራሉ፤ አንዳንዴም በሰው አእምሮ ውስጥ ጥበባቸውን በማሳደር ልዩ ልዩ ነገር እንዲፈጥር ያደርጋሉ። በተለይም የሰውን ልጅ ከምድረ ገጽ ጠርጎ ማጥፋት የሚችል የምርምርና የመሳሪያ ፈጠራ ላይ ትኩረት ስለሚያደርጉ «ኤርያ 51» አካባቢ ሲበሩ የሚታዩት እነሱ ናቸው በማለት ያስረዳሉ። ለዚህም ግብረ መልስ የሚሆን ስራ ግብረ ሰዶምን በመፍቀድ፤ ጾታን በመለወጥ፤ ክሂዶተ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ የሚያደርግ ህግ እንዲተገበር ያስደርጋሉ። በዚህም አሜሪካ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ትወስዳለች ይላሉ። ምክንያቱን ሲያስረዱ፤
«ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ» ራእ12፤9
ወደምድር ከነሰራዊቱ ወደቀው ሰይጣን ስራው ምንድነው? የሰው ልጅ የሱን የጥፋት መንገድ እንዲከተል ማድረጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ ባለው ግንኙነትና ከሰው ጋር በሚፈጥረው ውኅደት ሌላው ዩፎ የሚለው አካል የሱ ሰራዊት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? በማለት ይጠይቃሉ። ለዚህም ያልታወቁ በራሪ አካሎች የተባሉት ፍጡሮች ምስል እንደተዘገበው የኢሉሚናቲ ምስሎችን የተከተለ መሆኑ ነው። ለዚህም አለምን ለመቆጣጠር ሰይጣናዊና አስፈራሪ ፊልሞች ማምረት፤ በዘፋኞቻቸው የዓለሙን ህዝብ ቀልብ በመሳብ የዘፈን መንፈሱን የማስረጽ ተግባር እየሰራ መገኘቱን ይገልጻሉ። የሁለት ጣት ምልክት፤ በዓይን ቅርጽ ምስል፤  ወዘተ ስምምነት ይፈጽማል፤ያስፈጽማል።
ላስቬጋስ
 ስለዚህ ኤርያ 51 ምስጢራዊ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ሊያገልግል ቢችል አያስገርምም። ሌላውን ጉዳይ መንግስት የሰይጣንን ፈቃድ በህግ ይፈጽሙለታል።
  አንፈጽምም የሚሉትን ደግሞ ያስፈራራሉ ወይም ያስገድዳሉ። ከዚያ በፊት ግን በፊልሞቻቸው አስፈራሪ /horror/ እና በአስጸያፊ የወሲብ ተግባራቸው የሌላውን ቀልብ በመማረክ ወደተግባር እንዲቀየር ያበረታታሉ። ከዚያም በህግ እንዲጸድቅ ያስደርጋሉ። እንግዲህ ያልታወቁ የሚባሉት እነዚህ አካላት ለኋላው ዘመን የጥፋት መሳሪያ ያስታጥቃሉ፤ አሁን ደግሞ በመንፈስ ሰውን ይቆጣጠራሉ ማለት ነው።
አይ ኤርያ 51? አሜሪካ ውስጥ ያለሽ ሌላዋ አሜሪካ!!