(ሰበር ዜና) የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፤ ፀሐፊዎችና አጠቃላይ ማኅበረ ካህናቱ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቤቱታቸውን አቀረቡ!


   ስድስት ገጽ የያዘው የማኅበረ ካህናቱ አቤቱታ በግልባጭ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፤ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና ለሚመለከታቸው ክፍሎች ሁሉ ገቢ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል!
       (ደብዳቤውን ከታች አቅርበንላችኋል)
      ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ አይደለም በማለት ያሳሰቡ ሲሆን ይህ ተረፈ ደርግና በቤተ ክርስቲያን ታዛ የተጠለለ ነጋዴ ድርጅት የመጨረሻ እልባት ሊሰጠው የሚገባው ወቅት አሁን ነው በማለት ጠየቁ!
      ማኅበረ ቅዱሳንና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ሊቃነ ጳጳሳት በሚፈጥሩት ሁከት ቤተ ክርስቲያናችን እየታመሰች መቀጠሏ ማቆም አለበት በማለት ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል!
      የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ችግር ከአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር ጋር በሲኖዶስ የሚታይና የአስተዳደር ለውጥ ለማድረግም ሲኖዶሱ በሚሰጠው መመሪያ በምሁራን ልጆችዋ፤ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ በሕግ አዋቂዎች፤ በአስተዳደርና በማኔጅመንት እውቀትና ልምድ ባላቸው አባላት ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት በሚቀርብ የማሻሻያ ረቂቅ ደንብ እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረቴን መቆጣጠር አትችልም ባለ ዐመጸኛ ቡድን መሆን ስለማይገባው ቅዱስ ፓትርያርኩ አስቸኳይ መፍትሄ ይስጡን በማለት ተጠይቀዋል!
      21 ዓመት የተሸከምነውን ይህን ማኅበር ከእንግዲህ ተሸክመን በዚህ ዓይነት መልኩ ለመዝለቅ ስለማንችል መንግሥት አንድ እልባት እንዲሰጠን እንጮሃለን ብለዋል! በቃ የሚባልበት ወቅት ቢኖር አሁን ነው ያሉት ተሰብሰባዎቹ ወደፊት በዚህ ማኅበር ምክንያት ለሚመጣው ጉዳት ኃላፊነቱን አንወስድም ሲሉ ያላቸውን ፍርሃትም አሳስበዋል!
      ቅዱስ ፓትርያርኩም ጉዳዩን በቀላሉ እንደማይመለከቱትና መፍትሄም እንደሚሰጡ ቃል የገቡላቸው ሲሆን ማኅበረ ካህናቱ ያላቸውን ችግር ለመፍታትና ለመነጋገር የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ክፍት ሆኖ እንደሚያገለግላቸው ገልጸውላቸዋል!
   ከታች የቀረበው ጽሁፍና ማመልከቻ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በጠቅላይ ቤተክህነቱ አዳራሽ የቀረበ የማኅበረ ካህናቱ ፊርማና አቤቱታ ነው።
                       ዐቢይ ዜና

ማኅበረ ቅዱሳን በአዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ ለውጥ ምክንያት እየደረሰበት ያለው ተቋሞ ተጋግሎ ቀጥሏል፡፡ በየሆቴሉ በድብቅ ይሰበሰባሉ ሲባሉ የቆዩት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች በገሀድ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ተሰብስበው ፓትርያርኩንና አንዳድ የማኅበሩን ደጋፊ ሊቃነ ጳጳሳት አስጠነቀቁ፡፡ ጥያቄዎቻችን ምላሽ የማያገኙ ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በጥቁር ራስ (መነኮሳት ባልሆኑ) ሰዎች እንዲካሄድ በሕጋዊ መልኩ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰራተኞች ቤተክርስቲያኒቱ የአሰራር ለውጥ እንደሚያስፈልጋት አምነው ለውጡ ሁለንተናዊና መላውን የቤተክህነቱ ክፍል ሊያቅፍ እንደሚገባ ሕጉም ከዋናው ከሕገ ቤተክርስቲያን መጀመር እንዳለበትና በየደረጃው ደንቦችና መመሪያዎች ሊወጡ እንደሚገባው አስረድተው ይህንን የሚሰራው አካልም ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከሊቃውንት ጉባዔ፣ በየደረጃው ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሰራተኞች ፣ ከገለልተኛ ባለሙያዎች ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተወጣጣ ኮሚቴ መሰራት እንደሚገባው አስምረውበታል፡፡
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጥያቄያችሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ትኩረት ይፈልጋል  በማለት ኮሚቴ እንዲቋቋም ፈቅደዋል በቤተክህነቱ አዳራሽ መሰብሰብ እንደሚችሉ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ስብሰባው ያበሳጫቸው አቡነ እስጢፋኖስ ግለቱ ከብዷቸው ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ ግልጽነት የጎደለውና ቤተክርስቲያኗን ለአንድ ማኅበር ድብቅ ዓላማ እና ፍላጎት አጋልጦ የሰጠ በመሆኑ፣ የካህናት ቅነሳ በሚል አገልጋዮችን የሚበትን ፣ ቤተክርስቲያኒቱ ያሏትን ሊቃውንት ያላካተተ በመሆኑ፣ የሰንበት ትምህርት ቤትን በማዳከም በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ብዙ ማኅበር እንዲደራጅና ሕጋዊ እንዲሆን በማድረግ በወጣቱ ዘንድ መከፋፈል የሚፈጥር በመሆኑ እንደማይቀበሉት  አስታውቀዋል፡፡    ማኅበረ ቅዱሳን  በጥቅምቱ የሰበካ ጉባዔ ምልአተ ስብሰባ በተወሰነው መሠረት  የ55 ሚሊዮን የቤተክርስቲያኗ ምእመናን ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በወሰኑትባ በአቋም መግለጫ ባጸኑት ውሳኔ  መሠረት  ሀብትና ንብረቱን እንዲያሳውቅና በቤተክርስቲያኗ አሰራር መሠረት በሕጋዊ ሞዴሎች እንዲጠቀም ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለቅዱስ ፓትርያርኩ በ 5000 ሰራተኞች ፊርማ በቀረበውና ለመንግሥት አካላት ግልባጭ በተደረገው ደብዳቤ ተጠይቋል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን በተዘጋጀውና ለአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ብቻ እንዲተገበር በታለመው የመዋቅራዊ ጥናት ምክንያት  በሀገረ ስብከቱ ሥር በሚገኙ አድባራትና ገዳማት ሠራተኞችና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለው አለመግባባት ቀጥሏል፡፡ መዋቅራዊ ጥናቱን ይቃወማሉ የሚባሉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት በማምራት ቅዱስ ፓትርያርኩንና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትን አነጋግረዋል፡፡ የአቋም መግለጫቸውንም ለፓትርያርኩ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ የቤተክርስቲያን አካል ሆኖ እያለ ለመላዋ ቤተክርስቲያን መመሪያ አውጪ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን ወዴት ነው ያለው እንዳስባላቸው ተሰብሳቢዎቹ ለፓትርያርኩ አስረድተዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እራሱ ለቃለ አዋዲውና ለሕገ ቤተክርስቲያን ሳይገዛ እንዴት ሕግ አውጪ ሊሆን ቻለ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ መመሪያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ከሕገ ቤተክርስቲያን ጀምሮ በየደረጃው መመሪያና ደንብ እንዲወጣና ይህንንም አንድ ማኅበር ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ያሉ እና ገለልተኛ አካላት ሊያዘጋጁት ይገባል ብለዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ ማኅበሩ መዋቅራዊ ጥናቱን ለምን በድብቅ መስራት አስፈለገው፣ ሊቃውንት ለምን እንዲሳተፉ አልተፈለገም የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ለጥያቄዎቹ መልስ በሚሰጥበት ወቅት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የማኅበሩ የኢዲቶሪያል ኮሚቴ አባል ስለ መዋቅሩ አስፈላጊነት ለመግለጽ የሞከሩ ሲሆን አቡነ እስጢፋኖስ ግን ስለ ጥናቱ ብዙም መረጃ እንደሌላቸውና አንዳንዱንም ከተሰብሳቢው ወገን እንደሰሙ በመግለጽ እርስ በእርሱ የተምተታ መልስ ሰጥተዋል፡፡ መመሪያውና ጥናቱን ወድቆ ብናገኘውስ ምን ችግር አለው ሲሉ ምንጩን ለመደበቅ ሞክረዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄያቸውን ማይመልስ ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በጥቁር ራስ (መነኮሳት ባልሆኑ) ሰዎች እንዲካሄድ በሕጋዊ መልኩ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የተሰብሳቢዎቹ ጥያቄ አግባብ የሆነና በትኩረት መታየት እንዳለበት አስረድተው ከተሰብሳቢዎቹ ጉዳዩን የሚከታተል 15 ዐቢይ ኮሚቴ እና 20 ንዑሳን ኮሚቴዎች አስመርጠው በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ በመሰብሰብ ጉዳዩን በይበልጥ በትኩረት እንዲያጠኑ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለጊዜው እንዲቋረጥ ብፁአን አባቶች ሀሳብ የሰጡበት የመዋቅራዊ ጥናት ስብሰባ በአቡ እስጢፋኖስ ትእዛዝ እንደቀጠለ ሲሆን የሥልጠናው መሪ ማኅበረ ቅዱሳኑ አቶ ታደሰ ፍስሐ በሥልጠናው ተሳታፊዎች እናንተ እነማን ናችሁ? ከሊቃውንትስ ማንን ይዛችሁ ነው የምትሰሩት በሚል ለተነሳላቸው ጥያቁ በደፈናው የቤተክርስቲያን ልጆች ነን ከሊቃውንትም ታላቁን ሊቅ አቡነ እስጢፋኖስን ይዘን ነው የምንሰራው በማለት ምላሽ ሲሰጡ አዳራሹ በስላቅ ሳቅ ደምቋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኛ አቶ ደስታን በሥልጠናው ሥፍራ በወሬ አቀባይነት መድቦ በሬኒ ካፊና ሬስቶራንት የምሳ እና የሻይ እየተከፈለው አንዳንድ መረጃዎችን ለማኅበሩ ሥውር ብሎጎች እንዲያቀብል መድቦታል፡፡ የአዲሱ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አባል የነበረውና ወደ ቤተክህነት እቃ ሊያደርስ ተልኮ በድንገት ሠራተኛ የሆነው አሁንም በጠ/ቤተ ክህነቱ ገዳማት አስተዳደር ተጧሪ ሆኖ ደመወዝ የሚበላውን ይህንን ጨዋ የአድባራት እና ገዳማት አለቆችንንና ሰራተኞችን ስም በማጥፋት ተግባሩ ማኅበሩ አንቱታን ቸሮታል፡፡ በተጨማሪ እነ ጳውሎስ መልክአ ሥላሴም በዚሁ ተግባር በመሳተፍ ከቤተክህነቱ አደባባይ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 13 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
December 21, 2013 at 8:24 AM

የአዛኝ ቅቤ አንጓች ጴንጤ ለኦርቶዶክስ ቄስ አዝኖ አለቀሰ። መሳቂያ።

Anonymous
December 21, 2013 at 9:58 AM

እንደ እናንተ አባባል ቢሆን ገና ድሮ ሳይጀመር ቀርቶ ነበረ። ከመጠን በላይ ውሸታሞች ስለሆናችሁ እናንተንና ግብረ አበሮቻችሁን የሚያዝናና ይሆን እንደሆነ ነው እንጂ አእምሮ ያለውን ሰው ጆሮውን እንኳ አይኮረኩረውም። እንደ እናንተ የውሸትና የጥላቻ የምዝበራና የብረዛ አካሄድ ሳይሆን በትክክለኛው ግምት ሲታይ ግን ምንም ጊዜም በየትኛውም መንገድ ለውጥ ለሰው ልጅ አስደጋጭ ሊሆን የሚችልበት መንገድ አለ። ተቃዋሚ አለ ደጋፊ አለ በእናንተ በኩል እንደሚነገረው ከመጠን በላይ ተጋኖ ሳይሆን መጠነኛ ቁጥር ያላቸው ተቃውመውታል። ይህም በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል ጥቅመኞችና የለውጡን አካሄድ በሚገባ ያልተረዱ በእናንተ ዓይነቱ አሉባልታና አፍራሽ ዓላማ የተጠመዱ ናቸው። የወሬ ሱሰኛ ብቻ ሳትሆኑ ለአጥፊ ዓላማም የምትሠሩ በመሆኑ የለውጡ እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያኗን አስተዳደር መልካም እርምጃ የሚታደግ በመሆኑ ለመሰሎቻችሁ የእግር እሳት ነውና መፍጨርጨር አይቀርም። የሆና ሆኖ እውነት ይገለጣል የእናንተም ደባም በፊት ለፊት እየታየ ስለሆነ ሁሉንም በቅርቡ እናየዋለን እናንተ በውጪ ዓለም እያውደለዳልችሁ ወሬ መሥራቱ የቅጥረኝነት ስለሆነ ምንም አያስደንቅም።

Anonymous
December 21, 2013 at 9:08 PM

fake letter. 1. it does not include names of individuals. 2. many writing errors.

Anonymous
December 22, 2013 at 6:21 AM

ይሄን ፅሁፍ Getch Addis የተባለ ግለሰብ Facebook ላይ የፃፈው አስተያየት ነው።
(እርግጥ አንተ ጴንጤው የጴንጤዎችን የኢየሱስ አማላጅነት ልስበክ ባይ፥ የታቦትን ጣውላነት ለመናገር ትንፋሽ እስኪያጥርህ የምታወራ፥ የቅዱሳን አማላጅነትን የምታጥላላ ሰው ይሄን ስትፅፍ፤ ነገር ለማራገብ ያለህን ፅኑ ፍላጎት ቢያሳይም እንደ ቀደመው ሁሉ ምንም አይከሰትም። የአዋሳው ትዝ አለህ? (በነገራችን ላይ የበጋሻው የጴንጤና ተሃድሶ አድናቂ የነበረው ደጀ ሰላም ደጀ ሰላም ተዘግቶብሃል-ምስኪን)
ርዕስ፦
አስተያየት ወዲህ እውነታው ወዲያ! Today at 12:03am
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በዘመናዊ መልክ ለማደራጀት የለውጥ ሥራ አመራርና አደረጃጀት ለመተግበር በቅዱስ ሲኖዶር ተወስኖ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በሆኑ ባለሙያዎች ጥናቶች መካሄድ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የለውጥ ሥራ አመራርና አደረጃጀት ጥናቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የቅርብ ክትትል እየተደረገበት መሆኑም ይታወቃል፡፡ የባለሙያዎች የጥናት ቡድኑ ጥናቱን ካካሄደ በኋላ በጥናቱ ላይ ከትግበራ በፊት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችን እያወያየም ብዙ ዙሮችን ዘልቆአል፡፡ የዚህ ጥናት መሠረታዊ አስፈላጊነትና መነሻው በግርድፉ ለ2000 ዘመናት ያለአንዳች የሰው ሃይል እና የፋይናንስ መመሪያ በደጅ ጥናት የአሠራር “ስልት” ተዘፍቃ አንዳች የኃይማኖት ነቅዕ ሳይኖርባት ነገር ግን በመጥፎ የአሠራር ባለቤትነት ምሳሌ ሆና የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ አሠራር እራሷን ዋጅታ ጥቂቶች አላግባብ ሃብቷን እንደተለመደው ከሚያግበሰብሱባት የሚገባቸው ሊቃውንቷን ጠቅማ የምትጠቀምበትን አሠራር ለመዘርጋት ነው፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ዘመናዊና ግልጽ መመሪያን የመከተል አዝማሚያ የለመዱትን አላግባብ ጥቅም እንደሚያስቀርባቸው ከወዲሁ የተረዱት ግለሰቦች በተገኘ አጋጣሚ እና ባላቸው አቅም ሁሉ የጥናቱን ሂደት ከጅምሩ ለማክሰም ላይ ታች ሲሉ እንደሰነበቱ ከተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲዎች እየሰማን ነው፡፡ በጥናቱ ላይ የሚካሄደው ውይይት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በተቃረበበት በዚህ ሳምንት እንኳን የተወሰኑ የአጥቢያ ሠራተኞችን በማታለልና የሚጎዱ በማስመሰል የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ማስገባታቸው ከተለያዩ የዜና ምንጮች ተሰምቷል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ አጥቢያዎች ከወዲሁ “የተሰበሰቡት የድጋፍ ፊርማዎች አጥቢያውን አይወክሉም” ቢሉም፡፡ በዚህ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ ሂደትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በሙያቸው እንዲሠሩላት አምና የተቀበለቻቸውን የጥናት ቡድን “በኅቡዕ የተደራጀ” በማለት፣ “የሀገረ ስብከቱን ሠራተኞች እንደ ጋምቤላ ባሉ ጠረፍ ቦታዎች ለመመደብ ያለመ” በማለት የሌለ ስም በመስጠት፣ ጥናቱንም “የሠራተኞችን የሥራ ዋስትና አደጋ ውስጥ የሚከት ጥናት”፣… እና ሌሎችንም እያሉ የጥናት ሂደቱን ከመጀመሪያ እስካሁን አባታዊ መመሪያ በመስጠትና በመከታተል ለከረሙት ለቅዱስ ፓትርያርኩ አስገብተዋል፡፡ ከዚህ አልፎም የባለሙያዎች የጥናት ቡድን በየውይይት መድረኮቹ ስም ሳይጠቀስ ግብረ መልስ በሚሰበስብባቸው አስተያየት መስጫዎች በጣት የሚቆጠሩ ነገር ግን ለጥናቱ እና ለባለሙያዎች የጥናት ቡድኑ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች የሚሰጧቸው ውሃ የማያነሱ አስተያየቶች የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንዱ አስተያየት በግርድፉ እንደሰማሁት “ጥናቱን ያጠናችሁ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ስለሆናችሁ ዓላማችሁ ሥራ አጥ አባላቶቻችሁን በሀገረ ስብከቱ ለማስቀጠር እንደሆነ እናውቃለን፣ ከዚህ ይልቅ በጥርብ ድንጋይ (Coble Stone) ሥራmብታደራጇቸው ይሻላችኋል” የሚል ነበር፡፡ ከዚህ “አስተያየት” ሁለት ነገሮችን ማንሳት ፈለግኩ፡፡ “ጥናቱን ያጠኑት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው” የሚለው እና “ለማኅበሩ ሥራ አጥ አባላት ሥራ ለማስገኘት” የሚሉትን፡፡ በመሠረቱ ይኸ የለመደብን የጸለምተኝነት አመለካከት (Pessimism) ሆኖ እንጂ ጥናቱ ምንድነው? ምን ጥቅም ያስገኛል? ምን ጉድለት ይሸፍናል? የሚለው ማን አጠናው? ከሚለው መቅደም ነበረበት? በመሠረቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የቤተ ክርስቲያን አባላት ናቸው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ከመሆናቸው በፊት የቤተ ክርስቲያን አባላት ነበሩ፣ ዛሬም ናቸው፣ ወደፊትም እንዲሁ፡፡ አባላቱ ብቻ ሳይሆኑ ማኅበሩም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ነው፡፡ አገልግሎቱም የቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፡፡ ይህን ለማለት የፈለኩት እንደ እነሱ አባባል ቢሆን እንኳን ለማለት ነው እንጂ በጥናቱ እየተሳተፉ ካሉት ስንቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንደሆኑ ፈጣሪ ይወቀው፡፡ ሁለተኛው እነሱ ስለምሉት “ሥራ አጥ” የማኅበሩ አባላት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ይህ ፈጽሞ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ካለማወቅና መረጃ ከማጣት የተሰጠ አስተያየት ነው፡፡ እውነት ሥራ አጥ የሆነ የማኅበረ ቅዱሳን አባል አለ? እነዚህ ሰዎች ባያውቁት ነው እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን እኮ አባላቱ በትፍር ጊዜአቸው (ከሥራ መልስ፣ በሰንበት ቀናት እና በአዳር መርሐ ግብሮች) በሚያበረክቱት አገልግሎት አገልግሎቱን መሸፈን ባለመቻሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለሙያዎችን በሙሉ ጊዜ ቀጥሮ የሚያሠራ ማኅበር ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ሥራ አጥነት ኃጢአትም ጽድቅም ሆኖ ሳይሆን ለእውነታው ብቻ ነው ይህን የማነሳው፡፡ እንዲህ በጭፍን ጥላቻ ለሚመሩት ወገኖች ግን “ልቡና ይስጣቸው” ከማለት በሌላ በምን ልንረዳቸው ይገባ ይሆን?

Anonymous
December 22, 2013 at 7:53 AM

ስም አጥፊው ውሸታም፥ ሃሜተኛ ጴንጤ ለመሆኑ ይሄንን ጥያቄስ ያቀረቡት መነኩሴዎች አይደሉም እንዴ? እንዴት ነው እንዳንተ እንደ መናፍቅ ቅጥረኛው አባባል በጥቁር ራስ አንመራም የሚሉት? ራሳቸው ጥቁር ራስ ሆነው? ነው ወይስ የተሃድሶ ጴንጤ ቅጥረኛ፥ ወይም የሙስና ተባባሪ ሌባ ሲሆኑ ወዲያው ወደ ነጭ ራስነት ትቀይሩላችኋላችሁ? እናንተ እኮ ተዐምረኞች ናችሁ።የጌታ “የሱስ” ተዐምር።
ከሙሰኞቹና ከእንደ እናንተ አይነት የጴንጤ ቅጥረኞች ጋር የተያዘው የመጀመሪያ ትግል ሙስናና ስርቆት ማስወገድ ነው። ትግሉ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረት (አጥንት) ለብዙ ጊዜ ካለ ሃይ ባይ ሲግጡ የነበሩ ሌቦች፥ቅጥረኞች፥ እንደአንተ አይነት ሁለት ደሞዝ የሚቀበሉ ጴንጤዎችን (ውሾችን) -ምሳሌ ነው- ማስለቀቅ ነው። ይሄ ደሞ ከባድ በጣም ከባድ ነው። ውሻን ከአጥንቱ ማስጣል ከባድ ነው።
ሌላው እግዚአብሔርን፥ ቤተክርስቲያንን፥ ህዝብን ከሆነ የሚያገለግሉት ሁሉም እግዚአብሔርም፥ ቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ህዝቡ የሚላኩበት ቦታ ስላሉ የሚያናድዳቸው ነገር የለም። አገልግሎታቸውን ማከናወን ነው። ግን እንደአንተ የገንዘብ ቅጥረኞች ስለሆኑ ከአአ አብያተ ክርስቲያናት መውጣት ጨነቃቸው? ግራ የገባህ።
ሙስናም ይጠፋል፤ ተሃድሶም ይመነጠራል።

Anonymous
December 23, 2013 at 10:24 AM

ግብዝ ማቆች ቆሻሻ ስድባቸውን የሚተፉት ሲናደዱ ነው። በጋሻው በማቅ ስር ከመማቀቅ ነፃ ወጥቷል። ማቅም ፋይሉ ይዘጋል: የበጋሻው አገልግሎት ይቀጥላል።

Anonymous
December 23, 2013 at 10:24 AM

ግብዝ ማቆች ቆሻሻ ስድባቸውን የሚተፉት ሲናደዱ ነው። በጋሻው በማቅ ስር ከመማቀቅ ነፃ ወጥቷል። ማቅም ፋይሉ ይዘጋል: የበጋሻው አገልግሎት ይቀጥላል።

Anonymous
December 23, 2013 at 10:25 AM

ግብዝ ማቆች ቆሻሻ ስድባቸውን የሚተፉት ሲናደዱ ነው። በጋሻው በማቅ ስር ከመማቀቅ ነፃ ወጥቷል። ማቅም ፋይሉ ይዘጋል: የበጋሻው አገልግሎት ይቀጥላል።

Anonymous
December 23, 2013 at 10:25 AM

ግብዝ ማቆች ቆሻሻ ስድባቸውን የሚተፉት ሲናደዱ ነው። በጋሻው በማቅ ስር ከመማቀቅ ነፃ ወጥቷል። ማቅም ፋይሉ ይዘጋል: የበጋሻው አገልግሎት ይቀጥላል።

Anonymous
December 23, 2013 at 5:05 PM


ሃሃ ሃሃ ቂቂቂ
ተሃድሶ ጴንጤዎች ቆሻሻ ስድባቸውን ሲያዘንቡት ቆይተው ሌላውን ሰደበን ይላሉ።
ይሄ እኮ ነው ግብዝነት። ማቅ ፋይሉ ይዘጋል አልክ? ይሄን ነገር እኮ እንዳንተ አባባል በንዴት ቆሻሻ ስድብ የሚሳደበው፤ግብዙ ሙሉጋኔን ወልደሰይጣን ካለው እንኳን 10 ዓመት ሊሞላው ነው። የሚያሳዝነው የራሱና የተሃድሶ ፋይል ተዘጋ። በል አልቅስ ሁለት ደሞዝ ቀረ። ቀረ። ቀረ።
የማቅ አገልግሎት ይቀጥላል። ጴንጤ ከቤተክርስቲያኗ ይወገዳል።

Anonymous
December 23, 2013 at 6:53 PM

በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ብሎግ ላይ ብዙ ጊዜ እንደማነበው አብዛኛው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተነጣጠረ ራሱን የቻለ ተራ የጥላቻ ዘመቻ ከመሆኑ ሌላ ማኅበሩ ለሚውነጀልበት ጉዳይ አንድም ተጠጨባጭ የሆኑ ማስረጃዎች ሲቀርብ አንብቤም አላውቅም። አሁን ግን በትክክል እንደገባኝ ተራ ወሬ እየነዙ አላዋቂውን ለማሳሳትና ለጊዜው ጥርጥር ውስጥ ለመክተት በዓላማ የሚሠራ ብሎግ መሆኑን ከምንጊዜውም በበለጠ እየተረዳሁት ነው። አሁን ስለአዲስ አበባ ህ/ስብከት የመዋቅር ጥናት ላይ በተቃውሞ የተነሱ ጥቂት ግለሰቦች የተቃወሙት የብዙኃኑን አግልጋዮች የኑሮ መሻሻል እንጂ በማኅበሩ ላይ የሚያመጡት የቅንጣት ያህል ጉዳት አይኖርም። አንድ የማምንበት ጉዳይ አለ የጥናቱን ይዘት አንድ በአንድ በመተንተን ጎጂ ናቸው የሚሉትን እንኳ ነጥቦች አንስተው የገለጹት አንድም የሚታይ ቁም ነገር የለም። ይህ ከሆነ ዘንድ በግልጽ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አካሄድ በተለይ በአለፉት ሃያ ዓመታት የታየው የአስተዳደር ብልሹነት ካህናት፡ መነኮሳት ይሁኑ አይሁኑ በሚያጠራጥርበት ሁኔታ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ሰርገው በመግባታቸው አሁን የሚታየው ትርምስ ፈጠሪዎች የመሆናቸው አንዱ ትልቁ ማሳያ ሲሆን ይህንን ለማስቆም በማኅበርም ይሁን በግል በቤተ ክርስቲያን ልጅነት ለቤተ ክርስቲያን አጋር በመሆን የቆመ ወጣት ትውልድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱ ያስፈራቸውና በውስጥም ሆነ በውጪም ቤተ ክርስቲያኗን ለማዳከም የሚደረጉት ሤራ ከምንጊዜውም በበለጠ እየተገለጠ በመምጣቱ ነው። እናንተም የመድረኩ ተዋንያን በመሆናችሁ እውነት ለእናንተ ፍጽም እየራቀች ነው። ለጊዚያዊ ጥቅም ሲባል በቤተ ክርስቲያኗ የቆሸሸ እጅን ማንሳት የሚያመጣው መለኮታዊ ቅጣት ቀላል አይሆንምና ከወዲሁ ራሳችሁን መርምሩ።

Anonymous
December 24, 2013 at 12:35 PM

ሁልጊዜ ለውጥን የሚቃወሙት እራሳቸውን ማሳደግ የማይፈልጉና በራሳቸው የማይተማመኑ ሰዎች ናቸው

Anonymous
December 25, 2013 at 2:11 PM

musina ena nufake eskalkome MK tiglun ayakomim. yetshalew amarach huletun makomu let ke MK gar gingnunetu tenama yihonal

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger