Tuesday, April 30, 2013

አባ አብርሃም በአሜሪካ ያለውን የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ


http://awdemihreet.blogspot.com/) በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት /ቤት ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን /ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን /ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን /ቤት አላስረክብም በማለት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያልቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡

Monday, April 29, 2013

ወድቆም ያፈራል


Wedkom Yaferal Read in pdf

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ ዓርብ ሚያዝያ 18/2005 ዓ.ም.
ከጸሎት ክፍሎች አንዱ ስእለት ነው፡፡ ስእለት ለእግዚአብሔር የምንገባው ቃል ነው፣ እግዚአብሔርም የሚጠብቀው ብርቱ ነገር ነው /መክ. 5፡4-5/፡፡ በተሳልንበት ግለት እንድንፈጽመው ይጠበቅብናል፡፡ ስእለት ለእግዚአብሔር አመጣለሁ የምንለው የምስጋና መግለጫ ነው፡፡ አንዳንዶች ገንዘባቸውን፣ ሌሎች ሕይወታቸውን፣ የቀሩት ልጆቻቸውን፣ ውስኖች የሰጣቸውን ለእርሱ ለመስጠት ስእለት ይገባሉ፡፡ ስእለት መሳል ፈቃድ ነው፣ አለመፈጸም ግን ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሔርን እንዴት ይዋሸዋል?
ስእለት እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር የምስጋና መግለጫ ይዘን የምንመጣበት ነው፡፡ ስእለት የውለታው ምላሽ ሳይሆን የውለታው መታሰቢያ ነው ብንል ይገልጸዋል፡፡ በብዙ ጭንቀቶች ባለፍኩባቸው ዘመናት ሁሉ ስእለትን ለእግዚአብሔር እሳላለሁ፡፡ እነዚያን የከበዱኝን ወራቶች ሳስብ መከራው ከባድ ሆኖ ነው ወይስ እኔ ደካማ ሆኜ ነው? የሚለውን እስካሁን ልመልሰው አልቻልኩም፡፡ ብዙ የሀዘንና የስብራት ዘመኖችን እግዚአብሔር አሻግሮኛል፡፡ እንደ ፈቃዱም መልስ ሰጥቶኛል፡፡ እንደ ፈቃዱ ከልክሎኛል፣ እንደ ፈቃዱ ባርኮኛል፡፡

Sunday, April 28, 2013

የአሜሪካው ሲኖዶስ ስለተፈናቀሉ ዜጎች መግለጫ አወጣ



ቅዱስ ሲኖዶስ
The Holy Synod
4127 Redwood
Oakland, CA 94610
በአገራችን በኢትዮጵያ በአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበ ጥሪ
ሚያዚያ ፲፬ ቀን ፪ ሺ ፭ ዓ.ም"
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።የዋይታና የመራራ ልቅሶድምፅ በራማ ተሰማ፤ራሔል ስለ ልጆችዋ  አለቀሰች፤የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። " ኤር 31 ፡16
የተወደዳችሁ በአገራችን በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ተበትናችሁ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፤

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  ( Click here )