እውነቱ ስንናገር ጳጳሳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዘብ አልቆሙም!!የካህናቱና ጡረተኞች የተሰገሰጉበት የሰበካ ጉባዔ ምእመናን ተወካዮች በዓመት አንድ ጊዜ ተሰብስበው በሚመሰጋገኑበትና የድግስ ጋጋታ በሚያስተናግዱበት የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ስለመቻቻል የቀረበውን አጀንዳ አስታከው ጳጳሳቱ ስሜታቸውን መግለጻቸውን ሰምተን ጥቂት ተደነቅን። እንዴት ወንድ ወጣቸው? ብለንም ጥቂት አድናቆትን ቸርናቸው። ለካስ ከቀሚሳቸው ስር ሱሪ ታጥቀዋል?  ይሁን እንጂ  ሱሪ ነገረ ስር አይሆንምና ነገሩ አጋጣሚን የመጠቀም እንጂ የወንድነት አይደለም።
  በዚያች የመቻቻል መድረክ ለመተንፈስ ከመፈለጋቸው በስተቀር በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ለመፍታት አንዳችም ህልምና ርእይ እንደሌላቸው የተገነዘብንበት ሁኔታ ነበር። ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደተቋም የት ነበረች? አሁንስ የት ነው ያለችው? ወደፊት እንዴትና የት ትራመዳለች? ለሚለው አንኳርና ቁልፍ የመንፈሳዊ ጉዞ መልህቅ መጣያ የሚሆን የሃሳብ ወደብ አንዳችም ሳናይ በማለፉ ግንፍል ንግግራቸውን ታዘብነው። አንድም አባል ቢሆን ሲጎዳ ማየት ልብን እንደሚሰብርና መንፈሳዊ ልማት ማካሄድ የሚቻልበትን አንድም ጋት ይዞታን ማጣቱ ቢያንገበግብም  የቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ ችግር በመሬት ተወሰደብኝና አንድ አባል ታሰረብኝ በሚል አቤቱታ የሚገለጽ አልነበረም። ይሁን እንጂ ጳጳሳቱ ሲጮሁ የሰማነው ንግግር በቁራሽ መሬትና በአንድ ምእመን መጎዳት ላይ ማተኮሩ የችግሩን ስፋት ለመመልከት አለመቻላቸውን ያመላከተ ሆኖ አልፏል።

በጳጳሳቱ ሊታይ ያልቻለውና መታየት የነበረበት የቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥና የውጪ ችግር፤
  1/ ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል፤ ሲዘረፍ፤ ምእመናንና ምእመናት ሲሰደዱ፤ በአሸባሪና በአክራሪዎች ሲገደሉ መቆየታቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን አንድም ጊዜ የጳጳሳቱን የድፍረት ሱሪ በንግግር አላየንም። ለምን? አንድም የፍርሃት ቆፈን ወሮአቸዋል። አለያም የመንፈሳዊነት እንጥፍጣፊ አልቆባቸዋል። የመቻቻል ፖለቲካ ዲስኩር ሲፈነዳ አብሮ ማንዳዳት ያስተዛዝባል እንጂ አባቶች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር ዘብ ቆሙላት አያሰኝም።

2/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንግሥታዊ ሃይማኖት ሆና ለዘመናት በመቆየቷ ብቻ ጊዜ አመጣሾች እንደጠላት ቢመለከቷትም ዘመንና ወቅት እንደዚያ ሆና እንድታልፍ ያደረጋትን ከመቀበል ውጪ «መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው» የሚል ሕግ ለመቅረጽ ስለማትችል ይህንን ሁሉ አስልተው እንደባላንጣ ለሚቆጥሯት ወገኖች ለመንግሥት አካላትም ሆነ ለሌሎች የሃይማኖት ተቋሟት መናገር፤ ማስረዳትና ማሳመን የሚችል አቋም በቤተ ክህነቱ ፕሮግራም ውስጥ ባለመኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱ የነፍጠኞችና የትምክህተኞች መናኸሪያ ተደርጋ በሌሎች ዘንድ በተሳለው ስዕል የተነሳ አጋጣሚውን ጠብቀው ብድር የመመለስ ጨለምተኛ አካሄድ ሲታይ ያንን በመጠቆም ብቻ ችግሩን መግፈፍ አይቻልም። ስለዚህም ጳጳሳቱ መናገር የሚገባቸውን  ሰዓት ቀድሞ አሳልፈውት ዛሬ ለችግሩ ማልቀስ የቤተ ክርስቲያን ዘብ አያሰኝም።
  3/ ዋናው ችግር ከውስጥ መንፈሳዊ ማንነትን መታጠቅ ያስፈልጋል። ታሪክና ዘመን የሰጣቸውን ሥልጣንና እድሜ ሊሰሩበት እንደሚገባ የሚረዳ ውስጠት ሊኖራቸው የግድ ይላል። ውጪያዊ ተጽእኖን ለመጋፈጥና ለማሸነፍ መንፈሳዊ ትጥቅ የሌለው ሹም በጦር አውድማው ላይ የመጠቃትና የተሸናፊነት ድምጽ ማስተጋባቱ አይቀርም። ተመሪዎቹንም ለጥቃት ያጋልጣል። አሁንም ያየነው ያንን ጩኸት ነው።  ጳጳሳቱ ይህንን የመንፈሳዊ ማንነትን ትጥቅ በተዋቡባቸው አልባሳት ለመካካስ ይፈልጋሉ። ክብሩ ግን በመንፈሳዊ ስብእና እንጂ በመልክና በቁመና ስለማይገኝ ድፍረት፤ መንፈሳዊ ቅንዓትና ጥብዓት የራቃቸውም ለዚህ ነው።

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ዘረኝነትን፤ አድመኝነትን፤ ሙስናን፤ አድልዎን፤ ብቀላን፤ ዘረፋን፤ ግለኝነትን፤ ስብእናን የሚያጎድፍ አስነዋሪ ተግባራትን በማድረግም ይሁን የሚያደርጉትን ባለመገሰጽ፤ ይልቁንም ስር እንዲሰድና እንዲስፋፋ ምክንያት በመሆን ግምባር ቀደሞቹ ራሳቸው ጳጳሳቱ ናቸው። ጳጳሳቱ ራሳቸውን ያውቃሉ፤ ካህናቱም በትክክል ያውቋቸዋል።  ሌላው ቀርቶ ምእመናንም ጭምር። ምንም እንኳን እንዲህ ማለቱ ቢያሳፍርም እውነቱን አለመናገር በራሱ ወደፊት ሊቀጥል በሚችለው የቤተ ክርስቲያኒቱ መገፋት ላይ መፍትሄ እንዳይኖር ማድረግ ነውና ከመናገር ውጪ ሌላ መንገድ የለንም። ሰው ድካሙን አውቆ፤ በንስሀ ተመልሶ፤ ብርታት በሚሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለመሥራት እስካልተጋ ድረስ በልብስ ውስጣዊ ማንነትን ቢሸፍኑት ተግባር ማንነትን፤ የኃጢአት ዋጋ እዳን ሲያስከትል በግልጽ መታየቱ አይቀርም። የጥቃቱ መብዛት የኃጢአትን ደመወዝ እየተቀበሉ የመገኘት ምልክት ነው እንጂ እግዚአብሔር በፈተና ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ስለተዋት አይደለም።
   ከዚህ በፊት ስለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባወጣነው ጽሁፍ ስንጠቁም  «የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ቅጠል የሌለው ዛፍ አንድ ናቸው» ለማለት እንደሞከርነው ጉዳዩን በሂደት ስንመለከት ዛፍነቱ ከቅጠል አልባነት በከፋ መልኩ እየበሰበሰ በመሄድ ላይ እንዳለ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ጭብጥ ማቅረብ የሚቻልበት ሲሆን  በአጠቃላይ ጳጳሳቱ ከውጪያዊ ተግዳሮቶች በከፋ መልኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን እየገፉ ወደ ገደል በመንዳት ላይ እንደሚገኙ የሚያስረዳን እውነታ ነው። አዲስ አበባ ላይ የሚፈጸመው የቤተ ክርስቲያን የዐመጻ ተግባር ጊምቢ ላይ ዋጋ አያስከፍላትም ያለው ማነው?

ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ችግር የበሰበሰው የቤተ ክርስቲያኒቱ የመነኮሳት አባቶች አመራር ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል ማለት ይቻላል። በዚህ መልኩ ከቀጠለ በወለጋ ወይም በጋሞጎፋ መሬት ተወሰደ አለያም ገበሬ ተገረፈ ከሚለው ጩኸት ይልቅ ከውስጥ በሚመጣው የዐመጽ ተግባር  የተነሳ የሚከሰተው ጥፋት የከፋ ይሆናል።
  ከሰሞነኛው የሰበካ ጉባዔው ስብሰባ ላይ የማቅ ቀኝ ክንድ አቡነ ቄርሎስ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ድምጽ እንደሆኑ የተደሰኮረ ቢሆንም አቡነ ቄርሎስን የምናውቃቸው በዘመነ ሥራ አስኪያጅነታቸው ቤተ ክህነቱን ላስታ ላሊበላ ማድረጋቸውን እንጂ ዘረኝነትን ስለመዋጋታቸው አይደለም። ሌሎቹን በስምና በቦታ መጥራት ይቻላል። ይሁን እንጂ ጊዜና ቦታ የማይበቃን ስለሆነና ተግባራቱን በውል የሚያውቁ ስለሚያውቁት ሾላ በድፍን ማለቱን መርጠነዋል። ሌሎቹ ቢሆኑ እንዲሁ ናቸው!!

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአቡነ እስጢፋኖስን የሙስና ስፋትና ጥልቀት፤ የሰው ሽያጭና ከስራ ማፈናቀል ተግባር በማስረጃ አስደግፈን በሌላ ዓምድ እንመለስበታለን።
  ስናጠቃልል ጳጳሳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሽመድመድ ዋና ተጠያቂዎች ናቸው። የተቀበሉትን አደራ እስከሞት ድረስ የመወጣት አለያም ካልቻሉ ደግሞ ወደበረሃቸው የመግባት ግዴታ እንዳለባቸው ስለማያውቁ አሁን ደርሶ በመቻቻል ፖለቲካዊ መድረክ ላይ ወኔ የታጠቁ መስሎ መታየት አንድም እንደዚህ አልኩኝ ለማለት አለያም የማኅበረ ቅዱሳንን መነካት በተዘዋዋሪ መንገድ በችግሮች ሽፋን ለማካካስ ከመፈለግ የመነጨ ከመሆን አይዘልም። ጥያቄአችንም የሚነሳው ከዚህ ነው። ይህ «መቻቻል» የሚለው መድረክ ሳይመጣ በፊት የት ነበራችሁ? ነው ጥያቄያችን። በእነ አቡነ ገብርኤል ዓይነቶቹ የምትመራ ቤተ ክርስቲያን መቼም ከችግር አትጸዳም።

እውነታውን ስንናገር ጳጳሳቱ ለቤተ ክርስቲያን ዘብ አልቆሙም ነው የምንለው!!!
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 13 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
October 20, 2013 at 8:37 PM

አልቃሻው ህፃን ማላዘን ጀመረ።

Anonymous
October 21, 2013 at 6:56 AM

This article is absolutly true. Those so cold papasate and mk is working f or the devil.
maferiyawoch, shekachoch, woradoch, nachewu. derom endenesu ayinetoch nachew Getachinen asekayitewu yegedelut. gne betensawu yegna Geta del nesa. Delu mengizeam yeewunetegnawoch Christiyanoch newu. Amen.

Anonymous
October 21, 2013 at 4:52 PM

የኛ ሊቅ የሰጠው የክፍለ ዘመኑ አስተያየት!!!!

Anonymous
October 21, 2013 at 8:39 PM

የኛ ደደብ ጴንጤ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ገባው። ዋው። ተስፋ አለህ ማለት ነው።
ለካ አንዳንዴ ታውቃለህ።

Anonymous
October 21, 2013 at 10:27 PM

dedeb? this opinion is not belongs to a christian unless he is a paganist under the cover of religion.

Anonymous
October 23, 2013 at 7:14 AM

Thank you brothers. truth never die. our church leaders are not standing for truth or word of Lord God. Our church members every day going down due to our leaders are diving wrong way. In our church they are lot of blind drivers................bad leaders .......too selfish.......

Anonymous
October 23, 2013 at 4:21 PM

አስነዋሪ ዐረፍተ ነገር ነው ከእናንተ አልጠብቀውም ንስሐ ግቡ ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል ብሎጋችሁን እከታተላለሁ ግን ሰይጣንን እንኳን〈እግዚአብሔር ይገስጽህ ነው ያለው እኮ እንዴት እነዚህን አዛውንት አባቶች እንዲህ ትላላችሁ በሃይማኖታቸው አካሄድ እንኳን ቢያበሳጩ በእድሜ ታላቅነት ክብር ይገባቸዋል እኮ?ነገ እውነቱ ሲወጣ እናንተም ትገመገማላችሁ የቀረውን ሃሳብ በመልካም ነበር ያቀረባችሁት ይህ የጠቀሳችሁት ዓረፍት ነገር ግን 《የንባብ ፍላጎት(አፒታይት)ይዘጋል።አንባቢዎቻችሁን ይቅርታ መጠየቅ አለባችሁ በቀል የእግዚአብሔር በስድብ ብሶታችሁ አትወጡ በመልካም መንፈስ መልካምና በጎ ነገር አስተምሩ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።
ኒቆዲሞስ

Anonymous
October 23, 2013 at 4:23 PM


አስነዋሪ ዐረፍተ ነገር ነው ከእናንተ አልጠብቀውም ንስሐ ግቡ ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል ብሎጋችሁን እከታተላለሁ ግን ሰይጣንን እንኳን〈እግዚአብሔር ይገስጽህ ነው ያለው እኮ እንዴት እነዚህን አዛውንት አባቶች እንዲህ ትላላችሁ በሃይማኖታቸው አካሄድ እንኳን ቢያበሳጩ በእድሜ ታላቅነት ክብር ይገባቸዋል እኮ?ነገ እውነቱ ሲወጣ እናንተም ትገመገማላችሁ የቀረውን ሃሳብ በመልካም ነበር ያቀረባችሁት ይህ የጠቀሳችሁት ዓረፍት ነገር ግን 《የንባብ ፍላጎት(አፒታይት)ይዘጋል።አንባቢዎቻችሁን ይቅርታ መጠየቅ አለባችሁ በቀል የእግዚአብሔር በስድብ ብሶታችሁ አትወጡ በመልካም መንፈስ መልካምና በጎ ነገር አስተምሩ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።
ኒቆዲሞስ

Anonymous
October 23, 2013 at 4:29 PM

እንዴት ወንድ ወጣቸው?ብለንም ጥቂት አድናቆት ቸርናቸው ለካስ ከቀሚሳቸው ሥር ሱሪ ታጥቀዋል?ይሁን እንጂ ሱሪ ነገረ ሥር አይሆንምና ነገሩ አጋጣሚን የመጠቀም እንጂ የወንድነት አይደለም!》አስነዋሪ አረፍተ ነገር ከእናንተ የማይጠበቅ ነውና ንሥሐ ግቡበት እባካችሁ የሰውን የንባብ ፍላጎት አትዝጉበት መልካም ብሎጋችሁን አታበላሹት ይቅርታ ጠይቁ!
ኒቆዲሞስ

Anonymous
October 24, 2013 at 5:54 AM

ስድብ መቼም ለእንደናንተ ዓይነቱ እንደ እድል ሆኖ እንደ ዳቦ የታደለ ይመስላል። እኔ በጣም የሚገርመኝ በናንተ በኩል ስለ ቤተ ክርስቲያኗ ደህንነት ማሰብ ቀርቶ ክርስትናውም መኖሩ አጠራጣሪ ነው። በድረገጽ ተጠቅልላችሁ እንዲሁ አማርኛ በማሳመር የተንኮልና የአሉባልታውን ናዳ ታወርዱታላችሁ ከዚህ በዘለለ ግን ከቅጥረኝነት ወይም ከተራ ምቅኝነት አያልፍምና እራሳችሁን መርምሩ።

October 25, 2013 at 4:49 AM

በኢትዮጵያውያን ባህል ሱሪ የወንድነት፤ የድፍረትና የጀግንነት ምልክት ተደርጎ ይታሰባል። እንደዚህ እንደዛሬው ሴትና ወንዱን መለየት ከማይቻልበት ሰዓት ሳንደርስ በፊት ማለት ነው። ምንኩስና በሚባለው ስርዓት ደግሞ ቀሚስ መልበስ ብቻ ሳይሆን እንደሕግም የሚወሰደው አንገትን የማቀርቀር፤ የዝምታ፤ ራስን የማሳነስ፤ ዝቅ የማድረግ፤ ድፍረትና ወኔ የማጣት፤ ከማንኛውም የዚህ ዓለም ምድራዊ ተግዳሮት ጋር ፊት ለፊት ሳይጋጠሙ አንድዬ ያውቃል ብሎ ሁሉንም ትቶ የማለፍ ልምድን የሚያበረታታ ሥርዓት ነው። ቀሚስ ያጠለቁት መነኮሳቱ በዚያ ጉባዔ ላይ በተለየ መልኩ ለፌዴራል ባለስልጣናቱ ከምንኩስናው ባህል ወጣ ብለው እንደደፋር ወንድ መልስ መስጠታቸው፤ ለማፋጠጥ መሞከራቸው፤ ኧረ በቃን የማለት የድምጽ ዝንባሌያቸው እንደቀደመው የኢትዮጵያውያን ወንዳወንድ ጀግንነት መታየታቸውን ለመግለጽና ቀሚስ አጥልቆ ያለጠባዩ የሴቶችን ስፍራ ወስደው፤ ሴቶቹ ደግሞ በዘመኑ የወንዱን ስፍራ የመያዛቸውን ድንበር ጥሰው ለመናገር መቻላቸውን ለማመልከት የተጠቀምንበት ቃል በምድሩ ላይ ያለ እውነታና በባህላችንም ሲሰራበት የኖረ ነው። አዲስ ቃል አልተፈጠረም። እውነቱን ስንናገር በጾም በጸሎት የሚኖሩ እንዳሉ ሁሉ ቦርጫቸውን ተሸክመው መንቀሳቀስ የከበዳቸውም አሉ። ከቀሚሳቸው ስር ሱሪ ብቻ ሳይሆን መሸከም ያልቻሉት ትልቅ እሳትም አለ። ያፈጠጠ እውነት!!!!!

Anonymous
October 26, 2013 at 5:41 AM

በተለይ ስለቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ሁኔታዎች ሲዛቡ ማመልከት ተገቢ ቢሆንም የጽሑፉ መልእክት አስተማሪነት ያለው ቢሆን ይመረጣል። በአቀራረቡና በቋንቋ አጠቃቀሙ ይህ ድረ ገጽ ከአባ ሰላማ በጣሙን ይሻላል። ብዙ ጊዜ ስመለከተው የሁለቱም ዓላማ አንድ ነው። በተለይ የማቅን ስም በተገኘው አጋጣሚ ማብጠልጠል ይህም የሚያመለክተው እንደፖለቲካው አካሄድ ሆን ብሎ ለማጥላላትና በአላዋቂው ዘንድ ብዥታም ለመፍጠር በመስመር የተዘረጋ አሰራር እንደሆነ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ፕሮፓጋንዳ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ትልቅ ተጽእኖ አለው ይህም በታሪክ ታይቶአል። የእናንተም አቀራረብ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን በግልጽ ያስረዳል ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን አቀራረብ ሳይሆን የጥፋት ተልእኮ እንዳላው ነውና የሚያመለክተው እየበሰላችሁ እንጂ እያነሳችሁ አትሂዱ ነቀፋም ቢሆን የጥላቻ ሳይሆን ለእርምት አድርጉት። የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ሌላው በብርሃን ሲመላለስ እናንተ በጨለማው ውስጥ ቀራችሁ ስለዚህ ማንነታችሁን በግልጽ አሳውቁ አለበዚያ ግን የ እናንተ አካሄድ በዚህ ከቀጠለ ከወሬኛነት የዘለለ ዝናን አያተርፍላችሁምና አትልፉ። መተዳደሪያችሁ ከሆነ ግን ይቅርታ እጠይቃለሁ። ተሳዳቢነት ግን የሰነፍ ፀጋ መሆኑን አትዘንጉ።

Anonymous
November 28, 2013 at 2:21 PM

Our father proceed as you have begin. The holy spirit is working with you to return the you to return lost children! The devil understood the day are numbered and is working hard with Tehadiso against you. Previously they are saying they are against Mahibre Kidusan and they are labeling a new one who is opposed to Tehadiso as MK. Enough is enough leave our Fathers in peace. Even though you do not belong to us in faith we beg you to repent and return to EOTC and say our Fathers please lead to correct what we made wrong. Our Brother serving EOTC in Mk please excuse for we have insulted with satanic jealosity please allow us to work with you! I am sure time will come when God will make this right. Let us pray for It!

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger