ያገር ያለህ ወይም የዳኛ ያለህ!!!


ከእውነቱ ( ክፍል ሁለት)

በማህበሩ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ላይ ያስተዋልኩት ድካም፡

 የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የጫነችብንን ኢመጽሐፍቅዱሳዊ የባእላት አከባበርን ሕዝቡ በበለጠ
መልኩ እዲቀጥልበት ለማድረግ ሰምተናቸው ለማናውቃቸው ሰዎች የቅድስና ማእረግ
በመስጠት/በማሰጠት ሕዝቡ ከሥራ ይልቅ ባእል አክባሪ እንዲሆን መደረጉ፣
 በሌለ የጉልበትና የገንዘብ አቅም ሕዝቡ ለጽድቅ እየተባለ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች በመጓጓዝ
እንዲደክም መደረጉ /ፈጣሪ በቦታ የሚወሰን ይመስል/
 በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የጽላት ቀረጻና
የታቦት ተከላ ሥራ መሥራት፣
 እግዚአብሔርን ተርቦና ተጠምቶ በአውደ ምህረቱ ዙሪያ ለተሰበሰበው የዋህ ሕዝብ ፍቅር
የሚያስተምረውን የወንጌል ቃል ከመስበክ ይልቅ በእለቱ የሚከበረውን የጻድቅ ገድልና ታሪክ
ከሃይማኖትህን ጠብቅ የማስፈራሪያ መርገም ጋር በማሰማት ለጦርነት ማዘጋጀት፣
 ሕዝቡ በራሱ መረዳት ማን ምን እንደሆነ በእግዚአብሔር ቃል እውቀት እየመዘነ ሃሰቱንና
እውነቱን በመለየት የሚጠቅመውን እንዳይዝ መረጃ በሌለው አሉባልታ ተሞልቶ በውስጡ
ጥላቻና ቂም አዝሎ የራሱን ወገን እንዲጠላ በልዩ ወንጌል ሰባኪዎች መሰበኩ፣
 የበጉ ሐዋርያትና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ቀደምት የእምነት አባቶች አድርገውት የማያውቁትን
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ በጸበል ተገኘ ጋጋታ ሕዝቡን ማንገላታታቸው፣
 በአጠቃላይ ሕዝቡን በቃል እውቀት ሳይሆን በቅርስና በባንዲራ ፍቅር የራሱን ወንድም
በጭፍን ወግሮ የሚያሳድድ ሃይማኖተኛ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑን ይህ ጸሐፊ በራሱ ቤተ
ሰብ መካከል ባደረገው አጭርጥናት ሊያረጋግጥ ችሏል።

2/ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ማነው?

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተወልደው በማደግ ባህሏንና ትምህርቷን ጠንቅቀው የሚያውቁ
የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ነን ይላሉ፤ የኦርቶዶክስ ተሐድሶ ማህበር በሚል መጠሪያ ስም፡ ኦርቶዶክስ
ቤተ ክርስቲያናችን ከውጭና ከውስጥ በደረሱባት ልዩ ልዩ ተጽእኖ ምክንያት ከተመሰረተችበት
የክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ርቃ ልዩ ወንጌል በመስበክ የመስቀሉን የማዳን ሥራ ቸል ብላለች፤ ስለዚህ
ወደ ቀደመ የወንንጌል ጅማሬዋ ትመለስ፤ በእግዚአብሔር ቃል /መጽሐፍ ቅዱስ/ መስተዋት ፊቷን
በማየት ክፉ ሰዎች ያለበሷት የደብተራዎች፣ ያስማተኞችና የደጋሚዎች ልብስ በንጹሁና እንከን የለሽ
በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ልብስ /በክርስቶስ/ ይተካ በማለት ይጮሃሉ።

እንዲያውም እነዚህ ሰዎች የቤተ ክርስቲያናችን ወይም ያገራችን ታሪክ ይፈተሽና ይመርመር፤ ይዘነው
የተነሳነውንም የተሐድሶ ጥያቄና ሃገራዊ አጀንዳ ያገራችን ሽማግሌዎች፣ ጳጳሳት፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች
በአጠቃላይ ሕዝቡ ይስማውና ማን የኦርቶዶክስ ጠላትና ወዳጅ እንደሆነ ጠቅላላ ምእመኑ እውነቱን
ይረዳ በሚል ግልጽነት በይፋ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን መረዳት ችያለሁ።
እኔም እነዚህን አንዳንድ የኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያንን የተሀድሶ ሥራ አራማጆችን ጠጋ ብየ በመጠየቅ
የሚከተሉትን መረጃዎችን አግኝቻለሁ፡

1. የቤተ ክርስቲያናችን ጅማሬ ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ በወንጌል ላይ ብቻ የተመሰረተች መሆኗን፣

2. በመጀመሪያው ጳጳስ በወንጌል ላይ የተጀመረው ክርስትናችን ግን እኒሁ ጳጳስ ከሞቱ በኋላ፡
 በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር ስር በመውደቅ ለ1600 ዓመታት ከ110 በላይ በሚሆኑ
የውጭ ሀገር ጳጳሳት /የግብጽ የፖለቲካ ሠራተኞ/ መንፈሳዊ ቅኝ ተገዢዎች በመሆን አባይን
በመገደብ ሥራ ሠርተን እንዳንበላ እስካሁን ድረስ የ30 ቀናት ባእላት ባሪያዎች መደረጋችንና
ከእነዚህ መካከል አንዱ የካሊፋው ዋና ወኪል /አቡነ ሳዊሮስ/ እነደነበረ፣
 የዮዲት ጉዲት የ40 ዓመታት ግዛትና የቤተ ክርስቲያኗ መጽሐፍትና ካህናት መቃጠል፣
 የግራኝ ሙሐመድ የ15 ዓመታት ግዛትና የሙስሊም ክርስቲያኑ ሬሽዮ 9፡1 መድረሱና የቤተ
ክርስቲያኒቷን ውበት ማበላሸቱ፣

 ዘርዓ ያእቆብ በንግስናው ወራት በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተመዘኑ የድርሰት ጽሑፎችን በቤተ
ክርስቲያኒቷ ውስጥ ያለገደብ ማስገባቱና የተሃድሶን ጥያቄ ያነሱ መነኮሳትን መጨፍጨፉ
/የፕ/ር ጌታቸውን ደቂቀ እስጢፋኖስን መጽሐፍ መረጃ ይጠቅሳሉ/፣
 የቤተ ክርሰቲያኒቷ ሲሦ መንግሥት ውል መዋዋልና ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ መንግሥትን
ከሰሎሞንና ከዳዊት ጋር በማያያዝ የታቦትና የጽላት መጥቷል አፈታሪክ ጅማሬ /አቡነ ተክለ
ሐይማኖትን ተጠያቂ ያደርጋሉ/፣

 የደብተራ ቡድን በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ተነስቶ የመናፍስት አሠራር እስካሁን ድረስ
በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በሰፊው መለመዱ ……….. ወዘተ።
የመሳሰሉትን ነጥቦች በድፍረትና በማስረጃ በማቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቷ ከተመሰረተችበት የወንጌል
መሰረቷ ፈቀቅ ብላለችና ወደ ቀደመ የወንጌል ጅማሬዋ ትመለስ በማለት አጥብቀውና በነፍሳቸው
ተወራርደው ለዚህ ሥራ እንደተነሱ ጨክነው ይሟገታሉ። ይህም መንፈሳዊ መታደስ በአገሪቱ ውስጥ
ላለው ሁለንተናዊ ችግር /ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ችግር/ ዋና መፍትሄ ይሆናል
ብለው በማስራጃ ለማሳመን ይሞክራሉ።
ይህን ጉዳይም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ተረድቶና ማን ምን እንደሆነ ተገንዝቦ ለመንፈሱ፣ ለነፍሱና
ለሥጋው የሚበጀውን በመጽሐፍ ቅዱስ/በወንጌል ሚዛን መዝኖ የሚረባውን ይይዝ ዘንድ
ራእያቸውንና ዋና ተልእኳቸውን ለሕዝብ በይፋ ያቀርባሉ፡

የተሐድሶ ራእይ፡

‘‘ጥንታዊና ሐዋርያዊት የነበረች ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን በየዘመናቱ ከደረሰባት ውስጣዊና
ውጫዊ ተጽዕኖ የተነሳ ከተተከለችበት የእውነት ወንጌል በማፈንገጥ አሁን ላለችበት ውድቀት
በመዳረጓ ይህን ሁኔታዋን በከበረው የጌታችንና የመድኃኒታችን ቅዱስ ወንጌል በመመዘንና ወደ ቀደመ
የወንጌል ክብር በመመለስ በእጇ የሚገኘውን ተከታይና የተቀረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስቶስ
ኢየሱስን በማወቅና በማመን የሚገኘውን የዘላለም ሕይወት በማግኘት ለጌታችን ቀን ያለነውርና
ያለነቀፋ ሆኖ እንዲገኝ በማዘጋጀት ለአፍሪቃና ለተቀረው ዓለም የሚላኩ ቅዱሳን አገልጋዮችን
በማፍራት የሚጠበቅባትን የወንጌል አደራ ስትወጣ ማየት ነው’’

የተሐድሶ ተልዕኮ፡

1. የቤተ ክርስቲያኒቷን አንድነትና የሀገራችንን ጥቅም በጠበቀ መልኩ ምዕመናን በጌታችንና
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትክክለኛና እውነተኛ ተሀድሶ በማድረግ ለዘላለም
ሕይወት እንዲዘጋጁ መርዳት፣

2. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንደ የደረጃው በተዘጋጁ የወንጌል
ትምህርቶች በማሰልጠንና በማሳወቅ ለስብከተ ወንጌል ሥራ ማዘጋጀትና የአገልግሎት ቦታዎች
ሁሉ እውነትን በተረዱ አገልጋዮች እንዲሸፈኑ ማድረግ፣

3. በየዘመናቱ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ የገቡትን የስህተት ትምህርቶች ሥርዓቶችና ባሕሎች በቅዱሱ
ወንጌል በመዳኘት ከሕዝባችንና ከቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶቻችን እንዲወገዱ ማድረግ፣

4. ለአገራችን ኢትዮጵያ ዕድገትና ለዓለማችን ጥቅም በክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ከመልካም ዜጋ
ግንባታ ጀምሮ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ግዴታቸውን የሚወጡ ትጉህ
ሠራተኞችን ማፍራት፣

5. ጸረ ወንጌል ያልሆኑና ለክርስቶስ ወንጌል መስፋፋት ጠቀሜታ ያላቸውን ሥርዓቶች፣ ባህሎችና
ልማዶች ለክርስቶስ ወንጌል መሰበክ እንዲያገለግሉ መጠበቅና ማስጠበቅ።

Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 2 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
April 7, 2016 at 5:24 PM

እኔም መልስ የሚሰጥ ሰው ካለ በአቶ እውነቱ ጽሑፍ ላይ ተመስርቼ የሚከተሉትን ጥያቄዎችን ልጠይቅ:

1) ይች ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያናችን መቼ ይሆን የዓይናማ ሊቃውንቶቿን ምክር ሰምታ ተግባራዊ የምታደረገው?
2)ኦርቶዶክስ ቤ/ክ እስከ መቼ ድረስ ነው የፖለተከኞች ዋሻ የምትሆነው?የመንግሥትስ መሳሪያ መሆን ለምን?
3)ተሳቱ ቅዱሳን ምንኩስናን በጌታ ምትክ ወደ መንግሥተ ሰማይ መግቢያ መንገድ እውነትና የህይወት በር ነው ብለው ያስተማሩት የተሳሳተ ትምህርት በዛሬዎቹ በእኛ ጉዶች በዘር ላይ የተመሰረተ የጳጳስነት ሹመት ለማግኘት ብቻ ዋና መንገድ ሆነ እንዴ? ለባሰና ለሚበሰብስ የሥጋ ክብር ሲባል 40/50 ሚሊዮን የሚደርስን ሕዝብ ወደሞት መንዳት አይሆንባችሁም እናንተ የዘመናች ፈሪሳውያን?
4)በእውነት ይህን የጎረምሶችንና የስሜተኞችን የማቅን የጥፋት እንቅስቃሴን ሀይ የሚሉ ሽማግሌዎች አገሪቱ አጣች?
5)በመጨረሻም አቶ እውነቱ እንዳሉት በያለንበት ሁላችንም በዚህ የጋራ ጉዳያችን ላይ በግልጽ እንነጋገር ለመፍትሄውም ማን ምን እንደሆነ አውቀን ድርሻችንን እንወጣ ማለት እወዳለሁ!!! ለማቅ ወገኖቻችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታማኝ ልጆች ባረጀና ባፈጀ የስም ማጥፋት ሥራ - የጴንጤ ቅጥረኞች፣ ሃይማኖት አጥፊ ወዘተ በማለት ሕዝቡ ራሱ ወልዶና አስተምሮ ባሳደጋቸው ልጆቹ ላይ ጦር እንዲመዝ የማድረግ ዘመቻችሁን ባታቆሙ የመውጊያን ብረት ብትቃወሙ በእናንተ ይብስባችኋልና ቆም ብላችሁ ለራሳችሁ አስቡ!!!!!!!!!

Anonymous
April 22, 2016 at 3:17 PM

ወይኔ ወይኔ ወይኔ ቅድስቲቷ የአምነቴ ቤት የማህበራት ምስጦች አንዲህ ፈርፍረው ሊጨርሷት ነው መሰለኘ????፧

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger