ምንጭ፤ ዓውደምህረት ብሎግ
ሲኖዶሱ ለ15 ቀን የሚቆይ የምህላ አዋጅ አወጀ
በትናትናው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠ የጽሁፍ መግለጫ ሲኖዶሱ ከጳጉሜ 1 አስከ መስከረም 10 የሚቆይ የምህላ አዋጅ አውጇል፡፡ በብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፊርማ በተለቀቀ የጽኹፍ መግለጫ እንደሚያመለክተው ምህላው ጾምን አያካትትም፡፡ ዋነኛ አላማውም የተሻለ አባት ለቤተክርስቲያን እንዲያስነሳ ነው፡፡ የሰላም አምላክ አግዚዘብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ያምጣልን፡፡
የሱባኤው ዓላማ ተገቢ እና አስፈላጊ ቢሆንም ቀጥታ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር ከማተኮር ሁለቱ ሲኖዶሶች የሚዋሀዱበትን ሁኔታዎችን እና እርቁ የሚቀላጠፍበትን ሁኔታ የሚያመቻች ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት እርቅ እንዳይፈጸም እንቅፋት የሆኑት አቡነ ጳውሎስ ናቸው እየተባልን ኖረናል፡፡ አሁንስ ታድያ ምን እየተደረገ ነው? ምህላ አዲስ ፓትርያርክ ለመምረጥ ከሆነ እርቁ ለምን ያስፈልጋል? ከአሜሪካ መጥተው የሀዘኑ ጊዜ እስኪያልፍ ጠብቁ የተባሉት ሰዎችስ ምን ሊባሉ ነው? እውን አሁን ያሉት አባቶቻችን እርቁን ይፈልጉታል? ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባቶቻችን አንድ ብትሉን መልካም ነው፡፡