Wednesday, May 23, 2012

ሲኖዶሱ የሚመራው በማን ነው? በፓትርያርኩ ወይስ?


                                          ምንጭ፥ ዓውደ ምሕረት
የሰሞኑ የሲኖዶስ ስብሰባን ሂደት ላየ ሊለው የሚችለው ብዙ ነገር ይኖረዋል። በተለይ በስብሰባ ላይ በተነሳ ሀሳብ ሁሉ ላይ ከውጭ ካለው አየር ምክር የሚሹ አንዳንድ ጳጳሳት አካላቸውን ሲኖዶሱ ላይ አድርገው ልባቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ ውስጥ አስቀምጠው በማቅ ሳንባ ነው የሚተነፍሱት።  የሚተነፍሱበት አየር ደግሞ በልዩ ሁኔታ ማንያዘዋል በሚባል ኬሚስት የተሰራ ነው። ይህ ታዋቂ ኬሚስት የሚቀምመው ኬሚካል  በመጀመሪያ የሚሞክረውም አባ ሳሙኤል የሚባሉ ባለመንታ ችግር ጳጳስ ላይ ነው። እሳቸው ላይ በትክክል እንደሰራ ሲያውቅ እሳቸውን አስጨብጦ በእለቱ  የሚተነፍሱት አየር ለሚያጥራቸው ሌሎች ጳጳሳት ይልከዋል።
ከዚያማ ገበርዲኑን ለብሶ ቤተ ክህነት ግቢ ላይ መዞር ነው። ጋሻ ጃግሬዎቹ ሲከቡት የዛሬ አጀንዳ ይህ ይህ ነው፤ የሚወሰነውም ይሔ ነው እያለ ራሱን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ አስቀምጦ ያወራል። ማታ ላይም የኮሌጁ ምሩቃን ቢሮ ላይ መብራት አጥፍቶና መጋረጃ ጋርዶ ሰው የሌለ አስመስሎ ይቀመጣል እንዲህ እንደሚያድርግ የሚያውቁ የኮሌጁ ተማሪዎች ታድያ ማንያዘዋል የሚባል የሌሊት ሰይጣን አለ ብለውበመፍራትወደ ምሩቃኑ ቢሮ አካባቢ አይሄዱም።

ይህ ሰው  መሸት ሲል ሶስት ወይም አራት ሰዓት ላይ በአባ ሳሙኤል ስልክ ጥሪ መሰረት ወደ አባ ሳሙኤል ሄዶ ስብሰባው እንዴት ነበር? ብሎ ይጠይቃል። ታድያ አባ ሳሙኤልም በተለመደው ጀብደኛ ባህሪያቸው እንዲህ ተብሎ፤ እንዲህ ተደርጎ እንዲህ ተወሰነ ብለው ይነግሩታል። አጅሬም 6ሰዓት ወይም 7 ሰዓት ላይ ወጥቶ ይሄዳል። አንዳንዴም እዛው ያድራል። ያደረም ቀን፤ ወጥቶ የሄደም ቀን ተማሪ ያየዋል። ተማሪ ለጥናት ማታን ይመርጣልና ሹክክ ብሎ ከአባ ሳሙኤል ቤት ሲወጣ ያዩታል። ቀን ለደጀ ሰላም ብሎ አስቀድሞ ያዘጋጀውን ሪፓርት ያወጣና እሳቸው ካሉት ጋር ያስተያየዋል። የሚሻሻል ካለ አሻሽሎ፣ ቅመም መጨመር ካለበትም ጨምሮ «ደጀ ሰላም» ላይ ፖስት እንዲደረግ ለአሉላ ይልካል። አንዳንዴም ለአሉላ በስልክ ይነግረውና እሱ የራሱን ቅመም ጨምሮ ያወጣዋል። ታድያ ይህ ሁሉ ቅንጅት እያለ ደጀ ሰላም እውነት የማታወራው ብሎ ለሚጠይቅ ጠያቂ እንዲህ የሚል መልስ እንሰጠዋለን። ብዙ ጊዜ ደጀ ሰላም የተሳሳተ ዘገባ የምታወጣው በሶስት ዋና ዋና  ምክንያቶች ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርክነቱን ወንበር ሊጨብጥ የቀረው ትንሽ ነው!


  • በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማኅበረ ቅዱሳን ከተራ ማኅበርነት ወደ ሀገረ ስብከትነት  አደገ።
  • ሲኖዶሱ ሙሉ በሙሉ በማኅበረ ቅዱሳን እጁን ተጠምዝዞ እንደሚሰራ አስመሰከረ።
  • ማኅበረ ቅዱሳን ከእንግዲህ የቀረው ፓትርያርክነቱና ቤተመንግሥቱ ነው!
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ  የየሀገረ ስብከቶቹ  ጠቅላይ ጽ/ቤት ሆኖ ያገለግላል። ይህ ጽ/ቤት ደግሞ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በየ3 ዓመቱ በሚያደርገው ምርጫ በሚመድበው ሊቀጳጳስ ነው። እንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና አሥኪያጅ ሆነ ማለት ራሱን የቻለ ሀ/ስብከት  ሆነ ማለት ነው። የጠቅላይ ቤተክህነቱ መምሪያዎች ሊያዙት አይችሉም። ከዚያም በላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊያዙት፤ ሊናገሩትና ሊቆጡት አይችሉም ማለት ነው። በቀጥታ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚመደበው ሊቀጳጳስ በኩል ግንኙነቱ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር ብቻ ይሆናል ማለት ነው። እንዲህ ነው እንጂ ሹመት፤ መሾም ካልቀረ!! አንድ ማኅበር ባንድ ጊዜ እመር ብሎ አናት ላይ ፊጢጥ ብሎ ከመቀመጥ ወዲያ ሹመት ከወደየት ይገኛል? ከእንግዲህ  ከተቀመጠበት ደረጃ አንጻር ማኅበር መባሉ ዝቅ የሚያደርገው ስም ስለሆነ የቅዱሳን መምሪያ ወይም የወጣቶች ሀ/ስብከት እንዲባል ሲኖዶሱ በነካካው እጁ ስሙንም ማሻሻል ይገባዋል። ከዚያም አያይዞ ለዚሁ አዲስ ሀ/ስብከት አንድ ሊቀጳጳስ እንዲመድቡለትም ጥቆማውን እናቀርባለን።
አንድ ነገር ታዘብን። ቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ የሚባል አካል እንደሌላት ተረዳን። በአንድ ተራ ማኅበር እየተመሩ የእሱን ጉዳይ ብቻ ሲያነሱና ሲጥሉ ሦስትና አራት ቀናት ስብሰባ መወዘፍን ምን ይሉታል? ስንት ስራ መስራት እየቻሉ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ማውረድ እስኪያቅታቸው ድረስ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አጀንዳ ይዞ መከራከርን እውነት ሰዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመሩት እንድንል ያደርገናል።
 በመሰረቱ እኰ ማኅበረ ቅዱሳን አሸባሪ አመራር እንደሚነዳው መንግሥት በድብቅ ሳይሆን በግልጽ አውጆ እያለ ስለማኅበሩ አጀንዳ መያዝ ትልቅ ስህተት ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከፈጸሙት ስህተት ሁሉ ይህኛው ይከፋል። መንግስት ያስጠነቀቀውን ማኅበር ጉዳይ ለክርክር ማቅረብ አልነበረባቸውም። ከሽብር ተግባር ነጻና ትክክለኛ ማኅበር ስለመሆኑ በህግ አግባብ ከመንግስት ማረጋገጫ ሊያቀርብ ሲገባው ጭራሹኑ ከማኅበርነት ወደ ሀ/ ስብከትነት ማሳደግ እብደት ካልሆነ ጤንነት አይደለም። ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁንም ደግመው ሊያስቡበት ይገባል እንላለን። ከየጎዳናው እየጠሩ ድስት የደፉለት ሁሉ አንድ ላይ አድሞ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በጥቅም ሲተሳሰር እንዴት አሜን ብለው ሊቀበሉ ቻሉ? ብለን ፓትርያርኩን አጥብቀን እንጠይቃለን።
ይህ ማኅበር እስካሁን እየታዘዘ እንዳልቆየ የተጻፉለት ደብዳቤዎች አረጋጋጮች ናቸው። እሱ ራሱ አልቀበልም ብሎ በደብዳቤ አረጋግጧል። አንዴ ከኢህአዴግ፤ አንዴ ደግሞ ከተቃዋሚ ነኝ እያለ፤ ሌላ ጊዜ ከሀገር ቤቱ ሲኖዶስ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገለልተኛ እየመሰለ የተጓዘበትን ሁላችንም እናውቃለን። የወንድሞች ከሳሽና አሳዳጅ ስለመሆኑም ግፉን የቀመሱ ሁሉ ይመሰክራሉ። የተጓዘባቸውን ስልቶች ሁሉ ያጠናው መንግሥት ከሽብር አቀንቃኝ  ከሰለፊያ ጋር በአንድ ረድፍ አንዳስቀመጠው ነግሮናል። ስለሆነም አቡነ ጳውሎስ ይህንን የአድማና በጥቅም የተሳሰረ ውሳኔ አልፈርምም በማለት ውድቅ ሊያደርጉት ይገባል። ማኅበሩ አስቀድሞ ከሰለፊያ ተግባር ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማምጣት ይጠበቅበታል። ደጋፊዎቹ ጳጳሳትን በማስረጃና በሰው ምስክር ተጠንተው ብቁ ሆነው ያልተገኙ ካሉ ከማእረጋቸው መሰናበት አለባቸው።  ቄስ የነበሩ፤ ልጆች የወለዱ፤ ቅምጥ ያላቸው እንዳሉ ይወራል፤ የአንዳንዶቹም ይታወቃል። ለዚሁም ማሳያ የሚሆነው አባ ሚካኤል በፍርድ ቤት ባለልጅነታቸው መረጋገጡ ነው። እየተሸፋፈነ መቀመጡ ለቤተክርስቲያን ጠንቅ የሆነ ውሳኔ ለማስወሰን ያልተመለሱ ሰዎች ስብስብን አስገኘ። ስለዚህ አባ ገብርኤል፤ አቶ ኢያሱ ተብለው እንደነበረው፤ ማንነታቸው እንደገና ተመርምሮ ውሳኔ ሊሰጥባቸው ይገባል።ጨከን ያለ የሥርዓት ማስከበር አካሄድ መውሰድ ካልተቻለ ነገ ፓትርያርክነቱን አስቀድሞ ከዚያም ቤተመንግሥቱን እንደሚረከብ የሚጠራጠር ካለ ምንም የማያውቅ ብቻ ነው። አመኑንም አላመኑም ፓትርያርክ ጳውሎስ፤አንድ ነገር አስረግጠን እንነግርዎታለን። በማኅበረ ቅዱሳንና በደጋፊዎቹ ጳጳሳት ግብዓተ መሬትዎ ሊፈጸም የቀረው ጥቂት ነው። ከሆነለት ፓትርያርክነቱን ለሚታዘዝ የወሎ ጳጳስ ወይም ለሸዋ ሰው ብቻ ሰጥቶ ወደ ቤተመንግሥት ሰተት ብሎ ለመግባት ከጽዋ ማኅበርነት ወደ መምሪያ ተገዳዳሪነት፤ አሁን ደግሞ ወደ ሀገረ ስብከትነት ማደጉ ከምንም በላይ ማሳያ ነው።  ታዲያ ከእንግዲህ የቀረው ምንድነው? ይህ ሁሉ ለጽድቅ ነው እንዳይሉንና እንዳንስቅ። ነጋዴና ሸቃጭ፤  ጻድቅ ማኅበር አራት ኪሎ የለም እንልዎታለን። እያየነው የወጣው ይህ ሀረግ ተክሉን አንቆ ወዳሰበበት መጓዝ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ማኅበር አሳልፎ ከሰጠን በእውነትም ቤተክርስቲያኒቱ ለፈተናና ለውድቀት ተመርጣለች ማለት ነው።
ሰውዬው «ኵሉ ንምርዓይ ምቅናይ» ያለው ወዶ አይደለም ለካ! ሁሉ ቢገርመን ሁሉን ለማየት መቆየት ብለናል።

Tuesday, May 22, 2012

"ማኅበረ ቅዱሳን" የሚታዘዘው ለማን ነው?

                             http://awdeselam.blogspot.com
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታና የወደፊት ዕጣ የሚነጋገር ሁሉ የሚስማማበት አንድ ነገር አለ። ይኸውም "ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በአንድም በሌላም መንገድ በመከፋፈል እራሱን ብቸኛ የቤተ ክርስቲያንዋ ነጻ አውጪ አድርጎ የመመልከቱ ነገር ነው። አንዳንድ ጊዜማ ከማኅበሩ መመሥረት በፊት በቤተ ክርስቲያን ሥራ እንዳልተሠራ፣ እንዳልተደከመባት አድርጎ በድፍረት በመናገር የወጣቱን ክፍል ለማሞኘት ይሞከራል። 
ይህ ማኅበር ፊት የማያሳዩትን በስደት ውጪ ሀገር የሚኖሩትን አባቶች በማቃለልና ሃይማኖት ለዋጮች እንደሆኑ አስመስሎ በማቅረብ፣ ለብዙ ክብር የበቁትን፣ እያንዳንዳቸው ለቤተ ክርስቲያን ከሃምሳ ዓመታት በላይ የደከሙትን አባቶች በመናቅና በማዋረድ፣ ወጣቶች ለአባቶቻቸው አክብሮት እንዳይኖራቸው ሰድቦ በማሰደብ በስደት ባሉባቸው ቦታዎች ሲያሳድዳቸው ተስተውሏል አሁንም እየተስተዋለ ነው። በቅዱሳን ስም ራሱን ለሚጠራ ማኅበር የከበሩትን ማዋረዱ የተመረጡትን መናቁ ስሙ እንደማይገባው የሚያሳይ ነው።
ይህ ብቻ አይደለም። ይኸው ማኅበር በስደት ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ሲያሳድድ “ከአዲስ አበባ ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ሥር የምተዳደር ነኝ” … “ሲኖዶስ አንዲት ናት” … “ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጋር መደባለቅ ያስፈልጋል” በማለት በውጪ ያለውን ሕዝብ በመደለል ነው። ሙከራው እንዳሰበው ባይሳካለትም በቂ ጥፋት ለማጥፋት ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሟል።

ማኅበሩ እራሱን በአዲስ አበባ ሲኖዶስ ሥር እንደሆነ አድርጎ ቢያቀርብም በምግባሩ ግን እዚያም ያሉትን አባቶች መከፋፈሉና አልታዘዝ ባይነቱ ዓይን እያወጣ ከመጣ ቆይቷል። እስከ አሁን አንዳንዶች በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚገኙ መምሪያ ኃላፊዎችንና አንዳንድ አባቶችን በገንዘብ፣ ሌሎችንም ደካማ ጎናቸውን አሰመልክቶ ምስጢር እንደሚያወጣ በማስፈራራት አፋቸውን ለጉሞ ቆይቷል። የወደፊቱን እግዚአብሔር ያውቃል። እንደሚታወቀው ይህ ማኅበር “አጥፍተሃል” … “ተሳስተሃል” ... “አሁንስ በቃ! ... አልበዛም እንዴ?” የሚለውን ሁሉ “ተሐድሶ ናቸው” በማለት ወይም “ኑፋቄ አስተምረዋል” ብሎ ስም በማጥፋትና አመጽን በማስተባበር ቅን የቤተ ክርስቲያንዋን አገልጋዮች ስም እያጎደፈ ነው። ብዙዎች ጭንቅ ሆኖባቸው የማኅበሩን ድክመት እያወቁ ተሸክመው ባልተማሩ ልጆች እየታዘዙ “ስቀሉ ሲባሉ እየሰቀሉ” “አውርዱ ሲባሉ እያወረዱ” ማኅበሩ ሊያገኝ ከሚገባው በላይ ሥልጣን እንዲኖረው ምክንያት ሆነዋል።
ያም ሆነ ይህ “ይህቺ ባቄላ ያደረች እንደሆነ አትቆረጠምም” እንደተባለው ወይም “ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቆመን ማውረድ እንዳያቅተን” ተብሎ እንደተተነበየው ዓይነት ነገር እንዳይመጣ ሁሉም ሊያስተውል ይገባዋል።
የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ችግር ማለትም የአባቶች መለያየትን ማኅበሩ የጥፋት ተልእኮውን ለመፈጸም ተጠቅሞበታል እየተጠቀመበትም ነው::  እንዲያውም ሁለቱንም ሲኖዶሶች በማቃለልና ባለመታዘዝ የማኅበሩን አጀንዳ የሚያካሂዱ ጥቂት አባቶችን እያታለለ ራሱን እንደ ሦሰተኛ አማራጭ እያቀረበ ነው:: ለዚህም ነው በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ሰላም እንዲወርድ የማይፈልገው የተጀመረውን የሰላም የእርቅ እንቅስቃሴ ለማምከን የሚንቀሳቀሰው። በአባቶች መካከል ሰላምና እርቅ መምጣቱ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ሆኖ ሳለ በቤተ ክርስቲያን ሥር ነኝ ለሚለው ለ"ማኅበረ ቅዱሳን" አልዋጥ ማለቱ ማኅበሩ ድብቅና መሠሪ ተልእኮ እንዳለው በግልጽ የሚያሳይ ነው::