የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ለውጥ ከላዕላይ መዋቅር ይመነጫል እንጂ ለአንድ ሀ/ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ አይደለም!


  • የማኅበረ ቅዱሳን ሩጫ ሀገረ ስብከት የመቆጣጠር ስልት እንጂ ዘረፈ ብዙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ለመፍታት አያገለግልም።
  • ማኅበረ ካህናቱ ከማኅበረ ቅዱሳን አፈናና ስለላ ለመዳን መታገል ያለባቸው ዛሬ ነው!
  • ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ተቋማዊ ለውጥ የሚያስፈልገው ድርጅት ነው!
   ከዚህ ቀደም እንዳልነው ተቋማዊ ህዳሴና አስተዳደራዊ ለውጥ የሚያስፈልገው ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተናዎችና ተግዳሮቶችን  መነሻ ባደረገ መልኩ መሆን አለበት የሚለው ሃሳብ በመጀመሪያ ረድፍ የሚቀመጥ አጀንዳ ነው። ከላዕላይ መዋቅሩ ወይም ከዋልታው የለውጥ ተሐድሶ ባልተጀመረበትና ፈጽሞ ባልታሰበበት ሁኔታ በተናጠል የአንዱ ሀገረ ስብከት አጀንዳ እንደሆነ በመቁጠር በዚያ ዙሪያ መኮልኮል ውጤታማ ፍጻሜ ሊኖረው በፍጹም አይችልም።

 በተለይም ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን በተባለ አንጃ ተጠንስሶና የዲስኩር ውሃ ተሞልቶ ካህናቱ እንዲጠጡ በተዘጋጀው የስልጠና ወሬ የተነሳ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለውጥ ይመጣል ማለት ዘበት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ተቋማዊ ለውጥ የሚያስፈልገው አፈንጋጭ ድርጅት ሆኖ ሳለ የሀገረ ስብከቱ እቅድ ነዳፊ፤ አሰልጣኝና «የያብባል ገና» ዜማ ደርዳሪ ሆኖ መሰየሙ አስገራሚ ነው። እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ላይከዱት በልጆቻቸው ስም ቃለ መሃላ የገቡለት ሊቀ ጳጳስ እስጢፋኖስ «ተቀመጥ በወንበሬ፤ ተናገር በከንፈሬ» ብለው ለማኅበሩ ያስረከቡትን ሀገረ ስብከት ማኅበረ ካህናቱ አሜን ይሁን፤ ይደረግልን ብለው መቀበላቸው ያሳዝናል። በጣፈጠና በለሰለሰ አማርኛ ነገ ብርሃን ሊወጣልህ ነው እያሉ በማደንዘዝ ላይ የተጠመዱት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የአዲስ አበባን ችግር ከአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር በተለየ የመፍታት ምትሃታዊ ኃይል ስላላቸው ሳይሆን ማኅበረ ካህናቱ ማቅ የተባለውን ድርጅት ውስጣችን አናስገባም ብለው ለ21 ዓመት የታገሉትን ለመቋቋም ይቻለው ዘንድ ገሚሱን የስልጠናው ደጋፊና ገሚሱን የስልጠናው ተቃዋሚ አድርጎ ከፋፍሎ በመምታት እግሩን በመሃከል አደላድሎ ለመትከል ያለመ መሆኑን ሊጤን ይገባል።
  ማኅበረ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ መዋቅራዊና አስተዳደራዊ ለውጥ እንዲመጣ ካስፈለገ ከራሷ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና ምሁራን እንጂ ይህ ገንዘቡን በጓሮ እያደለበ፤ ስንት እንደነገደና ስንት እንዳተረፈ ካዝናው የማይታወቅ የመሰሪዎች ስብስብ ማኅበር በሚያረቀውና በሚያቀርበው የስልጠና መርሃ ግብር መሆን እንደሌለበት ማኅበረ ካህናቱ ሊገነዘብ ይገባል። የራሱን በጉያ ደብቆ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን ካዝና ለመቆጣጠር እቅድና ትልም ማውጣቱ ድፍረት ብቻ ሳይሆን ጳጳሳቱ እስከደገፉት የሚከለክለው እንደሌለ ያሳየበት አጋጣሚ ነው።
  መዋቅራዊውን ለውጥ ከግቡ ለማድረስ አቅሙና እውቀቱ ካላቸው ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከቅዱስ ሲኖዶስ መመንጨት አለበት። ከዚያም በተረፈ ቤተ ክርስቲያን ብትጠራቸው ይህንን ለመስራት ማገዝ የሚችሉ ቅን፤ የቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ ግድ የሚላቸው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ያለችበት የአስተዳደር ጉድለት ዘወትር የሚያንገበግባቸው ኦርቶዶክሳውያን ምሁራን ሞልተዋል። ስለዚህ ነጋዴ የወጣቶች መንጋ ስኬት ያገኘ ስለመሰለው ብቻ ሀገረ ስብከቱን ልዘዘው፤ ልናዘው ብሎ ስለጠየቀ ሊፈቀድለት አይገባም። ደረጃውም፤ አቅሙም ስላይደለ ሀይ ሊባል የሚገባው ሰዓት ቢኖር አሁን ነው።

 ስለሆነም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ማኅበረ ካህናት የሆናችሁ ሁላችሁም ይህ ካዝናውን በጓሮ የደበቀ ማኅበር የናንተን የአገልግሎት ካዝና እንዲቆጣጠር ልትፈቅዱለት አይገባም። እርግጥ ነው፤ የብዙ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳደሮች ጉድለት፤ ብክነትና ምዝበራ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። በእኛ እምነት ይህ ችግር የሚቀረፈው የቤተ ክርስቲያኒቱ ላዕላይ መዋቅር የችግሩን አንገብጋቢነትና ስፋት በጥልቀት ተመልክቶ በቤተ ክርስቲያኒቱ ምሁራንና ሊቃውንት አስጠንቶ አጠቃላይ የለውጥ እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ እንደሆነ እናምናለን። ከዚህ ውጪ አንዱን ጫፍ ለማኅበረ ቅዱሳን አሳልፎ በመስጠት ለውጥ ሊመጣ ስለማይችል ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ማሻሻል ጉዳይ እንዲወጣ መታገል ወቅቱ ዛሬ ነው።
በውስጥ ጉዳያችን ማኅበረ ቅዱሳን መግባት የለበትም ለማለት የማኅበረ ካህናቱ ድምጽ መሰማት ያለበት ዛሬ ነው።
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 3 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
December 15, 2013 at 7:19 PM

ደደብ ጴንጤ አንተን ብሎ መካሪ። ከዚህ ሁሉ ጥርግ ብለህ አትወጣም? አስመሳይ።

Anonymous
December 15, 2013 at 7:19 PM


የተሃድሶ መግነን ከአባ ጳውሎስ ጋር እንደ ጠዋት ጤዛ ጠፍቷል። ከአንተ አባባል በማደስ

ዋው መሻሻል ብፁዕ ወቅዱስ አልክ?
ብፅእት ወቅድስት ድንግል ማሪያም ይሄን የደነደነና በምንፍቅና የተሞላ ልብህን በምልጃዋ ታስተካክልልህ። መቼም አይዋጥልህም።


ስሙን ለሰው አዋሰው ይባል የለ? መናፍቁና ፀረ ወንጌሉማ አንተና ራሳችሁን በ30 ዲናር የሸጣችሁ ጓዶችህ ናችሁ። እንደፈሪሳዊ በውሸት ከመክሰስ በስተቀር ምንም የማታውቁ ጉዶች።

የወንድሞች ከሳሽ ግልገል ተሀድሶና የጴንጤ ተቀጣሪ ተላላኪዎች፤ ቀኑን ሙሉ ማቅ፥ ማህበረ ቅዱሳን እያላችሁ ስትከሱ ነው የምትውሉት። ፈሪሳዊያን ኢየሱስን ለቄሳር ሲከሱ በመንግስትህ መጣብህ እያሉ እንደነበረው አንተና መሰሎችህ ግልገል ጴንጤዎችም ለመንግስት ማቅ እኮ መንግስት ሊሆን ነው የሚፈልገው፤ ካልፈረሰ፥ የሸዋን መንግስት ሊመለስ ነው የሚፈልገው እያላችሁ አይደል እንዴ የክስ መአት ከቤተክህነት እስከ ደህንነት ቢሮ የምትደረድሩት?

በአባ ጳውሎስ ሞትማ እናንተም ግብአተ መሬታችሁ ተፈፀመ። ተንፈራገጣችሁ፥ ጣራችሁ ከመላላጥ በስተቀር ምንም ሳትፈጥሩ ቀራችሁ። ብራችሁ በከንቱ ፈሰሰ። በቀላሉ እንኳን ነጋዴው አሸናፊ አባ ጳውሎስ ሲያስነጥሱ መሃረብ በሚያቀርብበት ወቅት ቤተ ጳውሎስ የሚል መካነ ድር ነበረው፤ ሲሞቱበት ያንን ሰርዞ በራሱ ስም ይፅፍ ጀመር።ምስኪን። እሱም ተወገዘ።

ሙስናውና ንቅዘቱንማ እነ እጅጋየሁን፤ ኤልያስን፤ ሰረቀን ታካችሁ ስታስፋፉ አልነበር እንዴ? ለአባ ጳውሎስ እኮ ሃውልት እስከማቆም ሄዳችኋል። በጋሻውና ኤልዛቤል አልነበሩ እንዴ አደራጆቹ?

ጳጳሶቹ የናንተ ማስፈራራትና መደለያ ተቋቁመው፥ ተወጥተው ነው ከማህበሩ መውጣት ያልቻሉት? እናንተ ስማቸውን ካጠፋችሁት የበለጠ የሚጠፋ ስም አላቸው? በምርቃና ምን ያላላችኋቸው አለ? ሌላ እናንተ የማታውቁት አለባቸው? አንተ እንኳን እዚህ አቡነ ጎርጎርዮስን ስማቸውን ስታጠፋ አልነበር? አባ ሰላማ፤ ሙሉጋኔን ወልደሰይጣን ወይም ሙሉጌታና ዌብ ሳይቱ አውደምህረትና አንተ አቡነ ሳሙኤልን፤ አባ አብርሃምን፤ አባ ዲዮስቆሮስና ሌሎቹን ስም ስታጠፉ የምትውሉት? ተራ አሉባልተኞች፤ አንሶላ አጋፈናል ባይ ባለጌዎች። ደሞ ወንጌል እናውቃለን ባይ ግብዝ አስመሳዮች።

በሁለት፥ በሶስት ቢለዋ መብላት ለምዳችሁ እንዴት ለእውነትና ለእውነት ትቆሙ። የጴንጤ ተላላኪዎች፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስትሆኑ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ፤ ውጪ ስትወጡ የስደተኛው ተቆርቋሪ አይደል እንዴ የምትሆኑት? ይሄን አይደል እንዴ የምታደርጉት? ለምሳሌ ትዝታው ከሰረቀ ጋር ወግኖ ማህበሩን ለማፍረስ ተሯሯጠ። እንደውም ከጴንጤ በሚያገኘው ፈንድ በአቋቋመው የEBS ቲቪ ፕሮግራሙን ወክሎ ማቅን ከሰረቀ ጋር ሲከስ ቆየና አሜሪካ ሲመጣ የት ገባ ስደተኛው ሲኖዶስ። አቤት ሁለት፤ ሶስት ቢላ። እናንተ ጥቅም ካስገኘ የማትሸጡት ነገር የለም።

የፓለቲካ ክስህማ ያው እንደናንተ ግብዞች ከሆኑት ከፈሪሳዊያን የተማራችሁት ስለሆነ አይፈረድብህም። ርዕዮት የተባለችው ጋዜጠኛ ፎቶ አንስታ ለኤልያስ ክፍሌ በመላኳ እስር ቤት ናት። ኤልያስ መንግስት በሽብርተኝነት የከሰሰው ሰው ነው። ኤልያስ እንደናንተ ገንዘብ ካወጣ የማይሸጠው የሌለ ግለሰብ ነው። ለማቅ ያለው ጥላቻ ለወያኔ ካለውም ይበልጣል። ይሄን ሁሉ ወጣት ይዞ ወያኔን ስላልተቃወመለት ይጠላዋል። የሱ ሁለት የማይቀየሩ ጠላቶቹ ሁለቱ ናቸው። ልክ እንደሱ በጥላቻ የተሞላው ሙሉጌታ ወይም ጓደኞቹ እንደሚጠሩት ሙሉጋኔን ዲያቆን የሚለውን ስም ሳይጥል የፓለቲካ ዝባዝንኬና ማቅን የሚሳደብ ማንኛውንም ፅሁፍ ያወጣለታል። ሙሉጋኔን ከኤልያስ የሚለየው በአሁኑ ጊዜ ማቅ ብቻ ነው ጠላቱ። ወያኔን በመስደብ የተነሳው መሞነጫጨር አሁን በግልፅ የወያኔ ደጋፊነቱን አስመስክሯል፤ተገለበጠ ማለት ነው። ታዲያ ይሄ ከ“አሸባሪ” ጋር የተባበረ ፓለቲከኛ እያለ ወዴት ወዴት ነው?


ሲጠቃለል ያልበላህን አትከክ። አይናችሁ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጡ። ምንፍቅናህን ይዘህ ከሚመስሉህ ጋር የራስህን እምነት አራምድ። እስከመቼ በማታለል ትኖራላችሁ?

Anonymous
December 16, 2013 at 6:47 AM

መቼም እንዲሁ እንደተንተከተካችሁ ትቀሩ እንደሆነ ነው እንጂ ምንም እንደማታደርጉ እናንተም ታውቁታላችሁ። እናንተ መቼም ማህበሩን በጠላትነት የፈረጃችሁት ቤተ ክርስቲያኗን አንድም ለመመዝበር አንድም ለመበረዝ ዓላማ አድርጋችሁ የተነሳችሁበት መንገድ እየጠበበ ብሎም እየተዘጋ በመምጣቱ እንጂ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኗን የሚጎዳ የተለየ አካሄድ እንደሌለው እናንተው ራሳችሁ በሚገባ ታውቁታላችሁ ነገር ግን ዓላማችሁ ለቤተ ክርስቲያን አስባችሁ ሳይሆን ከላይ እንደጠቀስኩ ጥቅማ ጥቅሙ ስለሚጓደል ነውና አትልፉ። ዛሬ እውነቱ እየታወቀ የማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አጋርነቱ ከእናንተ ከጥላሸት መቀባት አልፎ ከምንጊዜውም በላይ የማኅበሩ በጎ አካሄድ እየተገለጸ በመሆኑ እናንተ ስለማኅበሩ የምታሰሙት የጥላቻ ሮሮ የእናንተኑ ማንነት የሚገልጽ እየመጣ ስለሆነ ምንም መልካችሁም ማንንታችሁ በአካል ባይገለጽም ሥራችሁ ግን ማንነታሁን በትክክል ስለሚያመለክት እንዲሁ የሥራ ፈት ሥራ ወሬ ስለሆንና መኖሪይችሁም ስለሆነ እየቀለላችሁ መሄዳችሁን ልብ በሉ። ይህንን ስጽፍ የማህበሩ አባል ሆኜ ሳይሆን በቤተ ክርስቲይን ልጅነቴ መሆኑን እንድታውቁትም እፈልጋለሁ። ማኅበሩም መልካም ሥራውን በእግዚአብሔር ፈቃድ ለፍጻሜ ያደርሰዋል እናንተም ሆናችሁ ጥቅመኞች ታፍራላችሁ ወይም በንስሐ ራሳችሁን መርምራችሁ እውነትን ለመናገር ትመልሳላችሁ የሚል ምኞቴ ተሟጦ አላለቀም። እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ።

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger