Wednesday, December 14, 2011

ማደናገር ይቁም! የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ድረገጽ


«ADOBE OF GOD»በሚል ርእስ የክርስቶስ ኢየሱስን የማዳን ስራ የሚያጥላላና ፍጹም ክህደት የተሞላበት ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ እንደነበር በባለፈው ወር የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በእርግጥም ከ75% በላይ ሕዝብ ክርስትናን በአንድም በሌላ ምክንያት ተቀብሎ የሚኖርና በአብዛኛውም ይህንኑ የእለት ከእለቱ መመሪያ አድርጎ በሚቀበል ሀገር ላይ ይህንን መሰሉን ፊልም መስራት መርገም ካልሆነ በረከት ያመጣል፣ ተብሎ አይታሰብም። ክርስቶስን ለማዋረድ መፈለግ ከክርስቶስ ማንነት ላይ አንዳች የሚያጎለው ነገር ባይኖርም
«የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?» ሮሜ 3፣3 እንዳለው ክርስቶስ ዛሬም፣ ነገም ያው እሱ መሆኑ ሳይጎድል አምልኰና ክብር በሚገባው ቦታ ተሳልቆና ክህደት ሲተካ ግን የረድዔትና የበረከት እጁን ላለመቀበል በፈለግነው ልክ የዚህ ዓለም ገዢን ማስተናገድ በመሆኑ ሊያስደነግጠን እንደሚገባ ለአፍታ መዘናጋት የለብንም። ይህንን ድርጊት ለምእመናንና ምእመናት በማዳረስ በመረጃው ላይ የወል ግንዛቤ ወስዶ አቋማችንን ለሚመለከተው ለማድረስ ሚዲያዎች ሰፊ ዘገባቸውን ሰጥተው ሰርተዋል። ይህ ሊመሰገን የሚገባው መንፈሳዊ ተግባር ነው። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ራሳቸውን የዚህ ጥረትና ትግል ዋነኛ አካል አድርገው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማእከላዊ ጽ/ቤት ግን «ፊልሙ እንዲሰራ ፈቅዷል» በማለት ድካምና ጥረቱን ውሃ በመቸለስ ከችግሩ ጎን ለጎን የችግሩ ዋነኛ ምህዋር እንደነበር ለማሳየት መሞከራቸው አስገራሚ ሆኗል። ከነዚህም መካከል የማኅበረ ቅዱሳኑ ሌላኛው እጅ የ«ደጀሰላም» ድረገጽ ከለጠፈው በኋላ ቤተክህነቱን የወነጀለበትን ጽሁፍ ያውርድ እንጂ ወንድሙ የሆነው «አንድ አድርገን» ለማንበብ ይህን ይጫኑ
እስካሁን ያስነብበናል። «ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ» በተሰኘው መጽሐፍ እንደተጠቆመው «እንቁ» መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን የእጅ አዙር መጽሔት መሆኑን ለመረዳት ብንችል ሁሉም በአንዴ ተቀባብለው ቤተክህነቱን ያለስራው ስም ሰጥተው «ADOBE OF GOD» ለተሰኘው የክህደት ፊልም ትብብሩን ሰጥቷል ሲሉ መጻፋቸው ካንድ ወንዝ መቀዳታቸውን እንደሚነግሩን እንገነዘባለን። የቤተክህነቱ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ነገሩ እጅግ ቢያስመርረው በድረገጹ ለተባለው ፊልም ከታቃውሞ ውጪ ድጋፍ አለመስጠቱን አስነብቦናል።
ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Friday, December 9, 2011

የጳጳሳት ጆሮ የተነፈገው የአዲስ አበባ ካህናት ጩኸት!


የጳጳሳት ጆሮ የተነፈገው የካህናት ጩኸት(to read in PDF click here)

ከደጀብርሃን፣

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የገንዘብና የንብረት ዘረፋ ሀገር ያወቀው፣ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ኰሌጅ፣ ሙአለ ህጻናት፣ አውቶቡስ፣ ታክሲ፣ ሆቴል፣የተለያየ ደረጃ ያላቸው ህንጻዎች፣ ሱቆች፣ የሚከራዩ አፓርትማዎች፣ የቤትና የንግድ መኪናዎች ያላቸውን አስተዳዳሪዎች፣ ፀሐፊዎች፣ ሂሳብ ሹሞች፣ የቁጥጥር ሠራተኞች፣ገንዘብ ያዢዎችና ንብረት ክፍሎችን ማየት እንግዳ ነገር አይደለም። ይህንን ሁሉ ሀብት ሲያጋብሱ የቀድሞ ደመወዛቸው ቢበዛ የአስተዳዳሪው ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር የሚበልጥ አልነበረም። የሌሎቹ ደግሞ ሺህ ብር ባልገባ ደመወዝ ነበር ይህንን ሁሉ ሃብት ማፍራት የቻሉት። የዘረፋ ቁንጮ እንደሆነ የሚነገርለትና አውቶቡስ፣ ት/ቤት፣ ትልቅ ህንጻ እንዳለው የሚነገርለት (ሊቀ ሊቃውንት)አባ እዝራ የሚባለው የሽማግሌ ማፊያ ለዚህ የሚጠቀስ አብነት ነው። ሊቀሊቃውንት ብላ ቤተክርስቲያን የምትጠራው ጡቷን ምጎ፣ ምጎ አጥንቷን ስላወጣው እውቀቱ ይሆን? ይህንን እንግዲህ እውቅና የሰጠው ሲኖዶስ የሚባለው የአባቶቹ ማኅበር ያውቃል። ሌሎቹንም የዘረፋ ሊቀ ሊቃውንት በስምና በአድራሻ ማንሳት ይቻላል። የሚያሳዝነው ግን ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴን ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ለማስነሳት የዘመቻው ፊት አውራሪዎች እነዚህ የቤተክርስቲያንን ሀብት እያገላበጡ የሚዘርፉ የቀን ጅቦች መሆናቸው ነው። ከማሳዘን አልፎ የሚገርመው ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም የቀን ጅቦቹን አፍ የዘጉት በየትኛውም የቤተክርስቲያን ገንዘብና የንብረት ቆጠራ ላይ አስተዳዳሪው፣ ፀሐፊውና ሂሳብ ሹሙ እጃቸውን ሳያስገቡ ቁጭ ብለው እንዲመለከቱና አገልጋይ ካህናቱ ብቻ በአንድነት ቆጥረው የተገኘውን ገንዘብ በሞዴል 64፣ የገባውን ንብረት በሞዴል 19 ገቢ አድርገው በግልጽ መጠበቅና ማስጠበቅ መቻላቸውን ሲኖዶስ የሚባለው ስብስብ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ለዘራፊዎቹ ጩኸት ምላሽ በመስጠት ባለፈው ጉባዔ ሥራ አስኪያጁን ከቦታው እንዲነሱ አድርጓል።
ከ5 ሚሊዮን ያላለፈውን ለጳጳሳት ደመወዝና ሥራ ማስኬጃ ፈሰስ የሚደረገውን የጠቅላይ ቤተክህነት ገቢ ወደ 27 ሚሊዮን ከፍ ስላደረጉላቸው ሽልማት መስጠቱ ይቅርና ይህንን አጠናክረህ ቀጥል ማለት አቅቷቸው እንደጥፋተኛ ሰው የልማቱን አባት ለቦታው አትሆንም ብሎ ማንሳት ሲኖዶስ በእውነት በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ነው? የሚያስብል ነገር ነው። የአባ ገ/ማርያምን መነሳት የሚሹ ወገኖች(ፓትርያርኩን ጨምሮ) የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ሊያስደርግ የሚችል ተግባር ለማየት ሲኖዶስ የሚባለው ክፍል በመንፈሳዊነት ደረጃ ይቅርና በመስማትና በማሽተት እንዴት ሳይረዳው ቀረ? ይልቁንም ጊዜውን በአባ ሠረቀ ጉዳይ ላይ የማኅበረ ቅዱሳንን ውክልና በማስፈጸም መጠመዱን ስራዬ ብሎ ዋለ እንጂ!! እውነትም የመንፈስ ቅዱስ ጉባዔ!!!!!!!
ከታች የቀረበው በሰዓታቱ፣በማኅሌቱ፣በቅዳሴው፣በፍትሃቱ ሌሊትና ቀን እየጮሁ ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ ካህናት ጩኸትና ትዳር አንፈልግም፣ እኛ መንኩሰናል፣ እያሉ ግን ብዙውን ጊዜያቸውን ሽቶ የተለወሰ ቀሚሳቸውን አስረዝመው፣ ወለተማርያም፣ወልደ ማርያም እያሉ የመበለት ቤቶችን የሚበዘብዙ አስተዳዳሪዎች መካከል የተደረገው የአቤቱታ ክርክርና ከላይ እስከታች ረዳት የሌለውን ካህን ድምጽ የሚያሳይ ነውና መልካም ንባብ ይሁንልዎ!! ኅሊናዎትም ፍርዱን ይስጥ!!ከታች ያለውን ተጭነው ያንብቡ!(http://dejebirhan.blogspot.com)

Thursday, December 8, 2011

መጽሐፈ ሰዓታት ምን ይላል?

                               መጽሐፈ ሰዓታት.............to read in PDF click here





«ሰዓሊ ለነ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት፣
ለውሉደ ሰብእ መድኃኒት፣
ወእስከ ለዓለም ሰፋኒት» ትርጉም--ለሰው ልጆች መድኃኒትና እስከዘለዓለም ገዢ የሆንሽ፣ የክርስቲያን ሰንበት ሆይ ለምኝልን ማለት ነው።
ሰንበተ ክርስቲያን የተባለችው ዕለት ለሰው ልጆች መድኃኒት በመሆኗ እንዲሁም እስከዓለም ፍጻሜ የሰው ልጆች ገዢ ስለሆነች እንድታማልደን እንጠይቃት ማለቱን መጽሐፈ ሰዓታት ይጠቁመናል።
እዚህ ላይ ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ።
1/ሰንበተ ክርስቲያን የምትባለው ምናልባትም ዕለተ እሁድ ናት። ሐዲስ ኪዳን ግእዙ «ወበእሁድ ሰንበት መጽአት ማርያም መግደላዊት ኀበ መቃብር»ዮሐ20፣1 «ማርያም መግደላዊት ወደመቃብር በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን መጣች»ይላል። ምንም እንኳን የእብራይስጡም ሆነ የጽርዑ መጽሐፍ ቅዱስ እሁድ ሰንበት የሚል ቃል ባይዝም እሁድ ብለው ያስቀመጡትን የግእዝ ተርጓሚዎች ተከትለን ብንሄድ እሁድ የተባለችው ቀን---
ሀ/እንዴት ሆና ነው የሰው ሁሉ ገዢ የምትሆነው?
ለ/ እሁድ በምን አፏ ነው የምልጃ ቃልን የምታሰማው?
ሐ/ እሷስ ከማነው የምታማልደን?
ሐ/ከሳምንቱ እለታት የተለየች ናት ካልን የጌታ እለታት ያልሆኑት የትኞቹ ናቸው?
መ/ድርሳነ ሰንበት የተሰኘው መጽሐፍ «ሰንበት» ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይለናል። ታዲያ ሰንበት የተባለው መድኃኔዓለም ያማልደናል ማለታቸው ነው?
2/ አስታራቂና አማላጅ የሆነችው እለተ ሰንበት ስለመሆኗ የተቀመጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ምንድነው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ወንጌልን ከሰበከላቸው በኋላ ወደቀደመው ከንቱ የሆነ አምልኰ ሲመለሱ ተመልክቶ እንዲህ ብሎ ነበር።
«ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ» ገላ 4፣8
እንደዚሁ ሁሉ እለተ እሁድ እግዚአብሔር ከቀናት እንደአንዱ የሰራት መሆኗ ተረስቶ ልክ አማልክት ወደመሆን የተቀየረች ይመስል አስታርቂን፣አማልጂን ማለት ጳውሎስ በባህሪያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ የተገዛችሁ ነበረ ያለውን ቃል እኛ ዛሬም እየፈጸምን መገኘታንን ያሳያል።