የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለ1600 ዓመትያህል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበላይ ሆና ስትመራ
መቆየቷ እርግጥ ነው። በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከቱት እድገትና መንፈሳዊ ልማት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።
ይልቁንም በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለመግባትና በቤተክርስቲያኒቱ የወርቅና የልዩ ልዩ ስጦታዎች ሀብት ማጋበስ እድል ሰጥቷቸዋል። ራሷን
በቻለች ጊዜም መሪዋና ኃላፊዋ የመሰረታት ክርስቶስ ነው፤ ከማለት ይልቅ በእኛ አመራርና ኃላፊነት ስር ካልሆናችሁ ፕትርክናውን አንፈቅድላችሁም
ሲሉ አስቸግረው እንደነበር የቅርብ ጊዜው ታሪክ ይነግረናል። እንደዚያም ሆኖ በብዙ ነገራችን የመመሳሰላችን ነገር እንዳለ ሁሉ ዋና
በሚባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ላይ ግን ትልቅ ልዩነታችንን በ1600 ዓመት ውስጥ ለምን እንደሆነ አልነገሩንም፤ ወይም እኛም አልጠየቅናቸውም።
በጅምላ የኦሪየንታል/ምስራቃዊ/ አብያተክርስቲያናት ሁላችንም አንድ ዓይነት እምነትና አስተምህሮ አለን እያልን በረጅም ታሪካችን
ውስጥ እስክንድሪያ እናታችን፤ ማርቆስ አባታችን ከማለት ውጪ አንድ ሊያደርገን በሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እስከዛሬ ባለን ልዩነት
የሚነገር ምንም ነገር አለመኖሩ አስገራሚ ነው። እውነቱ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን መካከል የሃይማኖቱ መመሪያ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሁለቱም ቤተክርስቲያን የቁጥር ልዩነት እንዳላቸው እርግጥ
ነው። ለምን? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሊቃውንት ጉባዔ ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን። እስከዚያው የልዩነትም ደረጃ ለማየት እዚህ
ላይ እንዘረዝራቸዋለን።
የግብጽ/ኮፕቲክ/ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት
መጻሕፍት ዝርዝር፤
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
1/ Genesis ዘፍጥረት
2/ Exodus ዘጸአት
3/ Leviticus ዘሌዋውያን
4/ Numbers ዘኁልቈ
5/ Deuteronomy ዘዳግም
6/ Joshua ኢያሱ ወልደ ነዌ
7/ Judges መሣፍንት
8/ Ruth ሩት
9/ 1 Samuel 1ኛ ሳሙኤል
10/ 2 Samuel 2ኛ ሳሙኤል
11/ 1 Kings 1ኛ ነገ
12/ 2 Kings 2ኛ ነገ
13/ 1 Chronicles 1ኛ ዜና
14/ 2 Chronicles 2ኛ ዜና
15/ Ezra እዝራ
16/ Nehemiah ነህምያ
17/ Tobit ጦቢት
18/ Judith ዮዲት
19/ Esther አስቴር
20/ Job ኢዮብ
21/ Psalms መዝሙር
22/ Proverbs ምሳሌ
23/ Ecclesiastes መክብብ
24/ Song of Solomon መሐልይ
25/ Wisdom ጥበብ
26/ Sirach ሲራክ
27/ Isaiah ኢሳይያስ
28/ Jeremiah ኤርምያስ
29/ Lamentations ሰቆቃ
30/ Baroch ባሮክ
31/ Ezekiel ሕዝቅኤል
32/ Daniel ዳንኤል
33/ Hosea ሆሴዕ
34/ Joel ኢዩኤል
35/ Amos አሞጽ
36/ Obadiah አብድዩ
37/ Jonah ዮናስ
38/ Micah ሚክያስ
39/ Nahum ናሆም
40/ Habakkuk እንባቆም
41/ Zephaniah ሶፎንያስ
42/ Haggai ሐጌ
43/ Zechariah ዘካርያስ
44/ Malachi ሚልክያስ
45/ 1 Machabees 1ኛ መቃቢስ
46/ 2 MachabeesPhilemon 2ኛ መቃቢስ ዘፊልሞና
************************************************
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት
1/ Matthew ማቴ
2/ Mark ማር
3/ Luke ሉቃ
4/ John ዮሐ
5/ Acts of Apostles የሐዋ
6/ Romans ሮሜ
7/ 1 Corinthians 1ኛ ቆሮ
8/ 2 Corinthians 2ኛ ቆሮ
9/ Galatians ገላ
10/ Ephesians ኤፌ
11/ Philippians ፊልጵ
12/ Colossians ቆላስ
13/ 1 Thessalonians 1ኛ ተሰ
14/ 2 Thessalonians 2ኛ ተሰ
15/ 1 Timothy 1ኛ ጢሞ
16/ 2 Timothy 2ኛ ጢሞ
17/ Titus ቲቶ
18/ Philemon ፊልሞ
19/ Hebrews ዕብ
20/ James ያዕ
21/ 1 Peter 1ኛ ጴጥ
22/ 2 Peter 2ኛ ጴጥ
23/ 1 John 1ኛ ዮሐ
24/ 2 John 2ኛ ዮሐ
25/ 3 John 3ኛ ዮሐ
26/ Jude ይሁዳ
27/ Revelation ራእይ
46+27= 73 ጠቅላላ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
መጽሐፍ ቅዱስ በተለምዶ 81 ወይም ሰማንያ ወአሐዱ ተብሎ የሚጠራው ምንም እንኳን ከሰማንያ አንድ ቢበልጥም የተባለውን እንዳለ ብንቀበል
ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በ8 /ስምንት/ መጻሕፍት የብልጫ ልዩነት አለ።
በመጽሐፍ ቅዱስ አምላካዊ መጽሐፍ ቁጥር ላይ አንድ
ካልሆንን እንዴት አንድ ዓይነት ዶግማና ቀኖና አለን ሊባል ይችላል? በመቃብያን መጻሕፍት ላይ ደግሞ በጭራሽ መጻሕፍቱ አንድ ዓይነት
አይደሉም። ለምን ልዩነቱ ተፈጠረ? በቅርጣግና /Chartage/ ጉባዔ
ላይ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ያላስገቧቸው
መጻሕፍት ለምን እንደመጽሐፍ ቅዱስ አካል ተቆጥረው በ2000 ዓ/ም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገቡ? የምላሽ ያለህ!!!!!!!!!!!!
ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ተጭነው ይመልከቱ