Sunday, June 3, 2012

ሁለቱን ሃሳቦች ማን ያስማማ?


የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? ………ሕዝቤ እውቀት በማጣት ጠፍተዋል»

አለማወቅ የአእምሮ እውርነት ነው። የአእምሮ እውርነት ደግሞ ከምንም በላይ ይከፋል። ሰው በአእምሮ እውርነት በሽታ ከተጠቃ ሰው ሳይሆን ለማዳ እንስሳ ይሆናል። እግዚአብሔር ደግሞ ሰው ያለውን ጉድለት እንዲሞላ አድርጎ ፈጠረው እንጂ እንደ ለማዳ እንስሳ አንዴ በተሞላለት አእምሮ እድሜውን ሁሉ እንዲኖር አድርጎ አልሰራውም።
ህጻናት ሳለን እንደ ህጻናት እናስባለን፤ እያደግን ስንመጣም ጤነኞች ከሆንን ከእድገታችን ጋር ተመጣጣኝ እውቀት በአእምሮአችን ይሞላል። የቅድሚያውን እውቀት ከቅርብ ወላጅ ከእናታችን እናገኛለን። ከወላጅ አባትና ከአጠቃላይ ቤተሰቦቻችን መረዳቶቻችን ይዳብራሉ። ግንኙነቶቻችን ከቤተሰብ አልፈው ወደ ጎረቤት ሲሻገሩ እንደዚያው እውቀቶቻችንም እየሰፉና እያደጉ ይመጣሉ።
መደበኛም ይሁን መደበኛ ባልሆኑ የእውቀት ተቋማት ስንገባ ደግሞ እውቀታችን ከማለዳዋ ፀሐይ የብርሃን ጸዳል ይበልጥ ሰፍቶ ወጋገኑ ሁሉን እንደሚገልጠው የረፋድ ላይ ብርሃን ሆኖ ለሌላውም መታየት ይጀምራል። እንደዚያ፤ እንደዚያ እያለ ከረፋዱ ወደ ቀትር፤  ከተሲዓት፤ ሰርክና እርበት ድረስ እውቀታችን ከሙላት ወደ ሙላት ይሻጋገራል። ይህ ለሰው እንጂ ለለማዳ እንስሳ የተሰጠ ጸጋ አይደለም። ስለዚህ የሰው ልጅ ክቡር ነው፤ የሚያሰኘው ለማወቅ የተሰራ አእምሮ ስላለው ነው።
 ይሁን እንጂ ሰው ለማወቅ መሪ ያስፈልገዋል። ያለ መሪ ምንም ነው። እግዚአብሔር ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ከመፍጠሩ በፊት የሚኖርበትን ቦታ አስቀድሞ አዘጋጅቶለታል። ለኑሮው ጉድለት ረዳት ሰጥቶታል። በሚኖርበት ሥፍራ ራሱን እንዲያበዛ፤ የሚኖርበትን ቦታ ሁሉ እንዲገዛ አድርጎታል። ይህ ሁሉ የሌለውን እውቀት ምሉዕ ለማድረግ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ምሪት መሆኑን ያሳየናል።
ዛሬም እንደዚሁ ነን። ምሪት ያስፈልገናል። በመግቢያችን ላይ እንዳስቀመጥነው ከቤተሰብ፤ ከማኅበረሰብ፤ መደበኛና መደበኛ ካልሆነ የእውቀት ስፍራ ወደእውቀት የሚመራን የሰው ምሪት የግድ ይሆናል ማለት ነው። ለዚህም ይመስላል፤«ሰው ለሰው መድኃኒቱ ነው» የሚባለው።

Saturday, June 2, 2012

የአንዳንድ የጳጳሳቶቻችን ገበና ምን ይመስላል?

  ምንጭ፦ አባ ሰላማ ብሎግ
የአንዳንድ ጳጳሳቶቻችንን ገበናዎች ይፋ ስናደርግ ሀዘን ነው የሚሰማን። እንዲህ እያደረግን ያለነው ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት ምግባረ ብልሹነት እየተስፋፋባት እንደሆነች ለማሳየት ነው እንጂ እነርሱን በግል ለማሳጣት አይደለም። ይህን መደበቅና ማለፍ ጉዳቱ ለቤተ ክርስቲያን እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ገበናችሁን እሸፍንላችኋለሁ ማለቱ እርሱ የፈለገውን እንዲፈጽሙለትና «በእከክልኝ ልከክልህ» ቃል ኪዳን እንዲተሳሰሩና እንዳሻው እንዲጠቀምባቸው በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ወደ ባሰ ጥፋት እየመራት ነው። እንደነዚህ ያሉትን አባቶች አሳፋሪ ታሪክ ማስፈራሪያ እያደረገ የሚሻውን እንዲፈጽሙለት እየተጠቀመበት ያለው ማኅበረ ቅዱሳንም ለጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን እንዳልቆመ አስመስክሯል።
 እንደ እነዚህ ያሉትን «ብፁዓን» «ጻድቃን» «ቅዱሳን» ምንትስ እያለ መሸንገሉም በጥፋታቸው እንዲገፉ አድርጓቸዋል እንጂ በክፉ ሥራቸው እንዲጸጸቱና ንስሃ እንዲገቡ አልረዳቸውም። የራሳቸውን ጉድ ሌላውን አለሀጢአቱ በማውገዝ ለመሸፈን እያደረጉት ያለው ጥረትም ለማኅበረ ቅዱሳን በር እንዲከፈትለትና የሲኖዶሱ የበላይ አካል እንዲሆን ነው ያደረገው። ስለዚህ ገበናቸው እንዲህ ይፋ ቢሆን፣ ጉዳዩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ትኩረት አግኝቶ ለቤተክርስቲያኑ አንዳች መፍትሔ ያመጣ ይሆናል በሚል ሐሳብ ገበናቸውን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ምናልባት ልብ ገዝተው ንስሃ ይገቡ ይሆናል።

የአፋልጉኝ ማስተወቂያ
ይህ ልጅ አያሳዝንም? ……. አያሳሳም? …… እርሱ ጠፍቶ እንዳይመስለዎ። አባቱን ማግኘት ባይችልም አባቱን ይፈልጋል፤ እንደሌላው በህግ እንደተወለደ ልጅ ከእናቱ ጋር አባቱን ማግኘትና አብሮ ለመኖር አልታደለም። ያለው አማራጭ አባቴ ማነው? እያለ በመጠየቅ ማደግ ነው። ማን ያውቃል? የማንነት ጥያቄው አንድ ቀን ምላሽ ያገኝ ይሆናል።

Friday, June 1, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር ! በቀሲስ መልአኩ


ካለፈው የቀጠለ………………………………………
ሌላው በዘመናችን የተደረገ ነውበካምቦዲያ ውስጥ ኬሜን ሩዥ የተባለው ኮሚኒስታዊ ድርጅት ሥልጣኑን ይዞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የገዛ ወገኖቹን በገደለበት ወቅት ነውበዚያን ወቅት በሀገሪቱ  እየተፈለጉና  እየታደኑ ይገደሉ  የነበሩት አሉ የሚባሉት የሀገሪቱ ምሑራን ነበሩ በካምቦዲያ መማር ወንጀል ነበር ለመማር መጣጣር የሚያስቀጣ ነበር የነሞዛርትን ረቂቅ ሙዚቃ ያሰማምሩ የነበሩ እጆች የምዕራባውያንን  ባሕል ልታመጡ ነው ተብለው ተቆረጡት የታሪክ መዛግብትን የሚመረምሩ ዓይኖች በአብዮቱ ላይ ታሴራላችሁ ተብለው እንዲጠፉ ተደረጉ  ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ተወረወሩ ማወቅ ወንጀል የሆነበት ወቅት ነበርና
ጊዜ ተመልሶ የመጣ የመሰለበት ወቅት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን አምጥቶልናል ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ማስቀባት፤ ቢቻል የሆነ የሚከሰስበት ነገር መፈለግ ቤተክርስቲያን መናፍቅ ትበለውም፤ አትበለውም በእነርሱ ጥቁር መዝገብ መናፍቅ እንደሆነ ማወጅ ማሳደምና እንዲባረር ማድረግ ቀዳሚው ነገር ነው።  ከሳሽ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ምስክር ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፈራጅ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሕግ አስፈጻሚ ማኅበረ ቅዱሳን  በሆነበት ሁኔታ ጉዳይህ አሰቃቂ ፍጻሜ ያገኛል። ከእሱ ከተስማማህ ትድናለህ፤ ካልተስማማህ ትጠፋለህ።ለዚህ አስዛኝ ሁኔታ ምሳሌ ምሳሌ የሚሆነን በአንድ ወቅት ማኅበሩ በሚያወጣው ጋዜጣ ላይ የከፍተኛ የቴዎሎጂ ኮሌጅን፤ ከምክትል ዲኑ ጀምሮ የኮሌጁን ዋና ጸሐፊ፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግዕዝ መምሕር፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግእዝ መምህርበኮሌጁ የቤተክርስቲያን ታሪክ መምህር፤ የኮሌጁን ሥራ መሪና የእንግሊዝኛ መምህር ስድስት ተማሪዎችን  ጨምሮ ተሐድሶዎች ናቸው ብሎ አውጥቷል ይህም የኮሌጁን ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ወደ ቅድስት ሥላሴ የተዛወሩ ሦስት አስተማሪዎች ተሐድሶ ማለቱን ሳይጨምር ነውይህ ጸሐፊ እስከሚያታውሰው ኮሌጁ ያሉት አስተማሪዎች ከስምንት እስከ አሥር ቢሆኑ ነውስለሆነም በማኅበረ ቅዱሳን ሚዛን ኮሌጁ ካሉት አስተማሪዎች ዘጠና በመቶዎች መናፍቃን ነበሩ ማለት ነው
ይህን ታሪክ ስጽፍ በስሜታዊነት ቢሆን አትፈረዱብኝ ልቤ እየደማ ነውና የምጽፈው ወደማን አቤት ይባላል? ወደ ማንስ ይኬዳል ? እግዚአብሔር እንዲፈርድ ከመጥራት ሌላ ማን ይባላል ?
"ለመሆኑ የእነዚህ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም አደባባይ የወጣው ቤተ ክርስቲያን መክራበት ነው ? ለምናቸው አልቅሳላቸው እባካችሁ ልጆቼ ስህተት አግኜባችኋለሁና ተመለሱ ብላቸው ነው ?  በፍጹም ! ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን የእነዚህን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተከሰሱብትን ምክንያት አያውቁም ። ወንጀሉን የሚያነቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ ላይ ነው። ከዚያም በየቤታቸው እነዚህን ካላባረራችሁልን የሚል ማስፈራራያ ይመጣላቸዋል።