ይህ ሀገር «Area 51» ይባላል። ስያሜውን ያገኘው
አሜሪካ በ1967 በቬትናም ላይ ወረራ በፈጸመች ጊዜ ከኦኪናዋ እየተነሳ እንዲደደበድብ ትዕዛዝ የተሰጠው የሲአይኤ የምስጢር ኮድ
በወቅቱ ኤርያ 51 ይባል ነበር። የያኔው ትዕዛዝ ተቀባይ የነበረው
ሲአይ ኤ ይህንን በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ሌላ አሜሪካ ብዙ ዓመታት ሲሰልል ከቆየ በኋላ በጥንቱ የቬትናም ኮድ «ኤርያ 51» ሲል ጠራው። በዚሁ መሰረት «Groome
Lake» ይባል የነበረው ይህ ቦታ «Area 51» ተብሎ ይጠራ ጀመረ። ኤርያ 51 የሚገኘው በግሩም ሌክ /ግሩም ሐይቅ/ ዳርቻ
በኒቫዳ ስቴት ውስጥ ነው። ከላስቬጋስ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ወደኒቫዳ ሲሄዱ በአስቤስቶስ ፋብሪካ ሠራተኞች በተቋቋመችውና በኋላም
ጥቂት ጡረተኞች የከተሙባት የራሔል ከተማን ለመጎብኘት የሚሄድ ሰው ወደግራ የሚታጠፍ ቀጥ ያለ ኮረኮች መንገድ ተከትሎ ከሄደ በአሜሪካ
ውስጥ ያለውን ሌላ አሜሪካ የሆነውን «ኤርያ 51» መግቢያ ያገኛል።
ነገር ግን እዚህ አሜሪካ ውስጥ ይገባ ዘንድ ማንም አይፈቀድለትም። 23 በ25 በሆነ ስኴር
ኪሎሜትር ውስጥ ያረፈው «ኤርያ 51» በረቀቁ ካሜራዎች የተተከለለት
ማለትም ከየትኛው አቅጣጫ የሚመጣ ሰው የሚናገረውን መጥለፍ የሚችል፤ ቪዲዮ ቀርጾ የማስተላለፍ ብቃት ያለው፤ ምን
እንደሚሰራ፤ ምን
እያደረገ እንዳለ በመለየት መተንተን የሚችል ሴንሰር የተገጠመበት ክልል ነው። በአደገኛ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍና
ቁጥራቸው በማይታወቅ
የጥበቃ ፖሊስ መኪና የታጠረው ይህ ሌላው አሜሪካ እስከመኖሩ የታወቀው ከ1960ዎቹ በኋላ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖ
በእምቢተኛነቱ ጸንቶ ለማለፍ የፈለገውን ግለሰብ ወይም ቡድን ከጉጉት ዓይን በበለጠ የሚከታተለው ፈጣኑ ጠባቂ ኃይል
በመኪና ከተፍ ብሎ ያለምንም ምርመራ የደረሰበትን ሊያጠፋው ይችላል። እጅግ አደገኛና ምስጢራዊ ክልል «ኤርያ 51»
እሱ ነው።
ከ1970ዎቹና 80ዎቹ ወዲህም
«ኤርያ 51» የሚባል ቦታ ስለመኖሩ እንጂ «በኤርያ 51» ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚሰራ ምናልባት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ያውቁ
እንደሆነ እንጂ ይህ ስፍራ እንኳን ለዓለም ሕዝብ በቅርቡ ላሉት ለራሔል ከተማ ሕዝቦች እንግዳ ሀገር ነው።
«ኤርያ 51» ተብሎ ከመሰየሙ በፊት ግሩም ሐይቅ ዳርቻ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ1942 ዓ/ም አሜሪካ የአውሮፕላን
ማረፊያ ነገር ነበራት። ዙሪያውን በተራራ የተከበበውን ይህንን የሀይቅ ዳርቻ ካምፕ በማድረግ በ1955 ዓ/ም ወደምስጢራዊ ተግባር
አዛወሩት። ይህ ካምፕ የአሜሪካ አቪየሽን መስሪያ ቤት የማያውቁት የራሱ አውሮፕላኖች አሉት። ከፔንታጎን ወይም ከመከላከያ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ልዩ ሀገር ነው። ብዙ አሜሪካኖች
የዚህን ቦታ ምንነት ለማወቅ ያደረጉት ሙከራ ከተወሰኑ ግምቶችና መላምቶች በስተቀር የተጨበጠ መረጃ ሊያገኙበት አልቻሉም። ሆሊውዶች
ደግሞ ይህንን ምስጢራዊ ስፍራ በፈጠራ ታሪክ ሞልተውት «AREA 51» የተባለ ፊልም ሰርተውበታል።
በኤርያ 51 የአየር ክልል አውሮፕላን መብረር አይችልም። በአካባቢው ለመብረር ለአየር ማማ ተቆጣጣሪ ማሳወቅ አለበት።
«ኤርያ 51» ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የሚኖሩበት ራሱን የቻለ ከተማ ነው። ምናልባትም የሳይንስ ጠበብቶች ስብስብ ከተማ ይሆናል።
የከተማው ዋናው ክፍል በምድር ውስጥና በተራራዎቹ የታችኛው ክፍል ሊሆን እንደሚችል የካርታ ጥናት ባለሙያዎች «ጉግል ማፕ» ን አይተው
ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በአንድ ወቅት አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቡድን አካባቢውን ለመሰለል ከረጅም ርቀት ምስል ማስቀረት በሚችሉ
ዘመናዊ ካሜራዎች እየታገዘ ቦታውን በቪዲዮ ለመቅረጽ ሞክሮ ነበር። በተወሰነ መልኩ የኤርያ 51 የመብራትና ድምቀትና የቦታ ስፋት
መረጃ ለማስቀረት ችሏል። ወደኤርያ 51 የሚገቡ የአውሮፕላን ማመላለሻዎችንም ተመልክቷል። ነገር እነማንን? ከየት? ለምን? የታወቀ
ነገር የለም።
ታዲያ «ኤርያ 51» የምን ከተማ ነው?
ከመነሻው በ1942 ዓ/ም የአውሮፕላን ማረፊያ የነበረው ይህ የግሩም ሀይቅ ስፍራ ወደተሻሻለና ምስጢራዊነቱ ወደተጠበቀ
ወታደራዊ የምርምር፤ የሙከራና የምርት ጣቢያ ተቀይሯል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ለዚህም የሚጠቀሰው አሜሪካ የታጠቀቻቸውና ማንም ያላገኛቸውን
ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች፤ ቦምበር ጄቶች፤ የስለላ መሳሪያዎች፤ ሰው አልባ ድሮን ጭምር የሚመረቱት በዚህ ከተማ ነው የሚል እምነት አላቸው።
ምክንያቱም እነዚህ ዘመናዊ የጦር ምርቶች በተለያየ ጊዜ ከዚህ ከኤርያ 51 ውስጥ እየተነሱ በአካባቢውን ትናንሽ ከተሞች ላይ ሲበሩ
ታይተዋልና ነው። ይህንንም የሚከታተል የረጅም ርቀት ካሜራዎችን ተክለው የዕለት ዕለቱን የሰማይ እንቅስቃሴ የሚከታተሉ የምርመራ
ጋዜጠኞች ለማረጋገጥ መቻላቸው ነው።
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውና ስለኤርያ 51 ምስጢራዊነት ትኩረት የሰጠው ዋናው ምክንያት ግን ሌላ ነው። ከኤርያ 51
የሚወጡና ወደኤርያ 51 የሚገቡ በዚህ ምድር ላይ ያልታዩ አካሎች የመኖራቸው ጉዳይ ነው። እነዚህ በረጅም ርቀት ካሜራዎች የኤርያ
51ን ሰማይ በሌሊት ምን ክስተት እንዳለው ለማየት ባደረጉት ሙከራ የበራሪ አካሎቹን ምስል ለማስቀረት ችለዋል። በጣም ፈጣንና ልዩ መልክ ያላቸው በራሪ አካሎች በኤርያ 51 ምን ያደርጋሉ?
ከማንስ ጋር ይገናኛሉ? ያስነሳው ልዩ ጥያቄ ነው።
በኤርያ 51 ቅርብ ርቀት በኒቫዳ በረሃ ባለችው ራሔል ከተማና አልፎ ተርፎም 130 ኪሎሜትር በምትርቀው በቀለጠው መንደር በቬጋስ ጎዳናዎችና ቤቶች ላይ
የእነዚህ የበራሪ አካሎች ምስል ይገኛል። ከዚህ በፊት ታዋቂው ደራሲና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ ስለነዚህ ያልታወቁ አካሎች ታሪክ አስነብበውን
እንደነበር አይዘነጋም። እነዚህ በራሪ አካላት በኤርያ 51 ምን ይሰራሉ? አሜሪካ ለደረሰችበት እጅግ የረቀቀ ምድራዊ ጥበብ እነዚህ
በራሪ አካላት ድርሻ ይኖራቸው ይሆን? በራሪ አካላሎቹ ወይም UFO የሚባሉት ከየት የሚመጡ አካላት ናቸው?
በራሄል ከተማ የምትገኝ አነስተኛ ምግብ ቤት (የምስሉን ዓይን ይመልከቱ) |
የነገረ መለኮት ምሁራን UFO ወይም ያልታወቁ በራሪ አካላት የተባሉት የወደቀው መልአክ ሰራዊት ናቸው ይላሉ። እነዚህ
ሰራዊት የሰይጣንን ፈቃድ ለመፈጸም ቃል በገቡ ሀገራት ውስጥ ስራቸውን ይሰራሉ፤ አንዳንዴም በሰው አእምሮ ውስጥ ጥበባቸውን በማሳደር
ልዩ ልዩ ነገር እንዲፈጥር ያደርጋሉ። በተለይም የሰውን ልጅ ከምድረ ገጽ ጠርጎ ማጥፋት የሚችል የምርምርና የመሳሪያ ፈጠራ ላይ
ትኩረት ስለሚያደርጉ «ኤርያ 51» አካባቢ ሲበሩ የሚታዩት እነሱ ናቸው በማለት ያስረዳሉ። ለዚህም ግብረ መልስ የሚሆን ስራ ግብረ
ሰዶምን በመፍቀድ፤ ጾታን በመለወጥ፤ ክሂዶተ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ የሚያደርግ ህግ እንዲተገበር ያስደርጋሉ። በዚህም አሜሪካ ግንባር
ቀደሙን ስፍራ ትወስዳለች ይላሉ። ምክንያቱን ሲያስረዱ፤
«ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ
መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ» ራእ12፤9
ወደምድር ከነሰራዊቱ ወደቀው ሰይጣን ስራው ምንድነው? የሰው ልጅ የሱን የጥፋት መንገድ እንዲከተል ማድረጉ ሳይታለም
የተፈታ ነው። ስለዚህ ባለው ግንኙነትና ከሰው ጋር በሚፈጥረው ውኅደት ሌላው ዩፎ የሚለው አካል የሱ ሰራዊት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን
ይችላል? በማለት ይጠይቃሉ። ለዚህም ያልታወቁ በራሪ አካሎች የተባሉት ፍጡሮች ምስል እንደተዘገበው የኢሉሚናቲ ምስሎችን የተከተለ
መሆኑ ነው። ለዚህም አለምን ለመቆጣጠር ሰይጣናዊና አስፈራሪ ፊልሞች ማምረት፤ በዘፋኞቻቸው የዓለሙን ህዝብ ቀልብ በመሳብ የዘፈን
መንፈሱን የማስረጽ ተግባር እየሰራ መገኘቱን ይገልጻሉ። የሁለት ጣት ምልክት፤ በዓይን ቅርጽ ምስል፤ ወዘተ ስምምነት ይፈጽማል፤ያስፈጽማል።
ላስቬጋስ |
ስለዚህ ኤርያ 51 ምስጢራዊ የግንኙነት ማዕከል
ሆኖ ሊያገልግል ቢችል አያስገርምም። ሌላውን ጉዳይ መንግስት የሰይጣንን ፈቃድ በህግ ይፈጽሙለታል።
አንፈጽምም የሚሉትን ደግሞ ያስፈራራሉ
ወይም ያስገድዳሉ። ከዚያ በፊት ግን በፊልሞቻቸው አስፈራሪ /horror/ እና በአስጸያፊ የወሲብ ተግባራቸው የሌላውን ቀልብ
በመማረክ ወደተግባር እንዲቀየር ያበረታታሉ። ከዚያም በህግ እንዲጸድቅ ያስደርጋሉ። እንግዲህ ያልታወቁ የሚባሉት
እነዚህ አካላት ለኋላው ዘመን የጥፋት መሳሪያ ያስታጥቃሉ፤ አሁን ደግሞ በመንፈስ ሰውን ይቆጣጠራሉ ማለት ነው።
አይ ኤርያ 51? አሜሪካ ውስጥ ያለሽ ሌላዋ አሜሪካ!!