(ከገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም ፤ (M. A. T.) አጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ) ከገጽ 56 ላይ ተሻሽሎ የተወሰደ፤
ከጥቁር ሕዝቦች መካከል በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካናት ውስጥ ብቸኛ ባለርስት ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ከዚያም ባሻገር ነጮቹንም በመቅደምና እስካሁንም ሳይኖራቸው ካሉት ምእራባውያን በላይ ከመካነ ስቅለቱና ከመካነ መስቀሉ ጣሪያ ላይ የሰፈሩ ብቸኛ ሕዝቦች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከጥንቱ ከተማ ውጪ የነበረና አሁን አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ተብላ በምትጠራው ክፍል፤ የኢትዮጵያ ጎዳና ላይ በ19ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ የታነጸችው የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በአካባቢው ብቸኛዋ የአበሾች ቤተክርስቲያን ናት።
በዚህች የ121 ዓመታት እድሜን ባስቆጠረች ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው፤ ነገር ግን ታሪካቸውን በአቧራና በተንኰል ድር የተሸፈነባቸው ታላቁ መምህር አባ ወልደ ሰማእት ናቸው። መምህር ወልደ ሰማእት ትውልዳቸው ሸዋ ቢሆንም ከሃይማኖት በስተቀር ዘርንና ጎጠኝነትን መሠረት አድርገው የማያምኑ ትልቅ አባት መሆናቸውን የሚያሳየው በወቅቱ የደረሰባቸው መከራና ያደረጉት ተጋድሎ ሕያው ምስክር ነው። መምህር ወልደ ሰማእት ምሁርና መጻሕፍት አዋቂ ነበሩ። ወደኢየሩሳሌም በማቅናት ከኢትዮጵያ ገዳም በ1856 ዓ/ም ገደማ ሄደው ከማኅበሩ አንድነት እንደተቀላቀሉ ታሪካቸው ይነገራል።
ግብጻውያን መነኰሳት በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ኢትዮጵያውያንን ለበቅሎዎቻቸው እያሰገዱ፤ በኢየሩሳሌም ያለውን ሀብትና ንብረት ደግሞ የቻሉትን ዘርፈውና ወስደው፤ በኋላ ላይ ደግሞ የፈለጉትን ለመስኮቦች ሸጠውና መነኮሳቱን ከርስታቸው ነቅለው ጸሎት ቤታቸውን በወረሷቸው ሰዓት መምህር ወልደ ሰማእት ወደ ኢየሩሳሌም ማቅናታቸው እንደ አንድ አጋጣሚ የሚቆጠር ነው። በዚያን ወቅት ኢትዮጵያውያን መነኮሳት የጸሎት ቤታቸውን ተቀምተው እሁድ እሁድን እንኳን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ተጠግተው ከሚያስቀድሱ በስተቀር ምንም መቀደሻ ሥፍራ አልነበራቸውም ነበር። መምህር ገ/መስቀል የኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት አበምኔት በሞት እንደተለዩ የመምህር ወልደ ሰማእት እውቀትና ትእግስት ታይቶ አበምኔትነቱን እንዲረከቡ ተደርገዋል። ከዚያም ከ1836 ዓ/ም ጀምሮ ጠፍ ሆኖ የቆየውን ገዳም ወደነበረበት ለመመለስ መምህር ወልደ ሰማእት ወደ ኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ዘንድ በመሄድ አንድም ንጉሡ በምጽዋ መጥቶ ድል ባደረጉት የቱርክ ሠራዊት ላይ የተቀዳጁትን ደስታ ለመግለጽ፤ በሌላ መልኩም የኢየሩሳሌም መነኮሳት ንጉሥ የሌላቸው ሕዝቦች ያህል ተቆጥረው ያለጸሎት ቤት በመንከራተት ላይ ስላሉ ንጉሡ መላ እንዲሰጧቸው አቤቱታቸውን አሰምተው ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስም በወቅቱ ከቱርኮች በምርኰ ያገኙትን አራት ሳጥን ገንዘብ ይሰጧቸዋል። መምህር ወልደሰማእትም የተሰጣቸውን ገንዘብ ይዘው በመመለስ ለጸሎት ቤት ማሰሪያና ለመነኮሳቱ ማረፊያ ቦታ እንዲሆን አሁን ደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት የተባለችው ቤተክርስቲያን ያለችበትን ርስት ገዙ። ከዚያም ከፈረንሳውያንና ቱርካውያን መሐንዲሶች ጋር በመነጋገር እራሳቸው መምህር ወልደሰማእት በነደፉት ዲዛይን መሠረት ቤተክርስቲያኒቱን በሚያዚያ ወር 1874 ዓ/ አስጀምረው ሊፈጸም ጉልላቱ ሲቀር በ1883 ዓ/ም አፄ ዮሐንስ መተማ ላይ አረፉ። የቤተክርስቲያኒና የመነኮሳቱ ማረፊያ ሥራ ፤ እንዲሁም በአሮጌው ከተማ ያለውን መንበረ ጵጵስና ባመጡት ገንዘብ ገዝተው፤ አስር ዓመታትን የፈጀባቸው ቤተክርስቲያኒቱ ግንባታ ሳይጠናቀቅ ገንዘቡ አለቀ። የተጀመረውን ያስፈጽሙላቸው ዘንድ ወደኢትዮጵያ ተመልሰው እንዳይጠይቁ ያስጀመሩት ንጉሥ አፄ ዮሐንስ አርፈው በምትካቸው አጼ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥትነቱን ተረክበዋል።
ከዚያም መምህር ወልደ ሰማእት ሁለት መነኮሳትን ከኢየሩሳሌም ወደ አዲሱ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒልክ ዘንድ ቤተክርስቲያኒቱ ያለችበትን ሁኔታ አስረድተው እሳቸው ማስፈጸሚያውን እንዲልኩላቸው ደብዳቤ አስይዘው ወደ ኢትዮጵያ ላኩ። አፄ ምኒልክም በደቡብና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ዘመቻ ከፍተው ሀገሪቱን አንድ በማድረግ ሥራ ላይ ተጠምደው ስለነበረና በወቅቱም ወረርሽኝ በሽታ በሀገሪቱ ገብቶ ስለነበረ የተፈለገውን ገንዘብ መላክ እንዳልቻሉ ምላሽ ይሰጣሉ። የተላኩት መነኮሳት ባዶ እጃቸውን መመለሳቸውን እንዳዩ መምህር ወልደሰማእት በአፄ ዮሐንስ ገንዘብ ከገዙት ሰፊ ይዞታ ውስጥ ከፊሉን መልሰው በመሸጥ፤ ቤተክርስቲያኒቱን በሽያጩ ገንዘብ በ1884 ዓ/ም አስጨርሰው ቅዳሴ ቤቱን ያከብራሉ።
ከቤተክርስቲያኑ ቅጽር መግቢያ በር ላይ እና ከቅድስቱ ዙሪያ የውጪው ግድግዳው ላይ ቤተክርስቲያኒቱን አፄ ዮሐንስ በላኩት ገንዘብ መፈጸሙን የሚገልጽ ጽሁፍ በወርቅ ዓምድ እንዲጻፍ ያስደርጋሉ።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የመምህር ወልደ ሰማእት መከራና ስደት ይጀምራል። ነገረ ሰሪና ሹመት ፈላጊ የሀገራቸው የሸዋ ሰብቀኛ ወንድሞቻቸው መነኮሳት ከአፄ ምኒልክ ዘንድ ይከሷቸዋል። እርስዎ ንጉሠ ነገሥቱ በሕይወት እያሉ በሞት የተለዩት ንጉሠ ነገሥት ስም እንዴት ይጻፋል? ብለው ስለከሰሷቸው መምህር ወልደ ሰማእት ለጥያቄ ወደ ኢትዮጵያ ይጠራሉ። መምህር ወልደ ሰማእትም የንጉሡን ጥሪ አክብረው ከሄዱ በኋላ ለምን የዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ስም እንዳልሰፈረ ሲጠየቁ፤ መምህር ወልደ ሰማእት ምንም ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሀቁን ግልጥልጥ አድርገው ይናገራሉ። መንበረ ጵጵስናውን፤ የደብረ ገነት ኪዳነ ምህረትን ቤተክርስቲያንን ሙሉ ይዞታና የመነኮሳቱን ማረፊያ የገዙት በአፄ ዮሐንስ የስጦታ ገንዘብ መሆኑንና ለማስፈጸሚያም መነኮሳት ልኬ ገንዘብ ባለመገኘቴ ከገዛሁት ርስት ላይ ቀንሼ በመሸጥ ያስፈጸምኩ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ገንዘብ ስለተፈጸመ፤ የጻፍኩት ያንን በመሆኑ ጥፋቴ ምንድነው? ብለው ይጠይቃሉ። መምህር ወልደ ሰማእት ምንም ዓይነት ጥፋት እንዳላጠፉ ቢታወቅም ሕያው የነበረውን ንጉሥ ትተው የሙቱን ንጉሥ ስም በማስጻፋቸው ብቻ በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደጥፋተኛ በግዞት እንዲቀመጡ ይወሰንባቸዋል። ከከንቲባ ገብሩ ደስታ ጋር ሌሎች ሁለት ሰዎች ተልከው የመምህር ወልደሰማእት ጽሁፍ እንዲቀየር ይደረጋል።
ሁሉም ነገሥታት የቤተክርስቲያን ፍቅር እንደነበራቸው ባይካድም በነገሪ ሰሪዎችና ሹመት ፈላጊዎች የተነሳ አንዳንዴ ትክክል ያልሆኑ ውሳኔዎች ይወሰዱ ነበር። መምህር ወልደሰማእትም ጥቂት ዓመታትን በዓይነ ቁራኛ እየተጠበቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ከቆዩ በኋላ አንዱን ቀን ሾልከው በመጥፋት ጎጃምንና ጎንደር አቋርጠው ሱዳን ይገባሉ። ዐረብኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገሩ ስለነበር የሱዳንንና የግብጽን በረሃ ያለምንም ችግር አቋርጠው ኢየሩሳሌም ገቡ። ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም የተቀበሏቸው «መምህራችን እንኳን በደህና መጣህ!» ብለው ሳይሆን «ምን ልትሰራ መጣህ?» በማለት ሲሆን ባቀኑት ገዳም ውስጥ ዳግም ስደተኛ ሆነው ከህንጻ ፍራሽ ዋሻ ውስጥ ጥቂት ጊዜ ይቆያሉ። የገዛ ወገኖቻቸው ገፍተው በማባረራቸውና ከባእዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ጥገኛ መሆን ስላስመረራቸው ከሃይማኖት ወንድሞቼ ልቀላቀል በማለት ወደ ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ ተሰደዱ። ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከመሄዳቸው በፊት የሀዘን እንባቸውን ከጉንጫቸው አፍሰው ረጭተዋል ተብሎ ይነገራል።
መምህር ወልደ ሰማእት እንደስማቸው ሰማእትነትን ተቀብለው ገዳመ አስቄስጥ ከገቡ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው አጽማቸውም እዚያው በክብር አርፏል። የደብረ ገነት ቤተክርስቲያን ታንጻ፤ የመነኮሳት ማረፊያ ተሰርቶና መንበረ ጵጵስና ራሱን ችሎ በመምህር ወልደ ሰማእት ብርቱ ትግል ከተፈጸመ በኋላ በግብጻውያን በኩል የሚመጣው ስደትና እንግልቱ ታግሶላቸው ሳለ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ተረጋግተው መቀመጥ ሲገባቸው እርስ በእርሳቸው መጣላትና መናቆር የዘወትር ሥራቸው ሆነ። ስምምነት በመካከላቸው ጠፋ። የእርስ በእርሳቸው ብጥብጥ እየበረታባቸው በመሄዱ የተነሳ በመምህራችን በመምህር ወልደ ሰማእት ላይ የፈጸምነው ግፍና የሀሰት ክስ እንደአቤል ደም ይከሰናልና በሕይወት አግኝተነው መምህራችንን ይቅር በለን እንዳንለው በሞት ስለተለየን ቢያንስ አጽሙን ከገዳመ አስቄስጥ አምጥተን በክብር እኛ ዘንድ እናሳርፈው በማለት መነኮሳት ወደ ገዳመ አስቄስጥ ይላካሉ። ከዚያም እንደደረሱ የመጡበትን ምክንያት ያስረዳሉ። የገዳመ አስቄስጥ ማኅበርም ሲመልሱላቸው፤ እንዲህ ዓይነቱን ደግ አበምኔታችሁን ለምን ቀድሞውኑ ተንከባክባችሁ አትይዙም ነበር? እኛስ ተራ መነኩሴ መስሎን ነበር፤ እንዲህ ዓይነት ትልቅ ገድል የፈጸመ መሆኑን አለማወቃችንን መጥታችሁ ስለነገራችሁን በጣም እናመሰግናለን፤ ይህስ ከቅዱሳኑ አንዱ ነውና አጽሙን አንሰጣችሁም! እግዚአብሔር እናንተ የጣላችሁትን ለእኛ ሰጥቶናል በማለት ይነግሯቸዋል።ኢትዮጵያውያኑ መነኮሳትም ባዶ እጃቸውን ተመልሰዋል።
መምህር ወልደ ሰማእት ያሳነጿትን የደብረ ገነት ኪዳነ ምህረትን ቤተክርስቲያን እንደባይተዋር በዓይናቸው አይተው ከተሰናበቱ በኋላ በግብጽ በረሃ በአስቄስጥ መቀበራቸው እውነት ነው። እውነቱን ብቻ በማመን የአፄ ዮሐንስን ስም በክብር በመጻፋቸው ብቻ ከወገኖቻቸው ስደትና መከራ እጣ ፈንታቸው ሆኖ እድሜአቸውን በሞት ፈጽመዋል።
እስከዛሬ በደንብ ያልተነገረው የመምህር ወልደ ሰማእት ታሪክ በአጭሩ ይህ ነው። ጎጠኝነትንና ዘር ቆጠራን በመዝራት እርስ በእርስ ከመበላላት ይልቅ ማን ምን ሰራ? እያልን በሙያውና በምግባሩ ብቻ ልንመዝን እንደሚገባ የመምህር ወልደ ሰማእት ታሪክ ሕያው ምስክር ነው። እንደ መምህር ወልደ ሰማእት ለእውነትና ለእውነት ብቻ መቆም የወንጌል ሰው የዘወትር ሥራው ሊሆን ይገባል!